Daily Archives: August 15, 2020
አቤቱታ አቀራረብ
የአቤቱታ አቀራረብ ስርዓትየአጣሪ ዳኝነት አቤቱታ የሚስተናገድበትስርዓት ከመደበኛው የፍትሐብሔር የክስ አቤቱታ አቀራረብ ስርዓት ይለያል፡፡አንድ የመስኩ ጸሐፊ ይህን የተለየየሚያደርገውን ባህርይ እንደሚከተለውይገልጸዋል፡፡A claim for judicial review is something out of the ordinary: the court decides the dispute without a trial. The point of a trial in an ordinary claim is to resolve the issues of fact on which a claim is based. The summary process in a claim for judicial review is designed on the assumption that resolving issues of fact is not the point of the litigation. The point is for the court to review the lawfulness of a public authority’s conduct, and there is often no dispute as to what the public authority has done or proposes to doaበእንግሊዝ የአስተዳደር ህግ የአጣሪ ዳኝነትአቤቱታ ማለት፤[A] claim to review the lawfulness of (i) an enactment; or (ii) a decision, action or failure to act in relation to the exercise of a public functionbበእንግሊዝ አጣሪ ዳኝነት አቤቱታ እንደመደበኛ ክስ በቀጥታ አይቀርብም፡፡መጀመሪያ የፍርድ ቤቱ ይሁንታያስፈልገዋል፡፡c ፍርድ ቤቱ አቤቱታውንመርምሮ ጉዳዩ በፍርድ ክለሳ መልክእንዲስተናገድ ካልፈቀደ በቀር አቤቱታውለተቃራኒው ወገን እንዲደርስአይደረግም፡፡ ይህ የፈቃድ ቅድመ ሁኔታየአጣሪ ዳኝነት አንዱና ዓይነተኛው መገለጫነው፡፡ አቤቱታው የሚቀርብበት ጊዜበገደብ መታጠሩ ደግሞ ሁለተኛው አንኳርባህርይ ነው፡፡ ክስ የማቅረቢያ ጊዜንበተመለከተ በመደበኛ የፍትሐ ብሔርክርክሮች ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው የይርጋደንብ ነው፡፡ ይርጋ ከጊዜ ገደብ ይለያል፡፡ይርጋ በተከራካሪው ወገን እስካልተነሳ ድረስፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ተፈጻሚአያደርገውም፡፡ በተጨማሪም ከጊዜ መጠኑአንጻር በዓመታት እንጂ በወራትአይለካም፡፡በአጣሪ ዳኝነት አቤቱታ ላይ የሚቀመጠውየጊዜ ገደብ የተንዛዙ ክርክሮች በውጤታማአስተዳደር ላይ የሚያስከትሉትን አሉታዊተጽዕኖ ለማስወገድ ያለመ ነው፡፡ ስለሆነምፍርድ ቤት ጊዜው ያለፈበትን አቤቱታበራሱ አነሳሽነት አይቀበልም፡፡ የጊዜውመጠንም በአማካይ ከሶስት ወራትአይበልጥም፡፡ የሶስት ወራት ጊዜውቢኖርም አቤቱታው ሳይውል ሳያድርወዲያኑ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ አቤቱታአቅራቢው እስከ ጊዜ ገደቡ ማብቂያ ድረስ ተኝቶ እንዲጠብቅ አይፈቀድለትም፡፡ይህም ማለት አቤቱታው በጊዜ ገደቡውስጥ ቢቀርብም አለአግባብ ከዘገየ ውድቅ ሊደረግ ይችላል፡፡d

You must be logged in to post a comment.