
ለጠቅላይ ሚኒስትር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ አካላትን ማቋቋሚያ ህጎች አዋጅ ቁጥር 257/1994 በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል። አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 257/1994” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል። መቋቋም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ከዚህ በኋላ (ምከር ቤቱ) እየተባለ የሚጠራ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል። ምክር ቤቱ እንዳስፈላጊነቱ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ሊኖሩት ይችላል። የምክር ቤቱ አባላት ምክር ቤቱ የሚከተሉት ቋሚ አባላት ይኖሩታል፣
የምክር ቤቱ ተግባር ምክር ቤቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት የሚመለከቱ የውጭና የመከላከያ ፖሊሲዎች እንዲጣጣሙ በማድረግና በሚገባ ተግባራዊ መደረጋቸውን በመከ ታተል ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያማክራል። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ምክር ቤቱ፣ ሀ/ ለሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት የሥጋት ምንጭ የሆኑ ሁኔታዎችን በመገምገም ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ሃሣብ ያቀርባል፤ ለ/ የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት ለማስጠበቅ የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚመለከቱ የአፈጻጸም መመሪያዎች ያመነጫል፤ ሐ/ የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት በሚነካ ማናቸውም ጉዳይ ላይ ይመከራል። ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93 መሠረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲደነገግም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ የሚወሰኑ ተግባሮችን ያከናውናል። የምክር ቤቱ ስብሰባዎች ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲጠራ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል። በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አባላት ከተገኙ ምልአተ ጉባዔ ይኖራል። ምክር ቤቱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት መመሪያ ሊያወጣ ይችላል። የምክር ቤቱ ኮሚቴዎች በዚህ አዋጅ አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት የሚቋቋሙ ኮሚቴዎች የሚኖሩዋቸው አባላትና ዝርዝር ተግባራቸው በምክር ቤቱ ይወሰናል።
