የፍርድ ቤቶች የአጣሪ ዳኝነት


የፍርድ ቤቶች የአጣሪ ዳኝነት

ስልጣንየዳኝነት ስልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ እንደሆነ የሚደነግገው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 79/1/ አጣሪ ዳኝነትን እንደሚጨምር አይጠቁምም፡፡ በህገ መንግስቱ ላይ የፌደራል የመጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ከክልሎች ውክልና ጋር በተያያዘ በስም ቢጠቀሱም የስልጣናቸው ምንጭ ህገ መንግስቱ ሳይሆን የተወካዮች ም/ቤት የሚያወጣው ህግ እንደሆነ በአንቀጽ 78/2/ ተመልክቷል፡፡ በአንጻሩ ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ የሚመነጨው የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የሰበር ስልጣን ከፊል ዳኝነታዊ ስልጣን ያላቸው አካላት የሚያስተላልፉትን ውሳኔ ህጋዊነት ለማጣራት ያስችለዋል፡፡ ይህ ስልጣን ከሁሉም የፌደራልና የክልል ፌደራል ፍርድ ቤቶች (የክልል የሰበር ችሎቶችን ሳይጨምር)በዓይነቱ የተለየና ብቸኛ ነው፡፡የፌደራል ፍ/ቤቶችመደበኛ ፍርድ ቤቶች የስልጣንን ህጋዊነት በሁለት ዓይነት መንገድ ይቆጣጠራሉ፤ በመደበኛ የፍትሐብሔር ክስ እና በአስተዳደራዊ ይግባኝ፡፡ መንግስት ተከራካሪ በሚሆንባቸው የፍትሐብሔር ጉዳዮች በርካታ የአስተዳደር ህግ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ በተለይም ከውል ውጪ ኃላፊነት፣ ከንብረት ህግ እና በከፊል ከውል ህግ የሚመዘዙ በርካታ የህጋዊነት ጥያቄዎች በተዘዋዋሪም ቢሆን አስተዳደሩ ለህግ እንዲገዛ ያስገዱዱታል፡፡ ፍ/ቤቶች ጠቅላላ ከሆነው መደበኛ ስልጣናቸው በተጨማሪ የአስተዳደሩን ተግባራት ህጋዊነት በይግባኝ እንዲያጣሩ በተለያዩ ዝርዝር ህጎች ላይ ተጨማሪ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ በፍሬ ነገርና በህግ ጉዳይ ላይ የሚፈቀድ ይግባኝ ከዜጋው መብት አንጻር ከአጣሪ ዳኝነት የበለጠ ጠቀሜታ አለው፡፡ ምክንያቱም ፍርድ ቤቱ ነገሩን እንደ አዲስ የማየትና ክርክሩ ከተቋጨ በኋላ በራሱ ተገቢ መስሎ የታየውን ውሳኔ ለማስተላለፍ የተለጠጠ ስልጣን ያጎናጽፈዋል፡፡ አጣሪ ዳኝነት ግን ህጋዊነትን ከማጣራት አይዘልም፡፡ የአስተዳደራዊ ውሳኔን በመቃወም ለፌደራል ፍ/ቤቶች ይግባኝ የማቅረብ መብት ከሚፈቅዱ ድንጋጌዎች መካከል የሚከተሉት በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፡፡የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትመረጃ ከማግኘት መብት ጋር በተያያዘ መረጃ ተጠይቆ መረጃውን የያዘው አካል በመከልከሉ ለእንባ ጠባቂ ተቋም ይግባኝ ከቀረበ በኋላ እንባ ጠባቂው በሚሰጠው ውሳኔ ላይaየአካባቢ ተቆጣጣሪዎች በሚሰጡት ውሳኔ እንዲሁም እንዲሁም በአካባቢ ላይ የደረሰ ጉዳትን አስመልክቶ ለአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር አቤቱታ ቀርቦ ሚኒስቴሩ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ bየፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤትከጥራት ጋር በተያያዘ ቡና የተያዘበት ወይም መጋዘኑ የታሸገበት ሰው ለእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ወይ አግባብ ላለው የክልል መንግስት አካል ቅሬታ አቅርቦ ተቀባይነት ካጣcየጀነቲክ ቁስ ማስተላለፊያ መደበኛ ውል አፈጻጸምን አስመልክቶ የሚነሳ ክርክርdለሰሊጥ ወይም ነጭ ቦሎቄ አቅራቢነት፣ ላኪነት ወይም አገልግሎት ሰጪነት የብቃት ማረጋገጫ ማመልከቻ ውድቅ ከተደረገ የህግ አተረጓጎምን በተመለከተ ወይም ተፈቅዶለት በዚህ ንግድ የተሰማራ ሰው ከጥራት ጋር በተያያዘ ሰሊጥ ወይም ነጭ ቦሎቄ ተይዞበት ለሚኒስትሩ ወይም አግባብ ላለው የክልል መንግስት አቤቱታ አቅርቦ ተቀባይነት ካጣeየጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት የቀረበ ማመልከቻ ተቀባይነት እንዲያጣ ወይም ፈቃድ የተሰጠው ጠበቃ በዲሲፕሊን ጥፋት ምክንያት ቅጣት በመጣል በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የተወሰደ እርምጃ (በህግ ጉዳይ ላይ ብቻ)fየሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበር ምዝገባ ባለመፍቀድ እንዲሁም ለስራ ውል መታገድ በቂ ምክንያት አለመኖሩን በመግለጽ በሚሰጠው ውሳኔ እና የስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪ የሚሰጠውን ትዕዛዝ በመቃወምgየዕፅዋት አዳቃዮች መብት መስጠትን፣ መከልከልን፣ መሰረዝን ወይም መገደብን በተመለከተ በሚሰጥ ውሳኔ ላይhየምርት ገበያ ባለስልጣን በሚሰጣቸው በአዋጁ በተመለከቱ ውሳኔዎችiየፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባ ውድቅ በማድረግ ወይም በመሰረዝ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሚሰጥ ውሳኔjየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ፈቃድ በመሰረዝ በሚሰጠው ውሳኔ እንዲሁም ባንኩ የሾመው ሞግዚት በሚያስተላልፈው ውሳኔkየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ፈቃድ በመሰረዝ በሚሰጠው ውሳኔlየፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ስልጣን በቀጥታ ከህገ መንግስቱ ይመነጫል፡፡ ሆኖም የስልጣኑን ወሰን የሚያሰምረው የህገ መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ ሀ የአማርኛውና እንግሊዝኛው ቅጂ ግልጽ መፋለስ ይታይበታል፡፡ በአማርኛው ንባብ የሰበር ችሎት መሰረታዊ ‘የህግ ስህተት ያለበትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔ’ የማረም ስልጣን ይኖረዋል፡፡ (ሰረዝ የተጨመረ) የእንግሊዝኛው ቅጂ ደግሞ Over any final court decision የሚል አገላላጽ በመጠቀም ስልጣኑን ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ በሰጠባቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ ይገድበዋል፡፡የድንጋጌውን ይዘት ዝርዝር የሚወስነው ህግ ከእንግሊዝኛው ቅጂ ጋር ይስማማል፡፡ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁ. 25/1988 አንቀጽ 10 የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የሰበር ስልጣን የሚያገኝባቸው ሶስት ጉዳዮች ተዘርዝረዋል፡፡ እነዚህም፤የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ አይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው ጉዳዮችየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው ጉዳዮችየክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት መደበኛ ችሎት በይግባኝ አይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው ጉዳዮችበሶስቱም ጉዳዮች በውሳኔ ሰጭነት የተጠቀሱት ተቋማት መደበኛ ፍርድ ቤቶች ብቻ ናቸው፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ረ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ ሀ የእንግሊዝኛው ቅጂ ላይ court የሚለው ቃል እንዲሁ ይህንኑ ሀሳብ ያንጸባርቃል፡፡ ሆኖም የአማርኛው ንባብ ውሳኔ ሰጭውን በዝምታ አልፎታል፡፡ ላይ ላዩን ሲታይ ዝምታው ለህገ መንግስታዊ ትርጉም በር የከፈተ አይመስልም፡፡ ‘የመጨረሻ ውሳኔ’ የሚለው አገላለጽ ፍርድ ቤትን ታሳቢ አድርጓል ቢባል ብዙዎችን ያስማማል፡፡ሆኖም ችግሩ ከቋንቋ አጠቃቀም ያልዘለለ የሚመስለው የአንቀጽ 80/3/ ሀ ድንጋጌ በተግባር ህገ መንግስታዊ ጥያቄ አስነስቶ የሰበር ችሎትን የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን አስፍቶታል፡፡ በሰ/መ/ቁ. 43511m ከአዋጅ ውጪ የተወረሱ ንብረቶችን በተመለከተ ከፊል ዳኝነታዊ ስልጣን የተሰጠው የፕራይቬይታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ ያስተላለፈው ውሳኔ በቀጥታ በሰበር እንዲታይ አቤቱታ ቢቀርብም አጣሪ ችሎቱ ጉዳዩ አስተዳደራዊ መሆኑን በመጠቆም ውድቅ አድርጎታል፡፡ ሆኖም በመዝገቡ ላይ አመልካች ሆነው የቀረቡት አቤቱታ አቅራቢዎች የውሳኔውን ህገ መንግስታዊነት በመሞገት ለህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ አቤቱታ አስገቡ፡፡ አጣሪውም ለጥያቄያቸው አዎንታዊ ምላሽ ባለመስጠቱ የመጨረሻ አማራጫቸውን በመጠቀም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አመለከቱ፡፡ ም/ቤቱ የችሎቱን ስልጣን በማረጋገጥ መዝገቡን ወደ ሰበር ችሎት መለሰው፡፡ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የቦርዱን ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም ስልጣን እንዳለው በማረጋገጥ የተሰጠው ይህ የም/ቤቱ ውሳኔ ‘የመጨረሻ ውሳኔ’ በሚል በህገ መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ ሀ ላይ የተቀመጠውን አገላለጽ ከእንግሊዝኛ ቅጂ ፍጹም የተለየ ይዘትና መልዕክት ሰጥቶታል፡፡ በውጤቱም ከፍርድ ቤት ውጭ ያሉ ከፊል የዳኝነት አካላት ላይ የሰበር ችሎት የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን እንዳለው አረጋግጧል፡፡የም/ቤቱ ውሳኔ ህገ መንግስታዊ ፋይዳው ስር ነቀልና መሰረታዊ ነው፡፡ የስር ፍ/ቤቶችን የህግ ስህተት በማረም ብቻ ተወስኖ የነበረው የሰበር ችሎት በም/ቤቱ ‘በተጨመረለት’ ስልጣን ከፊል ዳኝነታዊ ስልጣን የተሰጣቸው የአስተዳደር አካላት የሚያስተላልፉትን ውሳኔ ጭምር የማረም የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን ይኖረዋል፡፡ ችሎቱም ዳኝነታዊ የአስተዳደር ውሳኔዎችን ማረም ህገ መንግስታዊ ሚናው እንደሆነ በሌሎች ሁለት መዝገቦች በሰጣቸው ውሳኔዎች በተግባር አረጋግጧል፡፡በሰ/መ/ቁ. 92546n የድሮው ፍትሕ ሚኒስቴር የአሁኑ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የዲሲፕሊን ውሳኔ በቀጥታ ለሰበር ችሎት ቀርቦ ተሸሯል፡፡ አቤቱታ አቅራቢው በሚኒስትሩ የዲሲፕሊን እርምጃ የተወሰደው በዓቃቤ ህግ ላይ ሲሆን ጉዳዩ በሰበር ችሎት ከመስተናገዱ በፊት በሌላ ፍርድ ቤት አልታየም፡፡ በመዝገቡ ላይ የችሎቱ የዳኝነት ስልጣን አከራካሪ ጭብጥ ሆኖ ባይወጣም የህገ መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ ሀ እና አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 10 ተጠቅሶ የቀረበውን አቤቱታ ችሎቱ መቀበሉ ሲታይ የአጣሪ ዳኝነት ስልጣኑ ጠንካራ መሰረት እየያዘ እንደመጣ አስረጂ ነው፡፡ በሰ/መ/ቁ. 61221 ቅጽ 14o የተያዘው አቋም ይህንን ሀሳብ ያጠናክራል፡፡ በዚህ መዝገብ በሰፈረው የህግ ትርጉም በፍርድ ቤት እንዳይታዩ በመጨረሻ ማሰሪያ ድንጋጌ (finality clause) ገደብ የተደረገባቸው ውሳኔዎች ሳይቀር በችሎቱ የአጣሪ ዳኝነት ስር እንዲወድቁ ተደርገዋል፡፡ ጉዳዩ የታየው አዋጅ ቁ. 714/2003 እና 715/2003 ከመውጣታቸው በፊት ሲሆን ቀድሞ በነበሩት የጡረታ ህጎች የማህበራዊ ዋስትና ጉባኤ ውሳኔ የመጨረሻ በመሆኑ በይግባኝ ሆነ በቀጥታ ክስ በመደበኛ ፍ/ቤቶች ሊታይ አይችልም፡፡በሰ/መ/ቁ. 61221 የሰበር አቤቱታ የቀረበው የጉባዔውን የመጨረሻ ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡ ሆኖም በችሎቱ የዳኝነት ስልጣን ላይ በተጠሪ በኩል ተቃውሞ በመቅረቡ የስልጣን ምንጭ አከራካሪ ጭብጥ ሆኖ ወጥቷል፡፡ ይህንን በማስመልከት ህገ መንግስቱን እና አዋጅ ቁ. 25/88 በማጣቀስ የሚከተለው የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡ጉዳዩ በተነሳበት ጊዜ ስራ ላይ በነበረው ሕግ አግባብ ማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ነው ከተባለ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 በተመለከተው አግባብ ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ ከማቅረብ የሚከለክል ሕጋዊ አግባብ የለም፡፡የከተማ ፍ/ቤቶችበአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተማ የተቋቋሙት የከተማ ፍርድ ቤቶች በውስን ጉዳዮች ላይ ቢሆንም የማይናቅ የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን አላቸው፡፡ ስልጣናቸውን በሚወስኑት ህጎች ላይ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች መካከል የሚከተሉትp በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአጣሪ ዳኝነት የሚታዩ ናቸው፡፡የከተማውን መሪ ፕላን አፈጻጸም የሚመለከት የይዞታ ባለመብትነት፣ የፈቃድ አሰጣጥ ወይም የቦታ አጠቃቀምን በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮችከከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት የመቆጣጠር ስልጣንና ተግባር ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮችበየከተሞቹ ቻርተር ላይ በተመለከቱት የፋይናንስ ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ክሶችየከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ወይም በከተማው አስተዳደር ባለቤትነት ስር ያሉ ተቋማት የሚገቧቸውን አስተዳደራዊ ውሎች በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮችበከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ወይም በስሩ ባሉ ተቋማት መካከል የሚነሱ ክርክሮችየከተማው አስተዳደር ከሚያስተዳድራቸው የመንግስት ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮችበህግ ከተሰጣቸው የመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን በተጨማሪ በከፊል ጉዳዮች አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን በይግባኝ ያያሉ፡፡ ለምሳሌ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ቅሬታ ሰሚ ጉባዔ በሚሰጠው ውሳኔq የመጀመሪያና የይግባኝ ስልጣን አላቸው፡፡የከተማ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ክልል በህጉ ላይ በወጉ አልተሰመረም፡፡ ህግ አውጭው ‘በተመለከተ…በተያያዘ…’ በሚል የተጠቀመው አገላለጽ መብት ጠያቂውን ሆነ ፍርድ ቤቶችን ያደናግራል፡፡ የዳኝነት ስልጣን ሊወሰን የሚገባው በክስ ምክንያት፣ ፍርድ ቤቱ በሚሰጠው መፍትሄ ወይም በተከራካሪዎች ማንነት ነው፡፡ ለምሳሌ የይዞታ ባለመብትነትን በተመለከተ እንዲሁም ከአስፈፃሚ አካላት የመቆጣጠር ስልጣንና ተግባር ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮች እንደ ሁኔታው በፌደራል ወይም በከተማ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር ይወድቃሉ፡፡ ይዞታን የሚመለከት ክስ በሁከት ይወገድልኝ ወይም በመፋለም ክስ አሊያም ደግሞ በይዞታ ላይ ለደረሰ ጉዳት ካሳ በመጠየቅ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ከግንባታ ፈቃድ ወይም ስም ከማዛወር አስተዳደራዊ ግዴታ ጋር በተያያዘም ይዞታን የሚመለከት ጥያቄ ይነሳል፡፡ ከዚህ አንጻር በደፈናው ‘በተመለከተ…’ በሚል የተደለደለው የዳኝነት ስልጣን የመደበኛ እና የከተማ ፍ/ቤቶችን ድርሻ በአግባቡ አይለይም፡፡ህጉ ግልጽነት ቢጎድለውም ከሰበር ችሎት አካሄድ እና የህግ አውጭው ሀሳብ በመነሳት የከተማ ፍ/ቤቶች መደበኛ የፍትሐብሔር የዳኝነት ስልጣን እንዳልተሰጣቸው ድምዳሜ ላይ መድረስ እንችላለን፡፡ ህግ አውጭው እነዚህን ፍ/ቤቶች ሲያቋቁም ከተወሰኑት በግልፅ ከተነገሩት በስተቀር መደበኛውን የፍትሐብሔር ዳኝነት አላስተላለፈላቸውም፡፡ የሰበር ችሎት በበርካታ መዝገቦች ያንጸባረቀው አቋም ከዚህ ሀሳብ ጋር ይስማማል፡፡ ይህ ከተባለ በኋላ ግን ከላይ በቀረበው ዝርዝር ውስጥ ህግ አውጭው የወሰነው የዳኝነት ስልጣን ምን መልክ እንዳለው መለየት ያስፈልጋል፡፡ራሱን የቻለ የአስተዳደር ህግ ስርዓት ባላቸው አገራት በፍርድ ቤት የሚታዩ ጉዳዮች ሶስት ዓይነት ናቸው፤ የፍትሐብሔር፣ የወንጀል እና የአስተዳደር፡፡ በፈረንሳይ የአስተዳደር ክርክሮች ከመደበኛ ፍ/ቤቶች ተለይተው በተቋቋሙ የአስተዳደር ፍ/ቤቶች አማካይነት ይዳኛሉ፡፡ በጀርመን ራሱን ችሎ በተለይ በተቋቋመ የአስተዳደር ፍ/ቤት ይታያሉ፡፡ ከስልጣን ክፍፍል አንጻር መደባቸው ሲታይ የአስተዳደር ፍ/ቤቶች በፈረንሳይ በስራ አስፈፃሚው ስር የሚገኙ ሲሆን በጀርመን ግን በዳኝነት አካሉ የታቀፉ ናቸው፡፡ በእንግሊዝ የፍትሐብሔር ክርክሮችን የሚያስተናግዱት መደበኛ ፍ/ቤቶች የአስተዳደር ክርክሮችንም ደርበው ይዳኛሉ፡፡ በእርግጥ አስተዳደር ነክ ጥያቄዎች የሚቀርቡት ለከፍተኛው ፍ/ቤት ቢሆንም ፍ/ቤቱ ራሱን የቻለ የተለየ መዋቅር የለውም፡፡ በሶስቱም አገራት በመንግስትና በግለሰብ መካከል የሚካሄዱ ክርክሮች የሚዳኙበት መንገድ ቢለያያም አንድ ነገር ያመሳስላቸዋል፡፡ ይኸውም የዳኝነት ስልጣናቸው ዓይነት አጣሪነት (supervisory) ነው፡፡ የዚህ ስልጣን ወሰን የአስተዳደሩን ተግባራት ህጋዊነት ማረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ያለፉ የፍትሐብሔር ክርክሮችን መደበኛ ፍ/ቤቶች ይረከባሉ፡፡ ለምሳሌ አንድ የአስተዳደር ተቋም ከህግ የመነጨ ስልጣኑን በመጠቀም እርምጃ ሲወስድ ክርክሩ በአጣሪነት ዳኝነት ስር ይወድቃል፡፡ እንደማንኛውም ግለሰብ በሚፈጽማቸው የግል ተግባራት ሲከሰስ (ለምሳሌ የተቋሙ መኪና በአካል ወይም ንብረት ላይ ጉዳት በማድረሱ ከውል ውጭ በሚደርስ ኃላፊነት ካሳ ሲጠየቅ) ደግሞ መደበኛ ፍ/ቤቶች በፍትሐብሔር የዳኝነት ስልጣናቸው ያዩታል፡፡በከተማ ፍ/ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ስር ከተዘረዘሩት መካከል የይዞታ ባለመብትነትን በምሳሌነት ብንወስድ ከላይ ለመጠቆም እንደተሞከረው ጉዳዩ የሚታይበት ፍ/ቤት የሚለየው በክሱ ይዘት ነው፡፡ ከፍትሐብሔር ውጭ በአስተዳደሩ ላይ ሊቀርብ የሚችለው ክስ ህጋዊነት የሚጣራበት ክስ ነው፡፡ ይህም የሚያደርሰን መደምደሚያ የከተማ ፍርድ ቤቶች በህግ የተወሰነላቸው የዳኝነት ስልጣን ዓይነት የአጣሪ ዳኝነት (judicial review) ስልጣን እንደሆነ ነው፡፡

መንግሥት ህወሓት እየሠራ ያለውን ግፍና በደል ሊቀለብስ የሚችል ሥራ እየሠራ አይደለም – ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ


“መንግሥት ህወሓት እየሠራ ያለውን ግፍና በደል ሊቀለብስ የሚችል ሥራ እየሠራ አይደለም” – ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ – አዲስ ዘመን – ህወሓት እየሠራ ያለው ግፍና በደል በጣም ሰፊ ቢሆንም የፌዴራል መንግሥት ይህንን ሊቀለብስ የሚችል ሥራ እየሠራ አይደለም ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ አስታወቁ። ‹‹በጉዳዩ የፌዴራል መንግሥት ብዙ ጊዜ ጥያቄና ወቀሳ ቀርቦበታል። […]

መንግሥት ህወሓት እየሠራ ያለውን ግፍና በደል ሊቀለብስ የሚችል ሥራ እየሠራ አይደለም – ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ

አተርፍ ባይ አጉዳይ


አተርፍ ባይ አጉዳይ

፦፦፦፦፦፦፦አተርፍ ባይ አጉዳይ፦፦፦፦፦፦፦፦፦ የሚቀጥለው ትረካ አንዳንድ ከሳሾችና ተከሳሾች ነገሩ እውነት ነው ሲሉ ቢደመጥም እውነተኛነቱ በገለልተኛ ጠበቃ አልተረጋገጠም፡፡ አሜሪካ ውስጥ አንድ ጠበቃ በዓለም ገበያ ላይ ብዙም የማይገኝ ውድ ሲጋራ ከገዛ በኋላ ለንብረቱ በጣም በመሳሳት የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ ይገባለታል፡፡ የኢንሹራንስ ፖሊሲ በገዛ አንድ ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያ ዙር አረቦን (ፕሪሚየም) እንኳን ሳይከፍል ኢንሹራንስ የተገባላቸውን ሃያ አራቱንም ሲጋራዎች ሁሉ በየቀኑ እያጨሰ ጨረሳቸው፡፡ የመጨረሻዋን ሲጋራ እንደማገ በቀጥታ ወደ መድን ድርጅቱ በማምራት በፖሊሲው መሠረት ካሳ እንዲከፈለው ጠየቀ፡፡ ጠበቃው ለድርጅቱ በፃፈው የክፍያ አቤቱታ ላይ ሲጋራዎቹ ‘ተከታታይነት ባላቸው ትናንሽ እሳቶች’ እንደወደሙ በመግለጽ ክፍያ ቢጠይቅም የመድን ድርጅቱ ግን ጠበቃው መድን የተገባለትን ሲጋራ ራሱ በማጨስ መደበኛ ለሆነው አገልግሎት ያዋለው በመሆኑ ተጠያቂ አይደለሁም በማለት ለመክፈል ፍቃደኛ ሳይሆን ይቀራል፡፡ መቼም ቀጥሎ ምን እንደሚከተል ግልጽ ነው፡፡ ጠበቃው መድን ድርጅቱን ፍርድ ቤት ገተረው፡፡ ገትሮትም አልቀረ ረታው፡፡ ውሳኔውን የሰጡት ዳኛ መጀመሪያ የመድን ድርጅቱ ያቀረበውን ክርክር በመደገፍ ክሱ “ተልካሻና የማይረባ” መሆኑን በሐተታቸው ላይ ካሰፈሩ በኋላ እንዳሉት፤ “…ይሁን እንጂ ከሳሹ ጠበቃ ከተከሳሹ የመድን ፖሊሲ ገዝቷል፡፡ ተከሳሹም ሲጋራዎቹ መድን ሊገባላቸው እንደሚቻል በማረጋገጥ በእሳት ከወደሙ ክፍያ ሊፈጽም ዋስትና ሰጥቷል፡፡ በኢንሹራንስ ፖሊሲው ላይ ተቀባይነት የሌለው እሳት ወይም ሽፋን የማይሰጠው የእሳት አደጋ የትኛው እንደሆነ በግልፅ አልሰፈረም፡፡ ስለሆነም በውላቸው መሠረት ተከሳሽ ክፍያ ሊፈጽም ይገደዳል፡፡” በነገሩ የበሸቀው ተከሳሽ ድርጅት እንደገና ይግባኝ ጠይቆ ለተጨማሪ ክርክርና ወጪ ከመዳረግ ይልቅ ውሳኔውን እንዳለ መቀበል ስለመረጠ 15,000 ዶላር ለጠበቃው ከፍሏል፡፡ ታሪኩ ግን በዚህ አያበቃም፡፡ ጠበቃው ልክ ገንዘቡን ሲቀበል ወዲያውኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የኢንሹራንስ ክፍያ ለማግኘት ሲል ኢንሹራንስ የተገባለትን ዕቃ ራሱ በማውደሙ በማጭበርበር የኢንሹንስ ክፍያ በመቀበል ለፈጸመው ወንጀል በመድን ድርጅቱ ክስ ቀርቦበት ነው፡፡ በመቀጠል ጠበቃው ላጨሳቸው 24 ሲጋራዎች ለእያንዳንዱ 24 የወንጀል ክስ ቀርቦበት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የ24 ወራት እስራት እና የ24,000 ዶላር የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ተወስኖበታል፡፡

