
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 20/1967 የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት ድርጅት ደንብa “ኢትዮጵያ ትቅደም” አውጪው ባለሥልጣን የማስታወቂያ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት ድርጅት አዋጅ ቁጥር 15/1967 (ከዚህ ቀጥሎ “አዋጅ” እየተባለ በሚጠራው) በአንቀጽ 3 እና 9 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቶአል። አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት ድርጅት ደንብ ቁጥር 20/1967 ዓ.ም” ተብሎ ጠቀስ ይቻላል። ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም ካልሰጠው በቀር፣ በዚህ ደንብ ውስጥ፣ “ሰው” ፣ “ቴሌቪዥን” ፣ “ነጋዴ” ፣ “አዳሽ” ፣ “ሥልጣን የተሰጠው ሠራተኛ” እና “ድርጅት” በአዋጁ የተሰጣቸው ትርጓሜ ይኖራቸል። “መዝጋቢ ባልሥልጣን” ማለት የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት ድርጅት ወይም በዚህ ደንብ በአንቀጽ 4 እና 5 የተመለከቱትን ተግባሮችተ እንዲፈጽም ድርጅቱ የሚወክለው ሚኒስቴር ወይም ሌላ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ነው። ምዝገባ ነጋዴ፣ አዳሽ፣ የቴሌቪዥን ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሆነ ማንኛውም ሰው ይህ ደንብ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ90 ቀን ውስጥ መዝጋቢ ባለሥልጣን ዘንድ እየቀረበ መመዝገብ አለበት። ስለምዝገባ ፈቃድና የአገልግሎት ዋጋ መዝጋቢው ባለሥልጣን ማንኛውም ነጋዴ ወይም አዳሽ ሲመዘገብ፣ እንደነገሩ ሁኔታ በዚህ ደንብ በሠንጠረዥ ሀ ወይም ለ የተመለከተውን የምስክር ወረቀት ይሰጠዋል። መዝጋቢው ባለሥልጣን ማንኛውም የቴለቪዥን ባለቤት ወይም ባለይዞታ ሲመዘገብ በዚህ ደንብ በሠንጠረዥ ሐ የተመለከተውን ፈቃድ ይሰጠዋል። ማንኛውም የቴሌቪዥን ባለቤት ወይም ባለይዞታ ፈቃድ ስሰጠው ሃምሳ (50) ብር የአገልግሎት ዋጋ በየዓመቱ ለመዝጋቢው ባለሥልጣን ይከፍላል። መዝገብ ስለመያዝና ስለምርመራ ማንኛውም ነጋዴ፦ ሀ/ በእጁ የሚገኙትን ቴሌቪዥኖች ብዛት፣ ዓይነትና የመለያ ቁጥር፣ እንዲሁም ለ/ ያደረገውን የቴሌቪዥን ሽያጭ ወይም ኪራይ ብዛት፣ የቴሌቪዥኑን ዓይነት፣ መለያ ቁጥርና የገዢውን ወይም የተከራዩን ስምና አድራሻ ጭምር በመዝገብ መያዝ አለበት። ማንኛውም አዳሽ ለማደስ የተረከባቸውን ቴሌቪዥኖች ብዛት፣ ዓይነት፣ መለያ ቁጥርና፣ እንዲሁም የደንበኛውን ስምና አድራሻ በመዝገብ መያዝ አለበት፣ ማንኛውም ነጋዴ ወይም አዳሽ ማንኛውም ሥልጣን የተሰጠው ሠራተኛ ሲጠይቀው ለምርመራ ወይም ለቅጂ መዝገቡን የማቅረብ ግዴት አለበት። ማንኛውም የቴሌቪዥን ባለቤት ወይም ባለይዞታ ማንኛውም ምልጣን የተሰጠው ሠራተኛ ሲጠይቀው ፈቃዱን ለምርመራ የማቅረብ ግዴታ አለበት። ያለፈቃድ በቴሌቪዥን መጠቀም ስለመከልከሉ ማንኛውም ሰው በዚህ ደንብ መሠረት ፈቃድ ካልያዘ በቀር በቴሌቪዥን መጠቀም አይችልም። ደንብ ስለመተላለፍ ይህን ደንብ የጣሰ ወይም ያልፈጸመ ሰው በአዋጁ አንቀጽ 10 መሠረት ይቀጣል። ደንቡ ስለሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከመስከረም 3 ቀን 1968 ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል። አዲስ አበባ ነሐሴ 19 ቀን 1967 ዓ.ም ሻለቃ ያዕቆብ ገብረ እግዚአብሔር የማስታወቂያ ሚኒስትር ሠንጠረዥ ሀ የቴሌቪዥን ነጋዴ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ጉርድ ፎቶግራፍ የሴሪ ቁጥር ……………………………. የምስክር ወቀት ቁጥር ………………. የደረሰኝ ቁጥር ………………………. 1. የነጋዴው ስም ………………………. 2. አድራሻ ………………. 3. የፖ.ግ. ቁጥር …………………………. 4. ስልክ …………………… 5. ዜግነት ………………………………. 6. የሥራ ዓይነት ……………. 7. የንግድ ፈቃድ ቁጥር …………………………. የተመዘገበበት ቀን …………………………. ፊርማ …………………………. ማኅተም ………………………. ሠንጠረዥ ለ. የቴሌቪዥን አዳሽ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ጉርድ ፎቶግራፍ የሴሪ ቁጥር ……………………………. የፈቃድ ቁጥር …………………………. የደረሰኝ ቁጥር …………………………. 1. የአዳሹ ስም …………………………. 2. አድራሻ …………………. 3. የፖ.ግ. ቁጥር …………………………. 4. ስልክ …………………… 5. ዜግነት ………………………………. 6. የሥራ ዓይነት ……………. 7. የንግድ ፈቃድ ቁጥር …………………………. የተመዘገበበት ቀን …………………………. ፊርማ …………………………. ማኅተም ………………………. ሠንጠረዥ ሐ. የቴሌቪዥን ባለቤት ወይም ባለይዞታ የምስክር ወረቀት ጉርድ ፎቶግራፍ የሴሪ ቁጥር ……………………………. የፈቃድ ቁጥር …………………………. የደረሰኝ ቁጥር …………………………. 1.የባለቤት ወይም ባለይዞታ ስም ………………………… 2. አድራሻ …………… ሀ. መኖሪያ ………………. ለ. የሥራ ቦታ …………… 3.ዜግነት ……………………………………….ፖ.ሣ.ቁ ሀ. መኖሪያ ……… ለ. የሥራ ቦታ —————– – ስልክ ሀ. መኖሪያ …………. ለ. የሥራ ቦታ ………………. 4.ሥራ …………………………………………………………………………………………. 5.የመታወቂያ ካርድ ቁጥር ……………………………………………………………………. የቴሌቪዥን መለያ ………………………………………………………………………… ዓይነት መጠን የመለያ ቁጥር ………………………. ……………………… ……………………. ቀን …………………. ፊርማ …………………. ማኅተም ………………… ማሳሰቢያ፦ ይህ የፈቃድ ወረቀት የሚያገለግለው ለ19……… ዓ.ም ብቻ ነው። ዕድሳት ————————— ————————— ————————— ————————— ————————— —————————

You must be logged in to post a comment.