የመሰማት መብት


የመሰማት መብት በተከሰሰበት ጉዳይ መልስ ሳይሰጥ እንዲሁም ማስረጃውን ሳያሰማ የንግድ ፍቃዱ የተሰረዘበት ነጋዴ፣ የቤት ካርታው የመነከበት ግለሰብ፣ ከዩኒቨርሲቲ የተባረረ ተማሪ… ሁሉም የአስተዳደር በደል ሰለባዎች ናቸው፡፡

የመሰማት መብት በተከሰሰበት ጉዳይ መልስ ሳይሰጥ እንዲሁም ማስረጃውን ሳያሰማ የንግድ ፍቃዱ የተሰረዘበት ነጋዴ፣ የቤት ካርታው የመነከበት ግለሰብ፣ ከዩኒቨርሲቲ የተባረረ ተማሪ… ሁሉም የአስተዳደር በደል ሰለባዎች ናቸው፡፡ የአንድን ግለሰብ መብትና ጥቅም ሊጐዳ የሚችል ማንኛውም አስተዳደራዊ እርምጃ ከመወሰዱ በፊት ግለሰቡ የመሰማት ዕድል ሊያገኝ ይገባል፡፡ የመሰማት መብት በዘፈቀደ በሚወሰድ አስተዳደራዊ እርምጃ የተነሳ ዜጎች ህይወታቸውና ንብረታቸው ለአደጋ እንዳይጋለጥ ይከላከላል፡፡መሰማት ሲባል ከክስ እስከ ውሳኔ ድረስ ያሉ ዝርዝር የክርክር ሂደቶችን ያቅፋል፡፡ እያንዳንዱ ሂደት በራሱ ካልተሟላ በቂ የመሰማት ዕድል እንዳልተሰጠ ይቆጠራል፡፡ በአስተዳደር ዳኝነት ውስጥ የዚህ መብት ዝርዝር ሂደቶችና አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች በዋነኛነት የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ቅድመ-ክስ ማስታወቂያየክስ መሰማት ውሳኔ ሰጭው ባለስልጣን ለባለጉዳዩ /ለተከሳሹ/ በሚሰጠው የክስ ማስታወቂያ ይጀመራል፡፡ ማስታወቂያ ተከራካሪው እንዲቀርብ የሚሰጥ መጥሪያ ነው፡፡ በይዘቱ ባለጉዳዩ የቀረበበትን ክስ በሚገባ ተረድቶ መልሱን አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ የሚያስችለው በቂ ማስታወቂያ መሆን አለበት፡፡ ተከራካሪው ራሱን ለመከላከል የሚችለው የተከሰሰበትን ጉዳይ በማያሻማ ሁኔታ የተገለጸለት እንደሆነ ነው፡፡a ከዚህ አንጻር የክሱ ዓይነትና ምክንያት ቀጥተኛና ግልጽ በሆነ መንገድ በማስታወቂያው ላይ መስፈር ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ እንዲቀርብ የተጠራው ባለጉዳይ የመንግስት ሰራተኛ ወይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆነ በደፈናው ‘የዲሲፕሊን ክስ ስለቀረበብህ እንድትቀርብ!’ የሚል መጥሪያ ግልጽነት ይጐድለዋል፡፡ በተጨማሪም ከአንድ በላይ ክስ በቀረበ ጊዜ እያንዳንዱ ክስ በዝርዝር ሊገለጽ ይገባል፡፡ በሌላ መልኩ በክስ ማስታወቂያው ላይ የቀረበው የክስ አይነት ክሱ በሚሰማበት ቀን የተቀየረ እንደሆነ ክሱ እንዳልተገለጸ ወይም በቂ ማስታወቂያ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል፡፡ በስርቆት ተከሶ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ፊት እንዲቀርብ የተጠራ ተማሪ ክሱ በሚሰማበት ቀን የመጀመሪያው ክስ ተቀይሮ ‘በፈተና ማጭበርበር’ ተከሶ ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ ተማሪው የተቀጣው በቂ ማስታወቂያ ሳይሰጠው እንደመሆኑ ቅጣቱ መሰረታዊ የሆነውን የመሰማት መብት ይጻረራል፡፡ክሱ የሚሰማበት ጊዜና ቦታ‘በቂ’ ሊባል የሚችል የክስ ማስታወቂያ መለኪያ ባለጉዳዩ ራሱን በሚገባ እንዲከላከል በሚያስችል መልኩ በቂ መረጃና ጊዜ የሰጠ እንደሆነ ነው፡፡ ክርክሩን ለማካሄድ ስልጣን የተሰጠው አካል ተከራካሪዎች የሚመቻቸውን ጊዜ በመወሰን ክሱ ስለሚሰማበት ቦታ ትክክለኛ መረጃ እንዲኖራቸው በሚያስችል መልኩ መጥሪያውን መላክ ይጠበቅበታል፡፡ ጊዜው ሲገለጽ ትክክለኛው ሰዓት ጭምር መገለጽ አለበት፡፡ ቦታውም እንዲሁ ትክክለኛ መለያ አድራሻውን በመጥቀስ ለባለጉዳዩ/ለተከሳሹ በግልጽ ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡ከጊዜ ጋር በተያያዘ መልስ ለማቅረብ የሚሰጠው የዝግጅት ጊዜ እንደክሱ ክብደትና ውስብስብነት ሚዛናዊ የጊዜ መጠን መሆን ይኖርበታል፡፡ ዛሬ ክሱ ተሰጥቶት ለነገ መልስ መጠበቅ በተዘዋዋሪ የመሰማት መብትን እንደመንፈግ ይቆጠራል፡፡ በመጨረሻም ክሱን የሚሰማው አካል ትክክለኛ ማንነት በማስታወቂያው ላይ መመልከት ይኖርበታል፡፡የክስ ማስታወቂያ በአካል ስለመስጠትየጥሪ ማስታወቂያው በይዘቱ በቂ ሊባል የሚችል ቢሆንም ለባለጉዳዩ በአግባቡ እስካልዳረሰው ድረስ የመሰማት መብቱ ተጓድሏል፡፡ ባለጉዳዩ በቅርብ የሚገኝ ከሆነ በተቻለ መጠን መጥሪያው ለራሱ በአካል ሊሰጠው ይገባል፡፡ ከተገቢ ጥረት በኋላ ለማግኘት የማይቻል ከሆነ ማስታወቂያውን ቅርብ በሆነ ቦታ ላይ መለጠፍና ለተወሰነ ጊዜ በተለጠፈበት ቦታ እንዲቆይ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ጉዳዩ በሚሰማበት ቀን አለመቅረብ ክርክሩ በሌለበት እንዲቀጥል የሚያደረግ በመሆኑ የመጥሪያ በአግባቡ መድረስ የመስማት መብት አካል ተደርጐ መቆጠር ይኖርበታል፡፡ክርክርና ማስረጃ የማቅረብ መብትክስ የቀረበበት (ባለጉዳይ) ጉዳዩ በተቀጠረበት ቀን በአካል ወይም በወኪሉ ተገኝቶ ክርክሩን የመከታተል፤ መልስ፣ ክርክርና ማስረጃ የማቅረብ ዕድል ሊያገኝ ይገባል፡፡ ይህ መፈጸሙን ማረጋገጥ ክርክሩን የሚሰማው አካል ግዴታ ነው፡፡ መልሱ የሚቀርብበት መንገድ እንደየሁኔታው በቃል ወይም በጽሑፍ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚቀርበው የማስረጃ ዓይነት የቃል (የሰው ምስክር) ወይም የጽሑፍ ማስረጃ ሊሆን ይችላል፡፡ ማስረጃው በ3ኛ ወገን እጅ የሚገኝ ከሆነ ባለጉዳዩ እንዲቀርቡለት በጠየቀ ጊዜ ክርክሩን የሚሰማው አካል እንዲቀርቡ ማድረግ አለበት፡፡መስቀለኛ ጥያቄ የማቅረብ መብትባለጉዳዩ የተቃራኒ ወገን ክስና ማስረጃ በአግባብ ሊደርሰውና ሊመለከተው እንደሚችል ከዚህ በፊት ተገልጿል፡፡ የዚህ ዓላማ በአንድ በኩል ባለጉዳዩ የራሱን መከራከሪያና ማስረጃ በማቅረብ ክሱን በቀጥታ እንዲከላከል ሲሆን በሌላ በኩል የተቆጠረበትን ማስረጃ ማስተባበል እንዲያስችለው ጭምር ነው፡፡በፍርድ ቤት በሚካሄድ መደበኛ ክርክር መስቀለኛ ጥያቄ የምስክሮችን ተዓማኒነት ለማሳጣትና በአጠቃላይ እውነትን ለማውጣት ውጤታማ መሳሪያ ነው፡፡ ተከሳሹ መስቀለኛ ጥያቄ ለማቅረብ ዕድሉ ተነፍጐት የተሰጠ የምስክርነት ቃል ህጋዊ ብቃቱም አጠያያቂ ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን የአስተዳደር ክርክር በዓይነቱና በይዘቱ የፍርድ ቤት ክርክር መልክ ከያዘ ውጤታማ አስተዳደርን ወደ ኋላ መጎተቱ አይቀርም፡፡ ስለሆነም የመስቀለኛ ጥያቄ መቅረት ባለጉዳዩ ውጤታማ መከላከያ እንዳያቀርብ የሚያግደው ካልሆነ በስተቀር ውሳኔ ሰጭው አካል በመብቱ ላይ ገደብ ሊያደርግ ይችላል፡፡b ይሁን እንጂ ምስክርነቱ በቃለ መሀላ ስር የተሰጠ ከሆነ መስቀለኛ ጥያቄ መከልከል አይገባም፡፡ በዚህ ረገድ የ1967ቱ ረቂቅ አዋጅ መስቀለኛ ጥያቄ የማቅርብ መብት ለባለጉዳዩ የሚፈቅድ ግልጽ ድንጋጌ የለውም፡፡ በተቃራኒው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ረቂቅ የአስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ (1993) በአንቀጽ 6 (3)(ሐ) ላይ ይህን መብት በግልፅ አካቷል፡፡በአስተዳደራዊ ክርክሮች ላይ መስቀለኛ ጥያቄ የማቅረብ መብት ከሞላ ጎደል በሁሉም ህጎችቻን ላይ አልተካተተም፡፡ ልዩ ሁኔታ የሚገኘው በፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ 847/2006 ላይ ነው፡፡ በአንቀጽ 39/2/ እንደተመለከተው የዲሲፕሊን ክስ የቀረበበት ሰው የከሳሽን ምስክሮች መስቀለኛ ጥያቄ የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡ የመንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን ክስ በሚሰማበት ወቅት እንዲሁ ግራ ቀኙ መስቀለኛ ጥያቄ ማቅረብ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ በፌደራል መንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን አፈጻጸምና የቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርዓት ደንብ ቁ. 77/1994 አንቀጽ 17/5/ እንደሰፈረው የከሳሽ ምስክሮችን ተከሳሹ፤ የተከሳሽ መከላከያ ምስክሮችን የመንግስት መስሪያ ቤቱ ተወካይ፤ የዲሲፕሊን ኮሚቴው የጠራቸውን ተጨማሪ ምስክሮች ደግሞ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች መስቀለኛ ጥያቄ መጠየቅ ይችላሉ፡፡በጠበቃ ተወክሎ የመከራከር መብትየባለጋራን ክስና ማስረጃ ለማስተባበል የህግ ባለሙያ እገዛ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም፡፡ በተለይ ውስብስብ በሆኑ የአስተዳደር ክርክሮች ተካፋይ የሆነ ወገን ካለባለሙያ እገዛ ራሱን በውጤታማ መንገድ ለመከላከል ያለው ዕድል አነስተኛ ነው፡፡ ሆኖም በጠበቃ መወከል መሰረታዊ የመሰማት መብት አካል ተደርጐ አይቆጠርም፡፡ በመብቱ ላይ የሚጣለው ገደብ የራሱ አሳማኝ ምክንያቶች አሉት፡፡የአስተዳደራዊ ዳኝነት ክርክር ጥብቅ የሆነ የመደበኛ ፍ/ቤቶች ዓይነት የስነ-ስርዓት አካሄድ ሳይከተል በፍጥነት ጉዳዩን ለመቋጨት ያለመ ነው፡፡ የጠበቃ መኖር ክርክሩ የባሰ እንዲወሳሰብና ከተገቢው ጊዜ በላይ እንዲንዛዛ በማድረግ የክርክሩን ኢ-መደበኛ ባህርይ ያጠፋዋል፡፡ በአጠቃላይ አነጋገር በጠበቃ ውክልና ከሚታገዝ ይልቅ ባለጉዳዩ ራሱ የሚከራከርበት አስተዳደራዊ ክርክር በአጭር ጊዜ እልባት ያገኛል፡፡ ያም ሆኖ ግን ክርክር የሚካሄድበት ጉዳይ በባሉጉዳዩ መብትና ጥቅም ላይ ሊኖረው ከሚችለው አሉታዊ ውጤት አንጻር ማለትም የክርክሩን ክብደትና ውስብስነት መሰረት አድርጐ እንደየሁኔታው በጠበቃ የመወከል ጥያቄን ማስተናገድ ያስፈልጋል፡፡ምክንያታዊ ውሳኔዜጐች በሰውነታቸውና በንብረታቸው ላይ እርምጃ ሲወሰድ ከመንግስት ምክንያት ይሻሉ፡፡ አንዳችም ምክንያት የሌለው ውሳኔ የአስተዳደር በደል መገለጫ ነው፡፡ ኢ-ፍትሐዊነት በሁለት መልኩ ይገለጻል፤ የመጀመሪያው ምክንያት ሳይጠቀስ በደፈናው ውሳኔ ሲሰጥ፣ ሁለተኛው ደግሞ ውሳኔው በራሱ ፍርደገምድል፣ ሚዛናዊነት የጐደለውና በአሳማኝ ምክንያት ያልተደገፈ ሲሆን፡፡ለውሳኔ ምክንያት መስጠት በአስተዳደር ህግ ውስጥ ጉልህ ስፍራ እያያዘና እያደገ የመጣ መሰረተ ሀሳብ ነው፡፡ ያም ሆኖ ከአሜሪካው የአስተዳደር ስነስርዓት በስተቀር በእንግሊዝ ሆነ በህንድ ምክንያት እንዲሰጥ የሚያስገድድ በሁሉም የአስተዳደር አካላት ተፈጻሚ የሆነ ጠቅላላ ደንብ የለም፡፡ ሆኖም አልፎ አልፎ ማቋቋሚያው አዋጅ ለአስተዳደራዊ ውሳኔ ምክንያት እንዲሰጥ ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጣል፡፡አስተዳደራዊ ውሳኔ ሊኖረው የሚገባውን ይዘትና ቅርጽ በተመለከተ በ1967 ረቂቅ አዋጅ አንቀጽ 13 እንዲሁም በፌደራሉ ረቂቅ አዋጅ (1993 ዓ.ም.) አንቀጽ 32 ላይ ቅድመ ሁኔታዎቹ ተዘርዝረዋል፡፡ በዚሁ መሰረት አስተዳደራዊ ውሳኔ በጽሑፍ መሰጠት ያለበት ሲሆን ውሳኔውም የክርክሩን ፍሬ ነገር፣ የማስረጃዎች ፍሬ ጉዳይና ምንጭ፣ የነገሩን ጭብጥ አወሳሰን እንዲሁም በውሳኔው መሰረት ተመስርቶ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ የሚያመለክት መሆን ይኖርበታል፡፡ ምንም እንኳን በረቂቆቹ ላይ ‘ምክንያት’ የሚለው ቃል በግልጽ ባይጠቀስም የውሳኔ ምክንያትን የሚያያቋቁሙ ሁኔታዎች የተካተቱ እንደመሆኑ ምክንያት መስጠት እንደአስገዳጅ ሁኔታ ተቀምጧል ማለት እንችላለን፡፡በአንዳንድ አዋጆች ላይ ውሳኔን በምክንያት ማስደገፍ አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ለአብነት የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁ. 980/2008 አንቀጽ 6/2/ የንግድ ምዝገባ ማመልከቻ ውድቅ ከተደረገ መዝጋቢው አካል ምክንያቱን ገልጾ ለአመልካቹ ወዲያውኑ ማሳወቅ አለበት፡፡ከቀረጥ ዋጋ አወሳሰን ጋር በተያያዘ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ተጨማሪ መግለጫ ወይም ሰነድ ከዲክላራሲዮን አቅራቢው ከተቀበለ በኋላ ስለግብይት ዋጋው ትክክለኛነት ያለውን ጥርጣሬ ማስወገድ ካልቻለ ወይም ዲክላራሲዮን አቅራቢው ምላሽ ካልሰጠ በጉምሩክ አዋጅ ቁ. 859/2006 አንቀጽ 90 መሰረት ዋጋውን መወሰን እንዳልተቻለ ይቆጠራል፡፡ በዚሁ መሰረት የቀረበው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ተቀባይነት ያላገኘበት ምክንያት በጽሑፍ ለአስመጭው ወይም ለወኪሉ ይገለጽለታል፡፡cበነዳጅ አቅርቦት ስራ ለመሰማራት የተጠየቀ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ተቀባይነት ካላገኘ ምክንያቱ ለአመልካቹ ይገለጽለታል፡፡dየስደተኝነት ዕውቅና እንዲሰጥ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት ቢያገኝም ባያገኝም ውሳኔው ለአቅራቢው በጽሑፍ መገለጽ አለበት፡፡