የአስተዳደር መንግስት እና የአስተዳደር ህግ ውልደት/ የአስተዳደር ህግ ግብና ተግባራት//የህጉ ምንጮች፣ /የተፈጻሚነቱ


 የአስተዳደር መንግስት እና የአስተዳደር ህግ ውልደት/ የአስተዳደር ህግ ግብና ተግባራት//የህጉ ምንጮች፣ /የተፈጻሚነቱ

ወሰን በ19ኛው ክፍለ ዘመን ገኖ የነበረው የነፃ ገበያ (laisse faire) ንድፈ ሀሳብ በዋነኛነት ውስን የመንግስት ጣልቃ ገብነትና ሰፊ የግለሶቦች ነፃነትን ያቀነቅናል፡፡a በዚሁ ንድፈ ሀሳብ መሰረት የመንግስት ሚና ህግና ስርዓት ከማስጠበቅና አገርን ከጠላት ወረራ ከመከላከል የዘለለ መሆን የለበትም፡፡ ምርጥ መንግስት ማለት በስሱ (በትንሹ) የሚገዛ መንግስት ማለት ነው፡፡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን መምራት፣ መቆጣጠርና መግራት እንደ መንግስት ኃላፊነት አይቆጠርም፡፡ ሆኖም ነፃ የሆነው የገበያና የመንግስት ስርዓት እግረ መንገዱን ይዞ የመጣቸው አሉታዊ ውጤቶች በዋነኛነት ያረፉት በደካማውና ደሀው የህብረተሰብ ክፍል ጫንቃ ላይ ነበር፡፡ በሀብታምና ደሀ መካከል የተፈጠረው የሀብት ድልድል ልዩነት በእጅጉ እየሰፋ በመምጣቱ ሀብታም የበለጠ ሲበለፅግ ደሃው ግን ይባስ እየቆረቆዘ መሄድ ጀመረ፡፡ በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የነበረው የመደራደር አቅም ልዩነት ታይቶ ለማይታወቅ የጉልበት ብዝበዛ ምክንያት ሆነ፡፡ እነዚህ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠንቆች ለነፃ ገበያ ስርዓትና አስተሳሰብ ፈታኝ ሁኔታዎች ነበሩ፡፡ ስለሆነም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠንቆች መፍትሔ መስጠት የመንግስት ግዴታና ኃላፊነት የመሆኑ እውነታ ቀስ በቀስ እየተገለጠ መጣ፡፡b በተለይም የሁለተኛው የአለም ጦርነትን ተከትሎ የተከሰቱት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች የመንግስት ጣልቃ ገብነት አስፈላጊነትን ከመቼውም ጊዜ በላይ በገሃድ አስረግጠዋል፡፡ መንግስት ኃላፊነቱን መወጣት የሚችለው ደግሞ አወቃቀሩና አደረጃጀቱ ሲገፉት የሚፍረከረክ ዓይነት ‘ልል’ ወይም ውስን መንግስት መሆኑ ቀርቶ ጡንቻው የዳበረና ስልጣኑ የሰፋ ጠንካራ መንግስት ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠንቆች መፍትሔ መስጠት የመንግስት ግዴታ ነው ሲባል ሚናው ከተለመደው ስርዓትና ፀጥታ ማስከበር ባሻገር ሰፊና ውስብስብ አዎንታዊ ተግባራትን ወደ ማከናወን መሸጋገር እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡ በዚሁ መሰረት የመንግስት ሚና ቀስ በቀስ ከፖሊስነት (Police State) ወደ ማህበራዊ አገልግሎት አቅራቢነት ሊሸጋገር ችሏል፡፡ መንግስት በአገልግሎት አቅራቢነት ሚናው ውሀ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ መንገድ ወዘተ የመሳሰሉ መሰረታዊ ፍላጐቶችን የማሟላት ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ በተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅጣጫውን ፈር ለማስያዝና ፍትሐዊ የሀብት ድልድል እንዲኖር እንዲሁም ለደካማው የህብረተሰብ ክፍል ጥበቃና ከለላ ለማድረግ በአጠቃላይ የነፃ ገበያን አሉታዊ ውጤቶችን ለመቀነስ ሰፊና ተከታታይ ቁጥጥርና ክትትል (Regulation) ያደርጋል፡፡ አዲሱ የማህበራዊ መንግስት አዲሱን አዎንታዊ ሚናውን በብቃትና ውጤታማ በሆነ መንገድ ይወጣ ዘንድ በዓይነትና በይዘት የጠንካራ ስልጣን ባለቤት ሊሆን የግድ የሚል ሀቅ ነው፡፡c የስልጣን አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስልጣን በየጊዜው ወሰኑ፣ መጠኑና ቅርጹ እያደገና እየሰፋ በመጣ ቁጥር ግን የግለሰቦችን መብትና ነፃነት መንካቱ አይቀርም፡፡ የመንግስት ስልጣን እየተለጠጠ መሄድ አቅመቢስ ለሆነው ዜጋ የስጋት ምንጭ ነው፡፡ ፍፁም የሆነና ወደ ፍፁምነት የተጠጋ ስልጣን ወደ ህገ ወጥነትና የበዘፈቀደ ድርጊት የማምራት አደገኛ አዝማሚያ አለው፡: የአስተዳደር ህግ በየጊዜው እያደገ የመጣውን የመንግስት ‘ጡንቻ መፈርጠም’ በቅጡ ለመቆጣጠር በታሪክ ሂደት በተጓዳኝ የተፈጠረ የህግ መሳሪያ ነው፡፡ መንግስት ተግባራቱን ለማከናወን ፖሊሲ ቀርጾ፣ ህግ አውጥቶ በሚያስፈጽምበት ወቅት በስልጣን እና በፍትህ (የግለሰቦች ነፃነት) መካከል ቅራኔ መከሰቱ የማይቀር እውነታ ነው፡፡ ጥያቄው ቅራኔው እንዴት ይፈታል? ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ የዚህ ቅራኔ የራሱ ውጤት ሲሆን ቅራኔውን በአንፃራዊ መልኩ ለማስማማትና ለማጣጣም በታሪክ ሂደት ብቅ ያለ ተግባራዊ መሳሪያ ነው፡፡d የአስተዳደር ህግ በዕቅድ ታስቦ የተወለደ ሳይሆን በሁኔታዎች አስገዳጅነት የተፈጠረ ክስተት ነው፡፡ ህጉ በሁለት በጉልበት የማይመጣጠኑ ጐራዎች ማለትም በመንግስትና በግለሰብ መካከል ሚዛናዊነትንና ፍትሐዊነትን ለማስፈን ይጥራል፡፡ የአስተዳደር ህግ መንግስት በተለይ ስራ አስፈፃሚውና የአስተዳደር አካላት በህግ ከተፈቀደላቸው የስልጣን ክልል አልፈው ህገ ወጥ ድርጊት እንዳይፈጽሙ ቁጥጥር የሚያደርግና ይህንንም የሚያረጋግጥ ህግ ነው፡፡e በዚህም የህግ የበላይነት እንዲሰፍንና የግለሰቦች ህገ መንግስታዊ መብቶች እንዳይሸራረፉና እንዳይጣሱ ከለላ በመስጠትf ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ በተጨማሪም በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ያለው ስልጣን በአግባቡና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል መሪ ደንቦችን በማስቀመጥና ስነ ስርዓታዊ ቅድመ ሁኔታዎችን በመዘርጋት የተለያዩ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችን በመጠቀም የግለሰቦችና የዜጐች መብቶችና ነፃነቶች እንዳይገሰሱና እንዳይደፈሩ ከለላ በመስጠት የህገ መንግስት ማስፈፀሚያ ሆኖ ያገለግላል፡፡   የአስተዳደር ህግ ምንነት   ለአስተዳደር ህግ ብያኔ በማበጀት ረገድ የመስኩ ባለሙያዎች በከፊልም ቢሆን የተለያየ እይታ አላቸው፡፡ በእርግጥ የአስተዳደር ህግ የጥናት ወሰኑን አስመልክቶ የሚከሰት ልዩነት ካልሆነ በቀር በመሰረታዊ እሳቤው ላይ የተራራቀ አቋም የለም፡፡ እንደ ህንዳዊው የአስተዳደር ህግ ምሁር አይ.ፒ. ማሴይ አገላለጽ በአስተዳደር ህግ ትርጓሜ ላይ ያለው ልዩነት ምንጩ በየጊዜው እያደገና እየተወሳሰበ የመጣው አስተዳደራዊ ሂደት ሲሆን ይህም ሂደቱን በሙሉ አጠቃሎ የያዘ ወጥ ትርጉም ለመስጠት አስቸጋሪ አድርጐታል፡፡g ያም ሆኖ የአስተዳደር ህግ ትርጓሜ ቢያንስ ሁለት መሰረታዊ አላባውያንን ማካተት ይጠበቅበታል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የአስተዳደር ህግ ከይዘት ይልቅ ስነ ስርዓት ላይ የሚያተኩር ህግ ስለመሆኑ ግልጽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም የአስተዳደር ውሳኔው እንዴት ተሰጠ? እንጂ ይዘቱ ትክክል ይሁን አይሁን ፍርድ ቤቶች ሆነ የአስተዳደር ህግ ጣልቃ የሚገባበት ጉዳይ አይደለም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ማንኛውም የአስተዳደር ህግ ትርጓሜ የህጉን ዓላማ ግምት ውስጥ ያስገባ ተግባራዊ አቀራረብ እንዲያቅፍ ይጠበቅበታል፡፡ የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ዓላማ ወይም ተግባር ስልጣንን መቆጣጠር ነው፡፡h ያ ሲባል ግን የአስተዳደር አካላት ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩና እንዳይላወሱ ማነቆ ሆኖ ያግዳቸዋል ማለት አይደለም፡፡ የስልጣን ቁጥጥር ሲባል ማንኛውም ባለስልጣን ሆነ መስሪያ ቤት በህግ ተለይቶ ከተቀመጠለት የስልጣን ገደብ እንዳያልፍና ስልጣን ቢኖረውም እንኳን ስልጣኑን ፍትሐዊና አግባብ በሆነ መንገድ እንዲወጣ ያደርጋል ለማለት ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ዓላማና ተግባር ስልጣንን በተግባር መቆጣጠር እንደመሆኑ ይህን ባህርዩን ግምት ውስጥ ያላስገባ ብያኔ የተሟላ ተብሎ ሊወሰድ ሆነ ሊወደስ አይችልም፡፡ ለንጽጽር እንዲረዳን በመስኩ ባለሙያዎች ለአስተዳደር ህግ የተሰጡ ትርጓሜዎችን እንደሚከተለው እንጠቅሳለን፡፡ ቤርናርድ ሺዋሬዝ (Bernard Schwartz) የአስተዳደር ህግን ‘በውክልና ህግ የማውጣትና አስተዳደራዊ ዳኝነት የመስጠት ስልጣን ባላቸው የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ህግ’ በማለት ይገልፀዋል፡፡i ይህ ብያኔ ጠባብ ከመሆኑ በቀር ስለ ህጉ ይዘት ገላጭ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ በውክልና ስልጣን ህግ ከማውጣትና ከአስተዳራዊ የዳኝነት ስልጣን በተጨማሪ ይህ ስልጣን በፍርድ የሚታረምበትን የአጣሪ ዳኝነት (judicial review) ስነ-ስርዓት እንዲሁም በፖርላማና በተለያዩ ተቋማት የሚደረግ ቁጥጥርንም ያካትታል፡፡ ጄኒንግስ በበኩሉ የአስተዳደር ህግ ማለት ‘አስተዳደርን የሚመለከት ህግ ነው፡፡ ይህ ህግ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶችን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ግዴታ ይወስናል፡፡’ በማለት ይገልጸዋል፡፡j እንደ አይ.ፒ ማሴይ አስተያየት ይህ ትርጓሜ የአስተዳደር ህግን ከህገ መንግስት በግልጽ አይለይም፡፡ አስተዳደር ወይም ማስተዳደር ማለት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስልጣንን በመጠቀም የህብረተሰቡን ጉዳይ መምራት ማለት ነው፡፡k ለዚህም በዋነኛነት አደራ የተጣለባቸው አካላት የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የእነዚህ ተቋማት ስልጣንና ግዴታ በዝርዝር ህግ ተለይቶ ቢወሰንም የስራ አስፈፃሚው አካል ስልጣን በጠቅላላው የሚቀመጠው በህገ መንግስት ላይ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ሆነ ህገ መንግስት ሁለቱም የመንግስት አስተዳደርን ወይም የግለሰብና የመንግስትን ግንኙነት የሚመሩ ህጐች እንደመሆናቸው በመካከላቸው ያለው መለያ ክር በጄኒንግ ትርጓሜ ላይ በግልጽ ነጥሮ አልወጣም፡፡ ታዋቂው የህገ መንግስት ሊቅ ኤ. ቪ. ዲሴይ የአስተዳደር ህግን በሶስት ደረጃዎች ከፋፍሎ እንዲህ ይገልጸዋል፡፡l የአስተዳደር ህግ የመንግስት ባለስልጣናትን የህግ ስልጣንና ተጠያቂነት የሚወስኑትን የአንድ አገር የህግ ስርዓት የሚመለከት የህግ ክፍል ነው፡፡ ግለሰቦች ከመንግስት አካላት ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ያላቸውን መብትና ግዴታ ለይቶ ይወስናል፡፡ እነዚህ መብቶችና ግዴታዎች ተፈጻሚ የሚሆኑበትን ስርዓት ይዘረጋል፡፡ እንደ ማሴይ ትችት ይህ ትርጓሜ የአስተዳደር ህግ አንድ አካል የሆነውን አጣሪ ዳኝነት (judicial review) ብቻ የሚመለከት እንደመሆኑ በይዘቱ ጠባብ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ከአጣሪ ዳኝነት በተጨማሪ በህግ አውጭውና በተቋማት (ለምሳሌ በእንባ ጠባቂ ተቋምና ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን) አማካይነት የሚደረግ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችንም ያካትታል፡፡ ህጉ ከመንግስት ባለስልጣናትና ከአስተዳደር መስሪያ ቤቶች በተጨማሪ ከፊል የአስተዳደር አካላት ተብለው የሚፈረጁትን መንግስታዊ ኮርፖሬሽኖች፤ ዩኒቨርሲቲዎች እና በከፊል መንግስታዊ ነክ ስልጣን ያላቸውን ማህበራትm በተመለከተም ተፈጻሚነት አለው፡፡ በመጨረሻም ታዋቂው የህንድ ምሁር አይ.ፒ. ማሴይ ከላይ ከተሰጡት ሰፋ ያለና የህጉን ባህሪያትና ተግባራት ጠቅልሎ የያዘ ብያኔ እንደሚከተው ያስቀምጣል፡፡ የአስተዳደር ህግ የህዝብ አስተዳደር ህግ አካል ሲሆን የአስተዳደርና ከፊል አስተዳደር መስሪያ ቤቶችን አደረጃጀትና ስልጣን የሚደነግግ፣ አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሰጥበትን ደንብና መርህ የሚያስቀምጥ፣ እንዲሁም ከግለሰቦች መብትና ነፃነት ውሳኔው የሚታረምበትን ስርዓት የሚወስን የህግ ክፍል ነው፡፡n ይህ ትርጓሜ ከሞላ ጐደል ሁሉንም የአስተዳደር ህግ ባህርያት አጠቃሎ የያዘ በመሆኑ ተመራጭነት አለው፡፡ ከላይ ከቀረቡት የተለያዩ ትርጓሜዎች የሚከተሉት የጋራ ነጥቦች ይመዘዛሉ:: አንደኛ፤ የአስተዳደር ህግ የአስተዳደር እና ከፊል የአስተዳደር አካላት ያላቸውን ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት ያጠናል፡፡o የማንኛውም የአስተዳደር አካል የስልጣን ምንጭ የሚገኘው ከማቋቋሚያ አዋጁ (Enabling Act) ሲሆን አልፎ አልፎ በሌላ ዝርዝር ህግ ይወሰናል፡፡ በአስተዳደር ህግ የመጀመሪያው ጥያቄ ውሳኔ ወይም እርምጃ የወሰደው አካል በህግ የተሰጠው ስልጣን አለው? የሚል ነው፡፡ ከሌለ ድርጊቱ ከስልጣን በላይ ስለሆነ ዋጋ አልባ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ከድርጊቱ በስተጀርባ የህግ ስልጣን ካለ ውሳኔ ሰጪው ስልጣኑን በአግባቡና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንደተገለገለ ይጣራል፡፡ ካልሆነ ስልጣኑን ያለ አግባብ በሚገለገለው አካል ላይ ህጉ ቁጥጥር ያደርግበታል፡፡ ሁለተኛ፤ ህጉ ስልጣንን በመገልገል ሂደት ተፈጻሚ የሚሆኑ መሪ ደንቦችን፤ ስነ ስርዓቶችንና መርሆዎችን ያስቀምጣል፡፡ ህግ አውጭው ለአስተዳደር አካላት ስልጣን ሲሰጥ ስልጣኑ ተግባር ላይ በሚውልበት ጊዜ ህጋዊነቱንና ፍትሐዊነቱን የሚያረጋግጥ የስነ ስርዓት ቅድመ ሁኔታ አብሮ እንዲደነግግ ይጠበቃል፡፡ ለምሳሌ ያህል ደንብና መመሪያ በማውጣት ረገድ ከሚመለከተው አካል ጋር የመመካከርና የህትመት ቅድመ ሁኔታዎች፣ አስተዳደራዊ ውሳኔ ሲሰጥ የመሰማት መብትና የኢ- አድሎአዊነት መርሆዎችን በአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ ወይም በዝርዝር ህግ ማውጣት ይኖርበታል፡፡ እነዚህም በአስተዳደር ሂደቱ ውስጥ ፍትሐዊነትን በማረጋገጥ ረገድ ጉልህ ስፍራ አላቸው፡፡ ስልጣን በዘፈቀደ ሳይሆን በአግባቡ ስራ ላይ ዋለ ለማለት የሚቻለውም ያኔ ነው፡፡ ሶስተኛ፤ የአስተዳደር ህግ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችን በተመለከተ የሚያጠና ህግ ነው፡፡p ልጓም የሌለው ስልጣን ለዜጎች መብትና ነፃነት ፀር ነው፡፡ የተጠያቂነት መርሕ እውን እንዲሆን የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችም በግልጽ ተለይተው መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ስለሆነም የአስተዳደር ህግ በፍርድ ቤት፤ በአስተዳደር ፍርድ ቤት፤ በህግ አውጭው እና በተቋማት የሚደረጉ የስልጣን መቆጣጠሪያ መንገዶችን በተግባር እየፈተነ ያጠናል፡፡ አራተኛ፤ ህጉ በአስተዳደር አካላት ወይም በመንግስት ባለስልጣናት በተወሰዱ እርምጃዎች መብታቸው ለተጣሰና ነፃነታቸው ለተገፋ ዜጎች መፍትሔ ይሰጣል፡፡q መብት ያለ መፍትሔ ‘ላም አለኝ በሰማይ’ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ መብቱ የተጓደለበት ሰው አቤቱታ አቅርቦ መፍትሔ የሚጠይቅበትና የሚያገኝበት የህግ ክፍል ነው፡፡   የአስተዳደር ህግ ግብና ተግባራት የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ዓላማና ተግባር ስልጣንን መቆጣጠር ስለመሆኑ በመስኩ ምሁራን ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ሆኗል፡፡ ሆኖም በዚህ ብቻ ሳይወሰን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትንም ያከናውናል፡፡ እንደ ብዙዎች የአስተዳደር ህግ ሊቃውንት የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ግብ አስተዳደራዊ ፍትህን ማስፈን ሲሆን የሚከተሉት ተግባራት ይኖሩታል፡፡ ስልጣን መቆጣጠር (Control Function) የአስተዳደር ህግ ስራ አስፈፃሚው የመንግስት አካልና የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች፣ ሚኒስትሮች፣ ባለስልጣናትና ሌሎች ሹመኞች በህግ ተለይቶ የተሰጣቸውን ስልጣን አልፈው እንዳይሄዱና ህጋዊ ስልጣናቸውንም አለአግባብ እንዳይገለገሉበት ለመቆጣጠር የሚያስችለን የህግ ክፍል ነው፡፡ በመሆኑም ስልጣን በህገ ወጥ መንገድ አለአግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል በመከላከል እንደ መገደቢያ መሳሪያነት ያገለግላል፡፡r ግዴታ ማስፈፀም (Command Function) በአስተዳደሩ በሚፈፀም ድርጊት የዜጋው መብት ከሚጣስበት ሁኔታ ባልተናነስ ህጋዊ ግዴታን አለመወጣት በግል መብትና ጥቅም ላይ የከፋ ጉዳት ያስከትላል፡፡ የአስተዳደር ህግ ስልጣን በልኩና በአግባቡ ተግባር ላይ እንዲውል ከመቆጣጠር ባሻገር የአስተዳደር አካላት በህግ ተለይቶ የተጣለባቸውን ግዴታ እንዲወጡ አስገዳጅ የስነ ስርዓትና ተቋሟዊ ስልቶችን ይቀይሳል፡፡s አስገዳጅ የህግ ማዕቀፍ ከሌለ ግዴታ በፈቃድ ላይ የተመሰረተ ውዴታ ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡ የአስተዳደር ፍትህ ማስፈን በየትኛውም ህግን ለማስፈፀም ስልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል የሚወሰዱ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና እርምጃዎች የህዝብ አመኔታና ተቀባይነት እንዲያገኙ ፍትሐዊነታቸው በተጨባጭ ሊታይ ይገባል፡፡ የአስተዳደር ህግ አይነተኛ ተልዕኮ የአስተዳደር ፍትህን ማስፈን ነው፡፡t ግልጽነት ተጠያቂነትና የህዝብ ተሳትፎ የአስተዳደር ህግ በመንግስት አስተዳደር ስራ ውስጥ ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና የህዝብ ተሳትፎ እንዲረጋገጥ ተግባራዊ መሳሪያ በመሆን ያገለግላል፡፡ የስልጣን ልኩ ሳይታወቅና ከልክ በላይ የሆነ ስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቱ ሳይቀየስ ስለተጠያቂነት ማውራት የማይመስል ነገር ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ዜጎች መረጃ የማግኘት መብታቸውን በህግ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ በህዝብ አስተዳደር ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ የሚያስችሉ የስነ- ስርዓት ደንቦችን ይዘረጋል፡፡ ለተበደለ ወገን መፍትሔ መስጠት የአስተዳደር ህግ ዜጎች ለደረሰባቸው በደል በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ባሉ መንገዶች አቤቱታ አቅርበው በአነስተኛ ወጪ እና በቀላሉ መፍትሔ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡ ስለ አስተዳደር ህግ በተደጋጋሚ ቢወራ ‘አንጀት ጠብ’ የሚል፣ የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ፣ መፍትሔ እስከሌለ ድረስ ረብ የለሽነቱን ያጎላው እንደሆነ እንጂ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ የአስተዳደር ህጋቸው በዳበረ አገራት የመንግስት ባለስልጣናት በህዝብ ላይ ለሚፈፅሟቸው አስተዳደራዊ በደሎች በዝርዝር የተቀመጡ የመፍትሔ መንገዶች አሏቸው፡፡ በአንድ አገር ውስጥ የአስተዳደር ህግ ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራቱን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተወጥቷል ለማለት ከአገሪቱ የመንግስት አወቃቀር ስርዓት፤ ህገ መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ ዕድገትና የአስተዳደር ህግ ተቋማት መዳበር ከግምት ውስጥ በማስገባት አንፃራዊ በሆነ መልኩ የሚለካ ጉዳይ ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን በአንድ አገር ውስጥ ሁሉን አቀፍ ውጤታማና ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ የአስተዳደር ህግ ስርዓት አለ ለማለት ከሚከተሉት ሶስት ዋነኛ መርሆዎች አንጻር እየተመነዘረ መገምገም አለበት፡፡ የአስተዳደር ፍትህ የአስተዳደር በደል በፍርድ የሚታረምበትና አስተዳደራዊ ፍትሕ የሚገኝበት የፍርድ ሂደትና መንገድ እንዲሁም ተሞክሮ በአገራችን ውስጥ በግልጽ የሚታወቅ አይደለም፡፡ የአስተዳደር ፍትሕ የአስተዳደር ህግ ‘ልቡ’ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አስተዳደራዊ በደል አለቅጥ በተንሰራፋበት አገር ውስጥ የአስተዳደር ህግ ትንፋሽ ያጠረው ህላዌነቱ የሚያጠራጥር ህግ ነው፡፡ የከለላው መጠን የአስተዳደር ፍትህ ደረጃ አንጻራዊ መለኪያ ነው፡፡ የስራ አስፈፃሚው ተጠያቂነት የዚህ መርህ ዋና አላማ ህግ የማስፈፀም ስልጣን ያለው አካል ለሚፈፅመው ድርጊት እና ለሚወስደው እርምጃ በህዝብ ፊት ተጠርቶ እንዲጠየቅና ማብራሪያ እንዲሰጥ ለማስገደድ ነው፡፡ ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣንን የተቀበለ አካል ወይም ባለስልጣን የሚፈፅመው ድርጊት የህዝቡን ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆን ይኖርበታል፡፡ ውሳኔ ሰጭው ለድርጊቱ ትክክለኛነትና ፖለቲካዊ ተገቢነት ህግ አውጭው ፊት ተጠርቶ በመቅረብ ለማብራሪያ የሚገደድበት ስርዓት ከሌለ በቀር ተጠያቂነት አለ ማለት አይቻልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አስተዳደሩ በዜጎች መብት ለሚያደርሰው ጉዳት በፍርድ ሂደት ለድርጊቱ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡ መልካም አስተዳደር በዚህ መርህ መሰረት አስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሁሉን አቀፍ ተቀባይነት ላገኙ መሪ ደንቦች መገዛት አለበት፡፡ እነዚህም የፍትሀዊነት፣ ምክንያታዊነት፣ ሚዛናዊነትና የግልፅነት መርሆዎችን ያጠቃልላሉ፡፡ አስተዳደራዊ ውሳኔ በህጉ መሰረት መወሰዱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የውሳኔው መሰረት ከቅን ልቦና የመነጨ፣ ለባለጉዳዩ ግልፅ በሆነ አሰራርና መንገድ ያልተወሰደ ካልሆነ በስተቀር የመንግስት አስተዳደር ወደ መልካምነት ደረጃ ለመድረስ ገና ብዙ ይቀረዋል፡፡ የአስተዳደር ህግ እነዚህን መርሆዎች እንዲዳብሩ ከማድረግ አንፃር አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ስለሆነም የህጉ የእድገት ደረጃ የአንድ አገር የመልካም አስተዳደር ሁኔታ ጠቋሚ መለኪያ ነው ማለት እንችላለን፡፡

የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት አፈፃፀም።


የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት አፈፃፀም። ተደጋግሞ እንደተገለፀው የመንግስት ስልጣን በወርድም በቁመትም እየሰፋ በመጣ ቁጥር ለዜጐች መብትና ነፃነት ፀር ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ የስልጣንን አስፈላጊነት አምኖ ተቀብሎታል፡፡ ውጤታማ አስተዳደር እንዲሁም ቀልጣፋ የአገልግሎት አቅርቦት እንዲኖር የሚያስር ሳይሆን የሚፈታ ስልጣን ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ከህግና ከህገ መንግስት የሚያፈነግጥ ስልጣን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ የበዘፈቀደ ድርጊት፣ ‘እንደፈለግኩኝ እሆናለው እፈልጣለው እቆርጣለው!’ የሚል አካሄድ አቅመ ቢስ የሆነውን ዜጋ የመኖር፣ በነፃነት የመንቀሳቀስ፣ የመናገር፣ ሀሳብን የመግለፅና ንብረት የማፍራት መሰረታዊ መብት አለገደብ ይሸረሽራል፡፡ የአስተዳደር ህግ የሰብዓዊ መብትን በማስጠበቅ ረገድ ያለው ሚና የሁለቱን ትስስር በሚገባ ያሳየናል፡፡ ህጉ በሰብዓዊ መብት አጠባበቅና አፈፃፀም ላይ ያለውን አዎንታዊ ተፅእኖ በሚገባ ለመረዳት ከሰብዓዊ መብቶች አተገባበር አንፃር የመንግስትን ግዴታ መተንተኑ አግባብነት ይኖረዋል፡፡ እነዚህም ሚናዎች (ግዴታዎች) የማክበር (respect) የማስከበር (protect) እንዲሁም የመፈጸምና የማስፈፀም (enforcement) ናቸው፡፡ በመጀመሪያው መብቶችን የማክበር የመንግስት ሚና ዜጐች ነፃ ሆነው መብታቸውን ሲጠቀሙ ከየትኛውም የመንግስት አካል የሚመጣ ጣልቃ ገብነትን ይገድባል፡፡ በተለይም መሰረታዊ በሚባሉት በህይወት የመኖር፣ የመፃፍ፣ የመናገር፤ የፈለጉትን ሀይማኖት የመከተል፤ በነፃነት የመዘዋወርና ንብረት የማፍራት መብቶችና ነፃነቶች በተግባር የሚረጋገጡት መንግስት እጁን ሲሰበስብ ነው፡፡ እነዚህ መብቶች በመንግስት በተለይ በስራ አስፈፃሚውና በስሩ ባሉት የአስተዳደር ተቋማት ውሳኔ፤ ትዕዛዝ፤ ደንብና መመሪያ አማካይነት አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ ህገ መንግስቱ የበላይ ህግ እንደመሆኑ ይህን የሚቃረን ህግ፣ ውሳኔና አሰራር ሁሉ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ይህን መሰሉ የህገ መንግስታዊነት ጥያቄ በአስተዳደር ህግ ውስጥ አይወድቅም፡፡ ይሁን እንጂ የህገ መንግስታዊነት ብቻ የሚመስል ጥያቄ በአስተዳደር ህግ ማእቀፍ የሚሸፈንበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡ በአንድ የአስተዳደር ተቋም የወጣ መመሪያ በህግ አውጭው ከተሰጠ የውክልና ስልጣን በማለፍ የዜጐችን ሰብዓዊ መብት የሚገድብ ሆኖ ከተገኘ በውስጡ የህገ መንግስታዊነት (constitutionality) ጥያቄ ያዘለ ቢሆንም በዋናነት ግን የአስተዳደር ህግ ሊመልሰው የሚገባ የህጋዊነት (legality) ጥያቄ ነው፡፡ ልዩነታቸውን የበለጠ መረዳት እንዲያስችልን የሚከተለውን የድሮው የገቢዎች ሚኒስቴር የአሁኑ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መመሪያ እንመልከት፡፡ ማንኛውም የጉምሩክ ፖሊስ ሰላማዊ ስልፍና የስራ ማቆም አድማ ማድረግ አይችልም፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ለማንኛውም ሰው የተረጋገጠ መብት ነው፡፡ መብቱን የሚያጎናጽፈው የአንቀጽ 30 ንዑስ ቁጥር 1 እንዲህ ይነበባል፡፡ ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ አንድ መመሪያ በስራ አስፈፃሚው አካል ሲወጣ ከህግ አውጭው በግልጽ የተሰጠ የውክልና ስልጣን (Delegation) ሊኖር ይገባል፡፡ መመሪያው የውክልና ስልጣኑን ገደብ ካለፈ ከስልጣን በላይ (Ulta vires) ነው፡፡ ስለሆነም በህግ ፊት ዋጋ አልባ (null and void) ነው፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር ይህን መመሪያ ሲያወጣ የስልጣን ምንጩን የጉምሩክ ባለስልጣንን ለማቋቋምና አስራሩን ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁ. 368/1995 አንቀጽ 8 (2) (ሐ) እንደሆነ ይጠቅሳል፡፡ ይህ የተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ እንዲህ ይነበባል፡፡ የጉምሩክ ህግ እንዲያስከብር ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተመደበን የፖሊስ ኃይል ሚኒስቴሩ የፌደራል ፖሊስ አዋጅን ተከትሎ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት በስራ ያሰማራል፡፡ ያስተዳድራል፡፡ ጥፋት ሲገኝም ያሰናብታል፡፡ ይህ አንቀጽ የጉምሩክ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርግ በመመሪያ እንዲከለክል ለገቢዎች ሚኒስቴር ስልጣን አይሰጥም፡፡ ከተወካዮች ምክር ቤት ግልፅ ስልጣን ባልተሰጠበት ሁኔታ የወጣው ይህ መመሪያ ህጋዊነት ሆነ ተፈፃሚነት የለውም፡፡ የአስተዳደር ህግ ይህን መሰል መመሪያዎች በዘፈቀደ እየወጡ የዜጐችን መብትና ነፃነት እንዳይጥሱ በተለያዩ መንገዶች በመቆጣጠር መንግስት ሰብዓዊ መብት የማክበር ግዴታውን እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ የመንግስት የማስፈፀም ኃላፊነት አብዛኛውን ጊዜ ከማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ መብቶች ጋር በቀጥታ ተያይዞ ይነሳል፡፡ መንግስት በዜጐች መብት ላይ ጣልቃ አለመግባቱ ወይም እጁን መሰብሰቡ ብቻ አይበቃም፡፡ ለዜጋው መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማለትም ጤና፣ መብራት፣ ውሃ፣ መንገድ ወዘተ… ካላቀረበ ነፃ መሆን በራሱ ፋይዳ የለውም፡፡ የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት ትሰስር ከመንግስት የማስከበር ግዴታ አንጻርም ሊቃኝ ይችላል፡፡ ከዚህ አንጻር መንግስት ሰብዓዊ መብትን በማስከበር ኃላፊነቱ መብት እንዳይጣስ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶች በህግ እና በተቋማዊ አደረጃጀት የማጠናከር፣ በመብት መጣስ ጉዳት ለደረሰበት ዜጋ ፈጣን ፍትህ የሚያገኝበትን ስርዓት መዘርጋት አለበት ማለት ነው፡፡ በአጭር አገላለጽ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ መንግስት የዳበረ የአስተዳደር ህግ እና የአስተዳደር ህግ ስርዓት መቅረጽ፣ መትከልና ማጐልበት ይጠበቅበታል፡

ጣልቃ ገብ፦


ጣልቃ ገብ፦ በፍትሃ ብሔር ክርክር ተካፋይ ያልነበረ ሰው የክርክሩ ተካፋይ የሚሆንበትና መብቱንና ጥቅሙን ለማስከበር ተገቢውን ክርክር እንዲያቀርብ በህጉ የተዘረጋ ስርዓት ጣልቃ ገብ ወደ ክርከሩ የሚገባው በተከሳሽ ጠያቂነት ወይም በራሱ አነሳሽነት ሊሆን እንደሚችል የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41 ድንጋጌ ይዘት ያሳያል፡፡ በዚህ ድንጋጌ እንደተመለከተው ሌሎች ወገኖች በሚከራከሩበት ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሶስተኛ ወገን ከፍርድ ውሳኔ በፊት ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር እንዲፈቀድለት ሊከራከር ይችላል፡፡ ሆኖም የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብ ለመሆን ሌሎች ሰዎች በሚከራከሩበት ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ በቀጥታ መብቱንና ጥቅሙን የሚነካ መሆኑን የማስረዳት ግዴታውን መወጣት አለበት፡፡ በሌላ አገላለፅ ጣልቃ ልግባ ጥያቄ ተቀባይነት እንዲኖረው ውሳኔው የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነውን ሰው መብትና ጥቅም በሚጎዳ መልኩ በቀጥታ የሚፈጸም መሆኑንና ሌላ አዲስ ክስ በማቅረብ ለማስቀረት የማይቻል መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላል፡፡ ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ጣልቃ ገብ ልሁን በሚል ጥያቄ የሚያቀርብ ሰው ውሳኔው በቀጥታ መብቱንና ጥቅሙን የማይጎዳ ከሆነ እና አዲስ ክስ በማቅረብ ማስቀረት የሚቻልበት ሁኔታ ያለው ከሆነ ጥያቄው በህግ ፊት ተቀባይነት የሚያገኝበት ሁኔታ የሌለ መሆኑን ነው፡፡ ጣልቃ ልግባ የሚለው ወገን በተከራካሪ ወገኖች መካከል ባለው ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ መብቱን በምን አግባብና መልኩ ሊነካ እንደሚችል ማሳየት እንደአለበት የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41(2) ድንጋጌ ያሳያል፡፡ በመሆኑም አመልካቹ ዝርዝር ምክንያቱን በማስፈር ይህንኑ የማስረዳት ግዴታ አለበት፡፡ የጣልቃ ገብነቱ አቤቱታ ሊቀርብ የሚገባውም ጊዜ ለማራዘም፣ ክርክሩን ለማጓተት ሊሆን እንደማይገባው ከተጠቃሹ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ እንዲሁም ከፍትሃ ብሔር ስነ ስርዓት ህጉ መሰረታዊ አላማ የምንገነዘበው ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41 በአንድ ክስ ሌሎች ተከራካሪ ወገኖች በክርክር ላይ ባሉበት ጊዜ ማናቸውም ሶስተኛ ወገን በጉዳዩ ያገባኛል የሚል ሲሆን ከፍርድ ውሳኔ በፊት ጣልቃ ገብ ሆኖ ለመከራከር እንደሚችል እና የጣልቃ ገብነት ማመልከቻው በክሱ ውስጥ ያገባኛል የሚልበትን ምክንያት የሚዘረዝርና በተለይም የመብቱን ሁኔታ የሚገልጽ መሆን እንዳለበት፣ እንዲሁም የጣልቃ ገብነት ጥያቄ አቅራቢው በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር የሚያስችል መብት ያለው መሆን አለመሆኑ በቅድሚያ ሊወሰን እንደሚገባው፣ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል መብት የለውም በተባለ ጊዜ መሰናበት እንደሚገባው እና መብት አለው በተባለ ጊዜ ግን የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆን ከተደረገ በኃላ ከጣልቃ ገቡ መብት አንፃር ጭምር አጠቃላይ ክርክሩ ተመርምሮ ተገቢ ነው የሚባል ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ከፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 41 (1)፣ (2) እና (3) ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡ ቤትና ይዞታን በሚመለከት በሚደረግ ክርክር አንድ ጣልቃ ገብ አመልካች ክርክር በሚደረግበት ቤትና ይዞታ ላይ ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር መብት አለኝ በማለት መብቱን የሚያሳዩ ሰነዶችን አቅርቦ እያለ የባለይዞታነት ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር አላቀረብክም ተብሎ ከወዲሁ ጣልቃ ገብተህ ልትከራከር አትችልም ተብሎ አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ አግባብነት የለውም፡፡

ጠባቂ


 በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2089/2/ ድንጋጌ መሰረት ጥቅም የሌለው ግንኙነት መኖሩ ቢረጋገጥም የመኪና ባለሃብት ወይም ጠባቂ ጥፋት ማድረጋቸው ከተረጋገጠ በመኪናው በነጻ ተሳፍሮ ሲጓዝ ጉዳት ለደረሰበት ተሳፋሪ ተጠያቂነት አለባቸው፡፡ በድንጋጌው ስር “ጠባቂ” የሚለው ቃል የአማርኛው አቻ የእግሊዘኛ ቃሉ ‘’holder’’ በሚል የተቀመጠ ሲሆን ይህ ቃል በሕግ መዝገበ ቃላት ከተሰጠው ትርጉም አንዱ a person who possesses or uses property በሚል የተቀመጠ መሆኑን ታዋቂው የብላክስ ሎው መዝገበ ቃላት ያሳያል፡፡ ስለሆነም ጠባቂ የሚለው ቃል የሚመለከተው ለራሱ ጥቅም መኪናውን ይዞ የሚገኘውን ሰው ነው፡፡

የአስተዳደር መንግስት እና የአስተዳደር ህግ ውልደት


የአስተዳደር መንግስት እና የአስተዳደር ህግ ውልደት
በ19ኛው ክፍለ ዘመን ገኖ የነበረው የነፃ ገበያ (laisse faire) ንድፈ ሀሳብ በዋነኛነት ውስን የመንግስት ጣልቃ ገብነትና ሰፊ የግለሶቦች ነፃነትን ያቀነቅናል፡፡
a በዚሁ ንድፈ ሀሳብ መሰረት የመንግስት ሚና ህግና ስርዓት ከማስጠበቅና አገርን ከጠላት ወረራ ከመከላከል የዘለለ መሆን የለበትም፡፡ ምርጥ መንግስት ማለት በስሱ (በትንሹ) የሚገዛ መንግስት ማለት ነው፡፡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን መምራት፣ መቆጣጠርና መግራት እንደ መንግስት ኃላፊነት አይቆጠርም፡፡ሆኖም ነፃ የሆነው የገበያና የመንግስት ስርዓት እግረ መንገዱን ይዞ የመጣቸው አሉታዊ ውጤቶች በዋነኛነት ያረፉት በደካማውና ደሀው የህብረተሰብ ክፍል ጫንቃ ላይ ነበር፡፡ በሀብታምና ደሀ መካከል የተፈጠረው የሀብት ድልድል ልዩነት በእጅጉ እየሰፋ በመምጣቱ ሀብታም የበለጠ ሲበለፅግ ደሃው ግን ይባስ እየቆረቆዘ መሄድ ጀመረ፡፡ በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የነበረው የመደራደር አቅም ልዩነት ታይቶ ለማይታወቅ የጉልበት ብዝበዛ ምክንያት ሆነ፡፡ እነዚህ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠንቆች ለነፃ ገበያ ስርዓትና አስተሳሰብ ፈታኝ ሁኔታዎች ነበሩ፡፡ስለሆነም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠንቆች መፍትሔ መስጠት የመንግስት ግዴታና ኃላፊነት የመሆኑ እውነታ ቀስ በቀስ እየተገለጠ መጣ፡፡b በተለይም የሁለተኛው የአለም ጦርነትን ተከትሎ የተከሰቱት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች የመንግስት ጣልቃ ገብነት አስፈላጊነትን ከመቼውም ጊዜ በላይ በገሃድ አስረግጠዋል፡፡ መንግስት ኃላፊነቱን መወጣት የሚችለው ደግሞ አወቃቀሩና አደረጃጀቱ ሲገፉት የሚፍረከረክ ዓይነት ‘ልል’ ወይም ውስን መንግስት መሆኑ ቀርቶ ጡንቻው የዳበረና ስልጣኑ የሰፋ ጠንካራ መንግስት ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠንቆች መፍትሔ መስጠት የመንግስት ግዴታ ነው ሲባል ሚናው ከተለመደው ስርዓትና ፀጥታ ማስከበር ባሻገር ሰፊና ውስብስብ አዎንታዊ ተግባራትን ወደ ማከናወን መሸጋገር እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡በዚሁ መሰረት የመንግስት ሚና ቀስ በቀስ ከፖሊስነት (Police State) ወደ ማህበራዊ አገልግሎት አቅራቢነት ሊሸጋገር ችሏል፡፡ መንግስት በአገልግሎት አቅራቢነት ሚናው ውሀ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ መንገድ ወዘተ የመሳሰሉ መሰረታዊ ፍላጐቶችን የማሟላት ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ በተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅጣጫውን ፈር ለማስያዝና ፍትሐዊ የሀብት ድልድል እንዲኖር እንዲሁም ለደካማው የህብረተሰብ ክፍል ጥበቃና ከለላ ለማድረግ በአጠቃላይ የነፃ ገበያን አሉታዊ ውጤቶችን ለመቀነስ ሰፊና ተከታታይ ቁጥጥርና ክትትል (Regulation) ያደርጋል፡፡ አዲሱ የማህበራዊ መንግስት አዲሱን አዎንታዊ ሚናውን በብቃትና ውጤታማ በሆነ መንገድ ይወጣ ዘንድ በዓይነትና በይዘት የጠንካራ ስልጣን ባለቤት ሊሆን የግድ የሚል ሀቅ ነው፡፡cየስልጣን አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስልጣን በየጊዜው ወሰኑ፣ መጠኑና ቅርጹ እያደገና እየሰፋ በመጣ ቁጥር ግን የግለሰቦችን መብትና ነፃነት መንካቱ አይቀርም፡፡ የመንግስት ስልጣን እየተለጠጠ መሄድ አቅመቢስ ለሆነው ዜጋ የስጋት ምንጭ ነው፡፡ ፍፁም የሆነና ወደ ፍፁምነት የተጠጋ ስልጣን ወደ ህገ ወጥነትና የበዘፈቀደ ድርጊት የማምራት አደገኛ አዝማሚያ አለው፡:የአስተዳደር ህግ በየጊዜው እያደገ የመጣውን የመንግስት ‘ጡንቻ መፈርጠም’ በቅጡ ለመቆጣጠር በታሪክ ሂደት በተጓዳኝ የተፈጠረ የህግ መሳሪያ ነው፡፡ መንግስት ተግባራቱን ለማከናወን ፖሊሲ ቀርጾ፣ ህግ አውጥቶ በሚያስፈጽምበት ወቅት በስልጣን እና በፍትህ (የግለሰቦች ነፃነት) መካከል ቅራኔ መከሰቱ የማይቀር እውነታ ነው፡፡ ጥያቄው ቅራኔው እንዴት ይፈታል? ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ የዚህ ቅራኔ የራሱ ውጤት ሲሆን ቅራኔውን በአንፃራዊ መልኩ ለማስማማትና ለማጣጣም በታሪክ ሂደት ብቅ ያለ ተግባራዊ መሳሪያ ነው፡፡d የአስተዳደር ህግ በዕቅድ ታስቦ የተወለደ ሳይሆን በሁኔታዎች አስገዳጅነት የተፈጠረ ክስተት ነው፡፡ ህጉ በሁለት በጉልበት የማይመጣጠኑ ጐራዎች ማለትም በመንግስትና በግለሰብ መካከል ሚዛናዊነትንና ፍትሐዊነትን ለማስፈን ይጥራል፡፡የአስተዳደር ህግ መንግስት በተለይ ስራ አስፈፃሚውና የአስተዳደር አካላት በህግ ከተፈቀደላቸው የስልጣን ክልል አልፈው ህገ ወጥ ድርጊት እንዳይፈጽሙ ቁጥጥር የሚያደርግና ይህንንም የሚያረጋግጥ ህግ ነው፡፡e በዚህም የህግ የበላይነት እንዲሰፍንና የግለሰቦች ህገ መንግስታዊ መብቶች እንዳይሸራረፉና እንዳይጣሱ ከለላ በመስጠትf ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ በተጨማሪም በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ያለው ስልጣን በአግባቡና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል መሪ ደንቦችን በማስቀመጥና ስነ ስርዓታዊ ቅድመ ሁኔታዎችን በመዘርጋት የተለያዩ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችን በመጠቀም የግለሰቦችና የዜጐች መብቶችና ነፃነቶች እንዳይገሰሱና እንዳይደፈሩ ከለላ በመስጠት የህገ መንግስት ማስፈፀሚያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ የአስተዳደር ህግ ምንነትለአስተዳደር ህግ ብያኔ በማበጀት ረገድ የመስኩ ባለሙያዎች በከፊልም ቢሆን የተለያየ እይታ አላቸው፡፡ በእርግጥ የአስተዳደር ህግ የጥናት ወሰኑን አስመልክቶ የሚከሰት ልዩነት ካልሆነ በቀር በመሰረታዊ እሳቤው ላይ የተራራቀ አቋም የለም፡፡ እንደ ህንዳዊው የአስተዳደር ህግ ምሁር አይ.ፒ. ማሴይ አገላለጽ በአስተዳደር ህግ ትርጓሜ ላይ ያለው ልዩነት ምንጩ በየጊዜው እያደገና እየተወሳሰበ የመጣው አስተዳደራዊ ሂደት ሲሆን ይህም ሂደቱን በሙሉ አጠቃሎ የያዘ ወጥ ትርጉም ለመስጠት አስቸጋሪ አድርጐታል፡፡gያም ሆኖ የአስተዳደር ህግ ትርጓሜ ቢያንስ ሁለት መሰረታዊ አላባውያንን ማካተት ይጠበቅበታል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የአስተዳደር ህግ ከይዘት ይልቅ ስነ ስርዓት ላይ የሚያተኩር ህግ ስለመሆኑ ግልጽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም የአስተዳደር ውሳኔው እንዴት ተሰጠ? እንጂ ይዘቱ ትክክል ይሁን አይሁን ፍርድ ቤቶች ሆነ የአስተዳደር ህግ ጣልቃ የሚገባበት ጉዳይ አይደለም፡፡በሁለተኛ ደረጃ ማንኛውም የአስተዳደር ህግ ትርጓሜ የህጉን ዓላማ ግምት ውስጥ ያስገባ ተግባራዊ አቀራረብ እንዲያቅፍ ይጠበቅበታል፡፡ የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ዓላማ ወይም ተግባር ስልጣንን መቆጣጠር ነው፡፡h ያ ሲባል ግን የአስተዳደር አካላት ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩና እንዳይላወሱ ማነቆ ሆኖ ያግዳቸዋል ማለት አይደለም፡፡ የስልጣን ቁጥጥር ሲባል ማንኛውም ባለስልጣን ሆነ መስሪያ ቤት በህግ ተለይቶ ከተቀመጠለት የስልጣን ገደብ እንዳያልፍና ስልጣን ቢኖረውም እንኳን ስልጣኑን ፍትሐዊና አግባብ በሆነ መንገድ እንዲወጣ ያደርጋል ለማለት ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ዓላማና ተግባር ስልጣንን በተግባር መቆጣጠር እንደመሆኑ ይህን ባህርዩን ግምት ውስጥ ያላስገባ ብያኔ የተሟላ ተብሎ ሊወሰድ ሆነ ሊወደስ አይችልም፡፡ለንጽጽር እንዲረዳን በመስኩ ባለሙያዎች ለአስተዳደር ህግ የተሰጡ ትርጓሜዎችን እንደሚከተለው እንጠቅሳለን፡፡ቤርናርድ ሺዋሬዝ (Bernard Schwartz) የአስተዳደር ህግን ‘በውክልና ህግ የማውጣትና አስተዳደራዊ ዳኝነት የመስጠት ስልጣን ባላቸው የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ህግ’ በማለት ይገልፀዋል፡፡i ይህ ብያኔ ጠባብ ከመሆኑ በቀር ስለ ህጉ ይዘት ገላጭ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ በውክልና ስልጣን ህግ ከማውጣትና ከአስተዳራዊ የዳኝነት ስልጣን በተጨማሪ ይህ ስልጣን በፍርድ የሚታረምበትን የአጣሪ ዳኝነት (judicial review) ስነ-ስርዓት እንዲሁም በፖርላማና በተለያዩ ተቋማት የሚደረግ ቁጥጥርንም ያካትታል፡፡ጄኒንግስ በበኩሉ የአስተዳደር ህግ ማለት ‘አስተዳደርን የሚመለከት ህግ ነው፡፡ ይህ ህግ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶችን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ግዴታ ይወስናል፡፡’ በማለት ይገልጸዋል፡፡j እንደ አይ.ፒ ማሴይ አስተያየት ይህ ትርጓሜ የአስተዳደር ህግን ከህገ መንግስት በግልጽ አይለይም፡፡ አስተዳደር ወይም ማስተዳደር ማለት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስልጣንን በመጠቀም የህብረተሰቡን ጉዳይ መምራት ማለት ነው፡፡k ለዚህም በዋነኛነት አደራ የተጣለባቸው አካላት የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የእነዚህ ተቋማት ስልጣንና ግዴታ በዝርዝር ህግ ተለይቶ ቢወሰንም የስራ አስፈፃሚው አካል ስልጣን በጠቅላላው የሚቀመጠው በህገ መንግስት ላይ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ሆነ ህገ መንግስት ሁለቱም የመንግስት አስተዳደርን ወይም የግለሰብና የመንግስትን ግንኙነት የሚመሩ ህጐች እንደመሆናቸው በመካከላቸው ያለው መለያ ክር በጄኒንግ ትርጓሜ ላይ በግልጽ ነጥሮ አልወጣም፡፡ታዋቂው የህገ መንግስት ሊቅ ኤ. ቪ. ዲሴይ የአስተዳደር ህግን በሶስት ደረጃዎች ከፋፍሎ እንዲህ ይገልጸዋል፡፡lየአስተዳደር ህግ የመንግስት ባለስልጣናትን የህግ ስልጣንና ተጠያቂነት የሚወስኑትን የአንድ አገር የህግ ስርዓት የሚመለከት የህግ ክፍል ነው፡፡ግለሰቦች ከመንግስት አካላት ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ያላቸውን መብትና ግዴታ ለይቶ ይወስናል፡፡እነዚህ መብቶችና ግዴታዎች ተፈጻሚ የሚሆኑበትን ስርዓት ይዘረጋል፡፡እንደ ማሴይ ትችት ይህ ትርጓሜ የአስተዳደር ህግ አንድ አካል የሆነውን አጣሪ ዳኝነት (judicial review) ብቻ የሚመለከት እንደመሆኑ በይዘቱ ጠባብ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ከአጣሪ ዳኝነት በተጨማሪ በህግ አውጭውና በተቋማት (ለምሳሌ በእንባ ጠባቂ ተቋምና ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን) አማካይነት የሚደረግ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችንም ያካትታል፡፡ ህጉ ከመንግስት ባለስልጣናትና ከአስተዳደር መስሪያ ቤቶች በተጨማሪ ከፊል የአስተዳደር አካላት ተብለው የሚፈረጁትን መንግስታዊ ኮርፖሬሽኖች፤ ዩኒቨርሲቲዎች እና በከፊል መንግስታዊ ነክ ስልጣን ያላቸውን ማህበራትm በተመለከተም ተፈጻሚነት አለው፡፡በመጨረሻም ታዋቂው የህንድ ምሁር አይ.ፒ. ማሴይ ከላይ ከተሰጡት ሰፋ ያለና የህጉን ባህሪያትና ተግባራት ጠቅልሎ የያዘ ብያኔ እንደሚከተው ያስቀምጣል፡፡የአስተዳደር ህግ የህዝብ አስተዳደር ህግ አካል ሲሆን የአስተዳደርና ከፊል አስተዳደር መስሪያ ቤቶችን አደረጃጀትና ስልጣን የሚደነግግ፣ አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሰጥበትን ደንብና መርህ የሚያስቀምጥ፣ እንዲሁም ከግለሰቦች መብትና ነፃነት ውሳኔው የሚታረምበትን ስርዓት የሚወስን የህግ ክፍል ነው፡፡nይህ ትርጓሜ ከሞላ ጐደል ሁሉንም የአስተዳደር ህግ ባህርያት አጠቃሎ የያዘ በመሆኑ ተመራጭነት አለው፡፡ ከላይ ከቀረቡት የተለያዩ ትርጓሜዎች የሚከተሉት የጋራ ነጥቦች ይመዘዛሉ::አንደኛ፤ የአስተዳደር ህግ የአስተዳደር እና ከፊል የአስተዳደር አካላት ያላቸውን ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት ያጠናል፡፡o የማንኛውም የአስተዳደር አካል የስልጣን ምንጭ የሚገኘው ከማቋቋሚያ አዋጁ (Enabling Act) ሲሆን አልፎ አልፎ በሌላ ዝርዝር ህግ ይወሰናል፡፡ በአስተዳደር ህግ የመጀመሪያው ጥያቄ ውሳኔ ወይም እርምጃ የወሰደው አካል በህግ የተሰጠው ስልጣን አለው? የሚል ነው፡፡ ከሌለ ድርጊቱ ከስልጣን በላይ ስለሆነ ዋጋ አልባ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ከድርጊቱ በስተጀርባ የህግ ስልጣን ካለ ውሳኔ ሰጪው ስልጣኑን በአግባቡና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንደተገለገለ ይጣራል፡፡ ካልሆነ ስልጣኑን ያለ አግባብ በሚገለገለው አካል ላይ ህጉ ቁጥጥር ያደርግበታል፡፡ሁለተኛ፤ ህጉ ስልጣንን በመገልገል ሂደት ተፈጻሚ የሚሆኑ መሪ ደንቦችን፤ ስነ ስርዓቶችንና መርሆዎችን ያስቀምጣል፡፡ ህግ አውጭው ለአስተዳደር አካላት ስልጣን ሲሰጥ ስልጣኑ ተግባር ላይ በሚውልበት ጊዜ ህጋዊነቱንና ፍትሐዊነቱን የሚያረጋግጥ የስነ ስርዓት ቅድመ ሁኔታ አብሮ እንዲደነግግ ይጠበቃል፡፡ ለምሳሌ ያህል ደንብና መመሪያ በማውጣት ረገድ ከሚመለከተው አካል ጋር የመመካከርና የህትመት ቅድመ ሁኔታዎች፣ አስተዳደራዊ ውሳኔ ሲሰጥ የመሰማት መብትና የኢ- አድሎአዊነት መርሆዎችን በአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ ወይም በዝርዝር ህግ ማውጣት ይኖርበታል፡፡ እነዚህም በአስተዳደር ሂደቱ ውስጥ ፍትሐዊነትን በማረጋገጥ ረገድ ጉልህ ስፍራ አላቸው፡፡ ስልጣን በዘፈቀደ ሳይሆን በአግባቡ ስራ ላይ ዋለ ለማለት የሚቻለውም ያኔ ነው፡፡ሶስተኛ፤ የአስተዳደር ህግ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችን በተመለከተ የሚያጠና ህግ ነው፡፡p ልጓም የሌለው ስልጣን ለዜጎች መብትና ነፃነት ፀር ነው፡፡ የተጠያቂነት መርሕ እውን እንዲሆን የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችም በግልጽ ተለይተው መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ስለሆነም የአስተዳደር ህግ በፍርድ ቤት፤ በአስተዳደር ፍርድ ቤት፤ በህግ አውጭው እና በተቋማት የሚደረጉ የስልጣን መቆጣጠሪያ መንገዶችን በተግባር እየፈተነ ያጠናል፡፡አራተኛ፤ ህጉ በአስተዳደር አካላት ወይም በመንግስት ባለስልጣናት በተወሰዱ እርምጃዎች መብታቸው ለተጣሰና ነፃነታቸው ለተገፋ ዜጎች መፍትሔ ይሰጣል፡፡q መብት ያለ መፍትሔ ‘ላም አለኝ በሰማይ’ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ መብቱ የተጓደለበት ሰው አቤቱታ አቅርቦ መፍትሔ የሚጠይቅበትና የሚያገኝበት የህግ ክፍል ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ግብና ተግባራትየአስተዳደር ህግ ዋነኛ ዓላማና ተግባር ስልጣንን መቆጣጠር ስለመሆኑ በመስኩ ምሁራን ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ሆኗል፡፡ ሆኖም በዚህ ብቻ ሳይወሰን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትንም ያከናውናል፡፡ እንደ ብዙዎች የአስተዳደር ህግ ሊቃውንት የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ግብ አስተዳደራዊ ፍትህን ማስፈን ሲሆን የሚከተሉት ተግባራት ይኖሩታል፡፡ስልጣን መቆጣጠር (Control Function)የአስተዳደር ህግ ስራ አስፈፃሚው የመንግስት አካልና የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች፣ ሚኒስትሮች፣ ባለስልጣናትና ሌሎች ሹመኞች በህግ ተለይቶ የተሰጣቸውን ስልጣን አልፈው እንዳይሄዱና ህጋዊ ስልጣናቸውንም አለአግባብ እንዳይገለገሉበት ለመቆጣጠር የሚያስችለን የህግ ክፍል ነው፡፡ በመሆኑም ስልጣን በህገ ወጥ መንገድ አለአግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል በመከላከል እንደ መገደቢያ መሳሪያነት ያገለግላል፡፡rግዴታ ማስፈፀም (Command Function)በአስተዳደሩ በሚፈፀም ድርጊት የዜጋው መብት ከሚጣስበት ሁኔታ ባልተናነስ ህጋዊ ግዴታን አለመወጣት በግል መብትና ጥቅም ላይ የከፋ ጉዳት ያስከትላል፡፡ የአስተዳደር ህግ ስልጣን በልኩና በአግባቡ ተግባር ላይ እንዲውል ከመቆጣጠር ባሻገር የአስተዳደር አካላት በህግ ተለይቶ የተጣለባቸውን ግዴታ እንዲወጡ አስገዳጅ የስነ ስርዓትና ተቋሟዊ ስልቶችን ይቀይሳል፡፡s አስገዳጅ የህግ ማዕቀፍ ከሌለ ግዴታ በፈቃድ ላይ የተመሰረተ ውዴታ ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡የአስተዳደር ፍትህ ማስፈንበየትኛውም ህግን ለማስፈፀም ስልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል የሚወሰዱ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና እርምጃዎች የህዝብ አመኔታና ተቀባይነት እንዲያገኙ ፍትሐዊነታቸው በተጨባጭ ሊታይ ይገባል፡፡ የአስተዳደር ህግ አይነተኛ ተልዕኮ የአስተዳደር ፍትህን ማስፈን ነው፡፡tግልጽነት ተጠያቂነትና የህዝብ ተሳትፎየአስተዳደር ህግ በመንግስት አስተዳደር ስራ ውስጥ ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና የህዝብ ተሳትፎ እንዲረጋገጥ ተግባራዊ መሳሪያ በመሆን ያገለግላል፡፡ የስልጣን ልኩ ሳይታወቅና ከልክ በላይ የሆነ ስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቱ ሳይቀየስ ስለተጠያቂነት ማውራት የማይመስል ነገር ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ዜጎች መረጃ የማግኘት መብታቸውን በህግ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ በህዝብ አስተዳደር ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ የሚያስችሉ የስነ- ስርዓት ደንቦችን ይዘረጋል፡፡ለተበደለ ወገን መፍትሔ መስጠትየአስተዳደር ህግ ዜጎች ለደረሰባቸው በደል በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ባሉ መንገዶች አቤቱታ አቅርበው በአነስተኛ ወጪ እና በቀላሉ መፍትሔ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡ ስለ አስተዳደር ህግ በተደጋጋሚ ቢወራ ‘አንጀት ጠብ’ የሚል፣ የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ፣ መፍትሔ እስከሌለ ድረስ ረብ የለሽነቱን ያጎላው እንደሆነ እንጂ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ የአስተዳደር ህጋቸው በዳበረ አገራት የመንግስት ባለስልጣናት በህዝብ ላይ ለሚፈፅሟቸው አስተዳደራዊ በደሎች በዝርዝር የተቀመጡ የመፍትሔ መንገዶች አሏቸው፡፡በአንድ አገር ውስጥ የአስተዳደር ህግ ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራቱን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተወጥቷል ለማለት ከአገሪቱ የመንግስት አወቃቀር ስርዓት፤ ህገ መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ ዕድገትና የአስተዳደር ህግ ተቋማት መዳበር ከግምት ውስጥ በማስገባት አንፃራዊ በሆነ መልኩ የሚለካ ጉዳይ ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን በአንድ አገር ውስጥ ሁሉን አቀፍ ውጤታማና ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ የአስተዳደር ህግ ስርዓት አለ ለማለት ከሚከተሉት ሶስት ዋነኛ መርሆዎች አንጻር እየተመነዘረ መገምገም አለበት፡፡የአስተዳደር ፍትህየአስተዳደር በደል በፍርድ የሚታረምበትና አስተዳደራዊ ፍትሕ የሚገኝበት የፍርድ ሂደትና መንገድ እንዲሁም ተሞክሮ በአገራችን ውስጥ በግልጽ የሚታወቅ አይደለም፡፡ የአስተዳደር ፍትሕ የአስተዳደር ህግ ‘ልቡ’ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አስተዳደራዊ በደል አለቅጥ በተንሰራፋበት አገር ውስጥ የአስተዳደር ህግ ትንፋሽ ያጠረው ህላዌነቱ የሚያጠራጥር ህግ ነው፡፡ የከለላው መጠን የአስተዳደር ፍትህ ደረጃ አንጻራዊ መለኪያ ነው፡፡የስራ አስፈፃሚው ተጠያቂነትየዚህ መርህ ዋና አላማ ህግ የማስፈፀም ስልጣን ያለው አካል ለሚፈፅመው ድርጊት እና ለሚወስደው እርምጃ በህዝብ ፊት ተጠርቶ እንዲጠየቅና ማብራሪያ እንዲሰጥ ለማስገደድ ነው፡፡ ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣንን የተቀበለ አካል ወይም ባለስልጣን የሚፈፅመው ድርጊት የህዝቡን ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆን ይኖርበታል፡፡ ውሳኔ ሰጭው ለድርጊቱ ትክክለኛነትና ፖለቲካዊ ተገቢነት ህግ አውጭው ፊት ተጠርቶ በመቅረብ ለማብራሪያ የሚገደድበት ስርዓት ከሌለ በቀር ተጠያቂነት አለ ማለት አይቻልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አስተዳደሩ በዜጎች መብት ለሚያደርሰው ጉዳት በፍርድ ሂደት ለድርጊቱ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡መልካም አስተዳደርበዚህ መርህ መሰረት አስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሁሉን አቀፍ ተቀባይነት ላገኙ መሪ ደንቦች መገዛት አለበት፡፡ እነዚህም የፍትሀዊነት፣ ምክንያታዊነት፣ ሚዛናዊነትና የግልፅነት መርሆዎችን ያጠቃልላሉ፡፡ አስተዳደራዊ ውሳኔ በህጉ መሰረት መወሰዱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የውሳኔው መሰረት ከቅን ልቦና የመነጨ፣ ለባለጉዳዩ ግልፅ በሆነ አሰራርና መንገድ ያልተወሰደ ካልሆነ በስተቀር የመንግስት አስተዳደር ወደ መልካምነት ደረጃ ለመድረስ ገና ብዙ ይቀረዋል፡፡ የአስተዳደር ህግ እነዚህን መርሆዎች እንዲዳብሩ ከማድረግ አንፃር አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ስለሆነም የህጉ የእድገት ደረጃ የአንድ አገር የመልካም አስተዳደር ሁኔታ ጠቋሚ መለኪያ ነው ማለት እንችላለን፡፡

የተፈጻሚነቱ ወሰን የአስተዳደር ህግ የመንግስትንና የግለሰብ ግንኙት በሚገዛው የህዝብ አስተዳደር ህግ (Public law) ውስጥ ይመደባል፡፡ ይህም ማለት በሁለት ግለሰቦች ወይም በንግድ ድርጅቶች መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ በተጨማሪም ሁሉም በመንግስት እና ግለሰብ መካከል የሚፈጠር ግንኙነት በአስተዳደር ህግ ውስጥ አይወድቅም፡፡ ተፈጻሚነቱ የአስተዳደር አካላት በህግ የተሰጣቸውን ስልጣንና ግዴታ ተጠቅመው ህዝባዊ ተግባራት በሚያከናውኑበት ጊዜ ነው፡፡ ከህግ አውጭው የተሰጣቸውን ውክልና ተጠቅመው ደንብና መመሪያ ሲያወጡ እንዲሁም የግለሰቦችን መብትና ጥቅም የሚነካ አስተዳደራዊ ውሳኔ በሚሰጡበት ጊዜ ለአስተዳደር ህግ መርሆዎች ተገዢ ሊሆኑ ይገባል፡፡ አንድ መስሪያ ቤት ባወጣው መመሪያ ወይም በወሰደው የአስተዳደር ውሳኔ ምክንያት የሚነሳ ክርክር በአስተዳደር ህግ የሚመራ የአስተዳደር ክርክር ነው፡፡ከዚህ በተለየ መልኩ ከግለሰቦች ወይም ከድርጅቶች ጋር በሚመሰርቱት የውል ግንኙነት ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው መደበኛው የውል ህግ እንጂ የአስተዳደር ህግ አይደለም፡፡ ያም ሆኖ የውሉ አይነት በአስተዳደር ውል ውስጥ የሚመደብ ከሆነ የተለዩ የውል ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የኃላፊነታቸው ምንጭ በውል ላይ ካልተመሰረተ ተጠያቂነታቸው የሚወሰነው ከውል ውጭ የሚደርስ ኃላፊነትን በሚገዙት የፍትሐብሔር ድንጋጌዎች ነው፡፡ሌላው ከተፈፃሚነት ወሰን ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጥያቄ ህጉ የሚያካትታቸወ ውሳኔ ሰጪ አካላት የትኞቹ ናቸው? የሚለው ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ማለት አስተዳደር የሚመራበት ህግ እንደመሆኑ ፓርላማው በህግ አውጪነት ስልጣኑ በሚያወጣቸው ህጎች ወይም በሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች እንዲሁም ፍርድ ቤቶች በዳኝነት ስልጣናቸው በሚሰጧቸው ውሳኔዎች ላይ ተፈፃሚነት የለውም፡፡ መከላከያ ሰራዊትን የሚመለከቱ ጉዳዮችም ከዚህ ህግ ማእቀፍ ውጭ ናቸው፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአስተዳደር ህግ ከአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ባሻገር ብቸኛ አገልግሎት አቅራቢ የሆኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች (Public Corporations) ከደንበኞቻቸው ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይም ተፈፃሚነት እያገኘ ነው፡፡ አንድ የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ጋር ያለው ግንኙነት ምንም እንኳን በውል ላይ የተመሰረተ ቢሆንም አገልግሎቱን ከማግኘት መብት ጀምሮ እስከ አገልግሎቱ መቋረጥ ድረስ በድርጅቱ የሚወሰዱ እርምጃዎች ከምንም በላይ ፍትሐዊነታቸው መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ድርጅቱ በዋጋ አተማመን እና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚያደርጋቸው ማሻሻያዎችና ይህንን ተከትሎ የሚያወጣቸው የአሰራር ደንቦችና መመሪያዎች ለራሱ ለብቻው የሚተዉ ሳይሆን በህግ በተለይም በአስተዳደር ህግ ደንቦች መመራት ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህም ነው የመንግስት ልማት ድርጅቶች እንደ ነጋዴ ድርጅት መታየት የሌለባቸው፡፡በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት ቤቶችን የሚያስተዳድሩት የቀበሌ መስተዳድር እና የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሁለቱም ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት በተራ ውል ብቻ የተመሰረተ ቢመስልም ከዚህ ባለፈ በመንግስትና ግለሰብ ግንኙነት ማዕቀፍ ውስጥ መታየት አለበት፡፡ የመንግስት ቤቶችን የማስተዳደር ኃላፊነት የተሰጠው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንa ‘እንደማንኛውም ባለሃብት ቤቶቹን ለፈለገው ሰው የማከራየት ሕጋዊ መብት’b የለውም፡፡ ይልቅስ በህግ የተቋቋመበትን የቤት እጥረት የማቃለል ዓላማ፤..ለማሳካት የሚችሉ ግልፅ የአሠራር ሥርዓቶችን በመቀየስ የቤት ኪራይ ግልጋሎት የሚሰጥባቸውን መመዘኛዎች በማውጣት መመዘኛውን ለሚያሟሉ ሰዎች በቅደም ተከተል ክፍት ቤት ሲኖረው የማስተናገድ ግዴታና ኃላፊነት አለበት፡፡’cስለሆነም መንግስት ለዜጎቹ በሚያቀርባቸው አገልግሎቶች የሂደቱን ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ በእርግጥ የአስተዳደር ህግ ተፈፃሚነት ሊኖረው ይገባል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ሆነ የቀበሌ መስተዳድር አገልግሎታቸውን ለማቋረጥ በቂ የህግ ምክንያት ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ከመሆኑም በላይ ውሳኔያቸው ከህገ መንግስቱ የዜጐች መጠለያ የማግኘት መብት አንጻር መቃኘት ይኖርበታል፡፡በመጨረሻ የተፈጻሚነት ወሰኑ ከአስተዳደራዊ ውሳኔ ይዘትና ሂደት አንጻር የራሱ ገደብ እንዳለበት መገንዘብ ያሻል፡፡ አስተዳደር ህግ አካሄድን እንጂ ይዘትን የሚመለከት ህግ አይደለም፡፡ ትኩረቱ ደንብና መመሪያው እንዴት ወጣ? አስተዳደራዊ ውሳኔው እንዴት ተሰጠ? እንጂ የመመሪያው ወይም የውሳኔው ይዘት ትክክለኛ መሆን አለመሆን አይደለም፡፡ ድርጊቱ ትክክለኛ ነበረ ወይስ አልነበረም? የሚለው ጥያቄ ስለጉዳዩ በቂ እውቀት ላለው የአስተዳደር አካል የሚተው እንጂ በፍርድ ቤት ምላሽ የሚያገኝ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ያህል በግብር አወሳሰን ወቅት በህግ ተለይተው የተቀመጡ የተለያዩ ነገሮችን ታሳቢ በማድረግ የግብር ሰብሳቢው አካል የተወሰነ የገንዘብ መጠን ሊወስን ይችላል፡፡ የአስተዳደር ህግ የግብር አወሳሰኑን ህጋዊነት ወይም ፍትሐዊነት በተመለከተ ካልሆነ በስተቀር በእርግጥ የገንዘቡ መጠን ምን ያህል መሆን አለበት? የሚለውን ጥያቄ ለመዳሰስ ሆነ ለመመለስ ወሰኑ አይፈቅድለትም፡፡

 ንድፈ ሃሳባዊ አቅጣጫዎች።


ንድፈ ሃሳባዊ አቅጣጫዎች።

በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የህግ ሚና ውስብስብ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ በመንግስት አስተዳደር ስራ ወይም በአስተዳደራዊ ሂደት ውስጥ ሊኖረው የሚችለው አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖ እና ውጤት ተግባራዊ የሆነ ጥናትና ትንተና የሚያስፈልገው ጉዳይ ሆኗል፡፡ ከተግባራዊ መመዘኛው በተጨማሪ ዓይነተኛ ሚና እና ተግባሩን በተመለከተ የሚቀረጽበት ማዕዘን ወይም እይታ በተለያዩ ወገኖች የተለያየ አቋም ተይዞበት ይገኛል፡፡ ብዙዎቹ እንደሚስማሙበት ግን የአስተዳደር ህግ ለብቻው ተነጥሎ የሚጠና የህግ ክፍል ሳይሆን መሰረት ከሆኑት ተጨባጭ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታዎች ግንኙነት፤ ግጭትና ስምምነት እንዲሁም መስተጋብራዊ ውጤት አንጻር መታየት ይኖርበታል፡፡
ምንም እንኳን የአስተዳደር ህግን በተመለከተ ጐራ ለይቶ የተቀመጠ ፍንትው ያለ ንድፈ ሀሳብ ባይኖርም ጠቅለል ባለ መልኩሁለት አቅጣጫዎች እየተጓዘ ይገኛል፡፡ ሃርሎው እና ሮውሊንግ የተባሉ የአስተዳደር ህግ አጥኝዎች እነዚህን ሁለት ንድፈ ሀሳባዊ አቅጣጫዎች በመለየትየቀይ መብራት’ (የቁም!) ንድፈ ሀሳብ እናየአረንጓዴ መብራት’ (የእለፍ!) ንድፈ ሀሳብ የሚል ስያሜ በመስጠት የሚያንፀባርቁትንና የሚወክሉትን አቋም በተመለከተ ትንተና አቅርበዋል፡፡a
በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው የቁም ንድፈ ሀሳብ በአቀራረቡ ወግ አጥባቂ ሲሆን ቁጥጥርን ዓይነተኛ የአስተዳደር ህግ ሚና አድርጐ ይወስዳል፡፡ ንድፈ ሀሳቡ ከአስተዳደር ህግ መጸነስና መወለድ ጋር አብሮ የዳበረ የኋለኛው ዘመን (traditional) እይታን ያንጸባርቃል፡፡ ይህ ሲባል ግን ታሪካዊ ውልደቱንና አመጣጡን ለማሳየት እንጂ በአሁኑ ወቅት በተግባር የሚገለፅ አቀራረብ እንዳልሆነ ለመጠቆም አይደለም፡፡ የአስተዳደር ህግ የተነሳበት ዋነኛ አጀንዳ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የመንግስት ስልጣን በቅጡ መቆጣጠርና በዚህም የዜጐች መብትና ጥቅም እንዳይጣስ መከላከል ነው፡፡ የመንግስት ተቋማትና ባለስልጣናት ከስልጣናቸው ገደብ አልፈው በሚፈፅሙት ድርጊት የተነሳ በዜጐች ላይ በደል እንዳይደርስ ስልጣናቸው እንደፈረስ ልጓም መቆጣጠሪያ መሳሪያ ያስፈልገዋል፡፡
በቁም ንድፈ ሀሳብ መሰረት ይህ መሳሪያ የአስተዳደር ህግ ነው፡፡ የቁጥጥር መሳሪያ ከሆኑት መንገዶች አንዱ የአስተዳደራዊ ውሳኔ ህጋዊት በፍ/ቤቶች የሚታረምበት የአጣሪ ዳኝነት ስርዓት አንዱና ዋነኛው ሲሆን የቁም ንድፈ ሀሳብ /ቤቶች አስተዳደራዊ ተቋማትን የመቆጣጠር ጠንካራ ሚና እንዲኖራቸው በአጽንኦት ይከራከራል፡፡b
የንድፈ ሀሳቡን ዳራ በቅጡ ለመረዳት ምንጩ ከሆነው የነፃ ገበያ የፖለቲካ ፍልስፍና አንፃር መመርመሩ ጠቃሚ ነው፡፡ በዚህ ርዕዮተ ዓለማዊ እይታ ምርጥ መንግስት ማለት የታቀበ መንግስት ነው፡፡ ፒተር ለይላንድ እና ቴሪ ውድስ ይህንኑ በማጉላት እንዲህ ይላሉ፤
‘የቁም ንድፈ ሀሳብ’ አመጣጡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሰፍኖ ከነበረው የነፃ ገበያ ንድፈ ሀሳብ ነው፡፡ ነፃ ገበያ ለግለሰለቦች ነፃነት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአንፃሩ ግን የመንግስትን ስልጣን በጥርጣሬ በማየት ውስን አገዛዝን በዋነኛነት ይደግፋል፡፡c
የነፃ ገበያ ስርዓት ነፀብራቅ የሆነው የቁም ንድፈ ሀሳብ የመንግስትን ረጃጅም እጆች ለማሳጠር የአስተዳደር ህግን እንደ መቆጣጠሪያ መሳሪያ ይጠቀምበታል፡፡ ጠንካራ መንግስት በግለሰቦች እንቅስቃሴ ውስጥ በየጊዜው ጣልቃ እየገባ ስለሚያስቸግር የግለሰቦች ነፃነት ጠር ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በተግባር እንደታየው ግን 19ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ የመንግስት ስልጣንና ሚና ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እያደገ መጥቷል፡፡ የተለያየ ተግባራትን የሚያከናውኑ የአስተዳደር ተቋማት ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ይገኛል፡፡ እነዚህ ተቋማት በህግ አውጭው በሚሰጣቸው ስልጣን መሰረት መጠነ ሰፊ ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ በቁም ንድፈ ሀሳብ መሰረት በታሪክ ሂደት እያደገ የመጣውን የመንግስት ስልጣንና በየጊዜው የሚፈጠሩትን የአስተዳደር ተቋማት ከግለሰቦች ነፃነት ጐን ለጐን አጣጥሞ

መሄድ የሚቻለው በህግ ማዕቀፍ ጠንካራ ቁጥጥር ሲደረግባቸው ነው፡፡

ሁለተኛውን የእለፍ ንድፈ ሀሳብ ያየን እንደሆነ ከስሙ ለመረዳት እንደሚቻለው ለመንግስት ስልጣንና ለአስተዳደር ተቋማት የአረንጓዴ መብራት ማለትም የእለፍ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ በዚህ ንድፈ ሀሳብ መሰረት የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ሚና የመንግስትን ስራ ማቀላጠፍ ነው፡፡ ጣልቃ ገብነት ሳይኖር ሲቀር የመንግስት ቢሮክራሲ ውጤታማ በሆነ መንገድ ይሰራል፡፡ ስለሆነም የአስተዳደር ህግ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓትን ቀልጣፋ እንዲሆን በማድረግ ውጤታማነትን ማበረታታት ይኖርበታል፡፡ አስተዳደር በቁጥጥር ሰበብ እጆቹ የሚታሰሩ ከሆነ ተጨማሪ አስተዳደራዊ በደልን ከማስከተል በቀር ፋይዳ የለውም፡፡
ፖለቲካዊ ዳራውን ያየን እንደሆነ የማህበራዊ ዲሞክራሲ (social democracy) ንድፈ ሀሳብ ነፀብራቅ ነው፡፡d በዚህ ፖለቲካዊ ንድፈ ሀሳብ መሰረት መንግስት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አዎንታዊ በሆነ መንገድ በመሳተፍ አቅም ለሌለው ህብረተሰብ ማህበራዊ አገልግሎት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በዚህ ሂደት የአስተዳደር ህግ መንገድ ጠራጊነትሚና ሊኖረው ይገባል፡፡
የእለፍ እና የቁም ንድፈ ሀሳባዊ አቅጣጫዎች በየፊናቸው የአስተዳደር ህግን ዓይነተኛ ሚና ያንፀባርቃሉ፡፡ ስለሆነም የመጀመሪያው የማቀብ፤ ሁለተኛው ደግሞ የማሳለጥ ሚናዎችን ይወክላሉ፡፡ ፒተር ኬን ይህንን ሀሳብ እንደሚከተለው በተብራራ መልኩ ይገልጸዋል፡፡
We can think about government as having a complex set of (‘policy’) objectives and about administrative law as both facilitating and constraining the realization of those objectives. Law can facilitate by defining objectives and by creating institutions, conferring powers, and establishing processes for realizing those objectives. Law can constrain by specifying how such institutions must behave in operating such processes and exercising such powers lawfully, fairly, reasonably, and so on. Law as facilitator is concerned primarily with ends; law as constraint is concerned primarily with means to ends.
ከላይ የቀረበው ሀሳብ እንደሚያስረዳንእለፍእናቁምተብለው የተፈረጁት አመለካከቶች ተነጣጥለው የቆሙ አይደሉም፡፡ ዲሞክራሲያዊ ገፅታው ግምት ውስጥ ሳይገባ ማንኛውም የመንግስት አስተዳደር ስራ የሚሰራው የስልጣን አሰጣጥንና እና መገልገልን በሚመሩ ህጎች እየታገዘ ነው፡፡
የህጉ ምንጮች
የአስተዳደር ህግ የሚመራባቸው መርሆዎች እና ደንቦች ከተለያዩ ምንጮች ይገኛሉ፡፡ የአንዲት አገር የአስተዳደር ህግ የዛችን አገር ፖለቲካዊና ህገመንግስታዊ ስርዓትና አወቃቀር የሚያንጸባርቅና ከዚሁ አንጻር የተቀረጸ እንደመሆኑ እነዚህን ምንጮች ወጥ በሆነ መልኩ ማስቀመጥ ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂ አጠቀላይ ምልከታ በመነሳት ምንጮቹን እንደሚከተለው መዘርዘር ይቻላል፡፡
ህገ መንግሰት
የአንዲት አገር የአስተዳደር ህግ መልክና ቅርጽ ምን እንደሚመስል ለመረዳት መነሻችን የዛች አገር ህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊ ስርዓት ነው፡፡ ብዙዎቹ የአስተዳደር ህግ መርሆዎች መሰረታቸው የተተከለው በህገ መንግስት ላይ ከመሆኑም በላይ ወሰንና አፈጻጸማቸው እንዲሁ ለብቻው ተነጥሎ የቆመ አይደለም፡፡ የአስተዳደር ህግ ተፈጻሚነት የሚያገኘው በህገ መንግስት ማዕቀፍ ውስጥ ነው፡፡a
ህግ የመንግስት ስልጣን ዋነኛ ምንጩ በህግ አውጭው የሚወጣው ህግ ሲሆን በአስተዳደር ህግ ውስጥ በተለምዶ ማቋቋሚያ አዋጅ ወይም እናት ህግ እየተባለ ይጠራል፡፡ በአገራችን በፌደራልም ሆነ በክልል ደረጃ በተዋቀረው ህግ አውጪ አካል የሚወጣው አዋጅb የአስተዳደር መስሪያ ቤቶችን ስልጣን በግልጽ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ለይቶ ያስቀምጣል፡፡ ስለሆነም ይህ አዋጅ በአስተዳደር ህግ ጥናት ውስጥ በጥልቀት ሊመረምርና ሊተነተን ይገባዋል፡፡
ህግ አውጪው ስልጣን ከመስጠት በተጨማሪ ስልጣኑ ተግባር ላይ የሚውልበትን መንገድና ስርዓት ይደነግጋል፡፡ በስልጣን መገልገል ሂደት ተፈጻሚ የሚሆነው ስነስርዓት አብዛኛውን ጊዜ ስልጣን በሚሰጠው አዋጅ ላይ ይካተታል፡፡ በሌላ መልኩ ህግ አውጪው በሁሉም ስልጣን በተሰጣቸው አካላት ላይ በጠቅላላው ተፈጻሚ የሚሆን ወጥ ደንብ በማስቀመጥ ሁሉን አቀፍ ስርዓት ሊዘረጋ ይችላል፡፡
በዚህ ረገድ በአሜሪካ ... 1946 . የወጣው የአስተዳደር ስነስርዓት ደንብ (Administrative Procedure Act) ተጠቃሽ ነው፡፡ በውሳኔ አሰጣጥ ረገድ ተፈጻሚ የሚሆኑ ደንቦችና ስርዓቶች አስገዳጅነት ያላቸው እንደመሆኑ መጠን ስነስርዓቱን የሚጥስ ውሳኔ ጸንቶ የሚቆምበት የህግ መሰረት አይኖርም፡፡ በአጠቃላይ የስልጣን ምንጭ የሚወሰንበት መንገድ በአስተዳደር ህግ ጥናት ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡
ደንብና መመሪያ
በአገራችን በተለይም በፌደራል መንግስቱ ደረጃ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እና የተለያዩ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች በውክልና በሚተላለፍላቸው ስልጣን መሰረት ደንብና መመሪያ ያወጣሉ፡፡ የእነዚህ አስተዳደራዊ ድንጋጌዎች አወጣጥ ስርዓት እንዲሁም ህጋዊነታቸውና ህገ መንግስታዊነታቸው የሚረጋገጥበት መንገድ በህጉ አብይ ትኩረት ያገኘ ጉዳይ ሆኗል፡፡
በእርግጥ የእያንዳንዱ ደንብና መመሪያ ይዘት ከአስተዳደር ህግ ጥናት ወሰን ውጭ ነው፡፡ ህጉ እንደ ስልጣን መቆጣጠሪያ መሳሪያነቱ ደንብና መመሪያ በህግ በተቀመጠው የስልጣን ገደብ ውስጥ ህጋዊ ስርዓቱን ተከትሎ መውጣቱን ማረጋገጥ አይነተኛ ዓላማው ነው፡፡ በውክልና ህግ የማውጣት ስልጣን በአስተዳደር ህግ ውስጥ ያለው ቦታ መቃኘት ያለበትም ከዚሁ ነጥብ አንፃር ነው፡፡ ለህጋዊነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ደንብና መመሪያው ላይ አስገዳጅ ውጤት ኖሯቸው የተደነገጉት ጉዳዮች ስልጣን በሰጠው አዋጅ ስር የተሸፈኑ መሆናቸውን መመርመርን ይጠይቃል፡፡
የፍርድ ቤት ውሳኔዎች
መደበኛ /ቤቶች የስልጣን መገልገልን ህጋዊነትና ፍትሐዊነት በመቆጣጠር ለግለሰቦች መብትና ነፃነት መጠበቅ የሚያበረክቱ አስተዋጽኦ በአስተዳደር ህግ ጥናት ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ /ቤቶች አስተዳደሩ በህግ እንዲመራ እና ለህጋዊነት መርህ ተገዢ እንዲሆን በተጨማሪም በህግ የተሰጠውን ስልጣን በፍትሀዊ መንገድ እንዲገለገል የተለያዩ መለኪያዎችንና መስፈርቶችን በማስቀመጥ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በዚህ ህገመንግስታዊ ሚናቸው የመልካም አስተዳደር እሴቶች ገንቢ ተቋማት ናቸው፡፡ ከዚህ አንጻር የፌደራል እና የክልል መደበኛ ፍርድ ቤቶች በአስተዳደራዊ ክርክር የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች ለአስተዳደር ህግ ጥናት ግብዓት ናቸው፡፡ በተለይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም በመላ አገሪቱ በሚገኙ ፍርድ ቤቶች ላይ አስገዳጅነት ያለው እንደመሆኑ የአስተዳደር ህግን ተግባራዊ አፈጻጸም ለመመዘን ፋይዳው የጎላ ነው፡፡
ከመደበኛ /ቤቶች በተጨማሪ በአስተዳደር ተቋማት ውስጥ ወይም ለብቻቸው ገለልተኛ ሆነው የሚቋቋሙት በተለምዶ የአስተዳደር /ቤት በሚል የሚታወቁት የአስተዳደር ጉባዔዎች (Administrative Tribunals) የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች የአንዲት አገር የአስተዳደር ህግ እና የአስተዳደር ፍትህ ምን እንደሚመስልና ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለመረዳት አጋዥ ምንጮች ናቸው፡፡
ያም ሆኖ የመደበኛ /ቤት ሆነ የአስተዳደር ጉባዔዎች ውሳኔዎች በአስተዳደር ህግ ውስጥ ያላቸው ቦታ ውስን ነው፡፡ በየአስተዳደር መስሪያ ቤቱ በየጊዜው በሚሰጡት ውሳኔዎችና በሚወጡት ደንብና መመሪያዎች አማካይነት በዜጋው ላይ የሚፈጸሙት በደሎች ስፍር ቁጥር የሌላቸው ቢሆንም የፍ/ቤትን ደጃፍ የሚረግጡት ግን በጣት የሚቆጠሩት ናቸው፡፡ ከሚቀርቡት አቤቱታዎች መካከልም በተለያዩ የስነስርዓት ቅድመ ሁኔታዎች የተነሳ ዳኝነት ሳይታይ አብዛኛዎቹ ወዲያውኑ ውድቅ ይደረጋሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ውሳኔዎቹ አጠቃላዩን የአስተዳደር ሂደት ባህርይ እና አካሄድ ገላጭ ወይም ወካይ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

