ህጋዊነት በአገራችን ከስልጣን በላይ መርህን የሚደነግገው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 401 ንዑስ ቁጥር 1 እንደሚከተለው ይነበባል፡፡በሕግ የታወቀላቸው የተግባር ስልጣን ከሚዘረጋበት ውጭ ወይም በህጉ የተገደዱትን ሁኔታዎች ወይም ፎርም ባለመፈጸም…የሰውነት መብት የተሰጣቸው ድርጅቶች የሚፈጽሟቸው ስራዎች ፈራሾች ናቸው፡፡በድንጋጌው ላይ የሚስተዋለው ከቋንቋ አገላለጽ የመነጨ ብዥታ የእንግሊዝኛው ቅጂ ያጠራዋል፡፡ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡Acts performed by … bodies … in excess of the powers given to them by law or without the observance of the conditions or formalities required by law shall be of no effectበአማርኛው ላይ ‘በሕግ የታወቀላቸው የተግባር ስልጣን ከሚዘረጋበት ውጭ’ የሚለው አገላለጽ በእንግሊዝኛው ቅጂ in excess of the powers given to them by law በሚል ተተርጉሟል፡፡አስተዳደራዊ ውሳኔ፣ መመሪያ፣ ደንብ ወይም ሌላ ማናቸውም ድርጊት ለውሳኔ ሰጪው ወይም የውክልና ህግ አውጭው አካል በህግ ከፈቀደለት ስልጣን በላይ ከሆነ እንዲሁም አንዳችም የህግ ስልጣን ከሌለው ከስልጣን በላይ ነው፡፡ የስልጣን ምንጩ ህግ ነው፡፡ ስልጣን ገደቡን አልፏል የሚለው መደምደሚያ ላይ ለመድረስ አንዳንዴ ብርሀንን ከጨለማ የመለየት ያክል ቀላል ነው፡፡ አንድንድ ጊዜ ደግሞ ውስብስብ ከመሆኑ የተነሳ ከህግ፣ ከፖሊሲ እና ከህገ መንግስታዊ መርሆዎች ብሎም ከህግ አተረጓጎም መሰረታዊ ደንቦች አንጻር ጥልቅ ፍተሻ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ከዚህ በታች የቀረበው ዳሰሳ ከስልጣን ገደብ እና ህጋዊነት ጋር በተያያዘ የሰበር ችሎትን አቋም ያስቃኛል፡፡
- የፅንሰ ሀሳቡ አፈጻጸም በአገራችንየፅንሰ ሀሳቡ አፈጻጸም በአገራችን ስለ አገራችን ፍርድ ቤቶች የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን ከመወራቱ በፊት መጀመሪያ የጽንሰ ሀሳቡ ይዘትና አፈጻጸም ምን እንደሚመስል ጥቂት መንደርደሪያ ነጥቦችን …
- አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት (ከፊል የህግ አውጭነት ስልጣንአስተዳደራዊ ውሳኔ ሰጭነት (ከፊል የዳኝነት ስልጣን) 3-ስልጣንና ተግባራት የስልጣን ምንጭ የመንግስት ስልጣን በህግ ከተቀመጠለት ገደብ እንዳያልፍና ይህንንም በተግባር ለማረጋገጥ መጀመ…
- በህግ የተገደበ የመንግስት ስልጣ።በህግ የተገደበ የመንግስት ስልጣ። ህጋዊነት ገለልተኛና ነፃ የዳኝነት አካል ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ሰላምና ደህነት በሕግ የተገደበ የመንግስት ስልጣን የመንግስት፣ የባለስልጣናቱና እንደራሴዎቹ ሥልጣን መገደብ …
- የዕግድ ትዕዛዝ ዕግድ በፍትሐብሔር ክርክሮች ላይ ራሱን ችሎ እንደ ውሳኔ ወይም በክርክሩ መሀል እንደ ጊዜያዊ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡የዕግድ ትዕዛዝ ዕግድ በፍትሐብሔር ክርክሮች ላይ ራሱን ችሎ እንደ ውሳኔ ወይም በክርክሩ መሀል እንደ ጊዜያዊ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ዕግድ በውጤቱ ተከሳሹ ወይም ተጠሪው አንድ ድርጊት ከመፈ…
- መስቀለኛ መዘዝመስቀለኛ መዘዝ የተከሳሽ ተከላካይ ጠበቃ ምንም ላይፈይድለት ምስክሯን “እማማ እኔን ያውቁኛል?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ ምስክር — “እንዴት አላውቅህም አንተ ሞላጫ! አውቅሃለው እንጂ! ከልጅነትህ ጀምሮ አሳምሬ አውቅሃለው፡፡ …
