በጫት ላይ የሚከፈለውን ታክስ አሰባሰብ ፍትሐዊነት ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (11) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡


በጫት ላይ የሚከፈለውን ታክስ አሰባሰብ ፍትሐዊነት ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (11) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “የጫት ኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 767/2004” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፦ “ታክስ” ማለት በኢትዮጵያ በሚካሄድ የጫት ግብይት ላይ በዚህ አዋጅ መሠረት የሚከፈል የኤክሳይዝ ታክስ ነው፤ “ታክስ ከፋይ” ማለት የጫት ኤክሳይዝ ታክስ ከፋይ ነው፤ “የታክስ ባለስልጣን” ማለት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ነው፤ “ሰው” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ቢሆንም ባይሆንም ማንኛውም ድርጅት ነው፤ “ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 47 የተመለከተው ማንኛውም ክልል ሲሆን የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ይጨምራል፤ “ሚኒስቴር” ማለት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ነው፡፡ ታክስ የመክፈል ግዴታ ጫትን በይዞታው ስር በማድረግ፣ በማጓጓዘ ወይም በማንኛውም መንገድ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሰው በዚህ አዋጅ የተወሰነውን ታክስ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ የታክሱ ማስከፈያ ልክ በአገር ውስጥ ተመርቶ በመነሻው ክልል ጥቅም ላይ የሚውልና ወደ ሌላ ክልል የሚጓጓዝ ጫት በኪሎ ግራም ብር 5 /አምስት ብር/ የኤክሳይዝ ታክስ ይከፈልበታል፡፡ የታክሱ ማስከፈያ ቦታ በዚህ አዋጅ በጫት ላይ የተጣለው ታክስ የሚሰበሰበው የታክስ ባለሥልጣኑ አግባብነት ካላቸው ክልሎች ጋር በመመካክር በሚወስናቸው ቦታዎች ይሆናል፡፡ ታክሱን የመሰብሰብ ኃላፊነት በዚህ አዋጅ መሠረት በጫት ላይ የተጣለውን ታክስ የሚሰበስበው የታክስ ባለስልጣኑ ይሆናል፡፡ የታክስ ባለሥልጣኑ በዚህ አዋጅ መሠረት ከጫት ላይ የሰበሰበውን ታክስ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት በተደነገገው መሠረት የገቢው ባለቤት ለሆኑ ክልሎች በየወሩ ያከፋፍላል። ለውጭ ገበያ ስለሚቀርብ ጫት በውጭ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ላኪዎች፡- ለውጭ ገበያ በሚያቀርቡት ጫት ላይ ሊከፈል ለሚገባው ታክስ ክፍያ የሚውል ቫውቸር በታክስ ባለስልጣኑ ይሰጣቸዋል፤ ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡትን ጫት በአገር ውስጥ በሚያጓጉዙበት ጊዜ በጫቱ ላይ ሊከፈል ከሚገባው ቀረጥና ታክስ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ቫውቸር በታክሱ ማስከፈያ ቦታ ለተመደበው የታክስ ባለስልጣኑ ሠራተኛ ያስረክባሉ፤ የቀረጥና ታክሱ ሂሳብ በቫውቸር የተከፈለበትን ጫት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ቫውቸሩን በየወሩ ከታክስ ባለስልጣኑ ዘንድ ቀርበው ማወራረድ አለባቸው። በውጭ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ላኪዎች ጫቱን ወደ ውጭ ያልላኩ ከሆነ ታክሱንና የታክሱን 25 በመቶ በመቀጫ መልክ የመክፈል ግዴታ አለባቸው። የታክስ ባለስልጣኑ የዚህን አንቀጽ ዝርዝር አፈፃፀም የሚወስን መመሪያ ያወጣል። ሌሎች ግብርና ታክሶችን የመክፈል ኃላፊነት ማንኛውም በጫት ንግድ ሥራ ላይ የተሠማራ ግብር ከፋይ በዚህ አዋጅ ከተጣለው የኤክሳይዝ ታክስ በተጨማሪ ፀንተው በሚሠራባቸው ሕጎች መሠረት ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶችን የመክፈል ኃላፊነት አለበት፡፡ የኤክሳይዝ አዋጅ ተፈጻሚነት በዚህ አዋጅ ባልተደነገጉ ጉዳዮች ላይ የኤክሳይዝ አዋጅ ቁጥር 307/1994 (እንደተሻሻለ) ተፈጻሚነት ይኖረዋል። የተሻሩና ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ሕጎች የጫት ግብርን ለማስከፈል የወጣው አዋጅ ቁጥር 309/1979 በዚህ አዋጅ ተሽሯል፡፡ ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ሕግ ወይም የአሰራር ልምድ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ የጫት ግብርን ለማስከፈል በወጣው አዋጅ መሠረት መከፈል ሲገባው ይህ አዋጅ በሥራ ላይ እስከዋለበት ቀን ድረስ ያልተከፈለ ታክስ በዚያው አዋጅ መሠረት ገቢ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል፡፡ ሚኒስቴሩ ይህን አዋጅና በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሚወጡ ደንቦችን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.