መሰረታዊ የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች


መሰረታዊ የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች

መልካም አስተዳደር ምንም እንኳን በጥቅሉ ሲታይ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ተቋማዊ እንዲሁም የአመራር እና የአሰራር ሂደቶችን የሚመለከቱ ዘርፈ ብዙ እንደምታዎች ያሉት ቢሆንም በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ሲታይ ግን ከአስተዳደር ፍትህ ጋር አቻ ሆኖ ሊገለጽ ይችላል፡፡ መልካም አስተዳደር ዋና ግቡ ዜጐች ብቁና ውጤታማ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል እንዲሁም የሚደርስባቸውን አስተዳደራዊ በደል መቅረፍ እና አስተዳደራዊ ፍትህን እውን ማድረግ እንደመሆኑ ሁለቱን ነጣጥሎ ማየት ያስቸግራል፡፡ መልካም አስተዳደር ሆነ የአስተዳደር ህግ በራሳቸው አቅጣጫና ሂደት ተጉዘው የግባቸው መድረሻ አስተዳደራዊ ፍትህን ማስፈን ነው፡፡ ስለሆነም በይዘቱ ሰፊ በሆነ የመልካም አስተዳደር እሳቤ ውስጥ የአስተዳደር ህግ አንድ ቁስ ሆኖ በማገልገል የተቆራኘና የተዛመደ ተግባራዊ እገዛ ያደርጋል፡፡በመልካም አስተዳደርና በአስተዳደር ህግ መካከል ያለውን ተዛምዶ በቅጡ ለመቃኘት ህግ በአስተዳደሩ አካሄድ (Administrative behavior) ወይም በስራ አስፈፃሚው እንቅስቃሴ ላይ ምን አይነት አዎንታዊ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል? ለሚለው ጥያቄ በተግባር የታገዘ ጥልቅ ጥናት ምላሽ መስጠት ይጠይቃል፡፡ ይሁን እንጂ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያሉትን ሚናዎችና ተግባራት ቢያንስ እንደጠቅላላ ሀሳብ በመውሰድ የአስተዳደር ህግ እንደ አንድ የህግ ዘርፍ የራሱ አዎንታዊ ፋይዳ እንዳለው መደምደም እንችላለን፡፡ ያም ሆኖ ግን አስተዳደሩ መልካም እንዲሆን የአስተዳደር ህግ ስልጣን ከመቆጣጠር ባሻገር እንዴት ተቃኝቶ መቀረጽ አለበት? የሚለው ጥያቄ ለአስተዳደር ህግ አጥኚዎች ሆነ ምሁራን የውይይት ምንጭ ብቻ ሳይሆን የጥናት መሰረት መሆን ያለበት ጉዳይ ነው፡፡የመልካም አስተዳደር እና የአስተዳደር ህግን ተዛምዶ ለማየት የሁለቱም መድረሻ ከሆነው የአስተዳደር ፍትህ ትርጓሜ እንነሳለን፡፡ የአስተዳደር ፍትህ በህግ ስልጣን የተሰጣቸው የመንግስት አካላት ስልጣናቸውን በሚገለገሉበት ወቅት ከዜጐች መብትና ነፃነት አንጻር ፍትሃዊ መሆን እንዳለባቸው የሚደነግግ መርህ ነው፡፡ የመንግስት አስተዳደር ፍትሃዊ ሲሆን መልካም ይሆናል፡፡የአስተዳደር ፍትህን በማሳካት ረገድ ሁለት ዓበይት ነጥቦች ቁልፍ ቦታ ይኖራቸዋል፡፡ ይኸውም፡-አንደኛ፦ የመንግስት ባለ ስልጣናት ወይም የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ስልጣናቸውን በሚገለገሉበት ወቅት አነስተኛ ለሆኑ የስነ-ስርዓት ደንቦች እና ተቀባይነት ላላቸው መርሆዎች መገዛት አለባቸው፡፡ ከአነስተኛ የስነ-ስርዓት ደንቦች በተጨማሪ የመንግስት አስተዳደር ተቀባይነት ባላቸው የህግ፣ የአስተዳደርና የፍትህ መርሆዎች መመራት አለበት፡፡ከእነዚህ መካከል በዋናነት የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡የህጋዊነት መርህ (ህጋዊ ስልጣን ሳይኖር አንዳችም እርምጃ አለመውሰድ፤ በህጉ መሰረት መወሰን)የሚዛናዊት መርህ (የአስተዳደር አካላት ውሳኔ ወይም እርምጃ እንደየሁኔታው ብዙ ነገሮች ግምት ያስገባ እንጂ ፍርደገምድል መሆን የለበትም፡፡)የተመጣጣኝነት መርህ (የሚወሰደው እርምጃ ተፈጸመ ከተባለው ጥፋት አንፃር ተመጣጣኝ መሆን አለበት፡፡)የእኩልነት መርህ (ተመሳሳይ በሆኑ ሁኔታዎች ወይም ጉዳዮች አስተዳደሩ የተለያየ ውሳኔ ላይ መድረስ የለበትም፡፡ ተመሳሳይ ሁኔታዎች በተመሳሳይ መንገድ መወሰን አለባቸው፡፡)ለውሳኔ በቂ ምክንያት መስጠት (አስተዳደራዊ ውሳኔ የተወሰደበት ምክንያት በግልጽ መጠቀስ አለበት፡፡ ውሳኔውም ፈጽሞ የማያሳምንና ኢ- ምክንያታዊ መሆን የለበትም፡፡)ሁለተኛ፦ ከላይ የተመለከቱትን ደንቦችና መርሆዎች በመጻረር በህግ ከተወሰነው ስልጣን በላይ እርምጃ ከተወሰደ መብታቸው የተጐዳ ዜጐች አቤቱታ አቅርበው ፍትህ (መፍትሄ) የሚያገኙበት መንገድ መኖር አለበት፡፡ በአስተዳደር አካላት መብታቸው የተጣሰ ሰዎች ቀላል በሆነ ስነ-ስርዓት አቤቱታ አቅርበው ቀልጣፋ መፍትሔ የሚያገኙበት አሰራር ወይም መንገድ ከሌለ የአስተዳደር ፍትህ አለ ለማለት አይቻልም፡፡ ለምሳሌ አካልን ነፃ የማውጣት መብት በህገ-ወጥ መንገድ ከ48 ሰዓት በላይ የታሰረ ሰው ራሱ በቀጥታ ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን በቀላሉ አቤቱታ አቅርቦ ነፃ የሚለቀቅበት ፈጣን ስነ-ስርዓት ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በህገ ወጥ መንገድ ንብረቱን በአስተዳደደሩ የተቀማ ወይም ፈቃዱ አለአግባብ የተሰረዘበት ሰው ቀላል በሆነ ስነ-ስርዓት መፍትሔ የሚያገኝበት የህግ ድንጋጌ ሊኖር ይገባል፡፡ ለዚህም ነው የአስተዳደር ህግ መኖር ለአስተዳደራዊ ፍትህ ሆነ ለመልካም አስተዳደር ወሳኝ መሳሪያ ነው የሚባለው፡፡ የአቤቱታው ስርዓት እንዳለ ሆኖ የአስተዳደራዊ ፍትህ የሚገኝበት ተቋም ገለልተኛ፣ ተደራሽ እና ነፃ ሆኖ ቀልጣፋና ውጤታማ ግልጋሎት መስጠት መቻሉ የአስተዳደር ፍትህን በማሳካት ረገድ ዋናውና መሰረታዊው ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

ሕገወጥ ውል።


ሕገ ወጥ ውል።

በሕግ እንዲደረግ ያልተፈቀደ፤ የሕግ ክልከላ ያለበት ውል።

አንድ ውል ሕገወጥ ውል ነው የሚባለው ተዋዋዮቹ የተዋዋሉበት መሠረታዊ ጉዳይ ዓላማ በመሠረታዊና ሞራላዊ ይዘቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት በማድረግ መብትና ግዴታ እንዲፈጥሩበት በሕግ ያልተፈቀደ ወይም በሕግ ክልከላ የተደረገበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ለምሳሌ በሕገ መንግሥቱም ሆነ በአገሪቱ የወንጀል ሕግ እንደዚሁም በዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግ ማንኛውንም ሰብዓዊ ፍጡር በግዴታ አገልጋይነት መያዝ ወይም በሰው መነገድ የተከለከለ በመሆኑ ሰውን በግዴታ አገልጋይነት ለመያዝ ወይም በሰው ለመነገድ የተደረገ ውል በመሠረታዊ ባህሪውና ሞራላዊ ይዘቱ ሕገወጥ ውል /unlawfull contract/ ነው፡፡ አንድ ውል የተመሠረተበት መሠረታዊ ጉዳይ “object of contract” በሕግ ክልከላ የተደረገበት በሆነ ጊዜ ውሉ በሕግ ፊት የሌለና ምንም አይነት ሕጋዊ ውጤት የማያስከትል /void contract/ ነው፡፡ አንድ ውል በማናቸውም ሰው ወይም አካል ፈቃድና ስምምነት ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ የማይቻልና በማናቸውም መንገድ ለማስተካከልና ሕጋዊ ውጤት እንዲያገኝ ለማድረግ የማይቻል በሆነ ጊዜ ውሉ ከጅምሩ በሕግ ፊት እንዳልተደረገና እንደሌለ “Null or void contract” እንደሚሆን በዘርፉ ከተደረጉ ጥናቶች ለመገንዘብ ይቻላል፡፡

ውል በጠቅላላ የውል ሕግና በልዩ ።

የውል ሕግ ድንጋጌዎች ወይም በሌሎች ህጎች የተደነገገውን መስፈርት የማያሟላና ጉድለት ያለበት ውል
ከባለሀብቱ በቂ የሆነ የውክልና ሥልጣን ሣይኖረው ወይም ንብረቱን ለመሸጥ የሚያስችል መብት በሌለው ሰው የተደረገ የሽያጭ ውል፣ ውሉ በሕግ የተደነገጉ አስገዳጅ መስፈርቶችን የማያሟላ ነው፡፡ የዚህ ጉድለት መኖሩ ቢረጋገጥ ውሉ ባለሀብትነትን በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደነገጉትን አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች የማያሟላ “Illegal or invalid contract” የሚያደርገው ጉድለት ነው፡፡ የውሉን ጉድለት በማቃናት ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ለማድረግ የሚቻልበት መንገድና ሁኔታ ሲኖር ውሉ ከጅምሩ እንዳልተደረገ የሚቆጠር (null or void contract) ሣይሆን ጉድለት ያለበትና ፈራሽ “voidable or invalid contract” ሊሆን የሚችል ውል ነው፡፡

ESSENTIAL CONDITIONS OF MARRIAGE


Essential Conditions of Marriage

Article 6. – Consent.
A valid marriage shall take place only when the spouses have given their free and full consent.
Article 7. – Age
1) Neither a man nor a woman who has not attained the full age of eighteen years shall conclude marriage.
2) Notwithstanding the provisions of Sub-Article (1) of this Article, the Minister of Justice may, on the application of the future spouses, or the parents or guardian of one of them, for serious cause, grant dispensation of not more than two years.
Article 8. – Consanguinity.
1) Marriage between persons related by consanguinity in the direct line, between ascendants and descendants, is prohibited.
2) In the collateral line, a man cannot conclude marriage with his sister or aunt; similarly, a woman cannot conclude marriage with her brother or uncle.
Article 9. – Affinity
1) Marriage between persons related by affinity in the direct line is prohibited.
2) In the collateral line, marriage between a man and the sister of his wife, and a woman and the brother of her husband is prohibited.
Article 10. – Filiations not Established Legally.
The existence of a bond of natural filiation which is commonly known to the community is sufficient to render applicable the impediments to marriage referred to in Articles
8 and 9, notwithstanding that the filiation is not legally established.
Article 11. – Bigamy.
A person shall not conclude marriage as long as he is bound by bonds of a preceding marriage.
Article 12. – Representation not Allowed.
1) Each of the future spouses shall personally be present and consent to the marriage at the time and place of its celebration.
2) Notwithstanding the provisions of Sub-Art. (1) of this Article, marriage by representation may be allowed by the Ministry of Justice where it has ascertained that there is a serious cause and the person who intended to do so has fully consented thereto.
Article 13. – Fundamental Error.
1) Marriage concluded as a result of error in consent shall not be valid.
2) Consent is deemed to be vitiated as a result of error where such error is a fundamental error.
3) Without prejudice to the provisions of Sub-Article (2) of this Article, the following shall be considered to be fundamental errors:
(a) Error on the identity of the spouse, where it is not the person with whom a person intended to conclude marriage;
(b) Error on the state of health of the spouse who is affected by a disease that does not heal or that can be genetically transmitted to descendants;
(c) Error on the bodily conformation of the spouse who does not have the requisite sexual organs for the consummation of the marriage;
(d) Error on the behavior of the spouse who has the habit of performing sexual acts with person of the same sex.
Article 14. – Consent Extorted by Violence.
1) Marriage concluded as a result of consent which is extorted by violence shall be valid.
2) Consent is deemed to be extorted by violence where it is given by a spouse to protect himself or one of his ascendants or descendants, or any other close relative from a serious and imminent danger or threat of danger.
Article 15. – Judicially Interdicted Persons.
1) Any person who is judicially interdicted shall not be conclude marriage unless authorized, for that purpose, by the court.
2) An application to this effect may be made by the interdicted person himself or by his guardian.
Article 16. – Period of widowhood.
1) A woman may not remarry unless one hundred and eight days have elapsed since the dissolution of the previous marriage.
2) The provision of Sub-Article (1) of this Article shall not apply where:
(a) The woman gives birth to a child after the dissolution of her marriage;
(b) The woman remarries her former husband;
(c) It is proved by medical evidence that the woman is not pregnant;
(d) The court dispenses the woman from observing the period of widowhood.

CONCLUSION OF MARRIAGE


CONCLUSION OF MARRIAGE

– Various Forms of Marriage.

1) Marriage may be concluded before an officer of civil status.
2) Notwithstanding the provision of Sub-Article (1) of this Article, marriage may be concluded in accordance with the religion or custom of the future spouses.
Article 2. – Marriage Concluded before an Officer of Civil Status.
Marriage shall be deemed to be concluded before an officer of civil status when a man and a woman have appeared before an officer of civil status for the purpose of concluding marriage and the officer of civil status has accepted their respective consent.
Article 3. – Religious Marriage.
Religious marriage shall take place when a man and a woman have performed such acts or rites as deemed to constitute a valid marriage by their religion or the religion of one of them.
Article 4. – Marriage According to Custom.
Marriage according to custom shall take place when a man and a woman have performed such rites as deemed to constitute a valid marriage by the custom of the community in which they live or by the custom of the community to which they belong or to which one of them belongs.

Article 5. – Marriage Celebrated Abroad.

Marriage celebrated abroad in accordance with the law of the place of celebration shall be valid in Ethiopia so long as does not contravene public moral.

CRIMINAL LAW


Magistrate’s or Judge’s Warrant of Commitment of Witness Refusing to Answer or to Produce Document

(See section 349 Criminal Procedure Act)

To (name and designation of officer of Court)WHEREAS (name and description), being summoned (or brought before this Court) as a witness and this day required to give evidence on an inquiry into an alleged offence, refused to answer a certain question (or certain questions) put to him touching the said alleged offence, and duly recorded, or having been called upon to produce any document has refused to produce such document, without alleging any just excuse for such refusal, and for his refusal has been ordered to be detained in custody for (term of detention adjudged);This is to authorise and require you to take the said (name) into custody, and him safely to keep in your custody for the period of days, unless in the meantime he shall consent to the examined and to answer the questions asked of him, or to produce the document called for from him, and on the last of the said days, or forthwith on such consent being known, to bring him before this Court to be dealt with according to law, returning this warrant with an endorsement certifying the manner of its execution.Dated, this ………..day of……….19.(Seal of the Court) (Signature)

Set Aside Judgment given in Default  Art.197-Court having jurisdiction.


Set Aside Judgment given in Default
Art.197-Court having jurisdiction.
An application to set aside a judgment given in default may be made by the person sentenced in his absence to the court which passed the judgment.

Art.198- Time and form of application.

An application under this Title shall be made within thirty days from the date on which the applicant became aware of the judgment given in his absence and shall contain the reasons on which he bases his application.

Art.199- Grounds for granting application.

No application under this Title shall be granted unless the applicant can show:
(a) That he has no received a summons to appear: or
(b) That he was prevented by force majeure from appearing in person or by advocate.

Art.200- Action upon filing of application.

(1) on the filing of the application, a copy thereof shall be sent to the public prosecutor and the applicant and the public prosecutor shall be informed of the hearing date.
(2) Where the applicant, having been duly summoned, fails to appear on the hearing date, the application shall be dismissed.

Art-201-Hearing

(1) The applicant or his advocate shall speak in support of the application and the public prosecutor shall reply. The applicant shall have the right to reply.
(2) The court shall then give its decision on the application.

ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር


ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር

  1. ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር በተለይም የሴቶችና ሕጻናት ዝውውር እና ስደቶኞችን በሕገ- ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥር እየሰደደ እና እየተባባሰ ዜጎችን ለአስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና እንግልት እየዳረገ በመሆኑ፣ ችግሩን ለመፍታት በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ የሕግ ማዕቀፉ በመከላከል ላይ የተመሠረተ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

የወንጀሉ ተጎጂ ለሆኑ ሰዎች ጥበቃ፣ እንክብካቤ እና መልሶ ማቋቋም ሊደረግላቸው እንደሚገባ በመገንዘብ እና ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ዕድሜያቸውን፣ ጾታቸውንና ልዩ ፍላጎታቸውን ያገናዘበ የተለየ ጥበቃ፣ እንክብካቤ እና ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ በማመን፤

በወንጀል ሕጉም ሆነ በሌሎች ሕጎች የተቀመጡ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ከችግሩ ስፋት አንፃር በቂ ምላሽ የማይሰጡ በመሆናቸው እና በወንጀለኞች ላይ ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት ለመጣል የሚያስችል ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 18 (2) በተደነገገው መሠረት በሰዎች መነገድ የተከለከለ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ የተደራጁ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን ለመከላከል የተደረሰውን ዓለም አቀፍ ስምምነት ፈራሚ አገር በመሆኗ፣ ስምምነቱን ተከትለው በወጡት ሕገ-ወጥ የሰዎች በተለይም የሴቶችና ሕጻናት ዝውውር ለመከላከል ለመቆጣጠርና ወንጀል ፈጻሚዎችን ለመቅጣት በወጣው ፕሮቶኮል እና ስደተኞችን በሕገ-ወጥ መንገድ በየብስ፣ በባህርና በአየር ማስወጣትና ማስገባት ለመከላከል የወጣ ፕሮቶኮልን ያጸደቀች በመሆኗ፣ እንዲሁም ከሕገ መንግስቱ እና ከእነዚህ ዓለም አቀፍ ሰነዶች ጋር የተጣጣመና የተሟላ ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

ክፍል አንድ

ይህ አዋጅ “ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ስደተኞችን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 909/2007” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡-

“ሕገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪ” ወይም “ስደተኞችን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር አሻጋሪ” ማለት፦

በማንኛውም መንገድ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፣ ሕግን በመጣስ ወይም በራሱ ፈቃድ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወይም ስደተኞችን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል የፈፀመ ወይም ለመፈፀም የሞከረ፤

በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወይም ስደተኞችን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር የወንጀል ድርጊት ላይ በአባሪነት የተሳተፈ፤

ሌሎች ሰዎች በወንጀል ድርጊቱ እንዲሳተፉ ያደራጀ ወይም በተደራጀ የወንጀል ቡድን ውስጥ አመራር የሰጠ፤

ሰዎችን ከመኖሪያ አካባቢያቸው ጀምሮ የተስፋ ቃል በመስጠት ለወንጀል ድርጊቱ ወይም ለስደተኝነት የዳረገ፤

በማንኛውም መልኩ የወንጀል ድርጊቱን ያበረታታ፣ የወንጀል ድርጊቱ እንዲስፋፋ ያደረገ ወይም የተደራጀው የወንጀል ቡድን በዚህ አዋጅ የተደነገጉ ወንጀሎችን ለመፈፀም ማሰቡን እያወቀ ለጋራ ዓላማ በቡድን ለተሰባሰቡ ሰዎች አስተዋፅዖ ያደረገ፤

በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በሌላ አገር የሚገኝ ማንኛውም ሰው ነው።

“የተደራጀ የወንጀል ቡድን” ማለት በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በሌላ አገር የሚገኝወይም የሚንቀሳቀስ ሆኖ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የገንዘብ ወይም ሌላ ቁሳዊ ጥቅም ለማግኘት ዓላማ አንድ ወይም ከዚያ በላይ በዚህ አዋጅ የተደነገጉ ወንጀሎችን ለመፈፀም የተሰባሰቡና የሚንቀሳቀሱ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎችን የያዘና ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የተደራጀ ቡድን ሲሆን በማናቸውም መልኩ በሰዎች ለመነገድ የተቋቋመ ቡድንን ወይም ማህበርን ይጨምራል፤

“ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ድርጊት” ማለት በዚህ አዋጅ የተደነገገው ወንጀል፦

ከአንድ በላይ በሆኑ አገራት የተፈጸመ፤

በኢትዮጵያ የግዛት ክልል ውስጥ የተፈጸመ ሆኖ የድርጊቱ ዝግጅት፣ እቅድ፣ አመራር ወይም የገንዘብ ምንጭ በሌላ አገር የሆነ፤

የተፈጸመው በሌላ አገር ሆኖ የድርጊቱ ዝግጅት፣ እቅድ፣ አመራር ወይም የገንዘብ ምንጭ በኢትዮጵያ ከሆነ ወይም በሌላኛው አገር የግዛት ክልል አማካይነት የሆነ፤

የተፈፀመው ከአንድ በላይ በሆኑ አገራት በሚንቀሳቀስ የተደራጀ የወንጀል ቡድን የሆነ፤ ወይም

በኢትዮጵያ የግዛት ክልል ውስጥ ወይም በሌላ አገር የተፈፀመ ቢሆንም የወንጀሉ ውጤት በሌላ አገር ወይም በኢትዮጵያ ላይ የሆነ፤

ድርጊት ነው።

“ብዝበዛ” ማለት የሚከተሉትን ያካትታል፦

በሌሎች ሰዎች ዝሙት አዳሪነት መጠቀም ወይም ሌላ ማንኛውም አይነት ወሲባዊ ብዝበዛን፤

የጉልበት ብዝበዛ፣ የግዳጅ ሥራ ወይም አገልጋይነት፤

ባርነት ወይም ባርነት መሰል ተግባር፤

የወሲብ አገልጋይነትን ጨምሮ ሰውን የማይገባ አገልጋይ ማድረግ፤

በመያዣነት መያዝ ወይም አሳልፎ ለሌላ መስጠት፤

የሰው ልጅን አካል ማውጣት ወይም መውሰድ፤

አስገድዶ በልመና ተግባር ማሰማራት፤ ወይም

ህፃናትን ለወታደራዊ አገልግሎት ማሰማራት።

“ባርነት” ማለት የሌላ ሰው የባለቤትነት መብት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል እየተፈጸመበት ያለ ሰው የሚገኝበት ሁኔታ ወይም አቋም ነው፤

“ሰውን በማይገባ አገልጋይ ማድረግ” ማለት አንድ ሰው ሊያስቀረው፣ ሊከላከለው ወይም ሊቀይረው በማይችልበት ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጥ ወይም ሥራ እንዲሰራ ማድረግ ወይም ማስገደድ ነው፤

“የዕዳ መያዣ ማድረግ” ማለት በሌላ ሦስተኛ ወገን አስቀድሞ በማናቸውም ሁኔታ ግዴታ ለተገባ ወይም ለተጠየቀ ዕዳ የራስን ወይም ኃላፊ የሆነውን ሰው አገልግሎት በመያዣ ከማቅረብ የሚመነጭ ሆኖ የሚሰጠው አገልግሎት ዓይነትና የጊዜ መጠን ባልተወሰነበት ሁኔታ የሚከሰት ማንኛውንም ዓይነት በሰው ልጅ የመነገድ ተግባርን ታሳቢ የሚያደርግ የመያዣነት ተግባር ነው፤

“በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር” ማለት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የገንዘብ ወይም ሌላ ቁሳዊ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ሰዎችን ዜግነት ወደሌላቸው ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ወዳላገኙበት አገር በሕገ-ወጥ መንገድ በየብስ፣ በባህር ወይም በአየር ማስገባት ወይም እንዲወጡ ማድረግ ነው፤

“ዲፕሎማቲክ ሚሲዮን” ማለት እንደ አግባብነቱ የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ ሃገራት ያቋቋማቸው ኤምባሲዎች፣ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት፣ ቆንሲላ ጽሕፈት ቤቶች እና የክብር ቆንሲላዎች ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የውጭ አገር ኤምባሲዎች እና ቆንሲላ ጽሕፈት ቤቶች ማለት ነው፤

“ስደተኛ” ማለት በስደተኞች ጉዳይ አዋጅ የተመለከቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ ሰው ነው፤

“ተጎጂ” ማለት በዚህ አዋጅ የተደነገጉ የወንጀል ድርጊቶች የተፈፀበት ሰው ወይም የወንጀል ድርጊቱ በመፈፀሙ ጉዳት የደረሰበት ሰው ሲሆን ማንኛውንም የሥነ-ልቦና፣ ሞራላዊ፣ አካላዊ ወይም የኢኮኖሚ ጉዳት ወይም ሌላ መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የደረሰበት ሰው ነው፤

“ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀፅ 47 (1) የተመለከተው ማንኛውም ክልል ሲሆን ለዚህ አዋጅ አፈፃፀም ሲባል የአዲስ አበባንና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደርን ይጨምራል፤

“ሕጻን” ማለት ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነ ማንኛውም ሰው ነው፤

“ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፍትህ ሚኒስቴር ወይም የፍትህ ሚኒስትር ነው፤

“ፖሊስ” ማለት የፌዴራል ፖሊስ ወይም በዚህ አዋጅ ለተመለከቱ ጉዳዮች የፌዴራል ፖሊስ ሥልጣን በውክልና የተሰጠው የክልል ፖሊስ ነው፤

“ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤

ማንኛውም በወንድ ፆታ የተገለጸው አነጋገር ሴትንም ይጨምራል፡፡

ክፍል ሁለት

ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ስደተኞችን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎች

ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ የግዛት ክልል ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ የግዛት ክልል ውጪ ለብዝበዛ ዓላማ ሲባል፦

በአገር ውስጥ ሥራና ሠራተኛን ለማገናኘት ወይም ለሥራ ወይም ለሥራ ልምምድ ወደ ውጭ አገር መላክ በሚል ሽፋን፤

የጉዲፈቻ ስምምነት በማድረግ ወይም በጉዲፈቻ ሽፋን፤ ወይም

ለሌላ ማንኛውም አይነት ዓላማ፤

ዛቻን፣ ሀይልን ወይም ሌላ የማስገደጃ ዘዴ በመጠቀም፣ በማገት፣

በመጥለፍ፣ በተንኮል፣ በማታለል ወይም የተስፋ ቃል በመስጠት፣

ሥልጣንን አላግባብ በመጠቀም፣ የሰዎችን ለጥቃት ተጋላጭነት በመጠቀም ወይም ስለሌላው ኃላፊነት ያለበትን ሰው ፈቃድ ለማግኘት መደለያ ወይም ጥቅም በመስጠት ወይም በመቀበል ሰዎችን የመለመለ፣

ያጓጓዘ፣ ያዘዋወረ፣ ያስጠለለ ወይም የተቀበለ እንደሆነ ከ15 ዓመት እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና ከብር 150,000 እስከ ብር 300,000 በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡

በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው የወንጀል ድርጊት የተፈፀመው፦

በሕጻናት፣ በሴቶች ወይም በአዕምሮ ወይም በአካል ጉዳተኞች ላይ ከሆነ፤

ተጎጂው ለአካላዊ ወይም አዕምሯዊ ጉዳት ከተዳረገ፤

አደንዛዥ ዕፅ፣ መድሃኒት ወይም የጦር መሣሪያ በመጠቀም እንደሆነ፤

በመንግስት ባለሥልጣን ወይም ሠራተኛ ከሆነና ወንጀሉን የፈጸመው የተሰጠውን ኃላፊነት መከታ በማድረግ ከሆነ፤ ወይም

በተጎጂው ወላጅ፣ ወንድም፣ እህት፣ አሳዳጊ ወይም በተጎጂው ላይ ሥልጣን ባለው ሰው የሆነ እንደሆነ፤

አቤቱታ አቀራረብ


የአቤቱታ አቀራረብ ስርዓትየአጣሪ ዳኝነት አቤቱታ የሚስተናገድበትስርዓት ከመደበኛው የፍትሐብሔር የክስ አቤቱታ አቀራረብ ስርዓት ይለያል፡፡አንድ የመስኩ ጸሐፊ ይህን የተለየየሚያደርገውን ባህርይ እንደሚከተለውይገልጸዋል፡፡A claim for judicial review is something out of the ordinary: the court decides the dispute without a trial. The point of a trial in an ordinary claim is to resolve the issues of fact on which a claim is based. The summary process in a claim for judicial review is designed on the assumption that resolving issues of fact is not the point of the litigation. The point is for the court to review the lawfulness of a public authority’s conduct, and there is often no dispute as to what the public authority has done or proposes to doaበእንግሊዝ የአስተዳደር ህግ የአጣሪ ዳኝነትአቤቱታ ማለት፤[A] claim to review the lawfulness of (i) an enactment; or (ii) a decision, action or failure to act in relation to the exercise of a public functionbበእንግሊዝ አጣሪ ዳኝነት አቤቱታ እንደመደበኛ ክስ በቀጥታ አይቀርብም፡፡መጀመሪያ የፍርድ ቤቱ ይሁንታያስፈልገዋል፡፡c ፍርድ ቤቱ አቤቱታውንመርምሮ ጉዳዩ በፍርድ ክለሳ መልክእንዲስተናገድ ካልፈቀደ በቀር አቤቱታውለተቃራኒው ወገን እንዲደርስአይደረግም፡፡ ይህ የፈቃድ ቅድመ ሁኔታየአጣሪ ዳኝነት አንዱና ዓይነተኛው መገለጫነው፡፡ አቤቱታው የሚቀርብበት ጊዜበገደብ መታጠሩ ደግሞ ሁለተኛው አንኳርባህርይ ነው፡፡ ክስ የማቅረቢያ ጊዜንበተመለከተ በመደበኛ የፍትሐ ብሔርክርክሮች ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው የይርጋደንብ ነው፡፡ ይርጋ ከጊዜ ገደብ ይለያል፡፡ይርጋ በተከራካሪው ወገን እስካልተነሳ ድረስፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ተፈጻሚአያደርገውም፡፡ በተጨማሪም ከጊዜ መጠኑአንጻር በዓመታት እንጂ በወራትአይለካም፡፡በአጣሪ ዳኝነት አቤቱታ ላይ የሚቀመጠውየጊዜ ገደብ የተንዛዙ ክርክሮች በውጤታማአስተዳደር ላይ የሚያስከትሉትን አሉታዊተጽዕኖ ለማስወገድ ያለመ ነው፡፡ ስለሆነምፍርድ ቤት ጊዜው ያለፈበትን አቤቱታበራሱ አነሳሽነት አይቀበልም፡፡ የጊዜውመጠንም በአማካይ ከሶስት ወራትአይበልጥም፡፡ የሶስት ወራት ጊዜውቢኖርም አቤቱታው ሳይውል ሳያድርወዲያኑ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ አቤቱታአቅራቢው እስከ ጊዜ ገደቡ ማብቂያ ድረስ ተኝቶ እንዲጠብቅ አይፈቀድለትም፡፡ይህም ማለት አቤቱታው በጊዜ ገደቡውስጥ ቢቀርብም አለአግባብ ከዘገየ ውድቅ ሊደረግ ይችላል፡፡d

የስልጣን ቁጥጥር: ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ


የስልጣን ቁጥጥር: ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ

Democratic theory demands that all public servants, elected or nonelected, be accountable to the people. Obviously, this requires the creation of certain oversight mechanisms so that administrative behavior can be watched and controlled.aከሁሉም ስልጣንን የመቆጣጠር ኃላፊነትና ግዴታ ከተጣለባቸው ተቋማት መካከል የህዝብ ተወካዮች ስራ አስፈፃሚውንና በስሩ ያሉትን አስፈፃሚ አካላት በቅርበት የመከታተልና የመቆጣጠር አይነተኛ አደራና ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ድምዳሜው ከውክልና ዲሞክራሲ (representative democracy) መርህ ይመነጫል፡፡ ይህ መርህ ከተጠያቂነት ጋር ያለውን ትስስር አሜሪካዊው የፖለቲካ ሳይንስ እና የአስተዳደር ህግ ምሁር ተንታኝ እንደሚከተለው ይገልፀዋል፡፡The ideal of representative democracy is that important decisions are taken by our elected representatives. In practice, this is not possible. Parliamentary bodies are too large and fractious to be effective decision making organs. The role of such bodies is, therefore, often confined to scrutinising and passing legislative proposals initiated by a smaller executive committee of their members; and to calling members of that executive committee to account for their actions.bየሚኒስትሮች ም/ቤት ሆነ እያንዳንዱ የአስተዳደር መ/ቤት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የወጣን ህግና ፖሊሲ ለማስፈፀም በውክልና በሚሰጣቸው የስልጣን ገደብ ውስጥ ደንብና መመሪያ ማውጣት እንደሚጠበቅባቸው እሙን ነው፡፡ እነዚህ አካላት ይህን የህግ አውጭነት ስልጣን የሚያገኙት በቀጥታ ህገ-መንግስቱ ሳይሆን በውክልና ከተወካዮች ም/ቤት ብቻ ነው፡፡ የውሳኔ ሰጪነት (አስተዳደራዊ ዳኝነት) ስልጣን እንዲሁ በቀጥታ ከምክር ቤቱ ይመነጫል፡፡የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የህግ አውጪነት ስልጣናቸውን በከፊል ቆርሰው ሲያስተላልፉ ሆነ ለውሳኔ ሰጪው ዳኝነታዊ ስልጣን ሲሰጡ ስልጣን የተቀበለው አካል ከስልጣኑ ገደብ አለማለፉና ህጋዊ ስልጣኑንም ፍትሀዊ በሆነ መንገድ በአግባቡ የተገለገለበት ስለመሆኑ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡ ስልጣን ተቀባይን ከስልጣን ሰጪው በበለጠ የመቆጣጠር ኃላፊነት ያለበት አካል የለም፡፡በውክልና ዲሞክራሲ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ውስጥ የህዝብ ተወካዮች አይነተኛ ሚና በተለምዶ እንደሚታወቀው ህግ ማውጣት ሳይሆን ስራ አስፈፃሚውን በመቆጣጠር የመንግስትን ተጠያቂነት በተግባር ማረጋገጥ እንደሆነ ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል፡፡ በካቢኔ መንግስታዊ ስርዓት (Cabinet Government) ላይ ንጽጽራዊ ጥናት ያደረጉ ሁለት ምሁራን ይህንኑ ሀሳብ በማጉላት በአጭሩ እንደሚከተለው ይገልጹታል፡፡The essence of parliamentary democracy is the accountability of the government (or cabinet or executive or administration) to the legislature.cየውክልና ዲሞክራሲን በሚከተል ሀገር ውስጥ የህዝብ ተመራጮች አይነተኛ ሚና ህግ ማውጣት አይደለም፡፡ በዚህ አይነቱ የመንግስት ስርዓት ውስጥ የህዝብ ተወካዮች በቀጥታ የህዝቡን ጉዳይ መምራትና ማስተዳደር አቅም የላቸውም፡፡ ስለሆነም የስራ አስፈፃሚነት ተግባር እንዲያከናውኑ ከመካከላቸው ጥቂት ተወካዮች ይመርጣሉ፡፡ ከዚህ አንጻር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሁም ከሞላ ጎደል ሁሉም የሚኒስትሮች ም/ቤት አባላት ከህዝብ ተወካዮች መካከል የሚመለመሉ እንደመሆኑ ስራ አስፈፃሚው ‘ንዑስ የፓርላማ ኮሚቴ’ ነው ማለት እንችላለን፡፡በአገራችን አዋጆች የሚመነጩት ከስራ አስፈፃሚው አካል ነው፡፡ የህዝብ ተወካዮችና ስራ አስፈፃሚው አካል የአንድ ፓርቲ አባላት እንደመሆናቸው በስራ አስፈፃሚው የቀረበ ረቂቅ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውድቅ የሚደረግበት አጋጣሚ እጅግ በጣም ጠባብ ነው፡፡ ረቂቅ አዋጁን ውድቅ ማድረግ ከራስ ጋር መቃረን ይሆናል፡፡ በተወካዮችና በስራ አስፈፃሚው መካከል የሚፈጠር ፍጥጫ የመንግስትን ስልጣን በጨበጠው የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ወደ መሰነጣጠቅ ሊያመራ የሚችል የመከፋፈል አደጋ ምልክት በመሆኑ ፍጥጫው በዲሞክራሲያዊ ውይይትና የፓርቲ ዲሲፕሊን (ስርዓቱ ኢ-ዴሞክራሲያዊ ከሆነ ደግሞ በጡጫና በግልምጫ) ካልተወገደ የፓርቲው ህልውና አደጋ ውስጥ ይወድቃል፡፡ስለሆነም በውክልና ዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ የህዝብ ተወካዮች ይሁንታ አስቀድሞ የተፈታ ጉዳይ ስለመሆኑ ግምት መውሰድ ይቻላል፡፡ በህግ ማውጣት ሂደቱ ውስጥ ተወካዮች ከስራ አስፈፃሚው የሚመነጨውን ረቂቅ አዋጅ ቴክኒካልና ቀላል ለውጦች በማድረግ አዋጁን መልክ ከማስያዝ (በግልጽ አማርኛ ከቀለም ቀቢነት) ያለፈ ሚና የላቸውም፡፡ ይህ መሆኑ የተወካዮች ምክር ቤትን ሚና የሚያሳንስ ወይም እንደ ድክመት የሚቆጥር ሳይሆን የራሱ የውክልና ዲሞክራዊ መገለጫና ነፀብራቅ ተደርጐ መወሰድ ይኖርበታል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ‘ህግ አጽዳቂዎች’ እንጂ ህግ አውጪዎች አይደሉም፡፡ ቀዳሚው ህገ መንግስታዊ ሚናቸው ስራ አስፈፃሚውን በመከታተልና በመቆጣጠር የመንግስት ተጠያቂነትን በተግባር ማረጋገጥ ነው፡፡