You control the little person by law. The adult, however, is controlled by his own actions


You control the little person by law. The adult, however, is controlled by his own actions.Law is a good system.Enough prisons to enforce unpopular laws; There are not enough police forces and not enough courts. ትንሹን ሰው በህግ ትቆጣጠረዋለህ፡፡ ትልቅ ሰው ግን ሰናይ ምግባሩ ራሱ ይቆጣጠረዋል፡፡ሕግ ማለት መልካም ስርዓት ነው፡፡ሕዝብ ያልደገፈውን ህግ ለማስፈጸም በቂ እስር … Continue reading You control the little person by law. The adult, however, is controlled by his own actions

Ibu lewat!** Ada hari-hari yang sepertinya berlalu! Tapi kami telah melihat mereka lulus! Kita mengira ada malam dan siang, tetapi tidak ada siang dan malam yang tidak datang. Tapi ada prosesnya! Hal Ethiopia adalah tangisan ibu-ibu ini: Air mata akan mengalir! Hari ini berakhir untuk Ethiopia! Tidak diingat tapi hanya tertawa! **Luka dan bekas luka tidak sama sakitnya! Bekas Luka Bisa Mengingatkan Anda! Tapi lukanya masih sakit! Tapi bekas luka yang ditinggalkan oleh luka ini menyakitkan, tapi masih ada. Mari kita berpikir seperti manusia hari ini! Sebagai manusia, mari kita menangis untuk orang Etiopia! Mari kita singkirkan luka ini hari ini agar tidak menjadi bekas luka!.*Tesfish from Toronto!

በሀረሪ ሕዝብ ክልል መንግስት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ እና በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መካከል የምርጫ ጉዳይን አስመልክቶ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 207036 የሰጠው ውሳኔየሀረሪ ሕዝብ ክልል መንግሥት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ከክልሉ ውጭ የሚኖር የሐረሪ ሕዝብ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት አምስት አገራዊ ምርጫዎች በ6ኛው አገራዊ ምርጫም ከክልሉ ዉጭ ያሉ የብሔረሰቡ አባላት ለሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ሊመርጡ ይገባል በሚል ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን ማስተናገድ እንደማይቻል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡የሀረሪ ሕዝብ ክልል መንግሥት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ምርጫ ቦርዱ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም የይግባኝ ቅሬታውን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቧል፡፡ የፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 205809 ሚያዚያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ቦርዱ ከክልሉ ውጪ ያሉ ሐረሪዎች የመምረጥ መብትን አስቀድሞ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርግ ወስኗል፡፡በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይግባኝ ችሎቱ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ጉዳዩን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበ ቢሆንም የሰበር አቤቱታውን የተመለከተው የፍርድ ቤቱ ሰበር ችሎት በሰ/መ/ቁ 207036 ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ጉዳዩን በጥልቀት ከመረመረ በኋላ በሰጠው ውሳኔ የይግባኝ ሰሚ ችሎቱ የሰጠውን ወሳኔ አጽንቷል፡፡