- የተከሳሽየተከሳሽነት ብቃትና የመንግስት ስልጣን ገደብ እንዲ…የተከሳሽነት ብቃትና የመንግስት ስልጣን ገደብ እንዲ…: የከሳሽነት ብቃት ‘አንድን የአስተዳደር ተግባር በፍርድ ቤት ወይም በሌላ የዳኝነት ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መሞገት የሚችለው ማነው?’ የሚለው ጥያቄ በአስተዳ…
- አስተዳደራዊ ስልጣንአስተዳደራዊ ስልጣን ደንብና መመሪያ ማውጣት እንዲሁም የአስተዳደር ውሳኔ እና እርምጃ መውሰድ ህግ አስፈፃሚ አካላት ህግና ፖሊሲን ለመተግበር የሚያ…

MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE HOME
MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE HOME
አስተዳደራዊ ስልጣን

አስተዳደራዊ ስልጣንደንብና መመሪያ ማውጣት እንዲሁም የአስተዳደር ውሳኔ እና እርምጃ መውሰድ ህግ አስፈፃሚ አካላት ህግና ፖሊሲን ለመተግበር የሚያከናውኗቸው ተግባራት ናቸው፡፡ የእነዚህ አካላት ዋነኛ ስልጣንና ተግባር ህግ ማውጣት አሊያም ዳኝነት መስጠት ሳይሆን ማስተዳደር ነው፡፡ አስተዳደራዊ ስልጣን ከህግ ማውጣት እና ዳኝነት መስጠት ውጪ ያሉትን ተግባራት በሙሉ ያጠቃልላል፡፡ የአስተዳደር መ/ቤቶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ይህን የእለት ተእለት የአስተዳደር ስራ በማከናወን ነው፡፡በዚህ ስልጣን ስር ከሚወድቁ በርካታ ምሳሌዎችን መካከል ሪፖርት ማቅረብ፣ ፓስፖርት መስጠት፣ ፍቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ ፀጥታ ማስከበር፣ ክስ መመስረት፣ እድገትና ሹመት መስጠት፣ ምርመራ፤ ቁጥጥርና ክትትል ማካሄድ የምክር ሀሳብ መስጠት ወዘተ ሁሉም የአስተዳደር መ/ቤቶች አስተዳደራዊ ስልጣናቸውን በመጠቀም የሚያከናውኗቸው ስራዎች ናቸው፡፡እነዚህ ተግባራት የህግ መጣስ መኖርን አለመኖሩን ለማረጋገጥ መረጃ በመሰብሰብና በማጠናቀር ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ የመረጃ አሰባሰብና ጥንቅር ስርዓት የንግድ ድርጅቶች በየጊዜው በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ሊመሰረት ይችላል፡፡ ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ የመረጃ አሰባሰብ ስርዓቱ በአካል ተገኝቶ ቀጥተኛ እና የአካባቢ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ እና የማጣራት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡የመርማሪነት ስራ ህጉ ልዩ ስልጣን በሰጣቸው መርማሪዎች የሚከናወን ሲሆን የምርመራ ሂደቱም በህግ ማእቀፍ ውስጥ ይመራል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የፖሊስ የምርመራ ተግባር ነው፡፡ ፖሊስ ወንጀል ሲፈጸም ወይም ተፈጽሟል የሚል መረጃ ከደረሰው አሊያም ተገቢ ጥርጣሬ ካደረበት የወንጀል ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ በአካል በመገኘት ተጨባጭ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ እና ተጠርጣሪውን የመመርመር ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ ረገድ ሰፊ ስልጣናት አሉት፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የአስተዳደር መ/ቤቶች የመርማሪነት፣ የቁጥጥርና ክትትል ስልጣን በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ ለፖሊስ ከተሰጠው ስልጣን ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡በአስረጂነት በተወሰኑ ህጎች ለተቆጣጠሪዎች የተሰጣቸው መጠነ ሰፊ ስልጣን በማጣቀሻነት እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡የአካባቢ ተቆጣጣሪዎች ስልጣንaሳያሳውቁ ወይም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይዙ በማንኛውም ተገቢ መስሎ በሚታያቸው ጊዜ ወደ ማንኛውም ቦታ ወይም ቅጥር ግቢ መግባትማንኛውንም ሰው ብቻውን ወይም በምስክር ፊት የመጠየቅከብክለት ጋር ግንኙነት ያለውን ማንኛውንም ወረቀት፣ ማህደር ወይም ሌላ ሰነድ መፈተሽ፣ መገልበጥ ወይም ለይቶ መቅዳትየማንኛውንም ቁስ ናሙናዎች እንደአስፈላጊነቱ ያለክፍያ መውሰድና በአካባቢ ወይም በህይወት ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ አለመሆኑን ለመወሰን መመርመር ወይም ማስመርመርየአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ቁ. 300/1995 ወይም ሌላ ህግ መከበሩን ለማረጋገጥ ሸቀጥን፣ የአመራረት ሂደትን ወይም መገልገያን በፍቶግራፍ ማንሳት፣ መለካት፣ መሳል ወይም መፈተሽአዋጁን ወይም አግባብ ያለውን ሌላ ህግ በመተላለፍ ጥፋት ተፈጽሞበታል የተባለ መሳሪያን ወይም ሌላ ነገርን መያዝየዱር እንስሳት ቁጥጥር ሠራተኛbሕግን በመተላለፍ በይዞታ ስር የተደረጉ የዱር እንስሳት ወይም የዱር እንስሳት ውጤቶች ተደብቀዋል ብሎ ለማመን በቂ ምክንያት ሲኖር ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ወደ ማንኛውም ሰው መሬት፣ ህንጻ፣ ድንኳን፣ ተሸከርካሪ፣ የአየር መንኮራኩር ወይም ጀልባ ውስጥ የመግባትና የመፈተሸ እንዲሁም ሻንጣ ወይም እሽግ የመፈተሸሕግን በመተላለፍ በይዞታ ስር የተደረጉ የዱር እንስሳት ወይም የዱር እንስሳት ውጤቶችን እንዲሁም ጥፋቱ የተፈጸመባቸውን መሳሪያዎች እንዲወረሱ ለማድረግ እንዲቻል በቁጥጥር ስር የማድረግና የሚመለከተው አካል ባወጣው የመመዝገቢያ ቅፅ መሰረት ተገቢውን ደረሰኝ ሰጥቶ የመረከብየዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ማፅደቂያ አዋጅ ቁ. 541/1999 አንቀጽ 16 ድንጋጌዎች በመተላለፍ ጥፋት ሲፈጽም የተገኘን ሰው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዞ ለሚመለከተው ህግ አስከባሪ አካል ማስረከብየደን ውጤት ተቆጣጣሪcየደን ውጤቶችን የጫነ ወይም ለመጫኑ የሚጠረጠርን ማናቸውንም ማጓጓዣ በደን መግቢያና መውጫዎች እንደአስፈላጊነቱ በሚመረጡ የሀገር ውስጥ እና የድንበር መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ አስቁሞ መፈተሸየደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 542/1999 በመተላለፍ ተዘጋጅተው ሲጓጓዙ ወይም ተከማችተው የተገኙ የደን ውጤቶችን ከድርጊቱ ተጠያቂዎች ጋር የመያዝየእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴርየቡና ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አዋጅ ቁ. 602/2000 ለማስፈጸም የሚወጡ ደንብና መመሪያዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ ቡና ሊገኝበት ይችላል ተብሎ የሚገመትን መጋዘን፣ መኖሪያ ቤት፣ የመንግስት ድርጅት፣ ማጓጓዣ ወይም ማናቸውም ሌላ ቦታ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም አስቸኳይ ሁኔታ ሲኖር ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ የመፈተሽ፣ህገ ወጥ ቡና ሲያዝ የማሸግ፣ ምርቱን የማገድ፣ የመያዝ፣ ህገ ወጥነታቸው የማያጠራጥር ሲሆን የቡናው ባለቤት ለፍርድ ቤት ቅሬታ የማቅረብ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የመውረስና የመሸጥ