መሰረታዊ የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች


መልካም አስተዳደር ምንም እንኳን በጥቅሉ ሲታይ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ተቋማዊ እንዲሁም የአመራር እና የአሰራር ሂደቶችን የሚመለከቱ ዘርፈ ብዙ እንደምታዎች ያሉት ቢሆንም በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ሲታይ ግን ከአስተዳደር ፍትህ ጋር አቻ ሆኖ ሊገለጽ ይችላል፡፡ መልካም አስተዳደር ዋና ግቡ ዜጐች ብቁና ውጤታማ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል እንዲሁም የሚደርስባቸውን አስተዳደራዊ በደል መቅረፍ እና አስተዳደራዊ ፍትህን እውን ማድረግ እንደመሆኑ ሁለቱን ነጣጥሎ ማየት ያስቸግራል፡፡ መልካም አስተዳደር ሆነ የአስተዳደር ህግ በራሳቸው አቅጣጫና ሂደት ተጉዘው የግባቸው መድረሻ አስተዳደራዊ ፍትህን ማስፈን ነው፡፡ ስለሆነም በይዘቱ ሰፊ በሆነ የመልካም አስተዳደር እሳቤ ውስጥ የአስተዳደር ህግ አንድ ቁስ ሆኖ በማገልገል የተቆራኘና የተዛመደ ተግባራዊ እገዛ ያደርጋል፡፡በመልካም አስተዳደርና በአስተዳደር ህግ መካከል ያለውን ተዛምዶ በቅጡ ለመቃኘት ህግ በአስተዳደሩ አካሄድ (Administrative behavior) ወይም በስራ አስፈፃሚው እንቅስቃሴ ላይ ምን አይነት አዎንታዊ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል? ለሚለው ጥያቄ በተግባር የታገዘ ጥልቅ ጥናት ምላሽ መስጠት ይጠይቃል፡፡ ይሁን እንጂ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያሉትን ሚናዎችና ተግባራት ቢያንስ እንደጠቅላላ ሀሳብ በመውሰድ የአስተዳደር ህግ እንደ አንድ የህግ ዘርፍ የራሱ አዎንታዊ ፋይዳ እንዳለው መደምደም እንችላለን፡፡ ያም ሆኖ ግን አስተዳደሩ መልካም እንዲሆን የአስተዳደር ህግ ስልጣን ከመቆጣጠር ባሻገር እንዴት ተቃኝቶ መቀረጽ አለበት? የሚለው ጥያቄ ለአስተዳደር ህግ አጥኚዎች ሆነ ምሁራን የውይይት ምንጭ ብቻ ሳይሆን የጥናት መሰረት መሆን ያለበት ጉዳይ ነው፡፡የመልካም አስተዳደር እና የአስተዳደር ህግን ተዛምዶ ለማየት የሁለቱም መድረሻ ከሆነው የአስተዳደር ፍትህ ትርጓሜ እንነሳለን፡፡ የአስተዳደር ፍትህ በህግ ስልጣን የተሰጣቸው የመንግስት አካላት ስልጣናቸውን በሚገለገሉበት ወቅት ከዜጐች መብትና ነፃነት አንጻር ፍትሃዊ መሆን እንዳለባቸው የሚደነግግ መርህ ነው፡፡ የመንግስት አስተዳደር ፍትሃዊ ሲሆን መልካም ይሆናል፡፡የአስተዳደር ፍትህን በማሳካት ረገድ ሁለት ዓበይት ነጥቦች ቁልፍ ቦታ ይኖራቸዋል፡፡ ይኸውም፡-አንደኛ፦ የመንግስት ባለ ስልጣናት ወይም የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ስልጣናቸውን በሚገለገሉበት ወቅት አነስተኛ ለሆኑ የስነ-ስርዓት ደንቦች እና ተቀባይነት ላላቸው መርሆዎች መገዛት አለባቸው፡፡ ከአነስተኛ የስነ-ስርዓት ደንቦች በተጨማሪ የመንግስት አስተዳደር ተቀባይነት ባላቸው የህግ፣ የአስተዳደርና የፍትህ መርሆዎች መመራት አለበት፡፡ከእነዚህ መካከል በዋናነት የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡የህጋዊነት መርህ (ህጋዊ ስልጣን ሳይኖር አንዳችም እርምጃ አለመውሰድ፤ በህጉ መሰረት መወሰን)የሚዛናዊት መርህ (የአስተዳደር አካላት ውሳኔ ወይም እርምጃ እንደየሁኔታው ብዙ ነገሮች ግምት ያስገባ እንጂ ፍርደገምድል መሆን የለበትም፡፡)የተመጣጣኝነት መርህ (የሚወሰደው እርምጃ ተፈጸመ ከተባለው ጥፋት አንፃር ተመጣጣኝ መሆን አለበት፡፡)የእኩልነት መርህ (ተመሳሳይ በሆኑ ሁኔታዎች ወይም ጉዳዮች አስተዳደሩ የተለያየ ውሳኔ ላይ መድረስ የለበትም፡፡ ተመሳሳይ ሁኔታዎች በተመሳሳይ መንገድ መወሰን አለባቸው፡፡)ለውሳኔ በቂ ምክንያት መስጠት (አስተዳደራዊ ውሳኔ የተወሰደበት ምክንያት በግልጽ መጠቀስ አለበት፡፡ ውሳኔውም ፈጽሞ የማያሳምንና ኢ- ምክንያታዊ መሆን የለበትም፡፡)ሁለተኛ፦ ከላይ የተመለከቱትን ደንቦችና መርሆዎች በመጻረር በህግ ከተወሰነው ስልጣን በላይ እርምጃ ከተወሰደ መብታቸው የተጐዳ ዜጐች አቤቱታ አቅርበው ፍትህ (መፍትሄ) የሚያገኙበት መንገድ መኖር አለበት፡፡ በአስተዳደር አካላት መብታቸው የተጣሰ ሰዎች ቀላል በሆነ ስነ-ስርዓት አቤቱታ አቅርበው ቀልጣፋ መፍትሔ የሚያገኙበት አሰራር ወይም መንገድ ከሌለ የአስተዳደር ፍትህ አለ ለማለት አይቻልም፡፡ ለምሳሌ አካልን ነፃ የማውጣት መብት በህገ-ወጥ መንገድ ከ48 ሰዓት በላይ የታሰረ ሰው ራሱ በቀጥታ ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን በቀላሉ አቤቱታ አቅርቦ ነፃ የሚለቀቅበት ፈጣን ስነ-ስርዓት ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በህገ ወጥ መንገድ ንብረቱን በአስተዳደደሩ የተቀማ ወይም ፈቃዱ አለአግባብ የተሰረዘበት ሰው ቀላል በሆነ ስነ-ስርዓት መፍትሔ የሚያገኝበት የህግ ድንጋጌ ሊኖር ይገባል፡፡ ለዚህም ነው የአስተዳደር ህግ መኖር ለአስተዳደራዊ ፍትህ ሆነ ለመልካም አስተዳደር ወሳኝ መሳሪያ ነው የሚባለው፡፡ የአቤቱታው ስርዓት እንዳለ ሆኖ የአስተዳደራዊ ፍትህ የሚገኝበት ተቋም ገለልተኛ፣ ተደራሽ እና ነፃ ሆኖ ቀልጣፋና ውጤታማ ግልጋሎት መስጠት መቻሉ የአስተዳደር ፍትህን በማሳካት ረገድ ዋናውና መሰረታዊው ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

ተጠያቂነት ግልፅነት እና የህዝብ ተሳትፎ

ተጠያቂነት ግልፅነት እና የህዝብ ተሳትፎ የመልካም አስተዳደር ፅንስ ሃሳብ በቀጥታ ከሚጋራቸው የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች መካከል ግልፅነት፣ ተጠያቂነት እና የሕዝብ ተሳትፎ ዋናዎቹ ናቸው፡፡ በእነዚህ መርሆዎች ላይ የተተከለ መልካም አስተዳደርን በአንድ አገር ውስጥ በተጨባጭ ለማስፈን ከህግ ማእቀፍ ውጭ የተቋማዊና የአሰራር ለውጦች መዘርጋትና መዳበር ሰፊውን ድርሻ እንደሚይዝ እሙን ነው፡፡ ሆኖም የህግ ሚናም መዘንጋት የለበትም፡፡ የአስተዳደር ህግ ግልፅነት፣ ተጠያቂነት እና የህዝብ ተሳትፎ በተግባር መፈፀማቸውን በማረጋገጥ ረገድ አንድ ቁልፍ መሳሪያ ነው፡፡ግልፅነት በጠቅላላው በመንግስትና በግለሰብ መካከል ያለውን ግልፅ የመረጃ ልውውጥ ያመለክታል፡፡ ዜጎች የመንግስት አሰራሮች፣ ዕቅዶች፣ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን በተመለከተ በቂ መረጃ ከሌላቸው የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይሳናቸዋል፡፡ የመንግስት ባለስልጣናትም ከተጠያቂነት ያመልጣሉ፡፡ የመንግስት ገበና ሳይታወቅ ተጠያቂነት አይታሰብም፡፡በህግ ማእቀፍ ውስጥ ስናወራ ግልፅነት የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት ነው፡፡ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገ መንግስት የመንግስት አሰራር ለህዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበት በመርህ ደረጃ ይደነገጋል፡፡ ይህ ህገ- መንግስታዊ መርህ በተግባር የሚረጋገጠው ይህን የሚያስፈፅም ዝርዝር ህግ የወጣ እንደሆነ ነው’በአገራችን ዜጎች መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ስርዓት በ2002 ዓ.ም. በወጣው የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁ. 590/2002 የህግ ማዕቀፍ ተበጅቶተለታል፡፡ በተግባር ሲታይ ግን የመንግስት አዋጆች፤ ደንቦችና መመሪያዎች፣ አሰራሮችና ውሳኔዎች ግልፅነት ጉዳይ የሀገሪቱን የህግ ስርዓት ጥላሸት ቀብቶታል፡፡ የህጎች ህትመት እና ስርጭቱ አሁንም ድረስ በጣም በመጨረሻው ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን አዋጆችና ደንቦች ውጤት የሚኖራቸው በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ሲወጡ ቢሆንም በስርጭት ችግር የተነሳ ተደራሽ አይደሉም፡፡ግልፅነት ብቻውን ተነጥሎ የቆመ መርህ ሳይሆን ተጓዳኝ ከሆነው የሚስጥራዊነት ደንብ ጋር እየተመዘነ እና እየተመዛዘነ መለኪያ ሊበጅለት ይገባል፡፡ ግልፅነት ለመንግስት አሰራር እና ለህዝብ ጥቅም ወሳኝ እንደሆነ ሁሉ ከአገር ፀጥታና ደህንነት ብሎም ከዜጎች የግል መብት አንፃር የተወሰኑ መረጃዎች በሚስጥር እንዲጠበቁ ያስፈልጋል፡፡ በሚስጥር ሊጠበቁ የሚገባቸው መረጃዎች የመንግስት ባለስልጣናትና ሠራተኛው በኃላፊነቱ ደረጃ ለይቶ እንዲያዛቸው የሚያስችል ሚስጥራዊነታቸውን የመመደብና የመፈረጅ ዘዴና ስርዓት ሊኖር ይገባል፡፡የአስተዳደር ህግ የግልፅነት ብቻ ሳይሆን በህገመንግስቱ ላይ የተቀመጠውን የተጠያቂነት መርህ ማስፈጸሚያ መሳሪያ ጭምር ነው፡፡ ህጉ የአስተዳደር አካላትና ባለስልጣናት ለድርጊታቸው ተጠያቂ የሚሆኑበትን ስርዓት ከመዘርጋት ባሻገር ጠያቂ የሆኑ አካላትን በመለየት የተቀናጀ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልት ይቀይሳል፡፡ዴሞክራሲን እውነተኛ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ዜጎች በመንግስት አስተዳደር ውስጥ የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸው ነው፡፡ ህገ መንግስቱ ዜጎች የሚያስተዳድሯቸውን በመምረጥ ብቻ ሳይሆን በቀጥተኛ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ሉአላዊነታቸው እንደሚረጋገጥ ይደነገጋል፡፡a የሕዝብ ተሳትፎ በተወሰነ መልኩ አስገዳጅ በሆኑ ድንጋጌዎች በተግባር ሊተረጎም ይገባል፡፡ በተለይ በአስተዳደር መስሪያ ቤቶች የህግ ማውጣት ሂደት ውስጥ የአስተዳደር ህግ እና የሕዝብ ተሳትፎ ተነጣጥለው ሊታዩ አይችሉም፡፡ ውጤታማ የአስተዳደር ህግ ሲኖር በህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጠው ‘ህዝብ በመንግስት አስተዳደር ውስጥ የመሳተፍ’ መብቱ በተጨባጭ ይረጋገጣል፡፡

አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት (ከፊል የህግ አውጭነት ስልጣን)


አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት (ከፊል የህግ አውጭነት ስልጣን)

አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት (ከፊል የህግ አውጭነት ስልጣን) ህግ የማውጣት ስልጣን የህግ አውጭው ነው እንላለን እንጂ በተግባር ግን ህግ የሚወጣው በተወካዮች ም/ቤት ብቻ አይደለም፡፡ ይህ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በየትም አገር ያለ እውነታ ነው፡፡ በየጊዜው እያደገ ከሚመጣው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስብስብነት የተነሳ ህግ አውጭው ከልሂቅ እስከ ደቂቃ ለእያንዳንዱ ችግር መፍትሄ የሚሆን ህግ በአይነትና በጥራት ማቅረብ ይሳነዋል፡፡ አንድ የህግ ረቂቅ ውጤት ያለው ህግ ለመሆን ከሚፈጀው ረጅም ጊዜና ዝርዝር የስነ-ስርዓት ቅድመ ሁኔታ አንፃር ህግ አውጭው በየጊዜው ለሚፈጠር ችግር በየጊዜው አዋጅ እያወጣ መፍትሄ ለመስጠት በቂ ጊዜ የለውም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ዝርዝር ጉዳዮች ልዩ እውቀትን የሚጠይቁ እንደመሆኑ ውስን የሆነው የህግ አውጭው እውቀት የህግ ማውጣት ስልጣን በተግባር በከፊል የተገደበ እንዲሆንና ሌላ አማራጭ እንዲፈልግ ያስገድደዋል፡፡ ይህ አማራጭ በውክልና ስልጣን የሚወጣ ህግ (delegated legislation) ይባላል፡፡ ተግባራዊ ከሆኑት አስፈላጊ ምክንያቶች የተነሳ ህግ አውጭው ከህዝብ የተሰጠውን ህግ የማውጣት ስልጣን በከፊል ቆርሶ ለስራ አስፈፃሚውና ለአስተዳደር መ/ቤቶች ይሰጣል፡፡ በዚሁ መሰረት የሚኒስትሮች ም/ቤት በአዋጅ በሚሰጠው ስልጣን መሰረት ደንብ ይደነግጋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የአስተዳደር መ/ቤቶች በውክልና የህግ አውጭነት ስልጣናቸው መመሪያቸውን ያወጣሉ፡፡ ዋነኛ ስልጣኑ ህግ ማስፈፀም የሆነው ስራ አስፈፃሚው የመንግስት አካል በደንብና በመመሪያ የህግ አውጭነት ስልጣን ደርቦ መያዙ ከስልጣን ክፍፍል መርህ ጋር የሚጣረስ ቢሆንም የህግ አውጭው ጊዜና የእውቀት ውስንነት እንዲሁም የመንግስት አስተዳደርን ብቁና ውጤታማ ከማድረግ አንፃር በተግባር የግድ የሚል እውነታ ሆኗል፡፡ ሆኖም አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስልጣን በዚህ እውነታ ብቻ አይቋጭም፡፡ ያልተገደበ ስልጣን መኖር ለዜጐች መብትና ነፃነት መቼም ቢሆን አደገኛነቱ ጥርጥር የለውም፡፡ የአስፈላጊነቱ እውነታ ከዜጐች መብትና ነፃነት ጋር እንዲጣጣም ወይም እንዲታረቅ ተግባራዊ የስልጣን መቆጣጠሪያ መሳሪያ እንዲኖር ግድ ይላል፡፡ እንደ የአስተዳደር ህግ ምሁሩ ዌድ አገላለጽ ‘ከዜጐቹ ላይ ነፃነት ሲቀነስ ፍትህ መጨመር አለበት፡፡’ የመንግስት ስልጣኑ ሲለጠጥ በዛው ልክ የዜጐች መብትና ነፃነት እየተሸበሸበ (እያነሰ) ይመጣል፡፡ ስልጣን ሲጨምር ፍትህም አብሮ መጨመር አለበት፡፡ ከዚህ አንጻረ ስራ አስፈፃሚው ተጨማሪ የህግ አውጭነት ስልጣን ሲሰጠው ስልጣኑን በአግባቡና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እንደሚገለገል የሚያረጋግጥና የሚቆጣጠር የአስተዳደራዊ ድንጋጌ አወጣጥ ስነ ስርዓት ያስፈልጋል፡፡ በሚኒስትሮች ም/ቤት እና በአስተዳደር መ/ቤቶች የሚወጡ አስተዳደራዊ ድንጋጌዎች ከሌሎች የአስተዳደር ተግባራት የሚለያቸው መሰረታዊ ባህሪያት አላቸው፡፡ በዋናነት የሚከተሉትን ነጥቦች ይጠቀሳሉ፡፡ በውክልና የሚወጣ ህግ የተፈጻሚነቱ ወሰን በአንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት ላይ ሳይሆን በህብረተሰቡ በአጠቃላይ ወይም በተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ነው፡፡ ትኩረቱ በግለሰብና በመንግስት መካከል የሚነሱ የግል ክርክሮችን መፍታት ሳይሆን የህዝብ ጥቅምን ለማስጠበቅ የሚረዱ ፖሊሲዎችን ማስፈፀም ነው፡፡ ወደ ኋላ ተመልሶ ተመልሶ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡ ውጤቱና ተፈጻሚነቱ አስተዳደራዊ ድንጋጌው ከወጣ በኋላ ወደ ፊት ለሚከሰቱ ነገሮች ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ ውጤት ይኖረዋል፡፡ በይፋ ታትሞ ለህዝብ መሰራጨት ይኖርበታል፡፡ ከህትመት በፊት ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት የማማከር ቅድመ ሁኔታ ሊሟላ ይገባል፡፡ በአስተዳደሩ የሚወጡ ድንጋጌዎች አብዛኛውን ጊዜ በተግባር እንዲፈፀሙ በተጨማሪ የአስተዳደር ድርጊት /ውሳኔ፣ እርምጃ፣ ቅጣት/ መታገዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህም በራሳቸው ምሉዕ አይደሉም፡፡

From the day Prime Minister Abiy Ahmed came to power, the slogan, politics or patriotism that Ethiopia has been saying will not fall apart?


From the day Prime Minister Abiy Ahmed came to power, the slogan, politics or patriotism that Ethiopia has been saying will not fall apart? Who said Ethiopia will be destroyed or Ethiopia will be destroyed? Why did Prime Minister Abiy Ahmed, with his tribute to Isaias Afewerki, repeatedly use slogans unless he himself had the…

A Rebel leader and one of the most sought after men in the country.Now he sits in a mountain village with his satellite phone and plans how the war will continue for the rebels.


a rebel leader and one of the most sought after men in the country. Now he sits in a mountain village with his satellite phone and plans how the war will continue for the rebels. The war in Tigray County began last November when the armed wing of the TPLF, the Tigray People’s Liberation Front,…

Hundreds of thousands of Tigray mothers and children are dying of starvation in Ethiopia. This is an unprecedented massacre in all parts of the country at the behest of dictator Abiy Ahmed.This is how my country became! too bad.! በሃገራችን ኢትዮጵያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ እናቶችና ህፃናት በአስከፊ ሰው ሰራሽ ረሀብ እየረገፉ/እየሞቱ ነው፡፡ ይህ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እየተፈፀመ ያለው አስከፊ ሰቆቃና ረሃብ ግፍ በ አንባገነኑ አብይ አህመድ መራሹ አንባገነን መሪ ፍላጎት የተፈጸመ የዘርማጥፋት ዘመቻ ነው።ሀገሬ እንዲህ ሆነች! ያሳዝናል።!


Hundreds of thousands of Tigray mothers and children are dying of starvation in Ethiopia.  This is an unprecedented massacre in all parts of the country at the behest of dictator Abiy Ahmed.This is how my country became!  too bad.!   በሃገራችን ኢትዮጵያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ እናቶችና ህፃናት በአስከፊ ሰው ሰራሽ ረሀብ እየረገፉ/እየሞቱ ነው፡፡ ይህ በሁሉም…

ግዴታን አለመወጣት


ግዴታን አለመወጣት

ህጋዊ ግዴታ የተጣለበት አካል በቸልተኝነትና በንዝልልነት አሊያም ሆነ ብሎ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ግዴታውን ለመፈፀም ፍቃደኛ ሳይሆን ሲቀር ዜጋው በእርግጥም የአስተዳደር በደል ደርሶበታል፡፡ ግዴታውን ያልተወጣው አካል ተገዶ ግዴታውን እንዲፈጽም በማድረግ በደል ለደረሰበት ወገን ፍትህ ማጎናፀፍ የፍርድ ቤቶች ኃላፊነት ነው፡፡ የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት ሕገ መንግስቱን የማስከበር ግዴታና ኃላፊነት በህግ አውጭና ህግ አስፈፃሚው እንዲሁም በዳኝነት አካላት ላይ ይጥላል፡፡ በህገ-መንግስቱ ላይ የተመለከቱት መብቶችና ነፃነቶች በአስተዳደራዊ ድርጊት ብቻ ሳይሆን ግዴታን ባለመወጣት በሚፈፀም በደል ምክንያት እንዳይጣሱና እንዳይገረሰሱ በመጠበቅ ፍርድ ቤቶች ህገ-መንግስታዊ ግዴታቸውን ሊወጡ የሚችሉት ህገወጡን ድርጊት ሲሰርዙ (ሲሽሩ) እንዲሁም ግዴታውን ያልተወጣውን አካል ማስገደድ ሲችሉ ብቻ ነው፡፡ አንድ የአስተዳደር መስሪያ ቤት ግዴታውን አልተወጣም ተብሎ ከመወቀሱና ፍርድ ቤቱም የማስገደጃ ትዕዛዝ ከመስጠቱ በፊት መስሪያ ቤቱ ከህግ የመነጨ ግዴታ እንዳለበትና ግዴታው ለአመልካቹ በቀጥታ የሚፈጸም መሆኑ መረጋገጥ የሚኖርባቸው ፍሬ ነገሮች ናቸው፡፡ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል እንበልና የአንድ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት (ስም) የማዛወር እና ከተማዋን የማጽዳት ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ ስም የማዛወር ግዴታ በህግ የተቀመጠ ግዴታ ከመሆኑም በላይ ለአመልካቹ በቀጥታ የሚፈፀም ስለሆነ ስም ለማዛወር የሚያበቁ ህጋዊ ቅድመ-ሁኔታዎች ከተሟሉ ማዘጋጃ ቤቱ ዝውውሩን ሊያከናውን ይገደዳል፡፡ ፈቃደኛ ሳይሆን ከቀረ ግን በፍርድ ቤት አስገዳጅነት ስም ማዛወር ይኖርበታል፡፡ በሰ/መ/ቁ. 91622a አንደኛውን ተከራካሪ ባለመብት የሚያደርግ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ በስሙ የመመዝገብ ግዴታ ያለበት አካል ውሳኔ ያረፈበትን ቤት በሌላ ሰው ስም እንደተመዘገበ በመግለጽ ከግዴታው ሊያመልጥ እንደማይችል ችሎቱ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ከተማዋን የማጽዳት ግዴታ እንደ መጀመሪያው ለአንድ ግለሰብ የተሰጠ ሳይሆን ህዝባዊ ግዴታ (public duty) ነው፡፡ ስለሆነም በግዴታው አለመወጣት መብቱ ወይም ጥቅሙ የተነካበት ወገን ግዴታው እንዲፈጸምለት በፍርድ መጠየቅ አይችልም፡፡ አጣሪ ዳኝነት ሆነ የህዝብ ጥቅም ማስከበሪያ ክስ (Public interest litigation) ብዙም ባልተለመደበት በአገራችን ህዝባዊ ግዴታን ማስፈጸም በባህርዩ አስቸጋሪ የሚያደርጉት ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ ከተማ ለማጽዳት ማዘጋጃ ቤቱ በቂ የሰው ኃይል መቅጠር፣ የደረቅ ፍሳሽ ማስወገጃ መኪኖችን መግዛት ወዘተ…ይጠበቅበታል፡፡ ይህን ለማድረግ በቂ በጀት ካልተመደበለት የፍርድ ማስገደጃ ትዕዛዝ ተግባራዊ ፋይዳ አይኖረውም፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት የግዴታ ባህሪያት በተጨማሪ የሚፈጸመው ግዴታ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን ወይም ሊሟሉ የሚገባቸውን ፍሬ ነገሮች ግምት ውስጥ በማስገባት ውሳኔ ላይ የመድረስ ፈቃደ ስልጣን (discretion) የሚሰጥ ሊሆን ይችላል፡፡ በህጉ መሰረት የንግድ ፈቃድ የመስጠት ግዴታ ያለበት አካል ግዴታው የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ማረጋገጥና ውሳኔ ላይ መድረስ ብቻ ነው፡፡ ማመልከቻ ቀርቦለት መርምሮ ተገቢ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ፈቃደኛ ሳይሆን ቢቀር ማመልከቻውን አይቶ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ በፍርድ ሊገደድ ይችላል፡፡ ሆኖም ፍርድ ቤቱ ከዚህ አልፎ ራሱን በፈቃድ ሰጪው አካል ቦታ በመተካት የማመልከቻውን ትክክለኛነት መርምሮ ለአመልካቹ ፈቃድ እንዲሰጠው የማስገደጃ ትዕዛዝ ከመስጠት መቆጠብ አለበት፡፡

ሚዛናዊ የግብረ ስጋ ግኑኝነት


ሚዛናዊ የግብረ ስጋ ግንኙነት

ለመሆኑ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ከህግ አንፃር የተፈቀደው የግብረ ስጋ ግንኙነት አቅጣጫ (position) የትኛው ነው? በ ዶ እና ሞ (Doe Vs. Moe) መካከል በአሜሪካ ማሳቹሴትስ ግዛት የተካሄደ የይግባኝ ክርክር እና ውሳኔ ለዚህ ምላሽ የሚሰጥ ይመስላል፡፡ በመዝገቡ ላይ ይግባኝ ባይ የሆነው ግለሰብ “ፍቅረኛዬ የግብረስጋ ግንኙነት ስናደርግ ተገቢና ተስማሚ ያልሆነ አቅጣጫ እንድንጠቀም በማድረግ (በግልፅ አስገደደችኝ ባይልም ወትውታና ገፋፍታ የሚሉትን ቃላት ግን ተጠቅሟል) በዚህም የተነሳ በብልቴ ላይ የማይመለስ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ስለሆነ በቸልተኝነት ለፈጸመችው ድርጊት ተጠያቂ ስለሆች ካሳ ትክፈለኝ” በማለት በስር ፍርድ ቤት ክስ ያቀርባል፡፡ ሆኖም ፍርድ ቤቱ ክሱን ውድቅ አድርጎ ተከሳሽን በነፃ ያሰናብታል፡፡ ከሳሽ በውሳኔው ቅር ተሰኘና ይግባኝ አቀረበ፡፡ ይግባኙን የመረመሩት ዳኛ በስምምነት በሚደረግ የግብረስጋ ግንኙነት ሁለቱም ወገኖች ስለሚጠበቅባቸው ጥንቃቄ በተመለከተ ወጥ መለኪያ ወይም መስፈርት ለማስቀመጥ ፈታኝ እና አስቸጋሪ ሆኖባቸው ነበር፡፡ ስለሆነም የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ ሲያደርጉ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ “በስምምነት የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት ስርዓትን የሚገዙ ሁሉን ዓቀፍ የህግ ድንጋጌዎች የሉም፡፡ በተጨማሪም ይህንን ከስሜት አንፃር እሳታዊ በዓይነቱም ዥንጉርጉር በሆነው ግንኙነት ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የጋራ ተቀባይነት ያላቸው ልማዶች እና እሴቶች የሉም፡፡” በዚሁ መሠረት ፍርድ ቤቱ ድምዳሜ ላይ ከደረሰ በኋላ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ቸልተኝነት በተለመደው ሚዛናዊ ጥንቃቄ የማድረግ መለኪያ ማየት ወይም መወሰን እንደማይቻል በውሳኔው ላይ አስፍሯል፡፡ ሆኖም ፍርድ ቤቱ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ለሚደርስ ጉዳት መቼም ቢሆን ካሳ ሊከፈል እንደማይቻል ፍጹም አቋም ላይ አልደረሰም፡፡ በፍርድ ቤቱ የውሳኔ ሐተታ ላይ እንደተመለከተው በስምምነት በሚፈጸም የግብረ ስጋ ግንኙነት በአንደኛው ወገን ላይ ጉዳት በደረሰ ጊዜ ካሳ ሊከፈል የሚችለው ሌላኛው ቸልተኛ በሚሆንበት ወቅት ሳይሆን ከዚህ ከፍ ብሎ ግድየለሽነት መኖሩ ሲረጋገጥ ነው፡፡ በይግባኝ መዝገቡ ላይ የመልስ ሰጭ ቸልተኝነት የተረጋገጠ ቢሆንም ይግባኝ ባዩ ግድ የለሽ መሆኗን በሚገባ ስላላስረዳ ያቀረበው የካሳ ጥያቄ ውድቅ ተደርጎበታል፡፡

የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 20/1967 የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት ድርጅት


የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 20/1967 የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት ድርጅት ደንብa “ኢትዮጵያ ትቅደም” አውጪው ባለሥልጣን የማስታወቂያ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት ድርጅት አዋጅ ቁጥር 15/1967 (ከዚህ ቀጥሎ “አዋጅ” እየተባለ በሚጠራው) በአንቀጽ 3 እና 9 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቶአል። አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት ድርጅት ደንብ ቁጥር 20/1967 ዓ.ም” ተብሎ ጠቀስ ይቻላል። ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም ካልሰጠው በቀር፣ በዚህ ደንብ ውስጥ፣ “ሰው” ፣ “ቴሌቪዥን” ፣ “ነጋዴ” ፣ “አዳሽ” ፣ “ሥልጣን የተሰጠው ሠራተኛ” እና “ድርጅት” በአዋጁ የተሰጣቸው ትርጓሜ ይኖራቸል። “መዝጋቢ ባልሥልጣን” ማለት የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት ድርጅት ወይም በዚህ ደንብ በአንቀጽ 4 እና 5 የተመለከቱትን ተግባሮችተ እንዲፈጽም ድርጅቱ የሚወክለው ሚኒስቴር ወይም ሌላ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ነው። ምዝገባ ነጋዴ፣ አዳሽ፣ የቴሌቪዥን ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሆነ ማንኛውም ሰው ይህ ደንብ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ90 ቀን ውስጥ መዝጋቢ ባለሥልጣን ዘንድ እየቀረበ መመዝገብ አለበት። ስለምዝገባ ፈቃድና የአገልግሎት ዋጋ መዝጋቢው ባለሥልጣን ማንኛውም ነጋዴ ወይም አዳሽ ሲመዘገብ፣ እንደነገሩ ሁኔታ በዚህ ደንብ በሠንጠረዥ ሀ ወይም ለ የተመለከተውን የምስክር ወረቀት ይሰጠዋል። መዝጋቢው ባለሥልጣን ማንኛውም የቴለቪዥን ባለቤት ወይም ባለይዞታ ሲመዘገብ በዚህ ደንብ በሠንጠረዥ ሐ የተመለከተውን ፈቃድ ይሰጠዋል። ማንኛውም የቴሌቪዥን ባለቤት ወይም ባለይዞታ ፈቃድ ስሰጠው ሃምሳ (50) ብር የአገልግሎት ዋጋ በየዓመቱ ለመዝጋቢው ባለሥልጣን ይከፍላል። መዝገብ ስለመያዝና ስለምርመራ ማንኛውም ነጋዴ፦ ሀ/ በእጁ የሚገኙትን ቴሌቪዥኖች ብዛት፣ ዓይነትና የመለያ ቁጥር፣ እንዲሁም ለ/ ያደረገውን የቴሌቪዥን ሽያጭ ወይም ኪራይ ብዛት፣ የቴሌቪዥኑን ዓይነት፣ መለያ ቁጥርና የገዢውን ወይም የተከራዩን ስምና አድራሻ ጭምር በመዝገብ መያዝ አለበት። ማንኛውም አዳሽ ለማደስ የተረከባቸውን ቴሌቪዥኖች ብዛት፣ ዓይነት፣ መለያ ቁጥርና፣ እንዲሁም የደንበኛውን ስምና አድራሻ በመዝገብ መያዝ አለበት፣ ማንኛውም ነጋዴ ወይም አዳሽ ማንኛውም ሥልጣን የተሰጠው ሠራተኛ ሲጠይቀው ለምርመራ ወይም ለቅጂ መዝገቡን የማቅረብ ግዴት አለበት። ማንኛውም የቴሌቪዥን ባለቤት ወይም ባለይዞታ ማንኛውም ምልጣን የተሰጠው ሠራተኛ ሲጠይቀው ፈቃዱን ለምርመራ የማቅረብ ግዴታ አለበት። ያለፈቃድ በቴሌቪዥን መጠቀም ስለመከልከሉ ማንኛውም ሰው በዚህ ደንብ መሠረት ፈቃድ ካልያዘ በቀር በቴሌቪዥን መጠቀም አይችልም። ደንብ ስለመተላለፍ ይህን ደንብ የጣሰ ወይም ያልፈጸመ ሰው በአዋጁ አንቀጽ 10 መሠረት ይቀጣል። ደንቡ ስለሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከመስከረም 3 ቀን 1968 ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል።   አዲስ አበባ ነሐሴ 19 ቀን 1967 ዓ.ም ሻለቃ ያዕቆብ ገብረ እግዚአብሔር የማስታወቂያ ሚኒስትር       ሠንጠረዥ ሀ የቴሌቪዥን ነጋዴ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ጉርድ ፎቶግራፍ   የሴሪ ቁጥር ……………………………. የምስክር ወቀት ቁጥር ………………. የደረሰኝ ቁጥር ………………………. 1. የነጋዴው ስም ………………………. 2. አድራሻ ………………. 3. የፖ.ግ. ቁጥር …………………………. 4. ስልክ …………………… 5. ዜግነት ………………………………. 6. የሥራ ዓይነት ……………. 7. የንግድ ፈቃድ ቁጥር …………………………. የተመዘገበበት ቀን …………………………. ፊርማ …………………………. ማኅተም ……………………….           ሠንጠረዥ ለ. የቴሌቪዥን አዳሽ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ጉርድ ፎቶግራፍ የሴሪ ቁጥር ……………………………. የፈቃድ ቁጥር …………………………. የደረሰኝ ቁጥር …………………………. 1. የአዳሹ ስም …………………………. 2. አድራሻ …………………. 3. የፖ.ግ. ቁጥር …………………………. 4. ስልክ …………………… 5. ዜግነት ………………………………. 6. የሥራ ዓይነት ……………. 7. የንግድ ፈቃድ ቁጥር …………………………. የተመዘገበበት ቀን …………………………. ፊርማ …………………………. ማኅተም ……………………….             ሠንጠረዥ ሐ. የቴሌቪዥን ባለቤት ወይም ባለይዞታ የምስክር ወረቀት ጉርድ ፎቶግራፍ የሴሪ ቁጥር ……………………………. የፈቃድ ቁጥር …………………………. የደረሰኝ ቁጥር …………………………. 1.የባለቤት ወይም ባለይዞታ ስም ………………………… 2. አድራሻ …………… ሀ. መኖሪያ ………………. ለ. የሥራ ቦታ …………… 3.ዜግነት ……………………………………….ፖ.ሣ.ቁ ሀ. መኖሪያ ……… ለ. የሥራ ቦታ —————– – ስልክ ሀ. መኖሪያ …………. ለ. የሥራ ቦታ ………………. 4.ሥራ …………………………………………………………………………………………. 5.የመታወቂያ ካርድ ቁጥር ……………………………………………………………………. የቴሌቪዥን መለያ ………………………………………………………………………… ዓይነት መጠን የመለያ ቁጥር ………………………. ……………………… ……………………. ቀን …………………. ፊርማ …………………. ማኅተም ………………… ማሳሰቢያ፦ ይህ የፈቃድ ወረቀት የሚያገለግለው ለ19……… ዓ.ም ብቻ ነው። ዕድሳት ————————— ————————— ————————— ————————— ————————— —————————

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት መግቢያ እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣


የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት መግቢያ እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች፦ በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሰላም፣ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እድገታችን እንዲፋጠን፣ የራሳችን ዕድል በራሳችን የመወስን መብታችንን ተጠቅመን፣ በነፃ ፍላጎታችን፣ በሕግ የበላይነት እና በራሳችን ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ በጋራ ለመገንባት ቆርጠን በመነሳት፤ ይህን ዓላማ ከግብ ለማድረስ፣ የግለሰብና የብሔር/ብሔረሰብ መስረታዊ መብቶች መከበራቸው፣ የፆታ እኩልነት መረጋገጡ፣ ባሕሎችና ሃይማኖቶች ካለ አንዳች ልዩነት እንዲራመዱ የማድረጉ አስፈላጊነት ጽኑ እምነታችን በመሆኑ፤ ኢትዮጵያ ሀገራችን የየራሳችን አኩሪ ባሕል ያለን፣ የየራሳችን መልክዓ ምድር አሰፋፈር የነበረንና ያለን፣ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በተለያዩ መስኮችና የግንኙነት ደረጃዎች ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት ሀገር በመሆንዋ፤ ያፈራነው የጋራ ጥቅምና አመለካከት አለን ብለን ስለምናምን፤ መጪው የጋራ ዕድላችን መመስረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅማችንን በማሳደግ ላይ መሆኑን በመቀበል፤ ጥቅማችንን፣ መብታችንና ነፃነታችንን በጋራ እና በተደጋጋፊነት ለማሳደግ አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ የመገንባቱን አስፈላጊነት በማመን፤ በትግላችንና በከፈልነው መሰዋዕትነት የተገኘውን ዴሞክራሲና ሰላም ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ፤ ይህ ሕገ-መንግሥት ከዚህ በላይ ለገለጽናቸው ዓላማዎችና እምነቶች ማሰሪያ እንዲሆነን እንዲወክሉን መርጠን በላክናቸው ተወካዮቻችን አማካይነት በሕገ-መንግሥት ጉባዔ ዛሬ ኅዳር 29 ቀን 1987 አጽድቀነዋል። ምዕራፍ አንድ ጠቅላላ ድንጋጌዎች አንቀጽ 1 የኢትዮጵያ መንግሥት ስያሜ ይህ ሕገ-መንግሥት ፌዴራላዊና ዴሞክራሲያዊ የመንግሥት አወቃቀር ይደነግጋል። በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሚል ስም ይጠራል። አንቀጽ 2 የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን የፌዴራሉን አባሎች ወሰን የሚያጠቃልል ሆኖ በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት የተወሰነው ነው። አንቀጽ 3 የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሐል ቢጫ፣ ከታች ቀይ ሆኖ በመሐሉ ብሔራዊ ዓርማ ይኖረዋል። ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም ይቀመጣሉ። ከሰንደቅ ዓላማው ላይ የሚቀመጠው ብሔራዊ ዓርማ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች እና ሃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ የሚያንጸባርቅ ይሆናል። የፌዴራሉ አባሎች የየራሳቸው ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ ሊኖራቸው ይችላል። ዝርዝሩን በየራሳቸው ምክር ቤት ይወስናሉ። አንቀጽ 4 የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር የሕገ-መንግሥቱን ዓላማዎችና የኢትዮጵያ ሕዝቦች በዴሞክራሲ ሥርዓት አብረው ለመኖር ያላቸውን እምነት፣ እንዲሁም የወደፊት የጋራ ዕድላቸውን የሚያንጸባርቅ ሆኖ በሕግ ይወሰናል። አንቀጽ 5 ስለ ቋንቋ ማናቸውም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በእኩልነት የመንግሥት እውቅና ይኖራቸዋል። አማርኛ የፌዴራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ ይሆናል። የፌዴሬሽኑ አባሎች የየራሳቸውን የሥራ ቋንቋ በሕግ ይወስናሉ። አንቀጽ 6 ስለ ዜግነት ወላጆቹ/ወላጆቿ ወይም ከወላጆቹ/ከወላጆቿ አንደኛቸው ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያዊት የሆነ/የሆነች የኢትዮጵያ ዜጋ ነው/ናት። የውጭ ሀገር ዜጎች የኢትዮጵያ ዜግነት ሊያገኙ ይችላሉ። 3. ዜግነትን በሚመለከት ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። አንቀጽ 7 የፆታ አገላለጽ በዚህ ሕገ-መንግሥት ውስጥ በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም ዖታ ያካትታል። ምዕራፍ ሁለት የሕገ-መንግሥቱ መሰረታዊ መርሆዎች አንቀጽ 8 የሕዝብ ሉዓላዊነት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤቶች ናቸው። ይህ ሕገ-መንግሥት የሉዓላዊነታቸው መግለጫ ነው። ሉዓላዊነታቸውም የሚገለጸው በዚህ ሕገ-መንግሥት መሰረት በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸውና በቀጥታ በሚያደርጉት ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካይነት ይሆናል። አንቀጽ 9 የሕገ-መንግሥት የበላይነት ሕገ-መንግሥቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ ነው። ማንኛውም ሕግ፣ ልማዳዊ አሠራር፣ እንዲሁም የመግሥት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ-መንግሥት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም። ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግሥት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማኅበራት እንዲሁም ባለሥልጣኖቻቸው፣ ሕገ-መንግሥቱን የማስከበርና ለሕገ-መንግሥቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው። በዚህ ሕገ-መንግሥት ከተደነገገው ውጭ በማናቸውም አኳኋን የመንግሥት ሥልጣን መያዝ የተከለከለ ነው። ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ሕግ አካል ናቸው። አንቀጽ 10 ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሰብዓዊ መብቶችና ነፃነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው። የዜጎች እና የሕዝቦች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ። አንቀጽ 11 የመንግሥትና የሃይማኖት መለያየት መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው። መንግሥታዊ ሃይማኖት አይኖርም። መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም። ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም። አንቀጽ 12 የመንግሥት አሠራርና ተጠያቂነት የመንግሥት አሠራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት። ማንኛውም ኃላፊና የሕዝብ ተመራጭ ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ ይሆናል። ሕዝብ በመረጠው ተወካይ ላይ እምነት ባጣ ጊዜ ከቦታው ለማንሳት ይችላል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። ምዕራፍ ሶስት መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች አንቀጽ 13 ተፈጻሚነትና አተረጓጎም በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፌዴራል መንግሥትና የክልል ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚ እና የዳኝነት አካሎች በዚህ ምዕራፍ የተካተቱትን ድንጋጌዎች የማክበርና የማስከበር ኃላፊነትና ግዴታ አለባቸው። በዚህ ምዕራፍ የተዘረዘሩት መሰረታዊ የመብቶችና የነፃነቶች ድንጋጌዎች ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕግጋት፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶችና ዓለም አቀፍ ሠነዶች መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ ይተረጎማሉ። ክፍል አንድ ሰብዓዊ መብቶች አንቀጽ 14 የሕይወት፣ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና፣ የነፃነት መብት አለው። አንቀጽ 15 የሕይወት መብት ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው። ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም። አንቀጽ 16 የአካል ደህንነት መብት ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው። አንቀጽ 17 የነፃነት መብት በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ማንኛውም ሰው ወንድም ሆነ ሴት ነፃነቱን/ቷን አያጣም/አታጣም። ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ሊያዝ፣ ክስ ሳይቀርብበት ወይም ሳይፈረድበት ሊታሰር አይችልም። አንቀጽ 18 ኢሰብዓዊ አያያዝ ስለመከልከሉ ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት፣ ኢ-ሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው። ማንኛውም ሰው በባርነት ወይም በግዴታ አገልጋይነት ሊያዝ አይችልም። ለማንኛውም ዓላማ በሰው የመነገድ ተግባር የተከለከለ ነው። ማንኛውም ሰው በኃይል ተገዶ ወይም ግዴታን ለማሟላት ማንኛውንም ሥራ እንዲሠራ ማድረግ የተከለከለ ነው። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 “በኃይል ተገዶ ወይም ግዴታን ለማሟላት” የሚለው ሐረግ የሚከተሉትን ሁኔታዎች አያካትትም፤ ሀ/ ማንኛውም እስረኛ በእስራት ላይ ባለበት ጊዜ በሕግ መሰረት እንዲሠራ የተወሰነውን ወይም በገደብ ከእስር በተለቀቀበት ጊዜ የሚሠራውን ማንኛውም ሥራ፣ ለ/ ማንኛውም ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ሕሊናው የማይፈቅድለት ሰው በምትክ የሚሰጠውን አገልግሎት፣ ሐ/ የማኅበረሰቡን ሕይወት ወይም ደህንነት የሚያሰጋ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ወይም አደጋ በሚያጋጥምበት ጊዜ የሚሰጥ ማንኛውንም አገልግሎት፣ መ/ በሚመለከተው ሕዝብ ፈቃድ በአካባቢው የሚፈጸመውን ማንኛውም ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ የልማት ሥራ። አንቀጽ 19 የተያዙ ሰዎች መብት ወንጀል ፈጽመዋል በመባል የተያዙ ሰዎች የቀረበባቸው ክስና ምክንያቶቹ በዝርዝር ወዲያውኑ በሚገባቸው ቋንቋ እንዲነገራቸው መብት አላቸው። የተያዙ ሰዎች ላለመናገር መብት አላቸው፣ የሚሰጡት ማንኛውም ቃል ፍርድ ቤት በማስረጃነት ሊቀርብባቸው እንደሚችል መረዳት በሚችሉት ቋንቋ እንደተያዙ ወዲያውኑ ማስገንዘቢያ እንዲሰጣቸው መብት አላቸው። የተያዙ ሰዎች በአርባ ስምንት ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው።ይህም ጊዜ ሰዎቹ ከተያዙበት ቦታ ወደ ፍርድ ቤት ለመምጣት አግባብ ባለው ግምት የሚጠይቀውን ጊዜ አይጨምርም። ወዲያውኑ ፍርድ ቤት እንደቀረቡ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለመታሰር የሚያበቃ ምክንያት ያለ መሆኑ ተለይቶ እንዲገለጽላቸው መብት አላቸው። የያዛቸው የፖሊስ መኮንን ወይም የሕግ አስከባሪ በጊዜው ገደብ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተያዙበትን ምክንያት ካላስረዳ፣ ፍርድ ቤቱ የአካል ነፃነታቸውን እንዲያስከብርላቸው የመጠየቅ ሊጣስ የማይችል መብት አላቸው። ሆኖም ፍትሕ እንዳይጓደል ሁኔታው የሚጠይቅ ከሆነ ፍርድ ቤቱ የተያዘው ሰው በጥበቃ ስር እንዲቆይ ለማዘዝ ወይም ምርመራ ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ ሲጠየቅ አስፈላጊ በሆነ መጠን ብቻ ሊፈቅድ ይችላል። የሚያስፈልገውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ሲወስን ኃላፊ የሆኑት የሕግ አስከባሪ ባለሥልጣኖች ምርመራውን አጣርተው የተያዘው ሰው በተቻለ ፍጥነት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ያለውን መብት የሚያስከብር መሆን አለበት። የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም። በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም። የተያዙ ሰዎች በዋስ የመፈታት መብት አላቸው። ሆኖም በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ዋስትና ላለመቀበል ወይም በገደብ መፍታትን ጨምሮ በቂ የሆነ የዋስትና ማረጋገጫ እንዲቀርብ ለማዘዝ ይችላል። አንቀጽ 20 የተከሰሱ ሰዎች መብት የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ለሕዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመሰማት መብት አላቸው። ሆኖም የተከራካሪዎቹን የግል ሕይወት፣ የሕዝብን የሞራል ሁኔታና የሀገሪቱን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ብቻ ክርክሩ በዝግ ችሎት ሊሰማ ይችላል። ክሱ በቂ በሆነ ዝርዝር እንዲነገራቸው እና ክሱን በጽሑፍ የማግኘት መብት አላቸው። በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር፣ በምስክርነት እንዲቀርቡም ያለመገደድ መብት አላቸው። የቀረበባቸውን ማናቸውንም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ፣ ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዲሁም ምስክሮቻቸው ቀርበው እንዲሰሙላቸው የመጠየቅ መብት አላቸው። በመረጡት የሕግ ጠበቃ የመወከል ወይም ጠበቃ ለማቆም አቅም በማጣታቸው ፍትሕ ሊጓደል የሚችልበት ሁኔታ ሲያጋጥም ከመንግሥት ጠበቃ የማግኘት መብት አላቸው። ክርክሩ በሚታይበት ፍርድ ቤት በተሰጠባቸው ትእዛዝ ወይም ፍርድ ላይ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት አላቸው። የፍርዱ ሂደት በማይገባቸው ቋንቋ በሚካሄድበት ሁኔታ በመንግሥት ወጪ ክርክሩ እንዲተረጎምላቸው የመጠየቅ መብት አላቸው። አንቀጽ 21 በጥበቃ ስር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች መብት በጥበቃ ስር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቁ ሁኔታዎች የመያዝ መብት አላቸው። ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው፣ ከሃይማኖት አማካሪዎቻቸው፣ ከሐኪሞቻቸው እና ከሕግ አማካሪዎቻቸው ጋር ለመገናኘትና እንዲጎበኟቸውም ዕድል የማግኘት መብት አላቸው። አንቀጽ 22 የወንጀል ሕግ ወደኋላ ተመልሶ የማይሠራ ስለ መሆኑ ማንኛውም ሰው የወንጀል ክስ ሲቀርብበት የተከሰሰበት ድርጊት በተፈጸመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈጸሙ ወይም አለመፈጸሙ ወንጀል መሆኑ በሕግ የተደነገገ ካልሆነ በስተቀር ሊቀጣ አይችልም። እንዲሁም ወንጀሉን በፈጸመበት ጊዜ ለወንጀሉ ተፈጻሚ ከነበረው የቅጣት ጣሪያ በላይ የከበደ ቅጣት በማንኛውም ሰው ላይ አይወሰንም። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ቢኖርም፣ ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የወጣ ሕግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ከድርጊቱ በኋላ የወጣው ሕግ ተፈጻሚነት ይኖረዋል። አንቀጽ 23 በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት ስለመከልከሉ ማንኛውም ሰው በወንጀል ሕግና ሥርዓት መሰረት ተከሶ የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ጥፋተኛነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም። አንቀጽ 24 የክብርና የመልካም ስም መብት ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው። ማንኛውም ሰው የራሱን ስብዕና ከሌሎች ዜጎች መብቶች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በነፃ የማሳደግ መብት አለው። ማንኛውም ሰው በማንኛውም ስፍራ በሰብዓዊነቱ እውቅና የማግኘት መብት አለው። አንቀጽ 25 የእኩልነት መብት ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በሕግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል። በዚህ ረገድ በዘር፣ በብሔር፣ ብሔረሰብ፣ በቀለም፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው። አንቀጽ 26 የግል ሕይወት የመከበርና የመጠበቅ መብት ማንኛውም ሰው የግል ሕይወቱ፣ ግላዊነቱ፣ የመከበር መብት አለው። ይህ መብት መኖሪያ ቤቱ፣ ሰውነቱና ንብረቱ ከመመርመር እንዲሁም በግል ይዞታው ያለ ንብረት ከመያዝ የመጠበቅ መብት ያካትታል። ማንኛውም ሰው በግል የሚጽፋቸውና የሚጻጻፋቸው፣ በፖስታ የሚልካቸው ደብዳቤዎች፣ እንዲሁም በቴሌፎን፣ በቴሌኮሙኒኬሽንና በኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች የሚያደርጋቸው ግንኙነቶች አይደፈሩም። የመንግሥት ባለሥልጣኖች እነዚህን መብቶች የማክበርና የማስከበር ግዴታ አለባቸው።አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲፈጠሩና ብሔራዊ ደህንነትን፣ የሕዝብን ሰላም፣ ወንጀልን በመከላከል፣ ጤናንና የሕዝብን የሞራል ሁኔታ በመጠበቅ ወይም የሌሎችን መብትና ነፃነት በማስከበር ዓላማዎች ላይ በተመሰረቱ ዝርዝር ሕጎች መሰረት ካልሆነ በስተቀር የእነዚህ መብቶች አጠቃቀም ሊገደብ አይችልም። አንቀጽ 27 የሃይማኖት፣ የእምነትና የአመለካከት ነፃነት ማንኛውም ሰው የማሰብ፣ የሕሊና እና የሃይማኖት ነፃነት አለው። ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል፣ ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣ የመተግበር፣ የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል። በአንቀጽ 90 ንዑስ አንቀጽ 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሃይማኖት ተከታዮች ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋትና ለማደራጀት የሚያስችሏቸው የሃይማኖት ትምህርትና የአስተዳደር ተቋማት ማቋቋም ይችላሉ። ማንኛውንም ሰው የሚፈልገውን እምነት ለመያዝ ያለውን ነፃነት በኃይል ወይም በሌላ ሁኔታ በማስገደድ መገደብ ወይም መከልከል አይቻልም። ወላጆችና ሕጋዊ ሞግዚቶች በእምነታቸው መሰረት የሃይማኖታቸውንና የመልካም ሥነ ምግባር ትምህርት በመስጠት ልጆቻቸውን የማሳደግ መብት አላቸው። ሃይማኖትንና እምነትን የመግለጽ መብት ሊገደብ የሚችለው የሕዝብን ደህንነት፣ ሰላምን፣ ጤናን፣ ትምህርትን፣ የሕዝብን የሞራል ሁኔታ፣ የሌሎች ዜጎችን መሰረታዊ መብቶች፣ ነፃነቶች እና መንግሥት ከሃይማኖት ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚወጡ ሕጎች ይሆናል።         አንቀጽ 28 በስብዕና ላይ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና በሌሎች የኢትዮጵያ ሕጎች በሰው ልጅ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑትን ወንጀሎች፤ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር፣ ወይም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም።በሕግ አውጪው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግሥት አካል ውሳኔዎች በምሕረት ወይም በይቅርታ አይታለፉም። ከዚህ በላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሱትን ወንጀሎች ፈጽመው የሞት ቅጣት ለተፈረደባቸው ሰዎች ርዕሰ ብሔሩ ቅጣቱን ወደ ዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ሊያሻሽለው ይችላል። ክፍል ሁለት ዴሞክራሲያዊ መብቶች አንቀጽ 29 የአመለካከት እና ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ መብት ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል። ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ ነፃነት አለው። ይህ ነፃነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሀሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶችን ያካትታል። የፕሬስና የሌሎች መገናኛ ብዙኃን፣ እንዲሁም የሥነ ጥበብ ፈጠራ ነፃነት ተረጋግጧል።የፕሬስ ነፃነት በተለይ የሚከተሉትን መብቶች ያጠቃልላል፤ ሀ/ የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑን፣ ለ/ የሕዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት ዕድልን። ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሀሳቦችና አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ፕሬስ በተቋምነቱ የአሠራር ነፃነትና የተለያዩ አስተያየቶች የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጥበቃ ይደረግለታል። በመንግሥት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመግሥት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል። እነዚህ መብቶች ገደብ ሊጣልባቸው የሚችለው የሀሳብና መረጃ የማግኘት ነፃነት በአስተሳሰባዊ ይዘቱና ሊያስከትል በሚችለው አስተሳሰባዊ ውጤት ሊገታ አይገባውም በሚል መርህ ላይ ተመስርተው በሚወጡ ሕጎች ብቻ ይሆናል። የወጣቶችን ደህንነት፣ የሰውን ክብርና መልካም ስም ለመጠበቅ ሲባል ሕጋዊ ገደቦች በነዚህ መብቶች ላይ ሊደነገጉ ይችላሉ። የጦርነት ቅስቀሳዎች እንዲሁም ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎች በሕግ የሚከለከሉ ይሆናሉ። ማንኛውም ዜጋ ከላይ በተጠቀሱት መብቶች አጠቃቀም ረገድ የሚጣሉ ሕጋዊ ገደቦችን ጥሶ ከተገኘ በሕግ ተጠያቂ ሊሆን ይችላል። አንቀጽ 30 የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው። ከቤት ውጭ የሚደረጉ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች በሕዝብ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ ወይም በመካሄድ ላይ ያለ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ሰላምን፣ ዴማክራሲያዊ መብቶችንና የሕዝብን የሞራል ሁኔታ እንዳይጥሱ ለማስጠበቅ አግባብ ያላቸው ሥርዓቶች ሊደነገጉ ይችላሉ። ይህ መብት የወጣቶችን ደህንነት፣ የሰውን ክብርና መልካም ስምን ለመጠበቅ፣ የጦርነት ቅስቀሳዎች እንዲሁም ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎችን ለመከላከል ሲባል በሚወጡ ሕጎች መሰረት ተጠያቂ ከመሆን አያድንም። አንቀጽ 31 የመደራጀት መብት ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማኅበር የመደራጀት መብት አለው። ሆኖም አግባብ ያለውን ሕግ በመጣስ ወይም ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በሕገ ወጥ መንገድ ለማፍረስ የተመሰረቱ ወይም የተጠቀሱትን ተግባራት የሚያራምዱ ድርጅቶች የተከለከሉ ይሆናሉ። አንቀጽ 32 የመዘዋወር ነፃነት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት፣ እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነፃነት አለው። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገሩ የመመለስ መብት አለው። አንቀጽ 33 የዜግነት መብቶች ማንኛውም ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያዊት ከፈቃዱ/ከፈቃዷ ውጭ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን/ ዜግነትዋን ሊገፈፍ ወይም ልትገፈፍ አይችልም/አትችልም። ኢትዮጵያዊ/ ኢትዮጵያዊት ዜጋ ከሌላ ሀገር ዜጋ ጋር የሚፈጽመው/ የምትፈጽመው ጋብቻ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን/ ዜግነትዋን አያስቀርም። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የኢትዮጵያ ዜግነት በሕግ የሚያስገኘውን መብት፣ ጥበቃና ጥቅም የማግኘት መብት አለው። ማንኛውም ዜጋ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን የመለወጥ መብት አለው። ኢትዮጵያ ከአጸደቃቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር በማይቃረን መንገድ በሚወጣ ሕግ እና በሚደነገግ ሥርዓት መሰረት የኢትዮጵያ ዜግነት ለውጭ ሀገር ሰዎች ሊሰጥ ይችላል። አንቀጽ 34 የጋብቻ፣ የግልና የቤተሰብ መብቶች በሕግ ከተወሰነው የጋብቻ ዕድሜ የደረሱ ወንዶችና ሴቶች በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግባቸው የማግባትና ቤተሰብ የመመስረት መብት አላቸው። በጋብቻ አፈጻጸም፣ በጋብቻው ዘመንና በፍቺ ጊዜ እኩል መብት አላቸው። በፍቺም ጊዜ የልጆችን መብትና ጥቅም እንዲከበር የሚያደርጉ ድንጋጌዎች ይደነገጋሉ። ጋብቻ በተጋቢዎች ነፃና ሙሉ ፈቃድ ላይ ብቻ ይመሰረታል። ቤተሰብ የኅብረተሰብ የተፈጥሮ መሰረታዊ መነሻ ነው። ከኅብረተሰብና ከመንግሥት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው። በሕግ በተለይ በሚዘረዘረው መሰረት በሃይማኖት፣ በባሕል የሕግ ሥርዓቶች ላይ ተመስርተው ለሚፈጸሙ ጋብቻዎች እውቅና የሚሰጥ ሕግ ሊወጣ ይችላል። ይህ ሕገ-መንግሥት የግል እና የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ በተከራካሪዎች ፈቃድ በሃይማኖቶች ወይም በባሕሎች ሕጎች መሰረት መዳኘትን አይከለክልም። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። አንቀጽ 35 የሴቶች መብት ሴቶች ይሕ ሕገ-መንግሥት በአረጋገጣቸው መብቶችና ጥበቃዎች በመጠቀም ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው። ሴቶች በዚህ ሕገ-መንግሥት በተደነገገው መሰረት በጋብቻ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው። ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው። በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው። ሴቶች ከጎጂ ባሕል ተጽዕኖ የመላቀቅ መብታቸውን መንግሥት ማስከበር አለበት። ሴቶችን የሚጨቁኑ ወይም በአካላቸው ወይም በአዕምሮአቸው ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ሕጎች፣ ወጎችና ልማዶች የተከለከሉ ናቸው። ሀ/ ሴቶች የወሊድ ፈቃድ ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የማግኘት መብት አላቸው። የወሊድ ፈቃድ ርዝመት ሴቷ የምትሠራውን ሥራ ሁኔታ፣ የሴቷን ጤንነት፣ የሕፃኑንና የቤተሰቡን ደህንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሕግ ይወሰናል። ለ/ የወሊድ ፈቃድ በሕግ በሚወሰነው መሰረት ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የሚሰጥ የእርግዝና ፈቃድን ሊጨምር ይችላል። ሴቶች በብሔራዊ የልማት ፖሊሲዎች ዕቅድና በፕሮጀክቶች ዝግጅትና አፈጻጸም፣ በተለይ የሴቶችን ጥቅም በሚነኩ ፕሮጀክቶች ሀሳባቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲሰጡ የመጠየቅ መብት አላቸው። ሴቶች ንብረት የማፍራት፣ የማስተዳደር፣ የመቆጣጠር፣ የመጠቀምና የማስተላለፍ መብት አላቸው። በተለይ መሬትን በመጠቀም፣ በማስተላለፍ፣ በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው። እንዲሁም ውርስን በሚመለከት በእኩልነት የመታየት መብት አላቸው። ሴቶች የቅጥር፣ የሥራ ዕድገት፣ የእኩል ክፍያና ጡረታን የማስተላለፍ እኩል መብት አላቸው። ሴቶች በእርግዝናና በወሊድ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት ለመከላከልና ጤንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት፣ መረጃ እና አቅም የማግኘት መብት አላቸው። አንቀጽ 36 የሕፃናት መብት 1. ማንኛውም ሕፃን የሚከተሉት መብቶች አሉት፤ ሀ/ በሕይወት የመኖር፣ ለ/ ስምና ዜግነት የማግኘት፣ ሐ/ ወላጆቹን ወይም በሕግ የማሳደግ መብት ያላቸውን ሰዎች የማወቅና የእነሱንም እንክብካቤ የማግኘት፣ መ/ ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፣ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደህንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎች እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ፣ ሠ/ በትምህርት ቤቶች ወይም በሕፃናት ማሳደጊያ ተቋሞች ውስጥ በአካሉ ከሚፈጸም ወይም ከጭካኔና ኢሰብዓዊ ከሆነ ቅጣት ነፃ የመሆን። ሕፃናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰዱበት ጊዜ በመንግሥታዊ ወይም በግል የበጎ አድራጎት ተቋሞች፣ በፍርድ ቤቶች፣ በአስተዳደር ባለሥልጣኖች ወይም በሕግ አውጪ አካላት የሕፃናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰብ አለበት። ወጣት አጥፊዎች፣ በማረሚያ ወይም በመቋቋሚያ ተቋሞች የሚገኙ፣ በመንግሥት እርዳታ የሚያድጉ ወጣቶች፣ በመንግሥት ወይም በግል እጓለ ማውታን ተቋሞች ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ከአዋቂዎች ተለይተው መያዝ አለባቸው። ከጋብቻ ውጭ የተለወዱ ሕፃናት በጋብቻ ከተወለዱ ሕፃናት ጋር እኩል መብት አላቸው። መንግሥት ለእጓለ ማውታን ልዩ ጥበቃ ያደርግላቸዋል። በጉዲፈቻ የሚያድጉበትን ሥርዓት የሚያመቻቹና የሚያስፋፉ እንዲሁም ደህንነታቸውንና ትምህርታቸውን የሚያራምዱ ተቋሞች እንዲመሰረቱ ያበረታታል።   አንቀጽ 37 ፍትሕ የማግኘት መብት ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተውን ውሳኔ ወይም ፍርድ፤ ሀ/ ማንኛውም ማኅበር የአባላቱን የጋራ ወይም የግል ጥቅም በመወከል፣ ለ/ ማንኛውንም ቡድን ወይም ተመሳሳይ ጥቅም ያላቸውን ሰዎች የሚወክል ግለሰብ ወይም የቡድን አባል የመጠየቅና የማግኘት መብት አለው። አንቀጽ 38 የመምረጥና የመመረጥ መብት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም፣ በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሰረተ ልዩነት ሳይደረግበት የሚከተሉት መብቶች አሉት፤ ሀ/ በቀጥታ እና በነፃነት በመረጣቸው ተወካዮች አማካኝነት በሕዝብ ጉዳይ አስተዳደር የመሳተፍ፣ ለ/ ዕድሜው 18 ዓመት ሲሞላ በሕግ መሰረት የመምረጥ፣ ሐ/ በማናቸውም የመንግሥት ደረጃ በየጊዜው በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥና የመመረጥ። ምርጫው ሁሉ አቀፍ፣ በሁሉም እኩልነት ላይ የተመሰረተና በሚስጥር ድምፅ አሰጣጥ መራጩ ፈቃዱን በነፃነት የሚገልጽበት ዋስትና የሚሰጥ መሆን አለበት። በፖለቲካ ድርጅቶች፣ በሠራተኞች፣ በንግድ፣ በአሠሪዎችና በሙያ ማኀበራት ለተሳትፎ ድርጅቱ የሚጠይቀውን ጠቅላላና ልዩ የአባልነት መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ሰው በፍላጎቱ አባል የመሆን መብቱ የተከበረ መሆን አለበት። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 በተመለከቱት ድርጅቶች ውስጥ ለኃላፊነት ቦታዎች የሚካሄዱ ምርጫዎች ነፃና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ይፈጸማሉ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 ድንጋጌዎች የሕዝብን ጥቅም ሰፋ ባለ ሁኔታ የሚነኩ እስከሆነ ድረስ በሕዝባዊ ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ። አንቀጽ 39 የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች መብት ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ ያለ ገደብ የተጠበቀ ነው። ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ በቋንቋው የመናገር፣ የመጻፍ፣ ቋንቋውን የማሳደግ እና ባሕሉን የመግለጽ፣ የማዳበርና የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ መብት አለው። ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለው። ይህ መብት ብሔሩ፣ ብሔረሰቡ፣ ሕዝቡ በሰፈረበት መልክዓ ምድር ራሱን የሚያስተዳድርበት መንግሥታዊ ተቋማት የማቋቋም እንዲሁም በክልልና በፌዴራል አስተዳደሮች ውስጥ ሚዛናዊ ውክልና የማግኘት መብትን ያጠቃልላል። የብሔር፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መብት ከሥራ ላይ የሚውለው፤ ሀ/ የመገንጠል ጥያቄ በብሔር፣ በብሔረሰቡ ወይም በሕዝቡ የሕግ አውጪ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ የድምፅ ድጋፍ ተቀባይነት ማግኘቱ ሲረጋገጥ፣ ለ/ የፌዴራሉ መንግሥት የብሔር፣ የብሔረሰቡ ወይም የሕዝቡ ምክር ቤት ውሳኔ በደረሰው በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለጠያቂው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ ሲያደራጅ፣ ሐ/ የመገንጠሉ ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔው በአብላጫ ድምፅ ሲደገፍ፣ መ/ የፌዴራሉ መንግሥት መገንጠሉን ለመረጠው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ምክር ቤት ሥልጣኑን ሲያስረክብ፣ ሠ/ በሕግ በሚወሰነው መሰረት የንብረት ክፍፍል ሲደረግ ነው። በዚህ ሕገ-መንግሥት ውስጥ “ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ” ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለፀውን ባህርይ የሚያሳይ ማኅበረሰብ ነው። ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባሕል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልውና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የሥነ ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛው በተያያዘ መልክዓ ምድር የሚኖሩ ናቸው። አንቀጽ 40 የንብረት መብት ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት መሆኑ/መሆኗ ይከበርለታል/ ይከበርላታል። ይህ መብት የሕዝብን ጥቅም ለመጠበቅ በሌላ ሁኔታ በሕግ እስካልተወሰነ ድረስ ንብረት የመያዝና በንብረት የመጠቀም ወይም የሌሎችን ዜጎች መብቶች እስካልተቃረነ ድረስ ንብረትን የመሸጥ፣ የማውረስ ወይም በሌላ መንገድ የማስተላለፍ መብቶችን ያካትታል። ለዚህ አንቀጽ ዓላማ “የግል ንብረት” ማለት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይም ሕጋዊ ሰውነት በሕግ የተሰጣቸው ኢትዮጵያዊ ማኅበራት ወይም አግባብ በአላቸው ሁኔታዎች በሕግ በተለየ በጋራ የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የተፈቀደላቸው ማኅበረሰቦች በጉልበታቸው፣ በመፍጠር ችሎታቸው ወይም በካፒታላቸው ያፈሩት ተጨባጭ የሆነና የተጨባጭነት ጠባይ ሳይኖረው ዋጋ ያለው ውጤት ነው። የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ ነው። መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው። የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው። አፈጻጸሙን በተመለከተ ዝርዝር ሕግ ይወጣል። የኢትዮጵያ ዘላኖች ለግጦሽም ሆነ ለእርሻ የሚጠቀሙበት መሬት በነፃ የማግኘት፣ የመጠቀምና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት አላቸው። ዝርዝር አፈጻጸሙ በሕግ ይወሰናል። የመሬት ባለቤትነት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ መንግሥት ለግል ባለሀብቶች በሕግ በሚወሰን ክፍያ በመሬት የመጠቀም መብታቸውን ያስከብርላቸዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። ማንም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ፣ ወይም በገንዘቡ በመሬት ላይ ለሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል ሙሉ መብት አለው። ይህ መብት የመሸጥ፣ የመለወጥ፣ የማውረስ፣ የመሬት ተጠቃሚነቱ ሲቋረጥ ንብረቱን የማንሳት፣ ባለቤትነቱን የማዛወር ወይም የካሳ ክፍያ የመጠየቅ መብትን ያካትታል። ዝርዝር አፈጻጸሙ በሕግ ይወስናል። የግል ንብረት ባለቤትነት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መንግሥት ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ በመክፈል የግል ንብረትን ለመውሰድ ይችላል። አንቀጽ 41 የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የባሕል መብቶች ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ ውስጥ በማንኛውም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራትና ለመተዳደሪያው የመረጠውን ሥራ የመሥራት መብት አለው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ መተዳደሪያውን፣ ሥራውንና ሙያውን የመምረጥ መብት አለው። የኢትዮጵያ ዜጎች ሁሉ በመንግሥት ገንዘብ በሚካሄዱ ማኅበራዊ አገልግሎቶች በእኩልነት የመጠቀም መብት አላቸው። መንግሥት የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች የማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ሀብት ይመድባል። መንግሥት የአካል እና የአዕምሮ ጉዳተኞችን፣ አረጋዊያንንና ያለወላጅ ወይም ያለአሳዳጊ የቀሩ ሕፃናትን ለማቋቋምና ለመርዳት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም በፈቀደው ደረጃ እንክብካቤ ያደርጋል። መንግሥት ለሥራ አጦችና ለችግረኞች ሥራ ለመፍጠር የሚያስችል ፖሊሲ ይከተላል፤ እንዲሁም በሚያካሄደው የሥራ ዘርፍ ውስጥ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሥራ ፕሮግራሞችን ያወጣል፣ ፕሮጀክቶችን ያካሂዳል። መንግሥት ዜጎች ጠቃሚ ሥራ የማግኘት ዕድላቸው እየሰፋ እንዲሄድ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳል። ገበሬዎችና ዘላን ኢትዮጵያውያን በየጊዜው እየተሻሻለ የሚሄድ ኑሮ ለመኖር የሚያስችላቸውና ለምርት ካደረጉት አስተዋጽኦ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ተገቢ ዋጋ ለምርት ውጤቶቻቸው የማግኘት መብት አላቸው። መንግሥት የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የልማት ፖሊሲዎችን በሚተልምበት ጊዜ በዚህ ዓላማ መመራት አለበት። መንግሥት የባሕልና የታሪክ ቅርሶችን የመንከባከብና ለሥነጥበብና ለስፖርት መስፋፋት አስተዋፅኦ የማድረግ ኃላፊነት አለበት። አንቀጽ 42 የሠራተኞች መብት ሀ/ የፋብሪካና የአገልግሎት ሠራተኞች፣ ገበሬዎች፣ የእርሻ ሠራተኞች፣ ሌሎች የገጠር ሠራተኞች፣ ከተወሰነ የኃላፊነት ደረጃ በታች ያሉና የሥራ ጠባያቸው የሚፈቅድላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የሥራና የኢኮኖሚ ሁኔታዎችን ለማሻሻል በማኅበር የመደራጀት መብት አላቸው። ይህ መብት የሠራተኛ ማኅበራትንና ሌሎች ማኅበራትን የማደራጀት፣ ከአሠሪዎችና ጥቅማቸውን ከሚነኩ ሌሎች ድርጅቶች ጋር የመደራደር መብትን ያካትታል። ለ/ በንዑስ አንቀጽ (ሀ) የተመለከቱት የሠራተኛ ክፍሎች ሥራ ማቆምን ጨምሮ ቅሬታቸውን የማሰማት መብት አላቸው። ሐ/ በንዑስ አንቀጽ (ሀ) እና (ለ) መሰረት እውቅና ባገኙት መብቶች ለመጠቀም የሚችሉት የመንግሥት ሠራተኞች በሕግ ይወሰናሉ። መ/ ሴቶች ሠራተኞች ለተመሳሳይ ሥራ ተመሳሳይ ክፍያ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው። ሠራተኞች በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት ዕረፍት፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀኖች፣ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም ጤናማና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት አላቸው። እነዚህን መብቶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚወጡ ሕጎች በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት እውቅና ያገኙትን መብቶች ሳይቀንሱ የተጠቀሱት ዓይነት የሠራተኛ ማኅበራት ስለሚቋቋሙበትና የጋራ ድርድር ስለሚካሄድበት ሥርዓት ይደነግጋሉ። አንቀጽ 43 የልማት መብት የኢትዮጵያ ሕዝቦች በአጠቃላይም ሆነ በኢትዮጵያ ያሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች በተናጠል የኑሮ ሁኔታቸውን የማሻሻልና የማያቋርጥ እድገት የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው። ዜጎች በብሔራዊ ልማት የመሳተፍ በተለይም አባል የሆኑበትን ማኅበረሰብ የሚመለከቱት ፖሊሲዎችና ፕሮጀክቶች ላይ ሀሳባቸውን እንዲሰጡ የመጠየቅ መብት አላቸው። መንግሥት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገባቸው ስምምነቶችም ሆኑ የሚያደርጋቸው ግንኙነቶች የኢትዮጵያን የማያቋርጥ ዕድገት መብት የሚያስከብሩ መሆን አለባቸው። የልማት እንቅስቃሴ ዋና ዓላማ የዜጎችን እድገትና መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት ይሆናል። አንቀጽ 44 የአካባቢ ደህንነት መብት ሁሉም ሰዎች ንጹህና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት አላቸው። መንግሥት በሚያካሄዳቸው ፕሮግራሞች ምክንያት የተፈናቀሉ ወይም ኑሮአቸው የተነካባቸው ሰዎች ሁሉ በመንግሥት በቂ ዕርዳታ ወደ ሌላ አካባቢ መዘዋወርን ጨምሮ ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ወይም ሌላ አማራጭ ማካካሻ የማግኘት መብት አላቸው።           ምዕራፍ አራት የመንግሥት አወቃቀር አንቀጽ 45 ሥርዓተ መንግሥት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሥርዓተ መንግሥት ፓርላሜንታዊ ነው። አንቀጽ 46 የፌዴራል ክልሎች የፌዴራሉ መንግሥት በክልሎች የተዋቀረ ነው። ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት ነው። አንቀጽ 47 የፌዴራል መንግሥት አባላት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አባላት የሚከተሉት ናቸው፣ የትግራይ ክልል የአፋር ክልል የአማራ ክልል የኦሮሚያ ክልል የሱማሌ ክልል የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል የሐረሪ ሕዝብ ክልል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከቱት ክልሎች ውስጥ የተካተቱት ብሔሮች፣ ብሔሰቦች፣ ሕዝቦች በማንኛውም ጊዜ የየራሳቸውን ክልል የማቋቋም መብት አላቸው። የማንኛውም ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ የራሱን ክልል የመመስረት መብት ሥራ ላይ የሚውለው፤ ሀ/ የክልል መመስረት ጥያቄው በብሔሩ፣ በብሔረሰቡ ወይም በሕዝቡ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ማግኘቱ ሲረጋገጥና ጥያቄው በጽሑፍ ለክልሉ ምክር ቤት ሲቀርብ፤ ለ/ ጥያቄው የቀረበለት የክልል ምክር ቤት ጥያቄው በደረሰው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለጠየቀው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ ሲያደራጅ፤ ሐ/ ክልል የመመስረት ጥያቄው በብሔሩ፣ በብሔረሰቡ ወይም ሕዝቡ ሕዝበ ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ሲደገፍ፤ መ/ የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣኑን ለጠየቀው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ሲያስረክብ፤ ሠ/ በሕዝበ ውሳኔ የሚፈጠረው አዲስ ክልል ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልገው በቀጥታ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አባል ሲሆን ነው። 4. የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አባላት እኩል መብትና ሥልጣን አላቸው። አንቀጽ 48 የአከላለል ለውጦች የክልሎችን ወሰን በሚመለከት ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ክልሎች ስምምነት ይፈጸማል። የሚመለከታቸው ክልሎች መስማማት ካልቻሉ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የሕዝብን አሰፋፈርና ፍላጎት መሰረት በማድረግ ይወሰናል። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት የቀረበ ጉዳይ ከሁለት ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጥበታል። አንቀጽ 49 ርዕሰ ከተማ የፌዴራሉ መንግሥት ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን ይኖረዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነቱ ለፌዴራሉ መንግሥት ይሆናል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በዚህ ሕገ-መንግሥት በተደነገገው መሰረት በፌዴራሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይወከላሉ። የኦሮሚያ ክልል፣ የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። ምዕራፍ አምስት የሥልጣን አወቃቀር እና ክፍፍል አንቀጽ 50 ስለ ሥልጣን አካላት አወቃቀር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በፌዴራል መንግሥትና በክልሎች የተዋቀረ ነው። የፌዴራሉ መንግሥትና ክልሎች የሕግ አውጪነት፣ የሕግ አስፈጻሚነትና የዳኝነት ሥልጣን አላቸው። የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የፌዴራሉ መንግሥት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። ተጠሪነቱም ለሀገሪቱ ሕዝብ ነው። የክልል ከፍተኛ የሥልጣን አካል የክልሉ ምክር ቤት ነው፤ ተጠሪነቱም ለወከለው ክልል ሕዝብ ነው። ክልሎች፤ በክልልነትና ክልሎች አስፈላጊ ሆነው በሚያገኙአቸው የአስተዳደር እርከኖች ይዋቀራሉ። ሕዝቡ በዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች በቀጥታ ይሳተፍ ዘንድ ለዝቅተኛ እርከኖች በቂ ሥልጣን ይሰጣል። የክልል ምክር ቤት በክልሉ ሥልጣን ስር በሆኑ ጉዳዮች የክልሉ የሕግ አውጪ አካል ነው። ይህንን ሕገ-መንግሥት መሰረት በማድረግ የክልሉን ሕገ-መንግሥት ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፣ ያሻሽላል። የክልል መስተዳድር የክልሉ ከፍተኛ የሕግ አስፈጻሚ አካል ነው። የክልል የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ነው። የፌዴራሉ መንግሥትና የክልሎች ሥልጣን በዚህ ሕገ-መንግሥት ተወስኗል። ለፌዴራሉ መንግሥት የተሰጠው ሥልጣን በክልሎች መከበር አለበት። ለክልሎች የተሰጠው ሥልጣን በፌዴራሉ መንግሥት መከበር አለበት። የፌዴራል መንግሥት በዚህ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 51 ከተሰጡት ሥልጣን እና ተግባሮች እንዳስፈላጊነቱ ለክልሎች በውክልና ሊሰጥ ይችላል። አንቀጽ 51 የፌዴራል መንግሥት ሥልጣንና ተግባር ሕገ-መንግሥቱን ይጠብቃል፤ ይከላከላል። የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የልማት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ዕቅድ ያወጣል፤ ያስፈጽማል። የጤና፣ የትምህርት፣ የባሕልና ታሪካዊ ቅርስ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሀገር አቀፍ መመዘኛዎችና መሰረታዊ የፖሊሲ መለኪያዎችን ያወጣል፤ ያስፈጽማል። የሀገሪቱን የፋይናንስ፣ የገንዘብ፣ የውጭ ኢንቨስትመንት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ያወጣል፤ ያስፈጽማል። የመሬት፣ የተፈጥሮ ሀብትና የታሪክ ቅርሶች አጠቃቀምና ጥበቃን በተመለከተ ሕግ ያወጣል። የሀገርና የሕዝብ የመከላከያና የደህንነት እንዲሁም የፌዴራል መንግሥት የፖሊስ ኃይል ያደራጃል፤ ይመራል። ብሔራዊ ባንክን ያስተዳድራል፤ ገንዘብ ያትማል፤ ይበደራል፤ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ልውውጥን ይቆጣጠራል። ክልሎች ከውስጥ ምንጮች ስለሚበደሩበት ሁኔታ ሕግና መመሪያ ያወጣል። የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን ይወስናል፤ ፖሊሲውንም ያስፈጽማል፤ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ይዋዋላል፤ ያጸደቃል። የአየር፣ የባቡር፣ የባሕር መጓጓዣ፤ የፖስታና የቴሌካሙኒኬሽን አገልግሎቶች እንደዚሁም ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ክልሎችን የሚያገናኙ አውራ መንገዶችን ያስፋፋል፤ ያስተዳድራል፤ ይቆጣጠራል። ለፌዴራሉ መንግሥት በተሰጡት የገቢ ምንጮች ክልል ግብርና ቀረጥ ይጥላል፤ ያስተዳድራል፤ የፌዴራል መንግሥት በጀት ያረቃል፤ ያጸድቃል፤ ያስተዳድራል። ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ክልሎችን የሚያስተሳስሩ ወይም ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ወንዞችና ሀይቆችን አጠቃቀም ይወስናል፤ ያስተዳድራል። በክልሎች መካከል የሚደረግን የንግድ ግንኙነትና የውጭ ንግድን ይመራል፤ ይቆጣጠራል። በፌዴራል መንግሥት ገንዘብ የተቋቋሙ አንድ ወይም ከአንድ ክልል በላይ የሚሸፍኑ የአገልግሎት ተቋሞችን ያስተዳድራል፤ ያስፋፋል። ከክልል አቅም በላይ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ሲያጋጥም በክልሉ መስተዳድር ጥያቄ መሰረት የሀገሪቱን የመከላከያ ኃይል ያሰማራል። በዚህ ሕገ-መንግሥት የተረጋገጡትን የፖለቲካ መብቶች ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን እንዲሁም ምርጫን በሚመለከት ሕጎች ያወጣል። በሀገሪቱ በአጠቃላይም ሆነ በተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፤ አዋጁን ያነሳል። የዜግነት ጥያቄ ይወስናል። የኢምግሬሽንና የፓስፖርት፤ ወደ ሀገር የመግቢያና የመውጫ ጉዳዮችን፤ ስለስደተኞችና ስለ ፖለቲካ ጥገኝነት ይወስናል፤ ይመራል። የፈጠራና የድርሰት መብቶችን ይፈቅዳል፤ ይጠብቃል። አንድ ወጥ የመለኪያ ደረጃዎችና የጊዜ ቀመር ያወጣል። 21. የጦር መሣሪያ ስለመያዝ ሕግ ያወጣል። አንቀጽ 52 የክልል ሥልጣንና ተግባር በሕገ-መንግሥቱ ለፌዴራሉ መንግሥት በተለይ ወይም ለፌዴራሉ መንግሥትና ለክልሎች በጋራ በግልጽ ያልተሰጠ ሥልጣን የክልል ሥልጣን ይሆናል። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የክልሎች ሥልጣንና ተግባር የሚከተሉትን ያጠቃልላል፤ ሀ/ ራስን በራስ ማስተዳደርን ዓላማ ያደረገ ክልላዊ መስተዳድር ያዋቅራል፤ የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ይገነባል፤ ይህን ሕገ-መንግሥት ይጠብቃል፤ ይከላከላል፤ ለ/ የክልል ሕገ-መንግሥትና ሌሎች ሕጎችን ያወጣል፤ ያስፈጽማል፤ ሐ/ የክልሉን የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የልማት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ዕቅድ ያወጣል ያስፈጽማል፤ መ/ የፌዴራሉ መንግሥት በሚያወጣው ሕግ መሰረት መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን ያስተዳድራል፤ ሠ/ ለክልሉ በተወሰነው የገቢ ምንጭ ክልል ግብርና ታክስ ይጥላል፤ ይሰበስባል የክልሉን በጀት ያወጣል፤ ያስፈጽማል፤ ረ/ የክልሉን መስተዳድር ሠራተኞች አስተዳደርና የሥራ ሁኔታዎች በተመለከተ ሕግ ያወጣል፤ ያስፈጽማል፤ ሆኖም ለአንድ የሥራ መደብ የሚያስፈልጉ የትምህርት፣ የሥልጠናና የልምድ መመዘኛዎች ከአጠቃላይ የሀገሪቱ መመዘኛዎች ጋር የተቀራረቡ መሆናቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት ይኖርበታል። ሰ/ የክልሉን የፖሊስ ኃይል ያደራጃል፣ ይመራል፣ የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃል። ምዕራፍ ስድስት ስለፌዴራሉ መንግሥት ምክር ቤቶች አንቀጽ 53 የፌዴራል መንግሥት ምክር ቤቶች የፌዴራሉ መንግሥት ሁለት ምክር ቤቶች ይኖሩታል፤ እነዚህም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ናቸው። ክፍል አንድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንቀጽ 54 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፤ ሁሉ አቀፍ፣ ነፃ፣ ቀጥተኛ፣ ትክክለኛ በሆነና ድምጽ በሚስጥር በሚሰጥበት ሥርዓት በየአምስት ዓመቱ በሕዝብ ይመረጣሉ። የምክር ቤቱ አባላት በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፊ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ። የተለየ ውክልና ያስፈልጋቸዋል ተብሎ የታመነባቸው አናሳ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በምርጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ይሆናሉ። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። የምክር ቤቱ አባላት ቁጥር የሕዝብ ብዛትንና በልዩ ትኩረት ውክልና የሚሰጣቸው አናሳ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ቁጥር መሰረት በማድረግ ከ550 የማይበልጥ ሆኖ ከዚህ ውስጥ አናሳ ብሔረሰቦች ከ20 የማያንስ መቀመጫ ይኖራቸዋል።ዝርዝሩ በሕግ ይደነገጋል። የምክር ቤቱ አባላት የመላው ሕዝብ ተወካዮች ናቸው። ተገዥነታቸውም፤ ሀ/ ለሕገ-መንግሥቱ፤ ለ/ ለሕዝቡ፤ እና ሐ/ ለሕሊናቸው ብቻ ይሆናል። ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል በምክር ቤቱ ውስጥ በሚሰጠው ድምፅ ወይም አስተያየት ምክንያት አይከሰስም። አስተዳደራዊ እርምጃም አይወሰድበትም። ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፤ በወንጀልም አይከሰስም። ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል የመረጠው ሕዝብ አመኔታ ባጣበት ጊዜ በሕግ መሰረት ከምክር ቤት አባልነቱ ይወገዳል። አንቀጽ 55 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ሕገ-መንግሥት መሰረት ለፌዴራሉ መንግሥት በተሰጠው የሥልጣን ክልል ሕጎችን ያወጣል። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ሕግ ያወጣል፤ ሀ/ የመሬትና የተፈጥሮ ሀብት፤ እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ ወይም ከአንድ ክልል በላይ የሚያስተሳስሩ ወንዞችና ሀይቆች አጠቃቀምን በተመለከተ፤ ለ/ በክልሎች መካከል የሚኖረውን የንግድ ልውውጥ፤ እንዲሁም የውጭ ንግድ ግንኙነትን በተመለከተ፤ ሐ/ የአየር፣ የባቡርና የባሕር መጓጓዣ፤ የፖስታና የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን እንዲሁም ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ክልሎችን የሚያገናኙ አውራ መንገዶችን በተመለከተ፤ መ/ በዚህ ሕገ-መንግሥት የተደነገጉትን የፖለቲካ መብቶች አፈጻጸምን እንዲሁም ምርጫን በተመለከተ፤ ሠ/ የዜግነት መብትን፤ የኢምግሬሽን፤ የፓስፖርትን፤ ወደ ሀገር የመግቢያና የመውጫ ጉዳዮችን እንዲሁም የስደተኞችና የፖለቲካ ጥገኝነት ጉዳዮችን በተመለከተ፤ ረ/ አንድ ወጥ የመጠን መለኪያ ደረጃና የጊዜ ቀመርን በተመለከተ፤ ሰ/ የፈጠራና የሥነጥበብ መብቶችን በተመለከተ፤ ሸ/ የጦር መሣሪያ መያዝን በተመለከተ። የሠራተኛ ጉዳይ ሕግ ያወጣል። የንግድ ሕግ (ኮድ) ያወጣል። የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ያወጣል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ክልሎች በፌዴራሉ መንግሥት የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በግልጽ ባልተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ሕግ የማውጣት ሥልጣን ይኖራቸዋል። አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ሲባል በፌዴራል መንግሥት ሕግ እንዲወጣላቸው የሚያስገድዱ ለመሆናቸው በፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የታመነባቸው የፍትሐብሔር ሕጎችን ያወጣል። የፌዴራል መንግሥት፤ የሀገርና የሕዝብ መከላከያ፤ የደህንነትና የፖሊስ ኃይል አደረጃጀትን ይወስናል። በሥራ አፈጻጸማቸው ረገድ የሚታዩ መሠረታዊ የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶችና የሀገርን ደህንነት የሚነኩ ጉዳዮች ሲከሰቱ ያጣራል፤ አስፈላጊ እርምጃዎች እንዲወስዱ ያደርጋል። በአንቀጽ 93 በተመለከተው መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፤ የሕግ አስፈጻሚው የሚያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተመልክቶ ይወስናል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያቀርብለት የሕግ ረቂቅ መሰረት የጦርነት አዋጅ ያውጃል። የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ የልማት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን፤ የፋይናንስና የገንዘብ ፖሊሲን ያጸድቃል፤ ገንዘብን፤ የብሔራዊ ባንክ አስተዳደርን፤ የውጭ ምንዛሪንና ልውውጥን በተመለከተ ዝርዝር ሕግ ያወጣል። ለፌዴራል መንግሥት በተከለለው የገቢ ምንጭ ክልል ግብርና ታክስ ይጥላል። የፌዴራል መንግሥት በጀት ያጸድቃል። የሕግ አስፈጻሚው አካል የሚዋዋላቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ያጸድቃል። የፌዴራል መንግሥት ፍርድ ቤት ዳኞችን፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን፤ የኮሚሽነሮችን፤ የዋናው ኦዲተርን እንዲሁም የሌሎች ሹመታቸው በምክር ቤቱ መጽደቅ ያለበትን ባለሥልጣኖች ሹመት ያጸድቃል። የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያቋቁማል፤ ሥልጣንና ተግባሩን በሕግ ይወስናል። የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋምን ያቋቁማል፤ ተቋሙን የሚመሩ አባላትን ይመርጣል፤ ይሰይማል። ሥልጣንና ተግባሩን በሕግ ይወስናል። በማንኛውም ክልል ሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱና ክልሉ ድርጊቱን ማቆም ሳይችል ሲቀር፤ በራሱ አነሳሽነትና ያለ ክልሉ ፈቃድ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤትና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ጥያቄ ያቀርባል፤ በተደረሰበት ውሳኔ መሰረት ለክልሉ ምክር ቤት መመሪያ ይሰጣል። ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎች የፌዴራሉ መንግሥት ባለሥልጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የሕግ አስፈጻሚውን አካል አሠራር የመመርመር ሥልጣን አለው። ለሕግ አስፈጻሚው አካል በተሰጠ ማንኛውም ሥልጣን ላይ የምክር ቤቱ አባላት በአንድ ሦስተኛ ድምጽ ሲጠይቁ ምክር ቤቱ ይወያያል። ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ የመመካከርና አስፈላጊ መስሎ የታየውን እርምጃ የመውሰድ ሥልጣን አለው። ምክር ቤቱን የሚመሩ አፈጉባዔና ምክትል አፈጉባዔ ይመርጣል፤ ለምክር ቤቱ ሥራ የሚያስፈልጉትን ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ያዋቅራል። አንቀጽ 56 የፖለቲካ ሥልጣን በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጣምራ ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል ያደራጃል/ያደራጃሉ፤ ይመራል/ ይመራሉ። አንቀጽ 57 ስለሕግ አጸዳደቅ ምክር ቤቱ መክሮ የተስማማበት ሕግ ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ለፊርማ ይቀርባል፤ ፕሬዚዳንቱ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ይፈርማል። ፕሬዚዳንቱ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ካልፈረመ ሕጉ በሥራ ላይ ይውላል። አንቀጽ 58 የምክር ቤቱ ስብሰባና የሥራ ዘመን ከምክር ቤቱ አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይኖራል። የምክር ቤቱ የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ከሰኞ እስከ ሰኔ ሠላሳ ነው፤ በመካከሉም ምክር ቤቱ በሚወስነው ጊዜ የአንድ ወር ዕረፍት ይኖረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚመረጠው ለአምስት ዓመታት ነው፤ የሥራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ ተካሂዶ ይጠናቀቃል። ምክር ቤቱ ዕረፍት ላይ በሚሆንበት ጊዜ የምክር ቤቱ አፈጉባዔ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ከምክር ቤቱ አባላት ከግማሽ በላይ ስብሰባ እንዲጠራ ከጠየቁ አፈጉባዔው ስብሰባ የመጥራት ግዴታ አለበት። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባዎች በግልጽ ይካሄዳሉ፤ ሆኖም በምክር ቤቱ አባላት ወይም በፌዴራል የሕግ አስፈጻሚ አካል በዝግ ስብሰባ እንዲደረግ ከተጠየቀና ከምክር ቤቱ አባላት ከግማሽ በላይ ከደገፉት ዝግ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል። አንቀጽ 59 የምክር ቤቱ ውሳኔዎችና የሥነ-ሥርዓት ደንቦች በዚህ ሕገ-መንግሥት በግልጽ በተለይ ካልተደነገገ በስተቀር ማናቸውም ውሳኔዎች የሚተላለፉት በምክር ቤቱ አባላት የአብላጫ ድምጽ ነው። ምክር ቤቱ ስለ አሠራሩና ስለ ሕግ አወጣጡ ሂደት ደንቦችን ያወጣል። አንቀጽ 60 ስለምክር ቤቱ መበተን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ዘመኑ ከማለቁ በፊት አዲስ ምርጫ ለማካሄድ በምክር ቤቱ ፈቃድ ምክር ቤቱ እንዲበተን ለማድረግ ይችላል። በጣምራ የመንግሥት ሥልጣን የያዙ የፖለቲካ ድርጅቶች ጣምራነታቸው ፈርሶ በምክር ቤቱ የነበራቸውን አብላጫነት ያጡ እንደሆነ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተበትኖ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሌላ ጣምራ መንግሥት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለመመስረት እንዲቻል ፕሬዚዳንቱ የፖለቲካ ድርጅቶችን ይጋብዛል። የፖለቲካ ድርጅቶቹ አዲስ መንግሥት ለመፍጠር ወይም የነበረውን ጣምራነት ለመቀጠል ካልቻሉ ምክር ቤቱ ተበትኖ አዲስ ምርጫ ይደረጋል። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ወይም 2 መሰረት ምክር ቤቱ የተበተነ እንደሆነ ከስድስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አዲስ ምርጫ መደረግ አለበት። ምርጫው በተጠናቀቀ በሠላሳ ቀናት ውስጥ አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራውን ይጀምራል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተበተነ በኋላ ሀገሪቱን የሚመራው ሥልጣን ይዞ የነበረው የፖለቲካ ድርጅት ወይም የፖለቲካ ድርጅቶች ጣምራ የዕለት ተዕለት የመንግሥት ሥራ ከማከናወንና ምርጫ ከማካሄድ በስተቀር አዲስ አዋጆችን፣ ደንቦችንና ድንጋጌዎችን ማውጣት ወይም ነባር ሕጎችን መሻርና ማሻሻል አይችልም።           ክፍል ሁለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አንቀጽ 61 የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በፌዴራሉ መንግሥት አባል ክልሎች የሚገኙት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የሚልኩዋቸው አባላት የሚወከሉበት ምክር ቤት ነው። እያንዳንዱ ብሔር፣ ብሔረሰብ ሕዝብ ቢያንስ አንድ ተወካይ ይኖረዋል፤ በተጨማሪም የብሔር ወይም ብሔረሰቡ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ አንድ ተጨማሪ ወኪል ይኖረዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በክልል ምክር ቤቶች ይመረጣሉ፤ የክልል ምክር ቤቶች በራሳቸው ወይም በቀጥታ በሕዝብ እንዲመረጡ በማድረግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል እንዲወከል ያደርጋሉ። አንቀጽ 62 የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር ምክር ቤቱ ሕገ-መንግሥቱን የመተርጎም ሥልጣን ይኖረዋል። የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔን ያደራጃል። የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን አስከ መገንጠል መብትን በተመለከተ በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ በሕገ-መንግሥቱ መሰረት ይወስናል። በሕገ-መንግሥቱ የተደነገገው የሕዝቦች እኩልነትና በሕዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር ያደርጋል። ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር በጣምራ የተሰጡትን ሥልጣኖች ያከናውናል። በክልሎች መካከል ለሚነሱ አለመግባባቶች መፍትሄ ይፈልጋል። የክልሎችና የፌዴራሉ መንግሥት የጋራ ተብለው የተመደቡ ገቢዎች በሁለቱ መካከል የሚከፋፈሉበትን፤ እንዲሁም የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሎች ድጎማ የሚሰጥበትን ቀመር ይወስናል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ የፍትሐብሔር ጉዳዮችን ይለያል። ማንኛውም ክልል ይህን ሕገ-መንግሥት በመጣስ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፌዴራሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ያዛል። የምክር ቤቱን የተለያዩ ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ያቋቁማል። ምክር ቤቱ የራሱን አፈጉባዔና ምክትል አፈጉባዔ ይመርጣል፤ የራሱን የሥራ አፈጻጸምና የውስጥ አስተዳደር ደንብ ያወጣል። አንቀጽ 63 የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት መብት ማንኛውም የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት አባል በማናቸውም የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ በሚሰጠው አስተያየት ወይም ድምጽ ምክንያት አይከሰስም፤ አስተዳደራዊ እርምጃም አይወሰድበትም። ማንኛውም የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፤ በወንጀልም አይከሰስም። አንቀጽ 64 ውሳኔዎችና የሥነ ሥርዓት ደንቦች የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ምልዓተ ጉባዔ የሚኖረው ከአባላቱ ሁለት ሦስተኛው የተገኙ እንደሆነ ነው። ማናቸውም ውሳኔ የሚያልፈው ስብሰባ ላይ ከተገኙት የምክር ቤቱ አባላት ከግማሽ በላይ ድምፅ ሲደገፍ ብቻ ነው። አባላት ድምፅ መስጠት የሚችሉት በአካል ሲገኙ ብቻ ነው። አንቀጽ 65 ስለ በጀት የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በጀቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ያስወስናል። አንቀጽ 66 የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ሥልጣን የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የምክር ቤቱን ስብሰባዎች ይመራል። ምክር ቤቱን በመወከል ጠቅላላ የአስተዳደር ሥራዎችን ይመራል። ምክር ቤቱ በአባሎቹ ላይ የወሰነውን የዲስፕሊን እርምጃ ያስፈጽማል። አንቀጽ 67 ስብሰባና የሥራ ዘመን 1. የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ ይሰበሰባል። 2. የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል። አንቀጽ 68 በሁለቱም ምክር ቤቶች አባል መሆን የማይቻል ስለመሆኑ ማንኛውም ሰው በአንድ ጊዜ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት አባል ሊሆን አይችልም። ምዕራፍ ሰባት ስለ ሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት አንቀጽ 69 ስለ ፕሬዚዳንቱ ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ርዕሰ ብሔር ነው። አንቀጽ 70 የፕሬዚዳንቱ አሰያየም ለፕሬዚዳንትነት እጩ የማቅረብ ሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። የቀረበው እጩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ከተደገፈ ፕሬዚዳንት ይሆናል። የምክር ቤት አባል ፕሬዚዳንት ሆኖ ከተመረጠ የተወከለበትን ምክር ቤት ወንበር ይለቃል። የፕሬዚዳንቱ የሥራ ዘመን ስድስት ዓመት ይሆናል። አንድ ሰው ከሁለት ጊዜ በላይ ለፕሬዚዳንትነት ሊመረጥ አይችልም። የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ምርጫ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ከጸደቀ በኋላ ሥራውን ከመጀመሩ በፊት የጋራ ስብሰባው በሚወስነው ጊዜ ስብሰባው ፊት ለሕገመንግሥቱና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ያለውን ታማኝነት በሚቀጥሉት ቃላት ይገልጻል። “እኔ …………. በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በመሆን ሥራዬን ስጀምር የተጣለብኝን ከፍተኛ ኃላፊነት በታማኝነት ለመፈጸም ቃል እገባለሁ።” አንቀጽ 71 የፕሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባር የሕዝብ ተወካዮችን ምክር ቤትና የፌዴሬሸኑን ምክር ቤት ዓመታዊ የጋራ ስብሰባ ይከፍታል። በዚህ ሕገ-መንግሥት መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቃቸውን ሕጎችና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በነጋሪት ጋዜጣ ያውጃል።   ሀገሪቷን በውጭ ሀገሮች የሚወክሉትን አምባሳደሮችና ሌሎች መልዕክተኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ይሾማል። የውጭ ሀገር አምባሳደሮችንና የልዩ መልዕክተኞችን የሹመት ደብዳቤ ይቀበላል። በሕግ መሰረት ኒሻኖችና ሽልማቶችን ይሰጣል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕግ በተወሰነው መሰረት ከፍተኛ የውትድርና ማዕረጎችን ይሰጣል። በሕግ መሰረት ይቅርታ ያደርጋል። ምዕራፍ ስምንት የሕግ አስፈጻሚ አካል አንቀጽ 72 ስለ አስፈጻሚነት ሥልጣን የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የአስፈጻሚነት ሥልጣን የተሰጠው ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪዎች ናቸው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት በመንግሥት ተግባራቸው በጋራ ለሚሰጡት ውሳኔ የጋራ ኃላፊነት አለባቸው። በዚህ ሕገ-መንግሥት መሰረት በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ዘመን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን ነው። አንቀጽ 73 የጠቅላይ ሚኒስትሩ አሰያየም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል ይመረጣል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው የፖለቲካ ድርጅት ወይም ያገኙት የፖለቲካ ድርጅቶች የመንግሥት ሥልጣን ይረከባል/ይረከባሉ። አንቀጽ 74 የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣንና ተግባር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱ ርዕሰ መስተዳድር፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባሎችን ከሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት ወይም ለሥራው ብቃት ካላቸው ሌሎች ግለሰቦች መካከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት አቅርቦ ሹመታቸውን ያስጸድቃል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያወጣቸው ሕጎች፣ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል። የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይወክላል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣቸውን ፖሊሲዎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና ውሳኔዎች ተፈጻሚነት ይከታተላል። የሀገሪቱን የውጭ ፖሊሲ በበላይነት ያስፈጽማል። ኮሚሽነሮችን፣ የማዕከላዊ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን እና ዋና ኦዲተርን መርጦ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሹመታቸውን ያስጸድቃል። የመስተዳድሩን ሥራ አፈጻጸምና ብቃት ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊ የሆኑ የእርምት እርምጃዎችን ይወስዳል። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እና 7 ከተዘረዘሩት ውጭ የሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት የሲቪል ሹመቶችን ይሰጣል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው ሕግ ወይም በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት ኒሻኖችንና ሽልማቶችን ለፕሬዝዳንቱ አቅርቦ ያሰጣል። ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ፣ በመንግሥት ስለተከናወኑ ተግባራትና ስለወደፊት ዕቅዶች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየወቅቱ ሪፖርት ያቀርባል። በዚህ ሕገ-መንግሥትና በሌሎች ሕጎች የተሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል። 13. ሕገ-መንግሥቱን ያከብራል፤ ያስከብራል። አንቀጽ 75 ስለ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሀ/ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተለይተው የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል፣ ለ/ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖርበት ጊዜ ተክቶት ይሠራል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል። አንቀጽ 76 የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚኒስትሮች ምክር ቤት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ማኒስትር፣ ሚኒስትሮችና በሕግ በሚወሰን መሰረት ሌሎች አባሎች የሚገኙበት ምክር ቤት ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለሚወስነው ውሳኔ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ ነው። አንቀጽ 77 የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ ሕጎችና የተሰጡ ውሳኔዎች በሥራ መተርጎማቸውን ያረጋግጣል፣ መመሪያዎችን ይሰጣል። የሚኒስቴሮችንና በቀጥታ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆኑ ሌሎች የመንግሥት አካላትን አደረጃጀት ይወስናል፣ ሥራቸውን ያስተባብራል፣ ይመራል። የፌዴራሉን መንግሥት ዓመታዊ በጀት ያዘጋጃል፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል። የገንዘብና የፋይናንስ ፖሊሲን ተግባራዊነት ያረጋግጣል፣ ብሔራዊ ባንክን ያስተዳድራል፣ ገንዘብ ያትማል፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ይበደራል፣ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ልውውጥን ይቆጣጠራል። የፈጠራና የኪነ ጥበብ መብቶችን ያስጠብቃል። የኢኮኖሚያዊ፣ የማኅበራዊና የልማት ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎችን ይነድፋል፣ ያስፈጽማል። አንድ ወጥ የመለኪያ ደረጃዎችንና የጊዜ ቀመር ያወጣል። የሀገሪቱን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ያወጣል፣ ያስፈጽማል። ሕግና ሥርዓት መከበሩን ያረጋግጣል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፤ በዚህ ሕገ-መንግሥት በተደነገገው የጊዜ ወሰን ውስጥ፣ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስጸድቃል። የጦርነት ጉዳዮችን ጨምሮ በማናቸውም ጉዳዮች ላይ የሕግ ረቂቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚሰጠው ሥልጣን መሰረት ደንቦችን ያወጣል።         ምዕራፍ ዘጠኝ ስለፍርድ ቤቶች አወቃቀርና ሥልጣን አንቀጽ 78 ስለ ነፃ የዳኝነት አካል ነፃ የዳኝነት አካል በዚህ ሕገ-መንግሥት ተቋቁሟል። የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የዳኝነት አካል የፌዳራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይሆናል።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲደራጅ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ሊወስን ይችላል። ጉዳዩ በዚህ አኳኋን ካልተወሰነ የፌዴራል ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ለክልል ፍርድ ቤቶች ተሰጥቷል። ክልሎች፤ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች፣ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችና የክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ይኖራቸዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። የዳኝነት ሥልጣንን ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ወይም በሕግ የመዳኘት ሥልጣን ከተሰጠው ተቋም ውጭ የሚያደርግ፣ በሕግ የተደነገገን የዳኝነት ሥርዓት የማይከተል ልዩ ፍርድ ቤት ወይም ጊዜያዊ ፍርድ ቤት አይቋቋምም። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የክልል ምክር ቤቶች በአንቀጽ 34 ንዑስ አንቀጽ 5 መሰረት የሃይማኖትና የባሕል ፍርድ ቤቶችን ሊያቋቁሙ ወይም እውቅና ሊሰጡ ይችላሉ። ይህ ሕገ-መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በመንግሥት እውቅና አግኝተው ሲሰራባቸው የነበሩ የሃይማኖቶችና የባሕል ፍርድ ቤቶች በዚህ ሕገ-መንግሥት መሰረት እውቅና አግኝተው ይደራጃሉ። አንቀጽ 79 የዳኝነት ሥልጣን በፌዴራልም ሆነ በክልል የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ነው። በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተጽዕኖ ነፃ ነው። ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነፃነት ያከናውናሉ። ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም። ማንኛውም ዳኛ ከዚህ በታች በተመለከቱት ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር በሕግ ከተወሰነው የጡረታ ዕድሜ ከመድረሱ በፊት ከፈቃዱ ውጭ ከዳኝነት ሥራው አይነሳም፤ ሀ/ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በዳኞች የዲሲፕሊን ሕግ መሠረት ጥፋት ፈጽሟል ወይም ጉልህ የሆነ የሥራ ችሎታና ቅልጥፍና አንሶታል ብሎ ሲወስን፣ ወይም ለ/ በህመም ምክንያት ተግባሩን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን አይችልም ብሎ ሲወስን እና ሐ/ የጉባዔው ውሳኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤቶች ከግማሽ በላይ ድምፅ ሲጸድቅ። የማንኛውም ዳኛ የጡረታ መውጫ ጊዜ አይራዘምም። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራሉን መንግሥት የዳኝነት አካል የሚያስተዳድርበትን በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስወስናል፣ ሲፈቀድም በጀቱን ያስተዳድራል። የክልል የዳኝነት አካሎች በጀት በየክልሉ ምክር ቤቶች ይመደባል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራሉን የከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ሥልጣን ደርበው ለሚሠሩት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶችና የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የበጀት ማካካሻ ይሰጣል። አንቀጽ 80 የፍርድ ቤቶች ጣምራነትና ሥልጣን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ጉዳዮች ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል። የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ጉዳይ ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል። በተጨማሪ የፌዴራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 የተጠቀሰው ቢኖርም፣ ሀ/ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችሎት የማየት ሥልጣን ይኖረዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። ለ/ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዳዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችሎት የማየት ሥልጣን ይኖረዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክልሉ ከሚኖረው የዳኝነት ሥልጣን በተጨማሪ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል። የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣኑ መሰረት በሚሰጠው ውሳኔ ላይ የሚቀርበው ይግባኝ በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይታያል። የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል የዳኝነት ሥልጣኑ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ የሚቀርበው ይግባኝ በፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይታያል። አንቀጽ 81 ስለዳኞች አሿሿም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት በፌዴራል መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማሉ። ሌሎች የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን በተመለከተ በፌዴራል የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የቀረቡለትን እጩዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክርት ቤት አቅርቦ ያሾማል። የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አቅራቢነት በክልሉ ምክር ቤት ይሾማሉ። የክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የዳኞችን ሹመት ለምክር ቤቱ ከማቅረቡ በፊት የፌዴራሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በእጩዎቹ ላይ ያለውን አስተያየት መጠየቅና አስተያየቱን ከራሱ አስተያየት ጋር በማያያዝ ለክልሉ ምክር ቤት የማቅረብ ኃላፊነት አለበት። የፌዴራሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አስተያየቱን በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላቀረበ የክልሉ ምክር ቤት ሹመቱን ያጸድቃል። የክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አቅራቢነት በክልሉ ምክር ቤት ይሾማሉ። በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ዳኞች የዲሲፕሊንና የዝውውር ጉዳይ በሚመለከተው የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ይወሰናል።     አንቀጽ 82 የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አወቃቀር የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በዚህ ሕገ-መንግሥት ተቋቁሟል። የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አሥራ አንድ አባላት ይኖሩታል። አባላቱም የሚከተሉት ናቸው፤ ሀ/ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ ሰብሳቢ፤ ለ/ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ሰብሳቢ፤ ሐ/ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅራቢነት በሪፐብሉኩ ፕሬዚዳንት የሚሾሙ በሙያ ብቃታቸውና በሥነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው ስድስት የሕግ ባለሙያዎች፤ መ/ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ከአባላቱ መካከል የሚወክላቸው ሦስት ሰዎች። የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የሥራ ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ የሚያስችለው መዋቅር ሊዘረጋ ይችላል። አንቀጽ 83 ሕገ-መንግሥቱን ስለመተርጎም የሕገ መንግሥታዊ ክርክር ጉዳይ ሲነሳ በፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ውሳኔ ያገኛል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በሚያቀርብለት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳይ ላይ በሠላሳ ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል። አንቀጽ 84 የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሥልጣንና ተግባር የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን የማጣራት ሥልጣን ይኖረዋል። በሚያደርገው ማጣራት መሰረት ሕገ-መንግሥቱን መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል። በፌዴራሉ መንግስትም ሆነ በክልል ሕግ አውጪ አካላት የሚወጡ ሕጎች ከዚህ ሕገመንግሥት ጋር ይቃረናሉ የሚል ጥያቄ ሲነሳና ጉዳዩም በሚመለከተው ፍርድ ቤት ወይም በባለ ጉዳዩ ሲቀርብለት መርምሮ ለመጨረሻ ውሳኔ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል። በፍርድ ቤቶች የሕገ-መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ሲነሳ፣ ሀ/ ሕገ-መንግሥቱን መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ሳያገኘው ሲቀር ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ይመልሳል፤ በአጣሪ ጉባዔው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ባለጉዳይ ቅሬታውን ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በይግባኝ ማቅረብ ይችላል። ለ/ የትርጉም ጥያቄ መኖሩን ያመነበት እንደሆነ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመጨረሻ ውሳኔ ያቀርባል። የሚመራበትን ሥነ ሥርዓት አርቅቆ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል። ምዕራፍ አሥር የብሔራዊ ፖሊሲ መርሆዎችና ዓላማዎች አንቀጽ 85 ዓላማዎች ማንኛውም የመንግሥት አካል ሕገ-መንግሥቱን፣ ሌሎች ሕጎችንና ፖሊሲዎችን ሥራ ላይ ሲያውል በዚህ ምዕራፍ በተመለከቱት መርሆዎችና ዓላማዎች ላይ መመስረት አለበት። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ “መንግሥት” ማለት እንደየሁኔታው የፌዴራል መንግሥት ወይም የክልል መስተዳድሮች ማለት ይሆናል። አንቀጽ 86 የውጭ ግንኙነት መርሆዎች የኢትዮጵያን ሕዝቦች ጥቅም የሚያስጠብቅና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ማራመድ። የመንግሥታትን ሉዓላዊነትና እኩልነት ማክበር፣ በሌሎች ሀገሮች ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ አለመግባት። የሀገሪቱ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በጋራ ጥቅምና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ስምምነቶች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ። የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስከብሩና የሕዝቦቿን ጥቅም የማይፃረሩ ዓለም አቀፍ ሕጎችና ስምምነቶችን ማክበር። ከጎረቤት ሀገሮችና ከሌሎችም የአፍሪካ ሀገሮች ጋር በየጊዜው እያደገ የሚሄድ ኢኮኖሚያዊ ኅብረትና የሕዝቦች ወንድማማችነትን ማጎልበት። በሀገሮች መካከል የሚነሱ ግጭቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ ጥረት ማድረግ። አንቀጽ 87 የመከላከያ መርሆዎች የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮች፣ የብሔረሰቦች እና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋፅዖ ያካተተ ይሆናል። የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ የሚሾመው ሲቪል ይሆናል። የመከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በዚህ ሕገ-መንግሥት መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል። የመከላከያ ሠራዊቱ በማናቸውም ጊዜ ለሕገ-መንግሥቱ ተገዢ ይሆናል። የመከላከያ ሠራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ያከናውናል። አንቀጽ 88 ፖለቲካ ነክ ዓላማዎች መንግሥት በዴሞክራሲያዊ መርሆዎች ላይ በመመስረት ሕዝቡ በሁሉም ደረጃዎች ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለበት። መንግሥት የብሔሮችን፣ የብሔረሰቦችን፣ የሕዝቦችን ማንነት የማክበርና በዚሁ ላይ በመመርኮዝ በመካከላቸው እኩልነት፣ አንድነትና ወንድማማችነትን የማጠናከር ግዴታ አለበት። አንቀጽ 89 ኢኮኖሚ ነክ ዓላማዎች መንግሥት ሁሉም ኢትዮጵያውን የሀገሪቱ የተጠራቀመ ዕውቀትና ሀብት ተጠቃሚዎች የሚሆኑበትን መንገድ የመቀየስ ኃላፊነት አለበት። መንግሥት የኢትዮጵያውያንን የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ለማሻሻል እኩል ዕድል እንዲኖራቸው ለማድረግና ሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የሚከፋፈሉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ግዴታ አለበት። የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ እንዳይደርስ መከላከልና አደጋው ሲደርስም ለተጎጂው እርዳታ በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ። በእድገት ወደ ኋላ ለቀሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች መንግሥት ልዩ ድጋፍ ያደርጋል። መንግሥት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በሕዝብ ስም በይዞታው ስር በማድረግ ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት። የሀገር ልማት ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች በሚዘጋጁበት ወቅት መንግሥት ሕዝቡን በየደረጃው ማሳተፍ አለበት። የሕዝብንም የልማት እንቅስቃሴዎች መደገፍ አለበት። መንግሥት በሀገር ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት የሚሳተፉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነት አለበት። መንግሥት የሠራተኛውን ሕዝብ ጤንነት፣ ደህንነትና የኑሮ ደረጃ ለመጠበቅ መጣር አለበት። አንቀጽ 90 ማኅበራዊ ነክ ዓላማዎች የሀገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የትምህርት፣ የጤና አገልግሎት፣ የንጹህ ውሃ፣ የመኖሪያ፣ የምግብና የማኅበራዊ ዋስትና እንዲኖረው ይደረጋል። ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባሕላዊ ተፅዕኖዎች ነፃ በሆነ መንገድ መካሄድ አለበት። አንቀጽ 91 ባሕል ነክ ዓላማዎች መንግሥት መሰረታዊ መብቶችንና ሰብዓዊ ክብርን፣ ዲሞክራሲንና ሕገ-መንግሥቱን የማይቃረኑ ባሕሎችና ልማዶች በእኩልነት እንዲጎለብቱና እንዲያድጉ የመርዳት ኃላፊነት አለበት። የሀገር የተፈጥሮ ሀብቶችንና የታሪክ ቅርሶችን መጠበቅ የመንግሥትና የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። መንግሥት አቅም በፈቀደ መጠን ኪነጥበብን፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የማስፋፋት ግዴታ አለበት። አንቀጽ 92 የአካባቢ ደህንነት ጥበቃ ዓላማዎች መንግሥት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንጹህና ጤናማ አካባቢ እንዲኖረው የመጣር ኃላፊነት አለበት። ማንኛውም የኢኮኖሚ ልማት እርምጃ የአካባቢውን ደህንነት የማያናጋ መሆን አለበት። የሕዝብን የአካባቢ ደህንነት የሚመለከት ፖሊሲና ፕሮግራም በሚነደፍበትና ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የሚመለከተው ሕዝብ ሁሉ ሀሳቡን እንዲገልጽ መደረግ አለበት። መንግሥትና ዜጎች አካባቢያቸውን የመንከባከብ ግዴታ አለባቸው። ምዕራፍ አሥራ አንድ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች አንቀጽ 93 ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሀ/ የውጭ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ለመቋቋም የማይቻል ሲሆን፣ ማናቸውም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የሕዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት፣ የፌዴራሉ መንግሥት የሚንስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመደንገግ ሥልጣን አለው። ለ/ የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት የክልል መስተዳድሮች በክልላቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጁ ይችላሉ ዝርዝሩ ክልሎች ይህን ሕገ-መንግሥት መሰረት በማድረግ በሚያወጧቸው ሕገ መንግሥቶች ይወሰናል። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 (ሀ) መሰረት የሚታወጅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ሀ/ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ በታወጀ በአርባ ስምንት ሰዓታት ውሰጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረብ አለበት። አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ካላገኘ ወዲያውኑ ይሻራል። ለ/ ከላይ በንዑስ አንቀጽ (ሀ) ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባልሆነበት ወቅት የሚታወጅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረብ ያለበት አዋጁ በታወጀ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ነው። በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በምክር ቤቱ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ሊቆይ የሚችለው እስከ ስድስት ወራት ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ አንድን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በየአራት ወሩ በተደጋጋሚ እንዲታደስ ሊያደርግ ይችላል። ሀ/ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚታወጅበት ጊዜ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣቸው ደንቦች መሰረት የሀገርን ሰላምና ሕልውና፣ የሕዝብን ደህንነት፣ ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥልጣን ይኖረዋል። ለ/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣን በሕገ-መንግሥቱ የተቀመጡትን መሰረታዊ የፖለቲካና የዴሞክራሲ መብቶችን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማወጅ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ለማስወገድ ተፈላጊ ሆኖ በተገኘው ደረጃ እስከ ማገድ ሊደርስ የሚችል ነው። ሐ/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር የሚያወጣቸው ድንጋጌዎችና የሚወስዳቸው እርምጃዎች በማናቸውም ረገድ በዚህ ሕገመንግሥት አንቀጽ 1፣ 18፣25 እና 39 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 የተቀመጡትን መብቶች የሚገድቡ ሊሆኑ አይችሉም። በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚታወጅበት ወቅት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአባላቱና ከሕግ ባለሙያዎች መርጦ የሚመድባቸው ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ያቋቁማል። ቦርዱ አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚጸድቅበት ጊዜ ይቋቋማል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የሚከተሉት ሥልጣንና ኃላፊነቶች አሉት፤ ሀ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት የታሰሩትን ግለሰቦች ስም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፋ ማድረግና የታሰሩበትን ምክንያት መግለጽ። ለ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የሚወሰዱት እርምጃዎች በማናቸውም ረገድ ኢሰብዓዊ አለመሆናቸውን መቆጣጠርና መከታተል፣ ሐ/ ማናቸውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ ኢሰብዓዊ መሆኑን ሲያምንበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም የሚኒስትሮች ምክር ቤት እርምጃውን እንዲያስተካክል ሀሳብ መስጠት፣ መ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃዎች ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፈጽሙትን ሁሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ፣ ሠ/ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲቀጥል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ሲቀርብ ያለውን አስተያየት ለምክር ቤቱ ማቅረብ።     አንቀጽ 94 የፋይናንስ ወጪን በሚመለከት የፌዴራሉ መንግሥትና ክልሎች በሕግ የተሰጧቸውን ኃላፊነቶችና ተግባሮች ለማከናወን የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በየበኩላቸው ይሸፍናሉ፤ ሆኖም ማናቸውም ክልል በውክልና ለሚፈጽመው ተግባር የሚያስፈልገው ወጪ ሌላ ስምምነት ከሌለ በቀር ውክልናውን በሰጠው ወገን ይሸፈናል። የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሎች የተመጣጠነ እድገት እንቅፋት ካልሆነ በስተቀር ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ፣ ለመልሶ ማቋቋምና ለልማት ማስፋፊያ ለክልሎች ብድርም ሆነ እርዳታ ሊሰጥ ይችላል። የፌዴራሉ መንግሥት ክልሎች ለሚያስፈልጋቸው ወጪ የሚያደርገውን ድጎማ በሚመለከት ኦዲትና ቁጥጥር የማድረግ ሥልጣን ይኖረዋል። አንቀጽ 95 የፋይናንስ ገቢን በሚመለከት የፌዴራሉ መንግሥትና ክልሎች የሚዋቀረውን የፌዴራል አደረጃጀት የተከተለ የገቢ ክፍፍል ያደርጋሉ። አንቀጽ 96 የፌዴራል መንግሥት የታክስና የግብር ሥልጣን የፌዴራል መንግሥት በወጪና ገቢ ዕቃዎች ላይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ታክስና ሌሎች ክፍያዎች ይጥላል፣ ይሰበስባል። በፌዴራል መንግሥትና በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተቀጣሪዎች ላይ የሥራ ግብር ይጥላል፣ ይሰበስባል። በፌዴራል መንግሥት ባለቤትነት ሥር በሆኑ የልማት ድርጅቶች ላይ የንግድ ትርፍ ግብር፣ የሥራ ግብር፣ የሽያጭና የኤክሳይስ ታክስ ይጥላል፣ ይሰበስባል። በብሔራዊ የሎተሪ እና ሌሎች የዕድል ሙከራ ገቢዎች ላይ ታክስ ይጥላል፣ ይሰበስባል። በአየር፣ በባቡርና በባሕር ትራንስፖርት ገቢዎች ላይ ታክስ ይጥላል፣ ይሰበስባል። በፌዴራል መንግሥት ባለቤትነት ሥር በሚገኙ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች ገቢ ላይ ግብር ይጥላል፣ ይሰበስባል፤ ኪራይ ይወስናል። የፌዴራል መንግሥት አካላት ከሚሰጧቸው ፈቃዶችና አገልግሎቶች የሚመነጩ ክፍያዎችን ይወስናል፤ ይሰበስባል። የሞኖፖል ታክስ ይጥላል፣ ይሰበስባል። የፌዴራል የቴምብር ሽያጭ ቀረጥ ይጥላል፣ ይሰበስባል። አንቀጽ 97 የክልል መስተዳድሮች የታክስና የግብር ሥልጣን ክልሎች፣ በክልል መስተዳድርና በድርጅት ተቀጣሪዎች ላይ የሥራ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። የመሬት መጠቀሚያ ክፍያ ይወስናሉ፣ ይሰበስባሉ። በግል የሚያርሱና በኅብረት ሥራ ማኅበራት በተደራጁ ገበሬዎች ላይ የእርሻ ሥራ ገቢ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። በክልሉ በሚገኙ ግለሰብ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ትርፍ ግብርና የሽያጭ ታክስ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። በክልሉ ውስጥ በውሀ ላይ ከሚደረግ ትራንስፖርት በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። በክልል መስተዳድር በግል ባለቤትነት ስር ካሉ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ፤ በባለቤትነታቸው ስር ባሉ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች ላይ ኪራይ ያስከፍላሉ። በክልል መስተዳድር ባለቤትነት ስር በሚገኙ የልማት ድርጅቶች ላይ የንግድ ትርፍ፣ የሥራ ግብር፣ የሽያጭና ኤክሳይስ ታክስ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። በአንቀጽ 98 ንዑስ አንቀጽ 3 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በማዕድን ሥራዎች ላይ የማዕድን ገቢ ግብር፣ የሮያሊቲና የመሬት ኪራይ ክፍያዎች ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። በክልል መስተዳድር አካላት ከሚሰጡ ፈቃዶችና አገልግሎቶች የሚመነጩ ክፍያዎች ይወስናሉ፣ ይሰበስባሉ። ከደን የሚገኝ የሮያሊቲ ክፍያ ይወስናሉ፣ ይሰበስባሉ። አንቀጽ 98 የጋራ የታክስና የግብር ሥልጣን የፌዴራል መንግሥትና ክልሎች በጋራ በሚያቋቁሟቸው የልማት ድርጅቶች ላይ የንግድ ትርፍ ግብር፣ የሥራ ግብር፣ የሽያጭና የኤክሳይስ ታክስ በጋራ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። በድርጅቶች የንግድ ትርፍ ላይ እና በባለ አክሲዮኖች የትርፍ ድርሻ ላይ ግብርና የሽያጭ ታክስ በጋራ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። በከፍተኛ የማዕድን ሥራዎችና በማናቸውም የፔትሮሊየምና የጋዝ ሥራዎች ላይ የገቢ ግብርና የሮያሊቲ ክፍያዎች በጋራ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። አንቀጽ 99 ተለይተው ስላልተሰጡ የታክስ እና የግብር ሥልጣኖች በዚህ ሕገ-መንግሥት ተለይተው ያልተሰጡ ታክስና ግብር የመጣል ሥልጣኖችን በሚመለከት የፌዴሬሽኑ ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ይወስናሉ። አንቀጽ 100 የታክስና የግብር አጣጣል መርሆዎች ክልሎችና የፌዴራሉ መንግሥት ታክስና ግብር በሚጥሉበት ጊዜ የሚጠየቀው ታክስና ግብር ከምንጩ ጋር የተያያዘና በአግባቡ ተጠንቶ የተወሰነ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው። በመካከላቸው የሚኖረውን መልካም ግንኙነት የማይጎዳና ከሚቀርበው አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው። ለትርፍ የቆመ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር ክልሎች በፌዴራሉ መንግሥት ንብረት ላይ፣ የፌዴራሉ መንግሥትም በክልሎች ንብረት ላይ ግብር ወይም ቀረጥ የማስከፈል ሥልጣን አይኖራቸውም። አንቀጽ 101 ዋናው ኦዲተር ዋናው ኦዲተር በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማል። ዋናው ኦዲተር የፌዴራሉን የሚኒስቴርና ሌሎች መሥሪያ ቤቶች ሂሳቦች በመቆጣጠር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመደበው ዓመታዊ በጀት፣ በበጀት ዓመቱ ለተሠሩት ሥራዎች በሚገባ መዋሉን መርምሮ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባል። ዋናው ኦዲተር የመሥሪያ ቤቱን በጀት በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስጸድቃል። የዋናው ኦዲተር ዝርዝር ተግባር በሕግ ይወሰናል።     አንቀጽ 102 የምርጫ ቦርድ በፌዴራልና በክልል የምርጫ ክልሎች ነፃና ትክክለኛ ምርጫ በገለልተኝነት እንዲያካሂድ ከማንኛውም ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል። የቦርዱ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማሉ፤ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። አንቀጽ 103 የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን የሀገሪቱን የሕዝብ ቁጥር በየጊዜው የሚያጠናና ቆጠራ የሚያካሂድ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ይኖራል። የኮሚሽኑ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማሉ። ኮሚሽኑ ዋና ጸሐፊ፣ አስፈላጊ ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ይኖሩታል፣ የኮሚሽኑ ዓመታዊ በጀት በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይጸድቃል። የሕዝብ ቆጠራ በየአሥር ዓመቱ ይካሄዳል። በውጤቱም መሰረት የምርጫ ክልሎችን አከላለል የምርጫ ቦርድ በሚያቀርበው ረቂቅ መሠረት የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ይወስናል። የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። ስለ ሥራው አፈጻጸም በየጊዜው ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባል። አንቀጽ 104 የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሀሳብን ስለማመንጨት አንድ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሀሳብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ የደገፈው፣ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ የደገፈው ወይም ከፌዴሬሽኑ አባል ክልሎች ውስጥ አንድ ሦስተኛው የክልል ምክር ቤቶች በድምፅ ብልጫ የደገፉት ከሆነ ለውይይትና ለውሳኔ ለመላው ሕዝብና የሕገ-መንግሥቱ መሻሻል ለሚመለከታቸው ክፍሎች ይቀርባል።     አንቀጽ 105 ሕገ-መንግሥቱን ስለማሻሻል በዚህ ሕገ-መንግሥት ምዕራፍ ሦስት የተዘረዘሩት መብቶችና ነፃነቶች በሙሉ፣ ይህ አንቀጽ፣ እንዲሁም አንቀጽ 104 ሊሻሻሉ የሚችሉት በሚከተለው አኳኋን ብቻ ይሆናል፤ ሀ/ ሁሉም የክልል ምክር ቤቶች የቀረበውን ማሻሻያ በድምፅ ብልጫ ሲያጸድቁት፣ ለ/ የፌዴራሉ መንግሥት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቀው፣ እና ሐ/ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ማሻሻያውን ሲያጸድቀው ነው። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ከተዘረዘሩት ውጭ ያሉት የሕገ-መንግሥቱ ድንጋጌዎች ሊሻሻሉ የሚችሉት በሚከተለው አኳኋን ብቻ ይሆናል፤ ሀ/ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቁት፣ እና ለ/ ከፌዴሬሽኑ አባል ክልሎች ምክር ቤቶች ውስጥ የሁለት ሦስተኛ ክልሎች ምክር ቤቶች በድምፅ ብልጫ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቁት ነው። አንቀጽ 106 የመጨረሻ ሕጋዊ እውቅና ስላለው ቅጂ የዚህ ሕገ-መንግሥት የአማርኛ ቅጂ የመጨረሻው ሕጋዊ እውቅና ያለው ሰነድ ነው።          