ግልጽና ተጓዳኝ ስልጣን አብዛኛውን ጊዜ ለመንግስት አካላት የሚደለደለው ስልጣን አሻሚ ባልሆነ አነጋገር ይገለጻል፡፡


ግልጽና ተጓዳኝ ስልጣን
አብዛኛውን ጊዜ ለመንግስት አካላት የሚደለደለው ስልጣን አሻሚ ባልሆነ አነጋገር ይገለጻል፡፡

ግልጽና ቀጥተኛ ስልጣን በአስተዳደሩ ውስጥ ህጋዊነትን ያሰፍናል፡፡ በተጨማሪም ስልጣንን በመገልገል ረገድ ጥርጣሬና ብዥታን ያስወግዳል፡፡ በተግባር ሲታይ ግን ለውጤታማ አስተዳደር አስፈላጊ የሆኑትን ስልጣናትና ተግባራት መዘርዘር ያዳግታል፡፡ ስለሆነም በግልጽ ስልጣን ውስጥ አስፈላጊ የሆነ በዝምታ የሚተላለፍ ተጓዳኝ ስልጣን ይኖራል፡፡ አንድን ድርጊት ለመፈፀም ግልጽ የሆነ ስልጣን ሲሰጥ የድርጊቱ አካል የሆኑና ሌሎች አስፈላጊ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል በዝምታ የሚሰጥ ስልጣን ስለመኖሩ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የህጉን ዓላማና ግብ እንዲሁም የህጉን ድንጋጌዎች አነጋገር በጥልቀት መፈተሽ ይጠይቃል፡፡ ተጓዳኝ ስልጣን መኖሩን ለመወሰን የሚከተሉት ነጥቦች ግምት ውስጥ ይገባሉ፡፡የህጉ አነጋገር
ይህ የህግ አውጭውን ሀሳብ ለማወቅ ወሳኝነት አለው፡፡ ለምሳሌ የመንግስት እና የግል ድርጅት ሠራተኞች ኤጀንሲዎች በሚያስፈጽሟቸው አዋጆች መሰረት ለማናቸውም ዓይነት አበል ብቁ የሚያደርጉ ሁኔታዎች መሟላታቸውን የማረጋገጥና የአበሉን ዓይነትና መጠን የመወሰን ስልጣን አላቸው፡፡ ለአበል ብቁ የሚያደርጉ ሁኔታዎች በአዋጅ ቁ. 714/2003 እና 715/2003 የተለያዩ ድንጋጌዎች በዝርዝር ተለይተዋል፡፡ ኤጀንሲዎቹ እነዚህን ሁኔታዎች መኖራቸውን የመወሰን ስልጣናቸው ክርክር አያስነሳም፡፡ ለምሳሌ በአዋጅ ቁ. 714/2003 አንቀጽ 41 መሰረት ለሟች ሚስት ወይም ባል የሚከፈለው የጡረታ አበል ሟች ያገኝ ወይም ሊያገኝ ይችል የነበረው የጡረታ አበል 50 በመቶውን ነው፡፡ በዚሁ ድንጋጌ ላይ ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል በመቀበል ላይ እያሉ ጋብቻ ከፈጸሙ አበሉ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች ተመልክተዋል፡፡እነዚህን ጉዳዮች መወሰን በኤጀንሲዎቹ ስልጣን ስር ቢሆንም የባልነት ወይም ሚስትነት ጥያቄ በተነሳ ጊዜ ይህንን ማረጋገጥ ከስልጣናቸው ክልል በላይ ነው፡፡ ይህን መወሰን በመደበኛ የዳኝነት አካላት ስልጣን ስር ይወድቃል፡፡ ስለሆነም ‘ለአበል ብቁ የሚያደርጉ ሁኔታዎች’ የሚለው አነጋገር በሁለቱም አዋጆች ላይ መለኪያና መስፈርት የተቀመጠላቸውን ሁኔታዎች እንጂ በሌሎች ህጎች የሚወሰኑትን አያካትትም፡፡ የህግ አውጨው ሀሳብም ኤጀንሲዎቹ ለአበል ብቁ የሆኑ የሟች ሚስት ወይም ባል የሚከፈላቸውን መጠንና እና ክፍያውን የሚቋረጥባቸውን ሁኔታዎች እንዲወስኑ እንጂ ከመነሻው ባልነት ወይም ሚስትነትን በተመለከተ ማስረጃ አሰባስበው ውሳኔ እንዲሰጡ አይደለም፡፡
በግልጽ የተሰጠው ስልጣን ወሰን
ስልጣኑ በጠባቡ ከተሰጠ ተጓዳኝ ስልጣን ስለመኖሩ በጠባቡ መተርጐም ይኖርበታል፡፡ በአንጻሩ ሰፊ የሆነ ስልጣን በውስጡ አስፈላጊ የሆኑ ተጓዳኝ ስልጣናትን ያቅፋል፡፡
ለምሳሌ በተሽከርካሪ አደጋ የሶስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁ. 799/2005 አንቀጽ 13 ላይ እንደተመለከተው አንድ ተሽከርካሪ የመድን ተለጣፊ ምልክት ከሌለው የመድን ሽፋን እንደሌለው ስለሚያስቆጥረው የመድን ዋስትና ሰርተፊኬት እስኪመጣ ድረስ ፖሊስ ተሽከርካሪውን ይዞ የማቆየት ስልጣን አለው፡፡ በዚህ ድንጋጌ የፖሊስ የስልጣኑ ወሰን ጠባብ ነው፡፡ መኪናውን ከመያዝና ለማቆያ በተዘጋጀ ስፍራ ላይ ከማስቀመጥ ውጪ ሊወስድ የሚችለው ተጓዳኝ እርምጃ የለም፡፡
ይህንን የፖሊስ ስልጣን አካባቢንና ብክለትን የመቆጣጠር ኃላፊነት ካለባቸው አካላት ስልጣን ጋር ብናነጻጽረው ልዩነቱ በግልጽ ይታያል፡፡ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር ወይም የሚመለከተው የክልል ባለስልጣን በአካባቢ ላይ አደጋ እንዳያስከትል ከሚያሰጋ የስራ እንቅስቃሴ ሊመጣ የሚችል ጉዳትን ለመከላከል ድርጅትን እስከ መዝጋት ወይም ወደ ሌላ ቦታ እስከማዛወር የሚደርስ ማንኛውንም አስፈላጊ እርምጃ መውሰድ ይችላል፡፡ ድርጅትን እስከመዝጋትና ወደ ሌላ ቦታ እስከማዛወር የሚደርስ ስልጣን ድርጅቱን የማሸግና ሠራተኞች እንዳይገቡ የመከልከል እንዲሁም ጉዳት ለመቀነስ የሚያስፈልጉ ተጓዳኝ እርምጃዎችን የመውሰድ ስልጣን ጭምር ያካትታል፡፡
የህጉ ዓላማ
የህጉ አጠቃላይ ዓላማና ግብ በግልጽ ከተቀመጠው ስልጣን በተጨማሪ የህጉን ዓላማ ለማሳካት የሚረዱ ስልጣናት ስለመኖራቸው አመላካች ነው፡፡ ተጓዳኝ ስልጣን ሳይኖር የህጉን ዓላማ በተግባር ማሳካት የማይቻል ከሆነ በዝምታ የተሰጠ ስልጣን ስለመኖሩ ግምት ይወሰድበታል፡፡
የድርጊቱ ዓይነትና /ባህርይ/ ይዘት
በግልጽ የተሰጠው ስልጣን ማዕቀብ የሚጥል ድርጊት ወይም እርምጃ ከሆነ ተጓዳኝ ስልጣን ስለመኖሩ በጠባቡ መተርጐም ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ የመቆጣጠር ስልጣን በውስጠ ታዋቂነት የመከልከል ስልጣንን አይጨምርም፡፡

Reagan Foundation Asks Trump Campaign to Stop Using Reagan’s Name


The Washington Post reported that the Ronald Reagan Foundation asked the Trump campaign to stop using the former president’s name for the Trump campaign. Reagan Foundation to Trump, RNC: Quit Raising Money Off Ronald Reagan’s Legacy. The Ronald Reagan Presidential Foundation and Institute, which runs the 40th president’s library near Los Angeles, has demanded that […]

Reagan Foundation Asks Trump Campaign to Stop Using Reagan’s Name

Trump comments on the injury of his National Security Adviser to Corona


Right Now Times : US President Donald Trump said that recently he had “not seen” his National Security Adviser Robert O’Brien, who is infected with the Coronavirus. When asked by reporters on Monday, Trump said, “I haven’t seen him recently. I heard he tested. I didn’t see him.” He added that he does not know […]

Trump comments on the injury of his National Security Adviser to Corona

ምስክር።


<p class="has-drop-cap has-text-color" style="color:#002cdd" value="<amp-fit-text layout="fixed-height" min-font-size="6" max-font-size="72" height="80">ምስክሩ ለችሎቱ የመግቢያ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠ ነው፡፡ ስሙን፤ ዕድሜውን፤ መኖሪያ አድራሻውን ከተናገረ በኋላ ዳኛው <div><div>“የትምህርት ደረጃ?” ሲሉ ጠየቁት ፥፥፥፥፥ ምሰክር——“አቋርጫለው” ዳኛ——“ከስንት?”ምስክር——“ከ1ኛ ክፍል”</div></div>ምስክሩ ለችሎቱ የመግቢያ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠ ነው፡፡ ስሙን፤ ዕድሜውን፤ መኖሪያ አድራሻውን ከተናገረ በኋላ ዳኛው
“የትምህርት ደረጃ?” ሲሉ ጠየቁት ፥፥፥፥፥ ምሰክር——“አቋርጫለው” ዳኛ——“ከስንት?”ምስክር——“ከ1ኛ ክፍል”

Ide Sarapan (15): Pfannkuchen, Pancake dari Jerman yang Bisa Divariasikan Rasanya


Ide sarapan pagi berikut yang saya bagikan berasal dari negeri suami, Jerman. Resep ini sebetulnya mengingatkan saya pada crepes, jajanan yang sering saya beli dulu di Jakarta. Hanya saja, pancake ini tidak chruncy dan rasanya lebih empuk. Pancake asal Jerman ini disebut pfannkuchen. Saya beberapa kali memesannya di jajanan pekan budaya atau volkfest. Dan beberapa […]

Ide Sarapan (15): Pfannkuchen, Pancake dari Jerman yang Bisa Divariasikan Rasanya

አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስልጣን ባህርያትና የስልጣን 4-አስተዳደራዊ ድንጋጌ…


አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስልጣን ባህርያትና የስልጣን 4-አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስልጣንባህርያትና የስልጣን

አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስልጣን ባህርያትና የስልጣን 4-አስተዳደራዊ ድንጋጌ…

Modern Politics: Personality vs. Policy


One of the most intensely talked about topics in modern America is politics. Undeniably, political activism now seems to be everywhere and our day-to-day life has more political overtones than ever before. As a result, few areas of society are immune to the 24-7 political theatre playing out coast to coast. Some critics complain that […]

Modern Politics: Personality vs. Policy

በጫት ላይ የሚከፈለውን ታክስ አሰባሰብ ፍትሐዊነት ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (11) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡


በጫት ላይ የሚከፈለውን ታክስ አሰባሰብ ፍትሐዊነት ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (11) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “የጫት ኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 767/2004” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፦ “ታክስ” ማለት በኢትዮጵያ በሚካሄድ የጫት ግብይት ላይ በዚህ አዋጅ መሠረት የሚከፈል የኤክሳይዝ ታክስ ነው፤ “ታክስ ከፋይ” ማለት የጫት ኤክሳይዝ ታክስ ከፋይ ነው፤ “የታክስ ባለስልጣን” ማለት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ነው፤ “ሰው” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ቢሆንም ባይሆንም ማንኛውም ድርጅት ነው፤ “ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 47 የተመለከተው ማንኛውም ክልል ሲሆን የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ይጨምራል፤ “ሚኒስቴር” ማለት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ነው፡፡ ታክስ የመክፈል ግዴታ ጫትን በይዞታው ስር በማድረግ፣ በማጓጓዘ ወይም በማንኛውም መንገድ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሰው በዚህ አዋጅ የተወሰነውን ታክስ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ የታክሱ ማስከፈያ ልክ በአገር ውስጥ ተመርቶ በመነሻው ክልል ጥቅም ላይ የሚውልና ወደ ሌላ ክልል የሚጓጓዝ ጫት በኪሎ ግራም ብር 5 /አምስት ብር/ የኤክሳይዝ ታክስ ይከፈልበታል፡፡ የታክሱ ማስከፈያ ቦታ በዚህ አዋጅ በጫት ላይ የተጣለው ታክስ የሚሰበሰበው የታክስ ባለሥልጣኑ አግባብነት ካላቸው ክልሎች ጋር በመመካክር በሚወስናቸው ቦታዎች ይሆናል፡፡ ታክሱን የመሰብሰብ ኃላፊነት በዚህ አዋጅ መሠረት በጫት ላይ የተጣለውን ታክስ የሚሰበስበው የታክስ ባለስልጣኑ ይሆናል፡፡ የታክስ ባለሥልጣኑ በዚህ አዋጅ መሠረት ከጫት ላይ የሰበሰበውን ታክስ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት በተደነገገው መሠረት የገቢው ባለቤት ለሆኑ ክልሎች በየወሩ ያከፋፍላል። ለውጭ ገበያ ስለሚቀርብ ጫት በውጭ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ላኪዎች፡- ለውጭ ገበያ በሚያቀርቡት ጫት ላይ ሊከፈል ለሚገባው ታክስ ክፍያ የሚውል ቫውቸር በታክስ ባለስልጣኑ ይሰጣቸዋል፤ ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡትን ጫት በአገር ውስጥ በሚያጓጉዙበት ጊዜ በጫቱ ላይ ሊከፈል ከሚገባው ቀረጥና ታክስ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ቫውቸር በታክሱ ማስከፈያ ቦታ ለተመደበው የታክስ ባለስልጣኑ ሠራተኛ ያስረክባሉ፤ የቀረጥና ታክሱ ሂሳብ በቫውቸር የተከፈለበትን ጫት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ቫውቸሩን በየወሩ ከታክስ ባለስልጣኑ ዘንድ ቀርበው ማወራረድ አለባቸው። በውጭ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ላኪዎች ጫቱን ወደ ውጭ ያልላኩ ከሆነ ታክሱንና የታክሱን 25 በመቶ በመቀጫ መልክ የመክፈል ግዴታ አለባቸው። የታክስ ባለስልጣኑ የዚህን አንቀጽ ዝርዝር አፈፃፀም የሚወስን መመሪያ ያወጣል። ሌሎች ግብርና ታክሶችን የመክፈል ኃላፊነት ማንኛውም በጫት ንግድ ሥራ ላይ የተሠማራ ግብር ከፋይ በዚህ አዋጅ ከተጣለው የኤክሳይዝ ታክስ በተጨማሪ ፀንተው በሚሠራባቸው ሕጎች መሠረት ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶችን የመክፈል ኃላፊነት አለበት፡፡ የኤክሳይዝ አዋጅ ተፈጻሚነት በዚህ አዋጅ ባልተደነገጉ ጉዳዮች ላይ የኤክሳይዝ አዋጅ ቁጥር 307/1994 (እንደተሻሻለ) ተፈጻሚነት ይኖረዋል። የተሻሩና ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ሕጎች የጫት ግብርን ለማስከፈል የወጣው አዋጅ ቁጥር 309/1979 በዚህ አዋጅ ተሽሯል፡፡ ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ሕግ ወይም የአሰራር ልምድ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ የጫት ግብርን ለማስከፈል በወጣው አዋጅ መሠረት መከፈል ሲገባው ይህ አዋጅ በሥራ ላይ እስከዋለበት ቀን ድረስ ያልተከፈለ ታክስ በዚያው አዋጅ መሠረት ገቢ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል፡፡ ሚኒስቴሩ ይህን አዋጅና በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሚወጡ ደንቦችን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡

ደንብ ቁጥር 1/20


ደንብ ቁጥር 1/2001 የምርጫ ሕጎች2001 | የ10 ደቂቃ ንባብ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የመምረጥ እና ወይም የመመረጥ መብቱን በሥራ ላይ ሲያውል በምርጫ ሂደት የሚነሱ ክርክሮችን በወቅቱ በመፍታት ሁሉም ዜጋ ዲሞክራሲያዊ መብቱን በሥራ ላይ እንዲያውል ማስቻሉ ተገቢ በመሆኑ፣ ምርጫን ነፃና ፍትሃዊ ለማድረግ በምርጫ አፈጻጸም በየደረጃው የሚነሱ አቤቱታዎችን ተመልክቶ ወቅታዊ መፍትሄ የሚሰጥ በየደረጃው የሚቋቋመውን አካል አደረጃጀት እና አሠራር በመደንገግ በምርጫ ሂደት ለሚነሱ አቤቱታዎችና ክርክሮች አፈታት ግልጽ አሰራር ማስፈን በማስፈለጉ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በተሻሻለው የኢትዮጵያ ምርጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 19፣ አንቀጽ 19 ንዑስ አንቀጽ 12፣ አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 5፣ አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ 10፣ አንቀጽ 92 ንዑስ አንቀጽ 4 እና አንቀጽ 110 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል። ክፍል አንድ ጠቅላላ አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየደረጃው የሚቋቋም አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀትና አሠራር ደንብ ቁጥር 1/2001 ዓ.ም” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል። ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ፤ “ኢ.ፌ.ዲ.ሪ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነው። “የምርጫ ሕግ” ማለት የተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም. ነው። “ቦንድ” ማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ነው። “ተንቀሳቃሽ ወኪል” ማለት በምርጫ ለመወዳደር በተመዘገበ የፖለቲካ ድርጅት ወይም በግል እጩ ተወክሎ በአንድ ምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች እየተንቀሳቀሰ የምርጫ ሂደትንና የወከለውን ድርጅት ወይም የግል እጩ መብት መከበር የሚከታተል ሰው ነው። “ተቀማጭ ወኪል” ማለት በምርጫ ለመወዳደር በተመዘገበ የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል እጩ የሚወከልና በምርጫ ክልልና በምርጫ ጣቢያ ተቀምጦ የምርጫ ሂደትንና የወከለውን አካል መብት መከበርን የሚከታተል ሰው ነው። “የሕዝብ ታዛቢ” ማለት በእያንዳንዱ ምርጫ ክልል እና ምርጫ ጣቢያ ምርጫን እንዲታዘቡ በህዝብ የሚመረጡ ገለልተኛ የአካባቢ ነዋሪዎች ናቸው። “ክልል” ማለት በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 47 መሠረት የተቋቋመ ክልል ሲሆን ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል አዲስ አበባንና ድሬዳዋን ይጨምራል። “የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት” ማለት በምርጫ ሕጉ መሠረት በክልል ደረጃ ምርጫን የሚያስተባብር በቦርዱ በቋሚነት የሚቋቋም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ነው። “አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ” ማለት በየደረጃው በሚገኝ በክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት፣ ምርጫ ክልል እና የምርጫ ጣቢያ ለሚነሱ ቅሬታዎች አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሰጥ በምርጫ ህጉ እና በዚህ ደንብ መሠረት ለምርጫ ወቅት የሚቋቋም ኮሚቴ ነው። “የምርጫ ክልል” ማለት ለምርጫ አፈጻጸም እንዲያመች እና ህዝቡ ወኪሎቹን እንዲመርጥ በሕግ መሠረት የሀገሪቱ ግዛት ተከፋፍሎ የሚደራጅ የምርጫ አካባቢ ነው። “የምርጫ ጣቢያ” ማለት በየደረጃው በሚካሄዱ ምርጫዎች ምዝገባ የሚካሄድበት፣ መራጮች ድምፅ የሚሰጡበት እና ቆጠራ የሚካሄድበት ቦታ ነው። “የምርጫ አስፈጻሚ” ማለት በየደረጃው ለሚካሄዱ ምርጫ በተቋቀሙ የምርጫ ጽሕፈት ቤቶች በቋሚነት፣ በኮንትራት ወይም በጊዜያዊነት ተመድቦ በህግ መሠረት ምርጫን የሚያስፈጽም ሰው ነው። “አቤቱታ” ማለት በየደረጃው ለሚገኙ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አካላት በጽሑፍ የሚቀርብ ቅሬታ ነው። “ይግባኝ” ማለት በየደረጃው በሚገኙ የበታች አቤቱታ ሰሚ አካላት ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ሰው በዚህ ደንብና ቦርዱ ባዘጋጀው ቅጽ መሠረት በጽሑፍ ለበላይ አቤቱታ ሰሚ አካል የሚቀርብ አቤቱታ ነው። “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው። አተረጓጎም በዚህ ደንብ ለሚፈጠር የህግ ክፍተት የኢፌዲሪ ህገመንግሥትን እና የተሻሻለውን የኢትዮጵያ ምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም ጋር በማጣጣም መተርጎም አለበት። የተፈጻሚነት ወሰን ይህ ደንብ በምርጫ ህጉ መሠረት በየደረጃው በሚካሄዱ ምርጫዎች ለሚነሱ ቅሬታዎች ተፈጻሚ ይሆናል። የጾታ አገላለፅ በዚህ መመሪያ ውስጥ በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም ፆታ ያካትታል። ክፍል ሁለት ስለአቤቱታ ሰሚ አካል አደረጃጀት ጠቅላላ ቦርዱ በምርጫ ህጉ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 11 መሠረት በምርጫ ሂደት ለሚከሰቱ አለመግባባቶች አስተዳደራዊ መፍትሄ የመስጠት፣ ጉድለቶችን የማረምና ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን አለው። ለቦርዱ በመጀመሪያ ደረጃ ወይም በይግባኝ የሚቀርቡ አቤቱታዎች በምርጫ ህጉ ላይ በተደነገገው እና ቦርዱ የራሱን አሠራር እና የስብሰባ ስነስርዓት አስመልክቶ በሚያወጣው ደንብ መሠረት መርምሮ ውሳኔ ይሰጥባቸዋል። ቦርዱ ለሚቀርቡለት አቤቱታዎች በወቅቱ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችለው አሠራር በየደረጃው በሚገኙ የምርጫ ጽሕፈት ቤቶች ይዘረጋል። በምርጫ ሂደት በየደረጃው ስለሚኖሩ አቤቱታ ሰሚ አካላት ቦርዱ በምርጫ ህጉ እና በዚህ ደንብ መሠረት የሚከተሉት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴዎች በየደረጃው እንዲቋቋሙ ያደርጋል፤ የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ፣ የምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ፣ የምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ፣ የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀት በምርጫ ህጉ አንቀጽ 19(12) መሠረት እያንዳንዱ የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ያደራጃል። የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ፣ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ሶስት ይሆናሉ። የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ በመሆን ያገለግላል። የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከቦርዱ ጋር በመመካከር ከክልሉ የሕዝብ ታዛቢዎች መካከል ሁለት አባላት በቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይመደባሉ። ከህዝብ ታዛቢዎች መካከል የሚመረጡት የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት በተቻለ መጠን የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በተገቢው ሁኔታ በመመርመር ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል እውቀትና ልምድ ያላቸው እንዲሆኑ ይደረጋል። የምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀት በምርጫ ህጉ አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 5 ድንጋጌ መሠረት፤ በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ሦስት አባላት ያሉት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ያደራጃል። የምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ያገለግላል። የምርጫ ክልሉ ሁለት ታዛቢዎች የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባል ይሆናሉ። ከላይ በ ‘ሐ’ የተጠቀሱት ሁለት ታዛቢዎች በምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይሰየማሉ። ከሕዝብ ታዛቢዎች መካከል የሚመረጡት የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት በተቻለ መጠን የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በተገቢው ሁኔታ በመመርመር ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል እወቀትና ልምድ ያላቸው እ ንዲሆኑ ይደረጋል። የምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀት በምርጫ ህጉ አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ 1ዐ ድንጋጌ መሠረት፤ እያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያ ሦስት አባላት የያዘ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ያደራጃል። የምርጫ ጣቢያው የምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ይሠራል። የምርጫ ጣቢያው ሁለት የህዝብ ታዛቢዎች የምርጫ ጣቢያው የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባል ይሆናሉ። ከላይ በ ‘ሐ’ የተጠቀሱት ሁለት ታዛቢዎች በምርጫ ጣቢያው ኃላፊ ይሰየማሉ። ከሕዝብ ታዛቢዎች መካከል የሚመረጡት የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት በተቻለ መጠን የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በተገቢው ሁኔታ በመመርመር ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል እውቀትና ልምድ ያላቸው እንዲሆኑ ይደረጋል። ከአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ስለመነሳት ማንኛውም የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለኮሚቴው የቀረበን አቤቱታ ቀደም ሲል በሥራው ምክንያት ያየውና ውሳኔ የተሰጠበት ከሆነ በአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነቱ ተሰይሞ ለማየት አይችልም። ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ሁኔታ ሲከሰት ከሌሎቹ የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ ተተክቶ ጉዳዩን በጊዜያዊ ሰብሳቢነት እንዲያይ ይደረጋል። ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ሁኔታ የተከሰተው በክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሲሆን ከቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች አንዱ ተተክቶ በጊዜያዊ ሰብሳቢነት እንዲያይ ይደረጋል። ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ጉዳይ ውሳኔ ካገኘ በኋላ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ መደበኛ የሰብሳቢነት ሥራውን ይቀጥላል። የተጓደሉ አቤቱታ ሰሚ አባላትን ስለመተካት የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት በተለያየ ምክንያት ሲጓደሉ ወዲያውኑ መተካት አለባቸው። የተጓደሉት አባላት የሚተኩት በሚከተለው አሠራር ይሆናል፤ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ሲጓደሉ ወዲያውኑ በክልሉ ውስጥ ከተመረጡ የሕዝብ ታዛቢዎች መካከል በክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አማካኝነት ይተካሉ። የተጓደለው አባል የምርጫ ክልሉ ኃላፊ ሲሆን ከምርጫ ክልሉ እንዲሁም ከምርጫ ጣቢያው ሲሆን ከምርጫ ጣቢያ የምርጫ አስፈጻሚዎች መካከል አንዱ ተክቶ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴን በሰብሳቢነት ይመራል። የተጓደለው አባል ከሕዝብ ታዛቢዎች የተመረጠው ከሆነ በሰብሳቢው አማካኝነት ከቀሩት ታዛቢዎች መካከል አንዱ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው አባል ሆኖ እንዲተካ ይደረጋል። የተጓደለው ታዛቢ በተጠባባቂ ታዛቢነት ተመርጠው ከተያዙት ውስጥ ከፍተኛ ድምጽ ያለው እንዲተካ ይደረጋል። ክፍል ሦስት አቤቱታ ሰሚ አካላት በምርጫው ሂደት ለሚነሱ ቅሬታዎች ውሳኔ የሚሰጡበት አሠራር በመራጮች ምዝገባ ሂደት ስለሚነሱ ክርክሮች በመራጮች ምዝገባ ሂደት የሚነሱ ክርክሮች በምርጫ ሕጉ አንቀጽ 93 መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሁኔታ ውሳኔ ያገኛሉ፤ ማንኛውም ሰው በመራጭነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ሲያጋጥመው ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታውን አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው። መብት የሌለው ወይም በመራጭነት መመዝገብ የሌለበት ሰው ያለአግባብ ተመዝግቧል የሚል ተቃውሞ ያለው ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ተቃውሞውን ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው። የምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረቡለትን አቤቱታዎች መርምሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሣኔ ያሰጣል። የምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 ለቀረበለት አቤቱታ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ካልሰጠ፤ በመራጭነት ከመመዝገብ የተከለከለ ሲሆን በአቤቱታ አቅራቢው ጥያቄ እንደተስማማ ይቀጠራል። ለአቤቱታ አቅራቢው ይህንኑ የሚገልፅ ማስታወሻ ይሰጠዋል። ምርጫ ጣቢያውም በማስታወሻው መሠረት ይመዘግበዋል። አቤቱታው በመራጭነት መመዝገብ የሌለበት ሰው ያለአግባብ ተመዝግቧል የሚል ሲሆን አቤቱታ አቅራቢው ለምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በ48 ሰዓት ውስጥ ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው። በምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሚቀርብ ይግባኝ ውሣኔ ከተሰጠበት በ48 ሰዓት ውስጥ መቅረብ አለበት። የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ይግባኝ መርምሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል። የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ለወረዳው ፍርድ ቤ ት በ24 ሰዓት ውስጥ ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው። የወረዳው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔም የመጨረሻ ይሆናል። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 መሠረት የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ለቀረበለት ይግባኝ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ካለሰጠ፤ አቤቱታው ለመራጭነት ከመመዝገብ የተከለከለን ሰው ሲሆን በአቤቱታ አቅራቢው ጥያቄ እንደተስማማ ይቆጠራል። ለአቤቱታ አቅራቢው ይህንኑ የሚገለፅ ማስታወሻ ይሰጠዋል። ምርጫ ጣቢያውም በማስታወሻው መሠረት ይመዘግበዋል። ይግባኙ በመራጭነት የተመዘገበን ሰው በመቃወም ሲሆን ይግባኝ ባዩ በ24 ሰዓት ውስጥ ለወረዳ ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው። የወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል። የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት የምርጫ ጣቢያው ጽሕፈት ቤት ሥራውን ያከናውናል። በመራጭነት ከመመዝገብ በተከለለ ሰው የሚቀርብ አቤቱታ የመራጮች የምዝገባ የጊዜ ሠሌዳ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ይሆናል። የተመዘገበን መራጭ በመቃወም የሚቀርብ አቤቱታ ከመራጮች የምዝገባ ቀን ጀመሮ የመራጮች መዝገብ ለሕዝብ ይፋ የሚሆንበት ጊዜ እስከሚያልቅ ድረስ ይሆናል። በዕጩዎች ምዝገባ ሂደት ስለሚነሱ ክርክሮች በዕጩዎች ምዝገባ ሂደት የሚነሱ ክርክሮች በምርጫ ህጉ አንቀጽ 94 መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሁኔታ ውሳኔ ያገኛሉ፤ ማንኛውም ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት በዕጩነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ሲያጋጥመው ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታውን በፅሑፍ አቅርቦ መልስ የማግኘት መብት አለው። አንድ ዕጩ በዕጩነት መቅረብ የለበትም የሚል ተቃውሞ ያለው ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታውን በፅሑፍ አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው። የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮማቴ የቀረበለትን አቤቱታ መርምሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል። የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2 ለቀረበለት አቤቱታ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ካልሰጠ፤ በእጩነትት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ያጋጠመው ሰው ሲሆን የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በአቤቱታ አቅራቢው ጥያቄ እንደተስማማ ይቆጠራል። ለአቤቱታ አቅራቢው ይህንኑ የሚገልፅ ማስታወሻ ይሰጠዋል። አቤቱታ አቅራቢው ከአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው የተሰጠውን ማስታወሻ ለምርጫ ክልሉ በማቅረብ በእጩነት ይመዘገባል። አቤቱታው አንድን ዕጩ በእጩነት መቅረብ የለበትም የሚል ተቃውሞ ሲሆን አቤቱታ አቅራቢው በ72 ሰዓት ውስጥ ለክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል። ለዕጩነት ከመመዝገብ የተከለከለ የፖለቲካ ድርጅት ዕጩ ወይም የግል ዕጩ እንዲሁም የአንድን ዕጩ ምዝገባ የሚቃወም ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት የምርጫ ክልሉን አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ በመቃወም ለክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በ72 ሰዓት ውስጥ ይግባኝ ለማቅረብ ይችላል። የክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ ሲቀርብለት በ48 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል። በክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ይግባኝ ባይ ይግባኙን ውሳኔ ከተሰጠበት ጊዜ አንስቶ በ48 ሰዓት ውስጥ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል። ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል። ለክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ይግባኝ መርምር በ48 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ካልሰጠ፣ አቤቱታው በዕጩነት ከመመዝገብ የተከለከለው ሲሆን በይግባኝ አቅራቢው ጥያቄ እንደተስማማ ይቆጠራል። ለአቤቱታ አቅራቢው ይህንኑ የሚገልፅ ማስታወሻ ይሰጠዋል። አቤቱታ አቅራቢው ከአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው የተሰጠውን ማስታወሻ ለምርጫ ክልሉ በማቅረብ ይመዘገባል። የቀረበው ይግባኝ የአንድን ዕጩ ምዝገባ በመቃወም ሲሆን ይግባኝ ባዩ በ48 ሰዓት ውስጥ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው። የክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት የምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤት ሥራውን ያከናውናል። በዕጩነት ከመመዝገብ የተከለከለን የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል ዕጩን በሚመለከት የሚቀርብ አቤቱታ የዕጩ ምዝገባ የጊዜ ሠሌዳ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ይሆናል። የአንድን ዕጩ ምዝገባ በመቃወም የሚቀርብ አቤቱታ ከዕጩዎች የምዝገባ ቀን ጀምሮ የተመዘገቡ ዕጩዎች ይፋ እስከሚሆንበት ቀን ድረስ ይሆናል። በድምፅ አሰጣጥ ሂደት ስለሚነሱ ክርክሮች በድምፅ አሰጣጥ ሂደት የሚነሱ ክርክሮች በምርጫ ህጉ አንቀጽ 95 መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሁኔታ ውሳኔ ያገኛሉ፣ አንድ መራጭ ድምፅ ከመስጠት የሚያግደው ሁኔታ ሲፈጠር ወይም በመራጭነት መብቱ ላይ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቅሬታውን ወዲያውኑ ለምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በፅሑፍ በማቅረብ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው። የምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴውም፦ ጊዜያዊ ድምፅ እንዲሰጥ በማድረግ ጉዳዩን ወደ ምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት በመላክ ውሳኔ እንዲያገኝ ሊያደርግ ይችላል ወይም ጊዜያዊ ድምፅ መስጠት የለበትም ብሎ ሊወስን ይችላል። ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2 (ሀ) መሠረት ጊዜያዊ ድምፅ የሰጠ መራጭ ከምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ወይም እንደ ሁኔታው ከወረዳው ፍርድ ቤት የመምረጥ መብት እንዳለው የሚገልፅ ውሳኔ የድምፅ ማዳመሩ ከመጠናቀቁ በፊት ለምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት ካላቀረበ የሰጠው ጊዜያዊ ድምፅ ውድቅ ይደረጋል። ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2(ለ) የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት የሚቀርብ አቤቱታ የድምፅ መስጫ ሰዓት ለማለቁ በፊት ውሳኔ ማግኘት ይኖርበታል። ምርጫ ጣቢያውም በውሳኔው መሠረት ይፈፅማል። በምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ጊዜያዊ ድምፅ ከመስጠት የተከለከለ ሰው ወዲያውኑ ይግባኙን ለወረዳው ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል። የወረዳው ፍርድ ቤት የድምፅ መስጫው ሰዓት ከመጠናቀቁ በፊት ውሳኔ ይሰጣል፣ ውሳኔውም የመጨረሻ ይሆናል። ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2 “ለ” መሠረት ጊዜያዊ ድምፅ መስጠት የለበትም የተባለ ይግባኝ አቅራቢ በምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ወይም በወረዳው ፍርድ ቤት ድምፅ እንዲሰጥ ከተወሰነ፤ የድምፅ መስጫ ሰዓት ከመጠናቀቁ በፊት ለምርጫ ጣቢያው ውሳኔውን ካላቀረበ ድምፅ ሊሰጥ አይችልም። ከላይ በዚህ ንዑስ አንቀጽ “ሀ” የተደነገገው ቢኖርም የምርጫ ጣቢያው ተዘግቶ እና በምርጫ ጣቢያው በግቢ ውስጥ የተሰለፉ መራጮች ድምፅ በመስጠት ላይ ባሉበት ጊዜ ውሳኔውን ይዞ ከደረሰ እንዲመርጥ ይደረጋል። የአንድን መራጭ ድምፅ መስጠት የሚቃወም ሰው ከላይ በተደነገገው መሠረት አቤቱታውን በየደረጃው በፅሑፍ የማቅረብና ውሳኔ የማግኘት መብት አለው። ከላይ በንዑስ አንቀጽ 7 መሠረት የሚወሰን ውሳኔ እንደሁኔታው በዚህ አንቀፅ ከንዑስ አንቀጽ 2 እስከ 6 ባለው ድንጋጌ መሠረት ይፈፀማል። በቆጠራ ሂደትና ውጤት ስለሚነሱ ክርክሮች በቆጠራ ሂደትና ውጤት የሚነሱ ክርክሮች በምርጫ ህጉ አንቀጽ 96 መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሁኔታ ውሳኔ ያገኛሉ፤ በድምፅ ቆጠራ ሂደትና በውጤት ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል ዕጩ ወይም ወኪል ቅሬታውን ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አስመዝግቦ ይህንኑ ቅሬታ በ48 ሰዓት ውስጥ ለምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ከነማስረጃው በጽሑፍ ሊያቀርብ ይችላል። ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ቅሬታ የሚያቀርብ ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል ዕጩ ወይም ወኪል፤ ለምርጫ ጣቢያ ቅሬታ ያስመዘገበበትን ማስረጃ ከሚያቀርበው አቤቱታ ጋር ማያያዝ አለበት። ቅሬታ አቅራቢው በምርጫ ጣቢያ ካስመዘገበው ጭብጥ ውጪ የሆነ አዲስ ነገር ማቅረብ አይችልም። የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበለትን አቤቱታ እና ማስረጃ መርምሮ በ48 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል። የምርጫ ክልሉ ውሳኔ፤ ቅሬታ የቀረበበት ቆጠራ እንደገና እንዲካሄድ ወይም ቅሬታ የቀረበበት ቆጠራ ትክክል ስለሆነ ቅሬታው አግባብነት የለውም የሚል ሊሆን ይችላል። በቆጠራ ላይ የቀረበው ቅሬታ የምርጫ ክልሉን አጠቃላይ ውጤት በመሠረቱ የማይለውጠው ከሆነ ድጋሚ ቆጠራ ማካሄድ አያስፈልግም ብሎ ሊወሰን ይችላል። ሌላ አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነበትን ውሳኔ በህጉ መሠረት ሊወሰን ይችላል። የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ አቤቱታ አቅራቢ ውሳኔ በተሰጠው በ5 ቀን ውስጥ ይግባኝ ለቦርዱ ማቅረብ ይችላል። ቦርዱ የቀረበውን ይግባኝ መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል። ይግባኝ ባዩ ቦርዱ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም በ5 ቀን ውስጥ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይችላል። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ከላይ በንዑስ አንቀጽ 6 መሠረት ለቀረበለት ይግባኝ በተቻለ ፍጥነት ውሳኔ ይሰጣል። ውሳኔውም የመጨረሻ ይሆናል። የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ተግባርና ኃላፊነት በየደረጃው የሚገኝ የምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፤ በምርጫ ህጉ እና በዚህ ደንብ መሠረት በያለበት ደረጃ ለሚቋቀም አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ያገለግላል። በዚህ ደንብ መሠረት የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላትን ይሰይማል። ለአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ሥራ ያከፋፍላል። የሥራ ክፍፍሉ በቃለ- ጉባኤ ተመዝግቦ እንዲያዝ ያደርጋል። የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ውይይት እና ውሳኔ በቃለጉባኤ እንዲያዝና ለሚመለከተው አካል እንዲላክ ያደርጋል። ማናቸውንም ሰነዶች በአግባቡ እንዲጠበቁ ያደርጋል። ይግባኝ የማቅረብ መብት ላለው ሰው የተሟላ ሰነድ በመስጠት በይግባኝ መብቱ እንዲጠቀም ያደርጋል። በየደረጃው የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ከተመደቡ ሰዎች አንደኛው አባል በተደራቢነት በቃለጉባኤ ያዥነት በኮሚቴው ሰብሳቢ ተመድቦ የኮሚቴውን ቃለ ጉባኤዎች እና ውሳኔዎች በጽሁፍ ይይዛል። የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት በአቤቱታ የቀረበላቸውን ጉዳይ በመመርመር አፋጣኝ እና ህጋዊ ውሳኔ የመስጠት ኃላፊነት አለባቸው። ክፍል አራት ስለአቤቱታ አቅራቢ፣ አቤቱታ አቀራረብ እና አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አሠራር ስለ አቤቱታ አቅራቢ በምርጫ ህጉ አንቀጽ 79፣ 90 እና 91 ከተደነገገው በስተቀር የሚከተሉት አካላት ወይም ሰዎች የምርጫውን ሂደት አስመልክቶ አቤቱታ በፅሑፍ የማቅረብና በየደረጃው ውሳኔ የማግኘት መብት አላቸው። ማንኛውም ሰው በመራጭነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ሲያጋጥመው ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታውን አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው። በመራጭነት ለመመዝገብ መብት የሌለው ወይም በመራጭነት ለመመዝገብ ብቁ ያልሆነ ሰው ያለአግባብ ተመዝግቧል የሚል ተቃውሞ ያለው ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ተቃውሞውን ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው። ማንኛውም ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት በእጩነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ሲያጋጥመው ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታውን አቅርቦ መልስ የማግኘት መብት አለው። አንድ እጩ በእጩነት መቅረብ የለበትም የሚል ተቃውሞ ያለው ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታውን አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው። አንድ መራጭ ድምፅ ከመስጠት የሚያግደው ሁኔታ ሲፈጠር ወይም በመራጭነት መብቱ ላይ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቅሬታውን ወዲያውኑ ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በማቅረብ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው። በድምፅ ቆጠራ ሂደትና በውጤት ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል እጩ ወይም ወኪል ቅሬታውን ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አስመዝግቦ ይህንኑ ቅሬታ በ48 ሰዓት ውስጥ ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሊያቀርብ ይችላል። የአቤቱታ አቀራረብ እያንዳንዱ አቤቱታ አቅራቢ የሚያቀርበው አቤቱታ በፅሁፍ ሆኖ ሌላ አከራካሪ ጉዳይ በማያስከትል ሁኔታና ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት በሚያስችል መልክ ተዘጋጅቶ፤ አቤቱታው የተፃፈበት ቀን እና ሰዓት፣ የአቤቱታ አቅራቢውን ሙሉ ስምና አድራሻ፣ ለአቤቱታ መነሻ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ፣ እየተጠየቀ ያለውን መፍትሄ፣ የማስረጃ ዝርዝር፣ የሚቀርበው የሰው ማስረጃ በሆነ ጊዜ የምስክሮቹን ማንነት ዝርዝር እና አቤቱታው የሚቀርብበት አካል በግልፅ ያመላከተ መሆን አለበት። ለአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሚቀርብ አቤቱታ ወይም ይግባኝ ቦርዱ ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው ቅፅ በሶስት ቅጂ ተዘጋጅቶተ በአቤቱታ አቅራቢው መፈረም አለበት። ማንኛውም አቤቱታ በአቤት ባዩ ወይም በሕጋዊ ወኪሉ መቅረብ ይኖርበታል። አቤቱታ አቅራቢው የማያነብ እና ወይም የማይፅፍ ከሆነ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው አቤቱታው በቃል እንዲቀርብ በማድረግ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው አባላት በተገኙበት፤ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው የአቤቱታ አቅራቢውን ቃል ሰምቶ በጽሁፍ ይመዘግባል። የአቤቱታ አቅራቢውን ቃል ከላይ በዚህ ንዑስ አንቀጽ “ሀ” መሠረት ሲመዘግብ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን መስፈርት ያሟላ እንዲሆን ያደርጋል። ከላይ በዚህ ንዑስ አንቀጽ “ለ” መሠረት ወደ ጽሑፍ የተለወጠው አቤቱታ ለአቤቱታ አቅራቢው ተነቦለት በፅሁፍ ወይም በጣት አሻራ ወይም ጣት የሌለው ከሆነ በሚችለው ሌላ ምልክት እንዲፈርምበት ያደርጋል። ማንኛውም አቤቱታ ወይም ይግባኝ ለሚመለከተው አካል ከቀረበ በኋላ አቤቱታ አቅራቢው ወይም ይግባኝ ባዩ ወይም ህጋዊ ወኪሉ ጉዳዩን እንደማይቀጥልበት ወይም እንዳቋረጠ በፅሁፍ ከገለፀ አቤቱታ ወይም ይግባኝ ሰሚው አካል ይህንኑ ፅሁፍ ከአቤቱታው ወይም ከይግባኙ ጋር በማያያዝ በአጭር ቃለ ጉባኤ ጉዳዩን ይዘጋል። አቤቱታ ስለመቅረቡ የሚሰጥ ማስረጃ በየደረጃው ያለ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በማንኛውም ሰው ወይም አካል አቤቱታ ሲቀርብለት በዚህ ደንብ አንቀፅ 19 ያለውን መመዘኛ ያሟላ መሆኑን በማረጋገጥ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ለአቤቱታ መረከቢያ ማረጋገጫነት የተዘጋጀውን ቅፅ ሞልቶ በመፈረም ለአቅራቢው ይሰጠዋል፤ የአቤቱታ መረከቢያ ማረጋገጫ ቅፅም፤ አቤቱታው ገቢ የተደረገበት ቀንና ሰዓት፣ አቤቱታው የቀረበለትን አካል፣ አቤቱታው በዚህ ደንብ አንቀጽ 19 ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን ያሟላ መሆኑን፣ የአቤቱታውን መነሻ በአጭሩ እና የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ስምና ፊርማ መያዝ ይኖርበታል። ስለ ይርጋ ማንኛውም አቤቱታ ወይም ይግባኝ ሊቀርብ የሚችለው በምርጫ ህጉ መሠረት ሆኖ፤ በዚህ ደንብ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ መሠረት በመራጭነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ያጋጠመው ሰው በሆነ ጊዜ የመራጮች የምዝገባ የጊዜ ሠሌዳ እስከሚጠናቀቅበት ቀን ይሆናል። በዚህ ደንብ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ መሠረት መብት የሌለው ሰው ወይም በመራጭነት መመዝገብ የሌለበት ሰው ያለአግባብ ተመዝግቧል የሚል ሲሆን ከመራጮች የምዝግባ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ የመራጮች መዝገብ ለሕዝብ ይፋ እስከሚሆንበት የመጨረሻ ቀን ድረስ ይሆናል። በእጩነት ከመመዝገብ የተከለከለን የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል እጩን በሚመለከት ሲሆን የእጩ ምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ይሆናል። የአንድን እጩ ምዝገባ በመቃወም የሚቀርብ ሲሆን ከእጩዎች ምዝገባ ቀን ጀምሮ የተመዘገቡ እጩዎች ይፋ እስከሚሆኑበት ቀን ድረስ ይሆናል። በዚህ ደንብ አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ መሠረት አንድ መራጭ ድምፅ ለመስጠት የሚያግደው ሁኔታ ሲፈጠር ወይም በመራጭነት መብቱ ላይ ተቃውሞ ሲቀርብ እና ከተጣራ በኋላ ለማዳመር ወይም ለመጣል ጊዜያዊ ድምፅ በፖስታ እንዲሰጥ ከተደረገ የድምፅ ማዳመሩ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ሊያቀርብ ይችላል። ከላይ በንዑስ አንቀጽ 5 መሠረት ድምፅ ለመስጠት የሚያግደው ሁኔታ ተፈጥሮ ወይም በመራጭነት መብቱ ላይ ተቃውሞ በመቅረቡ ጊዜያዊ ድምፅ መስጠት የለበትም ተብሎ ሲወሰን የድምፅ መስጫ ሰዓት ከማለቁ በፊት ድረስ ውሳኔ እንዲሰጠው ማቅረብ ይኖርበታል። የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ስብሰባና ውሳኔ አሠጣጥ በየደረጃው የሚቋቋም የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ስብሰባ በሙሉ አባላት ይካሄዳል። የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የአቤቱታ አቅራቢውን አቤቱታና ማስረጃ እና አቤቱታ የቀረበበትን አካል ወይም የምርጫ አስፈጻሚውን ክፍል ምክንያትና መልስ ከሰማ እና የቀረበለትን ማስረጃ ካገናዘበ በኋላ ውሳኔ ይሰጣል። አቤቱታ አቅራቢውም ሆነ ቅሬታ የቀረበበት ሰው በኮሚቴው የመሰማት፣ ማስረጃውን የማሰማትና ራሱን የመከላከል መብት አለው። አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበለትን አቤቱታ ከመረመረ በኋላ በተባበረ ድምፅ ወይም በድምፅ ብልጫ ውሳኔ ይሰጣል። ድምፅ እኩል ከተከፈለ ሰብሳቢው የደገፈው ወገን የኮሚቴው ውሳኔ ይሆናል። የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው አቤቱታ የቀረበበት የምርጫ አስፈጻሚ ወይም አካል መልስ እንዲሰጥ አስፈላጊ አይደለም ብሎ ሲያምን ወይም መልስ መስጠት ሳይችል ሲቀር የአቤቱታ አቅራቢውን አቤቱታና ማስረጃ በመመርመር ብቻ ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል። የሀሳብ ልዩነት ያለው የኮሚቴ አባል ልዩነቱ በአጭሩ እንዲመዘገብለት ሊያደርግ ይችላል። ማንኛውም አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የውይይት ቃለ ጉባኤውን ወይም የሚሰጠውን ውሳኔ በጋራ ፊርማ ማረጋገጥ አለበት። የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ የሚከተሉትን አካቶ የያዘ መሆን ይኖርበታል፤ አቤቱታው የቀረበለትን ኮሚቴ ስም እና አድራሻ፣ የኮሚቴውን አባላት ስም ዝርዝርና ፊርማ፣ የአቤቱታ አቅራቢውን ሙሉ ስምና አድራሻ፣ የማስረጃዎች ይዘት እና/ወይም የምስክሮች ቃል በአጭሩ፣ ምክንያታዊ የሆነ የውሳኔ ሀተታ፣ በውሳኔው መሠረት መወሰድ ስለሚኖርበት እርምጃ እና ውሳኔው የተሰጠበት ቀንና ሰዓት። እያንዳንዱ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ፤ የቀረበን አቤቱታ ከቀረበለት ማስረጃ ጋር በማገናዘብ ይመረምራል፣ ውሳኔውንም በፅሁፍ ያሰፍራል። ከቀረበለት አቤቱታ ጋር ግንኙነት ያለው ወይም ያገባኛል ባይ ጥያቄ ሲያቀርብ ከአቤት ባዩ ጋር አብሮ እንዲሰማ እድል ሊሰጥ ይችላል። አቤቱታ ሰሚው ጥያቄ ሲያቀርብ ኮሚቴው በራሱ አስተያየት አቤቱታ አቅራቢውን እና አቤቱታ የቀረበበትን ወይም ውሳኔ ለመስጠት ይረዳኛል የሚለውን ሰው ጠርቶ ሊጠይቅ ወይም አስፈላጊ ማስረጃ እንዲቀርብለት ሊያደርግ ይችላል። አቤቱታ ሲቀበል መቼና በስንት ሰዓት እንደሚታይ እና የት እንደሚታይ እንዲሁም ውሳኔ መቼ እንደሚሰጥ ለአቤቱታ አቅራቢውና ለሚመለከታቸው ማሳወቅ አለበት። በየደረጃው የሚገኝ አቤቱታ ሰሚ አካል የቀረበለትን አቤቱታ ከተመለከተ በኋላ ውሳኔውን አቤቱታ ላቀረበው ሰው ወይም አካል በወቅቱ ማሳወቅ አለበት። የእያንዳንዱ አቤቱታ ውሳኔ በሶስት ቅጂ ተዘጋጅቶ፤ አንዱ ቅጂ ለአቤቱታ አቅራቢው ይሰጣል። ሁለተኛው ቅጂ በውሳኔው መሠረት ለሚፈፅም ወይም ውሳኔው ይግባኝ ለተባለበት አካል ይሰጣል። ሦስተኛው ቅጂ አቤቱታውን መርምሮ ውሳኔ በሰጠው አካል እጅ በሰነድነት ይያዛል። እያንዳንዱ ውሳኔ በአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተፈረመበት መሸኛ ይኖረዋል። ስለይግባኝ መብት ማንኛውም አቤቱታ አቅራቢ አቤቱታውን ባቀረበበት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ቅር ከተሰኘ በምርጫ ህጉ መሠረት በተደነገገው የጊዜ ገደብ ውስጥ ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው። በየደረጃው ያለ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮሚቴው በሰጠው ውሳኔ ላይ የይግባኝ መብት ላለው ሰው ወይም አካል፤ ይግባኝ የማቅረብ መብት እንዳለው፣ ይግባኙን ለማን ማቅረብ እንዳለበት፣ ይግባኙን ኮሚቴው ውሳኔ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ማቅረብ እንዳለበት፣ የማስረዳት ኃላፊነት አለበት፣ ማንኛውም አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የይግባኝ መብት ላለው ሰው፤ የኮሚቴውን ውሳኔ አንድ ቅጂ፣ ውሳኔ የተሰጠበትን አቤቱታ አንድ ቅጂ እና የተሰጠውን ውሳኔ እና አቤቱታ ቅጂዎች በአባሪነት የያዘ በአቤቱታ ሰሚው ኮሚቴ ሰብሳቢ ፊርማ የተረጋገጠ መሸኛ ደብዳቤ ሊሰጠው ይገባል። በየደረጃው የሚገኙ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴዎች፤ የዚህ ደንብ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 4 (ለ) እና አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 4 (ለ) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በየደረጃው በሚገኙ የበታች አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴዎች ተመርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ ያላገኘን ጉዳይ ማየት የለባቸውም። የቀረበላቸውን ይግባኝ በመመልከት የበታች አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴዎችን ውሳኔ ሊያፀኑ፣ በከፊል ወይም በሙሉ ሊለውጡ ወይም ሊያሻሽሉ ይችላሉ። የቀረበላቸውን ይግባኝ ተመልክተው አፋጣኝ ውሳኔ በመስጠት በየደረጃው ያሉ የምርጫ አስፈጻሚዎች ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መስጠት አለባቸው። ይግባኝ የቀረበለት አቤቱታ ሰሚ አካል በዚህ ደንብ መሠረት በተደነገገው ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል። የምርጫ ህጉ አስገዳጅ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ይግባኝ የሚቀርበው ለመደበኛ ፍርድ ቤቶች በሚሆንበት ጊዜ አግባብ ያለው የሕግ ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናል። የዚህ ደንብ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 8(ለ) እና አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 8(ለ) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ፍርድ ቤቶች በምርጫ ህጉ አንቀጽ 92/11/ መሠረት ቦርዱ ወይም በየደረጃው በሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚ አካላት በቅድሚያ ያልታየና የመጨረሻ ውሳኔ ያላገኘን የምርጫ ጉዳይ ማየት አይችሉም። ስለይግባኝ አቤቱታ አወሳሰን ይግባኝ የቀረበው ይግባኝ ሰሚ ለሆነው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ከሆነ እንደሁኔታው በዚህ ደንብ ስለመጀመሪያ ደረጃ አቤቱታ የተመለከቱ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ስለመተባበር ማናቸውም የፌዴራልም ሆነ የክልል የመንግሥት መሥሪያ ቤት፣ የፖለቲካ ድርጅት፣ ቡድን፣ የግል ድርጅት ወይም ግለሰብ ይህንን ደንብ በሥራ ላይ ለማዋል የመተባበር ግዴታ አለበት። ስለቅጣት ይህ ደንብ በሥራ ላይ እንዳይውል ያወከ ወይም ድንጋጌዎቹን የጣሰ ማንኛውም ሰው አግባብ ባለው ህግ ይቀጣል። የተሻሩ ደንቦች እና አሠራሮች ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ደንብ ወይም አሠራር በዚህ ደንብ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም። ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በቦርዱ ከፀደቀበት ከነሐሴ 13 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል። መርጋ በቃና (ፕሮፌሰር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ

የወ/ህ/ቁ. 2/5/፣ 24/1/፣ ወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41፣ 111፣ 112፣ 130፣ 131 ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 23፣ 13/2/፣ ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ሥምምነት አንቀጽ 14 ንዐስ አንቀጽ 7በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የተከለከለው የመጨረሻ ውሳኔ በሆነ ጥፋተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል ሲሆን ነው፡፡ በዚህም መሰረት በወንጀል ሥነ ሥርዓቱ ዓቃቤ ሕግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ጉዳዩ ክስ ለመመስረት የሚያስችል አይደለም በማለት ተጠርጣሪውን በነፃ የመልቀቅ የውሳኔ ሃሳብ በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የመከልከልን ጥያቄ የሚያስነሳ አይሆንም፡፡ በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የመከልከል ጥያቄ በፍርድ ቤት ጉዳዩ ታይቶ ተገቢ ነው የተባለ ውሳኔ መሰጠቱ ሲረጋገጥ ነው፡፡ወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 42// ሀ፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 23


ድጋሚ ያለመከሰስና ያለመቀጣት መብት
• አንድ ሰው በአንድ የወንጀል ድርጊት ክስ ቀርቦበት የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፋተኝነቱ ተረጋግጦ በተቀጣበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና ያለመከሰስና ያለመቀጣት መብት
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግስት መሠረታዊ የወንጀል ሕግ መርህ አድርጎ ከደነገጋቸው ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎች አንደኛው አንድ ሰው በአንድ የወንጀል ድርጊት ክስ ቀርቦበት የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፋተኝነቱ ተረጋግጦ በተቀጣበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና መከሰስና መቀጣት የለበትም የሚለው ነው፡፡ ይህ የወንጀል ሕግ መርህ በሕገ መንግስቱ ብቻ ሳይሆን በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 5 ተደንግጓል፡፡ ሕገ መንግስቱ በአንቀጽ 23 ‘’ማንኛውም ሰው በወንጀል ሕግና ሥነሥርዓት መሰረት ተከስሶ የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፋተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም‘’ በማለት ደንግጓል፡፡ የወንጀል ህግ መርሁ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው መርህ ሲሆን አገራችን ባጸደቀችው በዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ሥምምነት አንቀጽ 14 ንዐስ አንቀጽ 7 “No one shall be liable to be tried or punished again for an offence for which he has already been finally convicted or acquitted in accordance with the law and penal procedure of the country” በሚል መንገድ ተደንግጓል፡፡
ከህገ መንግስቱ አንቀፅ 23 አቀራረፅና ይዘት ለመረዳት የሚቻለው አንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው በድጋሚ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በአንድ ጉዳይ በድጋሚ ያለመከሰስና ያለመቀጣት መብቴን የሚጥስ ነው ብሎ ለመከራከርና የህገ መንግስቱም ድንጋጌ ተፈፃሚ እንዲሆንለት ለመጠየቅ ሁለት መሠረታዊ መስፈርቶች ሊሟሉ ይገባል፡፡ የመጀመሪያው ተከሣሹ በተመሣሣይ የወንጀል ድርጊት በወንጀል ህግና ሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት የተከሰሰ የነበረ መሆኑ ማረጋገጥ ነው፡፡ ሁለተኛው ተከሣሹ ከዚህ በፊት በተከሰሰበት ወንጀል ድርጊት የመጨረሻ በሆነ ፍርድ ጥፋተኛ ሆኖ የተቀጣ ወይም በነፃ የተለቀቀ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡
ዓቃቤ ሕግ በአንድ ተከሣሽ ላይ የወንጀል ክስ ለማቅረብ ወይም ላለማቅረብ የሚሰጠው ውሣኔና የወንጀል ክስ ለማቅረብ ከወሰነ በኋላ ተከሣሹ በኃላፊነት ሊጠየቅ የሚችልበትን የወንጀል ድርጊትና የወንጀል ሕግ ድንጋጌ በወንጀል የፍትህ ሥርዓቱና በወንጀል የፍርድ ሂደት ውስጥ እጅግ ወሣኝና የመጀመሪያውና መሠረታዊ ውሣኔና ክንውን ነው፡፡ ዓቃቤ ሕግ በአንድ ተከሣሽ ላይ የወንጀል ክስ ከማቅረቡ በፊት ተከሣሹ አንድ ወንጀል በመፈጸም ሃሣብ የሰራው አንድ የወንጀል ድርጊት ያስከተላቸውን ወይም ሊያስከትላቸው የሚችላቸውን ውጤቶች ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ በማገናዘብና አግባብነት ያላቸውን ህግ ድንጋጌዎች በመለየትና በመጥቀስ የወንጀል ክሱን በጥንቃቄ የማቅረብ ግዴታ እንዳለበት ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 24 ንዐስ አንቀጽ 1፣ ከወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 41፣ አንቀጽ 111 እና አንቀጽ 112 እና ሌሎች አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል፡፡
ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ክስ ሲያቀርብ በህግ የተጣለበትን ግዴታ ሣይወጣ ተከሣሹን በቀላል ወንጀል ኃላፊና ተጠያቂ የሚያደርግ የወንጀል ድንጋጌ ጠቅሶ ክስ አቅርቦ ተከሣሹም የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ በሚፈቅደው መሠረት የእምነት ክህደት ቃሉን ከሰጠና ተከራክሮ በቀረበበት የወንጀል ክስ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ ከተቀጣ ወይም በነፃ ከተለቀቀ በኋላ ዓቃቤ ሕግ ከዚህ በፊት በተከሰሽ ላይ የወንጀል ክስ ሳቀርብ የተከሳሽ ድርጊት በግል ተበዳይ ላይ ያስከተለውን ወይም ሊያስከትል የሚችለውን ውጤት በማገናዘብም ሆነ አግባብነት ያለውን የወንጀል ሕግ ድንጋጌ በመምረጥና በመጥቀስ ተሳሳቻለሁ በሚል በተከሣሹ ላይ በድጋሚ የወንጀል ክስ ቢያቀርብ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 23 እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 5 በምን መንገድ መተርጎምና ተፈጻሚ መሆን አለባቸው የሚለውን ነጥብ እንድንመረምር ያስገድደናል፡፡
የዚህ አይነት ክርክር ሲያጋጥም ከሁሉም በፊት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌው ሊያሳካው የሚፈልገውን ግብና ዓላማ መሠረት በማድረግ ክርክሩን በመመርመር መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የህገ መንግስቱን አንቀፅ 23 ትርጉምና የተፈፃሚነት ወሰን አስመልክቶ የሚነሱ አከራካሪ ጉዳዮች በህገ መንግስቱ አንቀፅ 13 ንዐስ አንቀፅ 2 መሠረት ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቃል ኪዳን ስምምነቶች በተለይም ከዓለም ዓቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ሥምምነት አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 7 ይዘት፣ ትርጉምና የተፈፃሚነት ወሰን ጋር ማገናዘብና መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የዚህ ዓለም ዓቀፍ የወንጀል ህግ መርህ መሠረታዊ ዓላማ የአንዲት አገር መንግስት ህግ አስከባሪ አንድ ጊዜ የወንጀል ክስ አቅርቦበትና ተከራክሮ የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት የወንጀል ድርጊት በሌላ ጊዜ ተከሳሹን በድጋሚ ለመክሰስና ለማስቀጣት የማይችል መሆኑን በመደንገግ ሰዎችን በአንድ ወንጀል ድርጊት በተደጋጋሚ በሚቀርብ የወንጀል ክስ ስጋት ውስጥ እንዳይወድቁ በመከልከል ለሰዎች የተረጋጋና ሰላማዊ ኑሮ ዋስትና እና ጥበቃ መስጠት ነው፡፡
የህገ መንግስቱ አንቀጽ 23 በአቀራረጹና በይዘቱ በአንድ በኩል ዓቃቤ ህግ ለአንድ የወንጀል ድርጊት በተለያየ ጊዜ የተለያየ የወንጀል ርዕስና የህግ ድንጋጌ በመጥቀስ ወይም ተመሳሳይ የወንጀል ህግ ድንጋጌ በመጥቀስ ተከሳሽ ተከስሶ በፍ/ቤት በተሰጠ የመጨረሻ ፍርድ ነፃ ከወጣ ወይም ከተቀጣ በኋላ በድጋሚ በወንጀል እንዳይከሰስና እንዳይጠየቅ የሚከለክል በሌላ አነጋገር የመንግስት የወንጀል ክስ የማቅረብ ሥልጣንን የሚገድብ መሰረታዊ ድንጋጌ ነው፡፡ በሌላ በኩል ድንጋጌው አንድ ተከሳሽ የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል ተብሎ ከወንጀል ክሱ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት ጉዳይ ላይ የወንጀል ክስና ተጠያቂነት ይመጣብኛል በሚል ጭንቀትና ሥጋት እንዳይሸማቀቅ ህገ መንግስታዊ ዋስትናና ጥበቃ በመስጠት ተከሳሹ በወንጀል ተከስሶ በመጨረሻ ፍርድ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት የወንጀል ድርጊት በድጋሚ የማይከሰስና የማይፈረድበት ስለመሆኑ ህገ መንግስታዊ ዋስትና ያለው መሆኑን በማረጋገጥ የተረጋጋ ህይወት እንዲኖር የማድረግ ዓላማና ግብ ያለው ነው፡፡
አንድ ሰው በወንጀል ህግና በወንጀል ስነ ስርዓት ተከስሶ የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ጥፋተኛ ሆኖ ተቀጥቷል ወይም በነፃ ተለቋል የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ የወንጀል ክስ የክስ መቃወሚያ ሆኖ መቅረብ ያለበት መሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 130 የተደነገገ ሲሆን ፍ/ቤቱ የቀረበውን የክስ መቃወሚያና ማስረጃ በመመርመር ውሳኔ መስጠት ያለበት መሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 131 ተደንግጓል፡፡ ሆኖም አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተከስሶ በመጨረሻ ፍርድ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት የወንጀል ድርጊት በድጋሚ ያለመከሰስና ያለመጠየቅ መብት መሰረታዊና ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ ክርክሩ በሚካሄድበት በማናቸውም ደረጃ ሊነሳ የሚችልና በማስረጃ ተረጋግጦ በተገኘ ጊዜ ፍ/ቤቶች ተቀብለው ብይን የሚሰጡበት የመከራከሪያ ነጥብ ነው፡፡
የወ/ህ/ቁ. 2/5/፣ 24/1/፣ ወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41፣ 111፣ 112፣ 130፣ 131 ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 23፣ 13/2/፣ ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ሥምምነት አንቀጽ 14 ንዐስ አንቀጽ 7
በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የተከለከለው የመጨረሻ ውሳኔ በሆነ ጥፋተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል ሲሆን ነው፡፡ በዚህም መሰረት በወንጀል ሥነ ሥርዓቱ ዓቃቤ ሕግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ጉዳዩ ክስ ለመመስረት የሚያስችል አይደለም በማለት ተጠርጣሪውን በነፃ የመልቀቅ የውሳኔ ሃሳብ በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የመከልከልን ጥያቄ የሚያስነሳ አይሆንም፡፡ በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የመከልከል ጥያቄ በፍርድ ቤት ጉዳዩ ታይቶ ተገቢ ነው የተባለ ውሳኔ መሰጠቱ ሲረጋገጥ ነው፡፡
ወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 42// ሀ፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 23

የስልጣን ቁጥጥር: ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ


የስልጣን ቁጥጥር: ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ የስልጣን ቁጥጥር: ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ theory demands that all public servants, elected or nonelected, be accountable to the people. Obviously, this requires the creation of certain oversight mechanisms so that administrative behavior can be watched and controlled.aከሁሉም ስልጣንን የመቆጣጠር ኃላፊነትና ግዴታ ከተጣለባቸው ተቋማት መካከል የህዝብ ተወካዮች ስራ አስፈፃሚውንና በስሩ ያሉትን አስፈፃሚ አካላት በቅርበት የመከታተልና የመቆጣጠር አይነተኛ አደራና ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ድምዳሜው ከውክልና ዲሞክራሲ (representative democracy) መርህ ይመነጫል፡፡ ይህ መርህ ከተጠያቂነት ጋር ያለውን ትስስር አሜሪካዊው የፖለቲካ ሳይንስ እና የአስተዳደር ህግ […]

የስልጣን ቁጥጥር: ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