Judge hammer on the table

አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስልጣን ባህርያትና የስልጣን 4-አስተዳደራዊ ድንጋጌ…


የአስተዳደር መንግስት እና የአስተዳደር ህግ ውልደት

ህገ መንግስታዊ ገደብበውክልና ህግ የማውጣት ስልጣን የአስፈላጊነቱ አጥጋቢ ምክንያት ተግባራዊ ችግሮች ቢሆኑም የመንግስት አስተዳደርን ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ ረገድ ራሱን የቻለ የጐላ ጥቅም አለው፡፡ በእርግጥ የስልጣን አምባገነንነትን ሊያስከትል ከመቻሉ የተነሳ የራሱ አደጋዎችም አሉት፡፡ አደጋውና አላስፈላጊ ጐኑ ሊወገድ የሚችለው ልኩ ተለይቶ በታወቀ ገደብ ውሰጥ ተግባር ላይ የዋለ እንደሆነ ነው፡፡ ውክልናው ግልጽ፣ የማያሻማ፣ ጠባብና ገደብ የተሰመረለት ሊሆን ይገባዋል፡፡የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ህግ የማውጣት ስልጣን ለተወካዮች ም/ቤት እንደተሰጠ በግልፅ ይደነግጋል፡፡a ይህ ስልጣን በውክልና እንዲተላለፍ የሚፈቅድ ግልጽ ድንጋጌ ግን አልሰፈረም፡፡ ስልጣኑን በውክልና እንዲያስተላልፍ የሚፈቅድለት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ ባይኖርም የተለያዩ ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ ውክልና ቢያንስ በተዘዋዋሪ የተከለከለ እንዳልሆነ ድምዳሜ ላይ ያደርሰናል፡፡ በተለይ አግባብነት ያለው የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 13 የሚኒስትሮች ም/ቤት የተወካዮች ም/ቤት በሚሰጠው ስልጣን መሰረት ደንብ የማውጣት ስልጣን እንዳለው ይደነግጋል፡፡ ከዚህ አንጻር የተጠቀሰው ድንጋጌ ህግ የማውጣት ስልጣንን በውክልና ማስተላለፍ ኢ- ህገ መንግስታዊ ስላለመሆኑ በቂ መከራከሪያ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፡፡ለአስተዳደር ህግ አስጨናቂው ጥያቄ ህገ መንግስቱ የተወካዮች ም/ቤት በውክልና ስልጣኑን እንዲያስተላልፍ የመፍቀዱ ነገር ሳይሆን በውክልና ሊተላለፍ የሚችለው ስልጣን ወሰንና ገደቡ የትላይ ነው? የሚለው ነው፡፡ ህግ አውጭው በህዝብ የተመረጠው ህግ ለማውጣት ነው፡፡ ስለሆነም የህግ አውጭነት ስልጣኑን ያለገደብ ወይም ሙሉ በሙሉ ለአስፈፃሚው አካል ማስተላለፍ የለበትም፡፡

የአስተዳደር መ/ቤቶችን የማቋቋም ስልጣን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የህግ አውጭነት ስልጣን በህጋዊነትና ህገ መንግስታዊነት ገደቦች አልተገታም፡፡ የተወካዮች ምክር ቤትም የህግ አውጭነት ስልጣኑን ለማስጠበቅ አቅም ያጣ ይመስላል፡፡ በውክልና ሰበብ የሚወጡትን ደንቦች ሊቆጣጠር ቀርቶ መሰረታዊ የህግ አውጭነት ስልጣኑን ጭምር እያጋራው ይገኛል፡፡ በ2001 ዓ.ም. በወጣው አዋጅ ቁ. 603/2001a የተወካዮች ምክር ቤት የውክልና ዲሞክራሲን መርህ ከስሩ የሚንድ መሰረታዊ የህግ አውጭነት ስልጣን ለሚኒስትሮች ም/ቤት አስተላልፏል፡፡ ይኸው አዋጅ በአዋጅ ቁ. 691/2001 ቀጥሎም በአዋጅ ቁ. 916/2008 ተተክቷል፡፡ በእነዚህ ህጎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት መነሻና መድረሻ የሌለው የህግ አውጭነት ስልጣን ተጎናጽፏል፡፡ በሶስቱም ህጎች የሚገኘው ድንጋጌ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ደንብ በማውጣት፣ ማንኛውም አስፈፃሚ አካል እንዲታጠፍ፣ ከሌላ አስፈፃሚ አካል ጋር እንዲዋሃድ ወይም እንዲከፋፈል በማድረግ፣ ተጠሪነቱ ወይም ሥልጣንና ተግባሩ እንዲለወጥ በማድረግ ወይም አዲስ አስፈፃሚ አካል እንዲቋቋም በማድረግ የፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን እንደገና የማደራጀት ሥልጣን እንዲኖረው ፈቅደዋል፡፡እንዲህ ዓይነቱን ግዙፍ ስልጣን በ1923 ዓ.ም. ህገ መንግስት አንቀጽ 11 እና 34 እንዲሁም በ1948 ዓ.ም. ህገ መንግስት (አንቀጽ 27) ንጉሱ አላስነካም ብለው በብቸኝነት ይዘውት ነበር፡፡ በ1980 ዓ.ም. በቆመው የደርግ ህገ መንግሰት እንዲሁ መ/ቤቶችን የማቋቋም ስልጣን በተዘዋዋሪ ከስራ አስፈፃሚው እጅ አልወጣም፡፡ በአንቀጽ 82/3/፣ 83/1/ እና 86/4/ በተሰጣቸው ስልጣን ዋናዎቹ ህግ አውጭዎች ምክር ቤቱ (Council of State) እና ፕሬዚዳንቱ ነበሩ፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት ግን የስራ አስፈፃሚውን ስልጣን የአስተዳደር ተቋማትን አደረጃጀት ከመወሰን እንዳያልፍ ገድቦታል፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 77/2/ እንደሰፈረው የሚኒስትሮች ም/ቤት የሚኒስቴሮችንና በቀጥታ ለራሱ ተጠሪ የሆኑ የመንግስት አካላት አደረጃጀት (በእንግሊዝኛው ቅጂ organizational structure) ይወስናል፡፡ አደረጃጀት ሲባል የአንድን ተቋም ውስጣዊ መዋቅር ይመለከታል፡፡ ማቋቋም፣ ማጠፍ፣ ማዋሃድ፣ መከፋፈል እንዲሁም ስልጣንና ተግባር መለወጥ በህዝብ ከተመረጡ ተወካዮች እጅ መውጣት የሌለበት መሰረታዊ የህግ አውጭነት ስልጣን ነው፡፡በውክልና ዲሞክራሲ መርህ መሰረት የሁሉም ስልጣን መነሻ እና ባለቤት የሆነው ህዝብ የሚያስተዳድሩትን ተወካዮች ሲመርጥ በምርጫው (ወዶና ፈቅዶ) በውክልና ስልጣኑን ያስረክባቸዋል፡፡ በህዝብ ያልተመረጡ የመንግስት ባለስልጣናት እና ሹመኞች ከእነዚህ የህዝብ ተወካዮች በከፊል ተቆርሶ ከሚሰጣቸው ስልጣን በስተቀር ከሌላ ምንጭ የሚያገኙት ስልጣን የለም፡፡ ሆኖም የተሻሩትን ጨምሮ አዋጅ ቁ. 916/2008 ስራ አስፈጻው ራሱ ስልጣን ሰጪ ራሱ ተቀባይ እንዲሆን በማድረግ ህግ አውጭውን ‘ከተወካዮች ም/ቤት ወደ ወካዮች ም/ቤት’ አሳንሰውታል፡፡

የአስተዳደራዊ ድንጋጌዎች ህጋዊነትና ህገ መንግስታዊነትማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ሲፈጠር መፍትሔ የመሻት ቀዳሚ ኃላፊነት የተጣለባቸው በየዘርፉ የተቋቋሙት የአስተዳደር መ/ቤቶች ናቸው፡፡ ከትምህርት አሰጣጥ ወይም ጥራት ጋር የተያያዘ ወይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ችግር ሲከሰት የትምህርት ሚኒስቴር እንቅስቃሴ ይጀምራል፡፡ በጉምሩክ ህግ አፈጻጸም አቤቱታዎች ሲጎርፉ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መፍትሔ ያፈላልጋል፡፡ በግንባታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች ጉዳት ሲደርስባቸው የሠራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ላይ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ትኩረት ሰጥቶ ስራ ይጀምራል፡፡ ችግሮችን ለመቅረፍ መላ መዘየድ ችግር የለውም፤ እንዲያውም ይበረታታል፡፡ይሁን እንጂ በአንድ አገር ውስጥ በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮች ሊቀረፉ የሚገባው በህግና በህገ መንግስት ማዕቀፍ ውስጥ ነው፡፡ ከፊል ጉዳዮች የተወካዮች ም/ቤትን ጣልቃ ገብነት ይሻሉ፡፡ የአስተዳደር መ/ቤቶች ችግር ፈቺነት በህግ ከተፈቀደላቸው ስልጣን በላይ ሊለጠጥ አይችልም፡፡ አዋጅ ሊመልሰው የሚገባውን መመሪያ ከቀደመው መ/ቤቶች ችግር ፈቺ መሆናቸው ቀርቶ ችግር ፈጣሪ ይሆናሉ፡፡ የአስተዳደር ድንጋጌዎች መመዘኛ አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ብቻ ሳይሆን በዋናነት ህጋዊነት ነው፡፡ የቄሳርን ለቄሳር እንዲሉ ተወካዮች ሊመክሩበትና ሊፈቱት የሚገባውን ችግር ተሿሚዎች በመመሪያ ለመቅረፍ መሽቀዳደም የለባቸውም፡፡ ከላይ የቀረበውን ሀሳብ በተጨባጭ የሚያሳዩ ጥቂት አስተዳደራዊ ድንጋጌዎች እንደሚከተለው ይጠቀሳሉ፡፡

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሠራተኞች አስተዳዳርፍትህ የማግኘት መብትን የሚደነግገው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 37/1/ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው፡፡የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሰራተኞች አስተዳደር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 155/2000 በልዩ ሁኔታ ሰራተኞችን ማሰናበትን በተመለከተ በአንቀጽ 37 እንደሚከተለው ደንግጓል፡፡1) በዚህ ደንብ በሌላ ሁኔታ የተደነገገው ቢኖርም ዋና ዳይሬክተሩ በሙስና የተጠረጠረንና እምነት ያጣበትን ሰራተኛ መደበኛውን የዲስፕሊን አፈፃፀም ስርዓት ሳይከተል ከስራ ማሰናበት ይችላል፡፡2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ በየትኛውም የፍርድ አካል ውሳኔ ወደ ስራ መመለስ አይችልም፡፡የህገ መንግስቱና የደንብ ቁ. 155/2000 ድንጋጌዎች በስም (አንቀጽ ቁጥር) ይመሳሰላሉ፡፡ በተግባር ግን ተጻራሪ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው መብት ያናጽፋል፤ ሁለተኛው ይነፍጋል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህገ መንግስቱን የማክበርና የማስከበር ግዴታ ከተጣለባቸው አካላት መካከል አንደኛው ነው፡፡ በዚህ ግዴታው የህግ አውጭነት ስልጣኑ ምንጭ የሆነው ህግ ያሰመረለትን ወሰን ሊያከብር ይገባል፡፡ ምክር ቤቱ ደንብ ቁ. 155/2000 ለማውጣት ህግ እንደፈቀደለት የሚጠቅሰው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ አዋጅ ቁ. 587/2000 አንቀጽ 19/1/ ለ ድንጋጌ ነው፡፡ ይዘቱ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡[የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን] ሠራተኞች አስተዳደር የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይመራል፡፡በስልጣን ምንጭነት የተጠቀሰው ህግ ም/ቤቱ የሠራተኞች አስተዳደርን በተመለከተ ደንብ እንዲያወጣ ይፈቅድለታል፡፡ ይሁን እንጂ ሠራተኞች በጥርጣሬ እንዲሰናበቱና በየትኛውም የፍርድ አካል መብቸውን እንዳይጠይቁ የሚከለክል ኢ-ህገ መንግስታዊ ደንብ እንዲያወጣ ስልጣን አልሰጠውም፡፡

ህጋዊነት


ህጋዊነት በአገራችን ከስልጣን በላይ መርህን የሚደነግገው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 401 ንዑስ ቁጥር 1 እንደሚከተለው ይነበባል፡፡በሕግ የታወቀላቸው የተግባር ስልጣን ከሚዘረጋበት ውጭ ወይም በህጉ የተገደዱትን ሁኔታዎች ወይም ፎርም ባለመፈጸም…የሰውነት መብት የተሰጣቸው ድርጅቶች የሚፈጽሟቸው ስራዎች ፈራሾች ናቸው፡፡በድንጋጌው ላይ የሚስተዋለው ከቋንቋ አገላለጽ የመነጨ ብዥታ የእንግሊዝኛው ቅጂ ያጠራዋል፡፡ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡Acts performed by … bodies … in excess of the powers given to them by law or without the observance of the conditions or formalities required by law shall be of no effectበአማርኛው ላይ ‘በሕግ የታወቀላቸው የተግባር ስልጣን ከሚዘረጋበት ውጭ’ የሚለው አገላለጽ በእንግሊዝኛው ቅጂ in excess of the powers given to them by law በሚል ተተርጉሟል፡፡አስተዳደራዊ ውሳኔ፣ መመሪያ፣ ደንብ ወይም ሌላ ማናቸውም ድርጊት ለውሳኔ ሰጪው ወይም የውክልና ህግ አውጭው አካል በህግ ከፈቀደለት ስልጣን በላይ ከሆነ እንዲሁም አንዳችም የህግ ስልጣን ከሌለው ከስልጣን በላይ ነው፡፡ የስልጣን ምንጩ ህግ ነው፡፡ ስልጣን ገደቡን አልፏል የሚለው መደምደሚያ ላይ ለመድረስ አንዳንዴ ብርሀንን ከጨለማ የመለየት ያክል ቀላል ነው፡፡ አንድንድ ጊዜ ደግሞ ውስብስብ ከመሆኑ የተነሳ ከህግ፣ ከፖሊሲ እና ከህገ መንግስታዊ መርሆዎች ብሎም ከህግ አተረጓጎም መሰረታዊ ደንቦች አንጻር ጥልቅ ፍተሻ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ከዚህ በታች የቀረበው ዳሰሳ ከስልጣን ገደብ እና ህጋዊነት ጋር በተያያዘ የሰበር ችሎትን አቋም ያስቃኛል፡፡

  • የፅንሰ ሀሳቡ አፈጻጸም በአገራችንየፅንሰ ሀሳቡ አፈጻጸም በአገራችን ስለ አገራችን ፍርድ ቤቶች የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን ከመወራቱ በፊት መጀመሪያ የጽንሰ ሀሳቡ ይዘትና አፈጻጸም ምን እንደሚመስል ጥቂት   መንደርደሪያ   ነጥቦችን  …
  • አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት (ከፊል የህግ አውጭነት ስልጣንአስተዳደራዊ ውሳኔ ሰጭነት (ከፊል የዳኝነት ስልጣን)       3-ስልጣንና ተግባራት የስልጣን ምንጭ የመንግስት   ስልጣን   በህግ   ከተቀመጠለት   ገደብ   እንዳያልፍና   ይህንንም   በተግባር   ለማረጋገጥ   መጀመ…
  • በህግ የተገደበ የመንግስት ስልጣ።በህግ የተገደበ የመንግስት ስልጣ። ህጋዊነት ገለልተኛና ነፃ የዳኝነት አካል ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ሰላምና ደህነት በሕግ የተገደበ የመንግስት ስልጣን የመንግስት፣ የባለስልጣናቱና እንደራሴዎቹ ሥልጣን መገደብ …
  • የዕግድ ትዕዛዝ ዕግድ በፍትሐብሔር ክርክሮች ላይ ራሱን ችሎ እንደ ውሳኔ ወይም በክርክሩ መሀል እንደ ጊዜያዊ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡የዕግድ ትዕዛዝ ዕግድ በፍትሐብሔር ክርክሮች ላይ ራሱን ችሎ እንደ ውሳኔ ወይም በክርክሩ መሀል እንደ ጊዜያዊ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ዕግድ በውጤቱ ተከሳሹ ወይም ተጠሪው አንድ   ድርጊት   ከመፈ…
  • መስቀለኛ መዘዝመስቀለኛ መዘዝ የተከሳሽ ተከላካይ ጠበቃ ምንም ላይፈይድለት ምስክሯን “እማማ እኔን ያውቁኛል?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ ምስክር — “እንዴት አላውቅህም አንተ ሞላጫ! አውቅሃለው እንጂ! ከልጅነትህ ጀምሮ አሳምሬ አውቅሃለው፡፡ …
  • የተከሳሽየተከሳሽነት ብቃትና የመንግስት ስልጣን ገደብ እንዲ…የተከሳሽነት ብቃትና የመንግስት ስልጣን ገደብ እንዲ…: የከሳሽነት ብቃት ‘አንድን የአስተዳደር ተግባር በፍርድ ቤት ወይም በሌላ የዳኝነት ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መሞገት የሚችለው ማነው?’ የሚለው ጥያቄ በአስተዳ…
  • አስተዳደራዊ ስልጣንአስተዳደራዊ ስልጣን ደንብና   መመሪያ   ማውጣት   እንዲሁም   የአስተዳደር   ውሳኔ   እና   እርምጃ   መውሰድ   ህግ   አስፈፃሚ   አካላት   ህግና   ፖሊሲን   ለመተግበር   የሚያ…

Powered By Blogger

MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE HOME

MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE HOME

አስተዳደራዊ ስልጣን

አስተዳደራዊ ስልጣንደንብና መመሪያ ማውጣት እንዲሁም የአስተዳደር ውሳኔ እና እርምጃ መውሰድ ህግ አስፈፃሚ አካላት ህግና ፖሊሲን ለመተግበር የሚያከናውኗቸው ተግባራት ናቸው፡፡ የእነዚህ አካላት ዋነኛ ስልጣንና ተግባር ህግ ማውጣት አሊያም ዳኝነት መስጠት ሳይሆን ማስተዳደር ነው፡፡ አስተዳደራዊ ስልጣን ከህግ ማውጣት እና ዳኝነት መስጠት ውጪ ያሉትን ተግባራት በሙሉ ያጠቃልላል፡፡ የአስተዳደር መ/ቤቶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ይህን የእለት ተእለት የአስተዳደር ስራ በማከናወን ነው፡፡በዚህ ስልጣን ስር ከሚወድቁ በርካታ ምሳሌዎችን መካከል ሪፖርት ማቅረብ፣ ፓስፖርት መስጠት፣ ፍቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ ፀጥታ ማስከበር፣ ክስ መመስረት፣ እድገትና ሹመት መስጠት፣ ምርመራ፤ ቁጥጥርና ክትትል ማካሄድ የምክር ሀሳብ መስጠት ወዘተ ሁሉም የአስተዳደር መ/ቤቶች አስተዳደራዊ ስልጣናቸውን በመጠቀም የሚያከናውኗቸው ስራዎች ናቸው፡፡እነዚህ ተግባራት የህግ መጣስ መኖርን አለመኖሩን ለማረጋገጥ መረጃ በመሰብሰብና በማጠናቀር ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ የመረጃ አሰባሰብና ጥንቅር ስርዓት የንግድ ድርጅቶች በየጊዜው በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ሊመሰረት ይችላል፡፡ ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ የመረጃ አሰባሰብ ስርዓቱ በአካል ተገኝቶ ቀጥተኛ እና የአካባቢ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ እና የማጣራት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡የመርማሪነት ስራ ህጉ ልዩ ስልጣን በሰጣቸው መርማሪዎች የሚከናወን ሲሆን የምርመራ ሂደቱም በህግ ማእቀፍ ውስጥ ይመራል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የፖሊስ የምርመራ ተግባር ነው፡፡ ፖሊስ ወንጀል ሲፈጸም ወይም ተፈጽሟል የሚል መረጃ ከደረሰው አሊያም ተገቢ ጥርጣሬ ካደረበት የወንጀል ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ በአካል በመገኘት ተጨባጭ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ እና ተጠርጣሪውን የመመርመር ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ ረገድ ሰፊ ስልጣናት አሉት፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የአስተዳደር መ/ቤቶች የመርማሪነት፣ የቁጥጥርና ክትትል ስልጣን በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ ለፖሊስ ከተሰጠው ስልጣን ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡በአስረጂነት በተወሰኑ ህጎች ለተቆጣጠሪዎች የተሰጣቸው መጠነ ሰፊ ስልጣን በማጣቀሻነት እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡የአካባቢ ተቆጣጣሪዎች ስልጣንaሳያሳውቁ ወይም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይዙ በማንኛውም ተገቢ መስሎ በሚታያቸው ጊዜ ወደ ማንኛውም ቦታ ወይም ቅጥር ግቢ መግባትማንኛውንም ሰው ብቻውን ወይም በምስክር ፊት የመጠየቅከብክለት ጋር ግንኙነት ያለውን ማንኛውንም ወረቀት፣ ማህደር ወይም ሌላ ሰነድ መፈተሽ፣ መገልበጥ ወይም ለይቶ መቅዳትየማንኛውንም ቁስ ናሙናዎች እንደአስፈላጊነቱ ያለክፍያ መውሰድና በአካባቢ ወይም በህይወት ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ አለመሆኑን ለመወሰን መመርመር ወይም ማስመርመርየአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ቁ. 300/1995 ወይም ሌላ ህግ መከበሩን ለማረጋገጥ ሸቀጥን፣ የአመራረት ሂደትን ወይም መገልገያን በፍቶግራፍ ማንሳት፣ መለካት፣ መሳል ወይም መፈተሽአዋጁን ወይም አግባብ ያለውን ሌላ ህግ በመተላለፍ ጥፋት ተፈጽሞበታል የተባለ መሳሪያን ወይም ሌላ ነገርን መያዝየዱር እንስሳት ቁጥጥር ሠራተኛbሕግን በመተላለፍ በይዞታ ስር የተደረጉ የዱር እንስሳት ወይም የዱር እንስሳት ውጤቶች ተደብቀዋል ብሎ ለማመን በቂ ምክንያት ሲኖር ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ወደ ማንኛውም ሰው መሬት፣ ህንጻ፣ ድንኳን፣ ተሸከርካሪ፣ የአየር መንኮራኩር ወይም ጀልባ ውስጥ የመግባትና የመፈተሸ እንዲሁም ሻንጣ ወይም እሽግ የመፈተሸሕግን በመተላለፍ በይዞታ ስር የተደረጉ የዱር እንስሳት ወይም የዱር እንስሳት ውጤቶችን እንዲሁም ጥፋቱ የተፈጸመባቸውን መሳሪያዎች እንዲወረሱ ለማድረግ እንዲቻል በቁጥጥር ስር የማድረግና የሚመለከተው አካል ባወጣው የመመዝገቢያ ቅፅ መሰረት ተገቢውን ደረሰኝ ሰጥቶ የመረከብየዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ማፅደቂያ አዋጅ ቁ. 541/1999 አንቀጽ 16 ድንጋጌዎች በመተላለፍ ጥፋት ሲፈጽም የተገኘን ሰው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዞ ለሚመለከተው ህግ አስከባሪ አካል ማስረከብየደን ውጤት ተቆጣጣሪcየደን ውጤቶችን የጫነ ወይም ለመጫኑ የሚጠረጠርን ማናቸውንም ማጓጓዣ በደን መግቢያና መውጫዎች እንደአስፈላጊነቱ በሚመረጡ የሀገር ውስጥ እና የድንበር መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ አስቁሞ መፈተሸየደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 542/1999 በመተላለፍ ተዘጋጅተው ሲጓጓዙ ወይም ተከማችተው የተገኙ የደን ውጤቶችን ከድርጊቱ ተጠያቂዎች ጋር የመያዝየእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴርየቡና ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አዋጅ ቁ. 602/2000 ለማስፈጸም የሚወጡ ደንብና መመሪያዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ ቡና ሊገኝበት ይችላል ተብሎ የሚገመትን መጋዘን፣ መኖሪያ ቤት፣ የመንግስት ድርጅት፣ ማጓጓዣ ወይም ማናቸውም ሌላ ቦታ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም አስቸኳይ ሁኔታ ሲኖር ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ የመፈተሽ፣ህገ ወጥ ቡና ሲያዝ የማሸግ፣ ምርቱን የማገድ፣ የመያዝ፣ ህገ ወጥነታቸው የማያጠራጥር ሲሆን የቡናው ባለቤት ለፍርድ ቤት ቅሬታ የማቅረብ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የመውረስና የመሸጥ

ህጋዊነት በአገራችን ከስልጣን በላይ መርህን የሚደነግገው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 401 ንዑስ ቁጥር 1 እንደሚከተለው ይነበባል፡፡በሕግ የታወቀላቸው የተግባር ስልጣን ከሚዘረጋበት ውጭ ወይም በህጉ የተገደዱትን ሁኔታዎች ወይም ፎርም ባለመፈጸም…የሰውነት መብት የተሰጣቸው ድርጅቶች የሚፈጽሟቸው ስራዎች ፈራሾች ናቸው፡፡በድንጋጌው ላይ የሚስተዋለው ከቋንቋ አገላለጽ የመነጨ ብዥታ የእንግሊዝኛው ቅጂ ያጠራዋል፡፡ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡Acts performed by … bodies … in excess of the powers given to them by law or without the observance of the conditions or formalities required by law shall be of no effectበአማርኛው ላይ ‘በሕግ የታወቀላቸው የተግባር ስልጣን ከሚዘረጋበት ውጭ’ የሚለው አገላለጽ በእንግሊዝኛው ቅጂ in excess of the powers given to them by law በሚል ተተርጉሟል፡፡አስተዳደራዊ ውሳኔ፣ መመሪያ፣ ደንብ ወይም ሌላ ማናቸውም ድርጊት ለውሳኔ ሰጪው ወይም የውክልና ህግ አውጭው አካል በህግ ከፈቀደለት ስልጣን በላይ ከሆነ እንዲሁም አንዳችም የህግ ስልጣን ከሌለው ከስልጣን በላይ ነው፡፡ የስልጣን ምንጩ ህግ ነው፡፡ ስልጣን ገደቡን አልፏል የሚለው መደምደሚያ ላይ ለመድረስ አንዳንዴ ብርሀንን ከጨለማ የመለየት ያክል ቀላል ነው፡፡ አንድንድ ጊዜ ደግሞ ውስብስብ ከመሆኑ የተነሳ ከህግ፣ ከፖሊሲ እና ከህገ መንግስታዊ መርሆዎች ብሎም ከህግ አተረጓጎም መሰረታዊ ደንቦች አንጻር ጥልቅ ፍተሻ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ከዚህ በታች የቀረበው ዳሰሳ ከስልጣን ገደብ እና ህጋዊነት ጋር በተያያዘ የሰበር ችሎትን አቋም ያስቃኛል፡፡

Professor Tawnya Plumb Receives Engagement Fellowship Award


In an effort to encourage and promote engagement in the community with the University of Wyoming, the Office of Engagement and Outreach (OEO) invited UW faculty to submit proposals for Faculty Engagement Fellowships. Three University of Wyoming faculty members were selected as recipients of the 2019 Faculty Engagement Fellowship awards, representing a wide range of […]

Professor Tawnya Plumb Receives Engagement Fellowship Award

የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት። —


የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት አፈፃፀምተደጋግሞ እንደተገለፀው የመንግስት ስልጣን በወርድም በቁመትም እየሰፋ በመጣ ቁጥር ለዜጐች መብትና ነፃነት ፀር ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ የስልጣንን አስፈላጊነት አምኖ ተቀብሎታል፡፡ ውጤታማ አስተዳደር እንዲሁም ቀልጣፋ የአገልግሎት አቅርቦት እንዲኖር የሚያስር ሳይሆን የሚፈታ ስልጣን ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ከህግና ከህገ መንግስት የሚያፈነግጥ ስልጣን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ የበዘፈቀደ ድርጊት፣ ‘እንደፈለግኩኝ እሆናለው እፈልጣለው እቆርጣለው!’ የሚል አካሄድ አቅመ […]

የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት።