MISCELLANEOUS PROVISIONS


Miscellaneous Provisions  

Article 319. – Inapplicable Laws.   1) The following provisions shall not be applicable in the Administrations where this Code applies: (a) Provisions of the Civil Code of 1960 on Persons (Book One, Article 198-338); (b) Provisions of the Civil Code of 1960 on Family and Successions (Book Two, Article 550-825). 2) Any laws, regulations, directives, decisions or practices inconsistent with this Code shall not be applicable on matters provided in this Code.   Article 320. – Rights Acquired Under Repealed Laws.   1) Unless otherwise expressly provided to the contrary, legal situations created prior to the coming into force of this Code shall remain valid notwithstanding that this Code modifies the conditions under which such situations may be created. 2) Unless otherwise expressly provide to the contrary, this Code shall not change effects arising out of legal situations created under the repealed law prior to the coming into force of this Code.   Article 321. – Registration.   1) The Federal Government shall, within six months from the coming into force of this Code, issue registration law applicable to the Administrations where this Code is to be enforced and establish the necessary institutions. 2) Until the Office of Civil Status is established in accordance with Sub-Art. (1) of this Article, certificates of birth, marriage, and other relevant certificated issued or to be issued by an appropriate authority of the Administration where this Code is applicable shall be deemed to have been issued by the Office of Civil Status and considered valid.   Article 322. – Pending Family Cases.   1) Family cases pending before court prior to the coming into force of this Code shall be settled in accordance with this Code. 2) All divorce cases pending before family arbitrators before the coming into force of this Code in accordance with the repealed law regular courts having jurisdiction. 3) The courts shall decide these case in accordance with the provisions of this Code.   Article 323. – Power to Issue Regulations.   1) The Council of Ministers may issue Regulations for the implementation of this Code. 2) The Administrations where this Code shall be applicable may issue directives and Rules of procedure necessary for the implementation of this Code.

Contract of Supplies


Contract of supplies

Art. 3297 – Performance of contract.
(1)    The supplier shall have the initiative and choice as regards the manner of performing the contract.
(2)    He may apply to whom he things fit for the purchase of the materials and articles required for the performance of his obligations.Art. 3298 – Risks.
(1)    The supplier shall bear the risks of the loss of the thing which supervenes through force majeure until the acceptance of the thing by the administrative authorities.
(2)    The administrative authorities shall be bound by the liability of a depositary during the time between the dare of the deposit of the supplies in their warehouse and that on which a final decision is taken as to the acceptance or rejection thereof.Art. 3299 – Acceptance of merchandise.
The acceptance of merchandise shall take place in the manner and at the time specified in the contract.
Art. 3300 – Postponement of acceptance.
(1)    The administrative authorities may postpone the acceptance where the supplies are defective.
(2)    In such case, they shall inform the supplier of the time within which he shall remedy the defects of the supplies.Art. 3301 – Rejection of merchandise.
The administrative authorities shall reject the supplies which are not in conformity with the contract where such defect takes away the utility which such supplies have for the administrative authorities and the supplier is unable or refuses to remedy such defect within the required time.Art. 3302 – Expenses of verification of merchandise.
(1)    The expenses of the verification of the merchandise shall be borne by the supplier as regards the operations effected in his establishment and by the administrative authorities as regards other operations.
(2)    The supplier may be present at the verifications.
(3)    He shall be informed of the time chosen for such operations and be admitted to put forward his remarks.Art. 3303 – Liability of supplier.
(1)    The exercise of supervision on the part of the administrative authorities shall not affect the liability of the supplier.
(2)    It shall not restrict the right of the administrative authorities is to reject the supplies which are recognized to be defective at the time of acceptance or to cause to be repaired during the period of warranty the parts which are recognized to be defective.Art. 3304 – Performance by reason of default.
(1)    In the case of a contract of supplies, the performance by reason of default may be ordered where the supplier fails to carry out an urgent delivery or a contract has been cancelled.
(2)    The administrative authorities shall take the place of the defaulting supplier in purchasing the supplies from another supplier or in manufacturing them themselves.
(3)    Nothing shall affect the right of the administrative authorities to claim damages from the defaulting supplier.Art. 3305 – Power of the court.
(1)    The court may not cancel the sanctions of coercion or of dissolution applied by the administrative authorities against the other party to a contract of supplies.
(2)    In such contracts, it may only investigate whether the sanctions have been applied under conditions of such nature as to create a right to compensation in favour of the supplier.
(3)    Nothing shall affect the provision of art. 3306.Art. 3306 – Preliminary claim to the administrative authorities.
(1)    The supplier shall firstly make his claim to the administrative authority in the case and within the measure in which the contract imposes upon him such preliminary procedure.
(2)    A recourse to the judicial authorities which is not preceded by the obligatory claim to the administrative authorities shall not be admissible.
(3)    Where the contract prescribed a period for the claim to the administrative authorities and the supplier has failed to make such claim in due time, such claim shall be barred and the recourse to the judicial authorities shall not be admissible.

የስልጣን ባህርይ እና መገለጫው።


የስልጣን ባህርይ እና መገለጫው


በአስተዳደር ህግ ውስጥ ስልጣን (power) የሚለው ጽንስ ሀሳብ ከአንድ አስተዳደራዊ ድርጊት በስተጀርባ ህጋዊ ብቃት መኖሩን ያመለክታል፡፡ የአስተዳደር መ/ቤቶች ወይም የመንግስት ባለስልጣናት የአንድን ግለሰብ ወይም ድርጅት መብትና ጥቅም የሚነካ ድርጊት ሲፈፅሙ ይህን የሚፈቅድላቸው ከህግ የመነጨ ስልጣን ሊኖራቸው ይገባል፡፡

ስልጣን ሁሉ ገደብ አለው፡፡ ይህ የአስተዳደር ህግ መነሻ ነው፡፡ የስልጣን ልኩና ገደቡ ካልተሰመረ የመንግስት አስተዳደር በህጋዊነት ማዕቀፍ ውስጥ አይከናወንም፡፡

ስልጣን የፍፁምነት ባህርይ የለውም፡፡ ፍፁም ስልጣን ዘውዳዊ (ንጉሳዊ) ስልጣን ብቻ ነው፡፡ ስልጣን ፍፁም ከሆነ የአስተዳደር ህግ ሆነ ህግ በጠቅላላው አያስፈልግም፡፡ ለዚህም ነው የስልጣን ገደብ የአስተዳደር ህግ መነሻና መሰረቱ ነው የተባለው፡፡ በአጠቃላይ አነጋገር የስልጣን መገልገል በተለያዩ መለኪያዎች፤ ቅድመ ሁኔታዎች እና ስነ ስርዓቶች ገደብ ይበጅለታል፡፡ በስልጣን ላይ የሚደረግ ገደብ በተለያየ መልኩ ይገለጻል፡፡

ለአብነት በሚከተሉት ህጎች ላይ ስልጣን የተሰጠበትንና የተገደበበትን መንገድ እንመልከት፤

የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነትን በማወቅ በአስተዳደር ክፍል ለአንድ ሰው የተሰጠ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ማስረጃው የተሰጠው ሰው የዚሁ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት እንደሆነ እንደሚያስቆጥረው በፍ/ህ/ቁ. 1195/1/ ተመልክቷል፡፡ ሆኖም ይህ የሕሊና ግምት በ1196 ላይ የተዘረዘሩት የሚከተሉት ምክንያቶች መኖራቸው ማስረዳት ከተቻለ ፈራሽ ይሆናል፡፡

(ሀ) የባለርስትነት የምስክር ወረቀት የተሰጠው ከደንብ ውጭ በሆነ አሠራር ወይም ይህን ለመስጠት ሥልጣን በሌለው የአስተዳደር ክፍል የሆነ እንደሆነ

(ለ) የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት የተሰጠው በማይረጋ ጽሑፍ መሠረት የሆነ እንደሆነ ወይም ለከሳሹ መቃወሚያ ሊሆን በማይችል ጽሑፍ መሠረት የሆነ እንደሆነ

(ሐ) ከሳሹ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ያገኘው፤ የገዛው የእርስት የምስክር ወረቀት ከተሰጠ በኋላ መሆኑን ማስረዳት የቻለ እንደሆነ

በፌደራል መንግስት የፋይናንስ አስተዳደር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁ. 879/2009 አንቀጽ 2/20/ በድሮው አዋጅ ቁ. 648/2001 ላይ ተጨማሪ ሆኖ በገባው አንቀጽ 73 መሰረት በማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት የተሾመ ወይም የተመደበ ሰው በአዋጆቹና አዋጆቹን ተከትለው በወጡት ደንብ እና መመሪያዎች መሠረት እንደሁኔታው ዕቅድ ወይም የሂሣብ ሪፖርት ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴሩ ወይም ለውጭ ኦዲተር ያላቀረበ ወይም መቅረቡን ያላረጋገጠ ወይም በውጭ ኦዲት ወይም በውስጥ ኦዲት ሪፖርት በተመለከተው መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ያልወሰደ ወይም እርምጃ መወሰዱን ያላረጋገጠ እንደሆነ ኃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣቱ ከብር 5 ሺ እስከ ብር 10 ሺ በሚደርስ ቅጣት ይቀጣል፡፡

የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ በአዋጅ ቁ. 923/2008 አንቀጽ 42/2/ ስር የተመለከተውን ጥፋትa መፈጸሙ ሲረጋገጥ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም አግባብ ያለው ባለሥልጣን የሚከተሉትን ፈቃድ የማገድ አስተዳደራዊ እርምጃዎች የመውሰድ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

ሀ) ድርጊቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጸመ ከሆነ ለሦስት ወር፣

ለ) ድርጊቱ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ከሆነ ለስድስት ወር፣

ሐ) ድርጊቱ ለሦስተኛ ጊዜ የተፈጸመ ከሆነ ለአሥራ ሁለት ወር፣

ከላይ በምሳሌነት የቀረቡት ድንጋጌዎች በአጠቃላይ ይዘታቸው ስልጣን ሰጭ ቢሆኑም በዝርዝር ሲፈተሹ የስልጣኑን ገደብ ጭምር ያሰምራሉ፡፡ በፍ/ህ/ቁ. 1196 (ተ.ቁ. 1) የተዘረዘሩት ሶስት ሁኔታዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የመሰረዝ ስልጣን በተሰጠው አካል ላይ የተቀመጡ ገደቦች ናቸው፡፡ ስረዛው ህጋዊነት እንዲኖረው በሁኔታዎቹ ስር ያሉ የፍሬ ነገር እና የህግ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ለምሳሌ የምሰክር ወረቀቱ ከደንብ ውጭ በሆነ አሠራር ተሰጥቷል በሚል ለመሰረዝ መጀመሪያ ለዚሁ ዓላማ ተብሎ የወጣ ደንብ መኖሩ መረጋገጥ አለበት፡፡ በመቀጠል በምስክር ወረቀቱ አሰጣጥ ላይ ደንቡን በሚቃረን መልኩ የተፈጸመው ተግባር ምን እንደሆነ ተለይቶ መታወቅና በማስረጃ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ከደንብ ውጭ የሆነው አሰራር ምስክር ወረቀቱን ለማሰረዝ የሚያበቃና መሰረታዊ ካልሆነ የመሰረዝ እርምጃው የሚወሰድበት አሳማኝ ህጋዊነት ምክንያት የለም፡፡ ለምሳሌ የቴምብር ቀረጥ ሳይከፈል ከተረሳ ክፍያው ሊፈጸም ይገባል እንጂ በዚህ እንጭፍጫፊ ምክንያት ብቻ የስረዛ እርምጃ ሊወሰድ አይገባም፡፡

በተራ ቁ. 2 ላይ እንዲሁ እያንዳንዱ ሐረግ የስልጣን ገደብን ይወስናል፡፡ በመጀመሪያ በመንግሥት መሥሪያ ቤት የተሾመው ወይም የተመደበ ሰው ሪፖርት የማቅረብ፣ እንዲቀርብ የማስደረግና በሪፖርቱ መሰረት ማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ስልጣንና ተግባሩ ስለመሆኑ ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ ከዚያም አልፎ ግዴታውን ስላለመወጣቱ በፍሬ ነገር ረገድ በበቂ ማስረጃ መደገፍ ይኖርበታል፡፡ ፍሬ ነገሮቹም ግዴታውን ስላለመወጣቱ አሳማኝ ድምዳሜ ላይ የሚያደርሱ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ግልጽ ከሆነው ገደብ በተጨማሪ በቅጣት አወሳሰኑ ላይ ህግ አውጭው በተዘዋዋሪ ማዕቀብ አድርጓል፡፡ የቅጣ መጠኑ ከ5 ሺ እስከ 10 ሺ ብር ድረስ እንደመሆኑ የጥፋቱ ደረጃ እና ቅጣቱ ሚዛናዊ በሚባል መልኩ የተመጣጣኝነትን መለኪያ ማሟላት ይኖርበታል፡፡

በተራ ቁ. 3 ላይ ጥፋት ተብሎ በህጉ የተዘረዘረው ድርጊት በማስረጃ ሊደገፍና ቅጣቱ ሲወሰን ቅደም ተከተሉን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡ ከድንጋጌው ይዘት ከሚመዘዙት ገደቦች በተጨማሪ በአዋጁ ሌሎች ድንጋጌዎች ላይ ውሳኔ ሰጭው ስልጣኑን ሲገለገል ሊከተላቸው የሚገቡ የስነ ስርዓት ቅድመ ሁኔታዎች ተዘርግቷል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 26 በተቀመጠው ስርዓት መሰረት መብቴ ተጥሷል የሚል ሰራተኛ አቤቱታውን አዘጋጅቶ ሲያቀርብ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም አግባብ ያለው ባለሥልጣን የአቤቱታውን ቅጂና ደጋፊ ሰነዶች በማያያዝ አቤቱታ የቀረበበት ኤጀንሲ በአሥር የሥራ ቀናት ውስጥ መልሱን በጽሁፍ እንዲያቀርብ የመጥሪያ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ የመጥሪያ አሰጣጥ ስርዓቱ በአዋጁ ላይ ባይጠቀስም ድንጋጌው የተከሳሹን የመሰማት መብት የማስጠበቅ ዓላማ ያለው እንደመሆኑ መጥሪያው በአግባቡ ሊደርሰው ይገባል፡፡ መጥሪያ ሳይላክና ተከሳሹ ደርሶት መልሱን ሳያቀርብ ሚኒስቴሩ ወይም ባለስልጣኑ በራሱ አነሳሽነት ቅሬታ የቀረበበትን ድርጊት አጣርቶ የሚወስደው እርምጃ ህገ ወጥ ነው፡፡ ምክንያቱም ተከሳሹ ሳይሰማ አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በአዋጁ ስልጣን አልተሰጠውም፡፡

Appeals and Applications to Set Aside Judgments Given in Default


Appeals and Applications to Set Aside Judgments Given in Default

TITLE 1

Appeal

Art.181-Principle

(1) An appeal shall lie in accordance with the provisions of his Book from a judgment of a criminal court whether it be a judgment convicting, discharging or acquitting an accused person.
(2) A second appeal shall lie in accordance with the provisions of Art. 182.

Art.182- Courts having appellate jurisdiction.

(1) An appeal shall lie from the decision of:
(a) A Woreda Court to the Awradja Court in whose area of jurisdiction such Woreda Court lies.
(b) An Awradja Court to the High Court:
(c) The High Court to the Supreme Imperial Court.
(2)A second appeal shall lie from a decision of:
(a) the Awradja Court in its appellate jurisdiction to the High Court:
(b) the High Court in its appellate jurisdiction to the supreme Imperial Court.

Art.183-Applicaton to His Imperial Majesty’s Chilot.

(1) Nothing in Art.182 shall prevent an appellant who has exhausted his rights of appeal under Art.182 from applying to His Imperial Majest’s Chilot for a review of the case.
(2) The application to His Imperial Majesty Chilot shall be accompanied by:
(a) A copy of the judgment or judgment with which the applicant is dissatisfied; and
(b) A reasoned memorandum setting forth clearly and concisely the reasons on which the applicant bases his request for a review.

Art.184-No interlocutor appeals.

No interlocutory appeal shall lie from a decision of the court:
(a) Granting or refusing an adjournment under Art.94:0r
(b) Regarding an objection under Art.131;or
(c) Regarding the admissibility or non-admissibility of evidence under Art.146.but any such decision may form the subject of a ground of appeal where an appeal is lodged against conviction, discharge or acquittal.

Art.185-Appeal against conviction and sentence.

(1) A convicted person may appeal against his conviction sentence; Provided that no appeal may be lodged by a convicted person who has pleaded guilty and has been convicted on such plea except as to the extent or the legality of the sentence.
(2) The public prosecutor may appeal against a judgment of acquittal, discharge or on the ground of inadequacy of sentence.
(3) Where a prosecution is conducted by a private prosecutor the private prosecutor may appeal in the same manner as is provided in sub-article (2).
(4) An appeal by a young person or by an incapable person shall be through his legal representative.

Art.186-Appeal where injured party claims compensation

(1) Where the court refuses to grant compensation under Art.100 penal Code the injured party may appeal against such decision.
(2) Where the court grants compensation the accused may appeal against such decision.
(3) An appeal shall lie against the amount of compensation awarded in accordance with the provisions of Art.2153 Civil Code.
(4) An appeal under this Article shall be heard by the criminal court of appeal where there is an appeal against conviction or sentence, but shall be heard by the civil court of appeal where there is no appeal against conviction or sentence or such appeal is withdrawn.

Art.187.Notice of appeal and memorandum of appeal.

(1) Notice of appeal against a judgment shall be given by the appellant or his advocate within fifteen days of the delivery of the judgment appealed against. On receipt of such notice of appeal, the registrar shall cause the judgment appealed against to be copied and handed to the appellant or his advocate and where the appellant is in custody the copy shall be sent to the superintendent of the prison in which he is confined for service on the appellant. Such copy shall be dated when completed and the date on which it is handed to the appellant or his advocate or is sent to the superintendent of the prison shall be certified by the registrar .
(2) The memorandum of appeal under Art, 189 shall be filed within thirty days of the receipt of the copy of the decision appealed against. The notice and memorandum of appeal shall be field in the registry of the court which gave the judgment appealed against.
(3) Where the appellant is in custody the superintendent of the prison in which he is confined shall forward the memorandum of appeal without delay to the curt against whose decision an appeal is made.
(4) A copy of the memorandum of appeal shall be served on the respondent to the appeal.

Art.188-Stay of execution.

(1) Where a convicted person has given notice of appeal no sentence of flogging shall be carried out until the appeal has been heard or abandoned by the appellant.
(2) Where an accused person is released on bail pending the hearing of his appeal the sentence of imprisonment shall not commence until the court of appeal delivers its judgment.
(3) Any measures which have been ordered by the court against whose judgment an appeal has been filed shall be carried out notwithstanding an appeal.
(4) There shall be no stay of execution in respect of the payment of compensation or costs.
(5) An application for stay of execution may be make to the court of appeal at any time before the appeal is heard or at the hearing of the appeal.

Art.189-Content of memorandum of appeal.

(1) The memorandum of appeal shall set forth concisely and under distinct heads the grounds of objection to the judgment appealed against without and arguments and such ground shall be numbered consecutively. The memorandum shall be accompanied by a copy of the judgment appealed against. The memorandum of appeal shall state the nature of the relief that is sought.
(2) The memorandum of appeal shall be signed by the appellant and his advocate, if any.

Art.190-Record and exhibits to be forwarded to court of appeal.

(1) On receipt of the memorandum of appeal the court against whose judgment an appeal has been filed shall prepare without delay within fifteen days a copy of the record and forward it together with the appeal record (if any ), the notice and the memorandum of appeal and all exhibits to the court of appeal.
(2) The court of appeal may dispense with the making of a copy of the record where the making of such copy may delay unduly the hearing of the appeal and the Court may order the original file to be produced.

Art.191- Application for leave to appeal out of time.

(1) Where notice of appeal or a memorandum on appeal is filed out of time, the court against whose judgment the appeal is filed shall refuse to accept such notice or memorandum and shall require the person submitting such notice or memorandum to apply in writing to the court of appeal for leave to appeal out of time.
(2) The application shall state clearly the reasons why the appeal should be heard out of time and the reasons which occasioned the delay.
(3) The court of appeal shall not give leave to appeal out of time unless it is satisfied that the delay was occasioned by the default of the applicant.
(4) Where leave to appeal out of time is given the court of appeal shall fix the date by which the memorandum of appeal is to be filed.

Art.192-Hearing

The president of the court of appeal shall fix a day on which the appeal will be heard and the parties to the appeal shall be notified. The appellant shall open the appeal, the respondent shall reply and the appellant shall be entitled to reply.

Art.193-Absence of a party to the appeal.

(1) Where the appellant or his advocate is not present on the day fixed for the appeal and he has been notified of the hearing date, the appeal shall be struck out:
Provided that the appeal may be restored to the list where the appellant or his advocate can show that he was not present owing to circumstances beyond his control.
(2) Where the respondent or his advocate is not present the appeal shall proceed in his absence.

Art:194-Additional evidence.

(1) In dealing with an appeal the court of appeal, if it thinks additional evidence is necessary , shall record its reasons and may take such evidence itself.
(2) Evidence taken in pursuance of sub-art (1) shall be taken as if it were evidence taken at the trial in the court of first instance.

Art.195- Power of court of appeal.

(1) At the hearing of an appeal the court of appeal shall dismiss the appeal where there is no sufficient ground for interference.
(2) Where it consider that there is sufficient ground for interference, the court of appeal may:
(a) On an appeal from an order of acquittal or discharge reverse such order and direct that the accused be retried by a court of competent jurisdiction or find him guilty and sentence him according to law; or
(b) On an appeal from conviction and sentence:
(i) reverse the finding and sentence and acquit the accused: or
(ii) with or without altering the finding, maintain, increase or reduce the sentence:
(C) on an appeal from conviction only reverse the finding and sentence and acquit the accused;
(d) on an appeal from sentence the conviction but alters the sentence or vice versa a second appeal shall lie only in respect of the conviction or sentence which has been altered.

Art.196-where one appeal in case concerning several convicted persons.

(1) Where a court of appeal hears an appeal which concerns several convicted persons but only one of them appeals, it may direct that its judgment be applied to those other accused as though they had appealed where:
(a) The judgment is to the benefit of the appellant, and
(b) Had the accused appealed they would have benefitted similarly,
(2) No order made to the prejudice of an appellant may be applied to a person who has not appealed.

  የምርጫ ሕጎችደንብ ቁጥር 1/2001


  • ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የመምረጥ እና ወይም የመመረጥ መብቱን በሥራ ላይ ሲያውል በምርጫ ሂደት የሚነሱ ክርክሮችን በወቅቱ በመፍታት ሁሉም ዜጋ ዲሞክራሲያዊ መብቱን በሥራ ላይ እንዲያውል ማስቻሉ ተገቢ በመሆኑ፣ ምርጫን ነፃና ፍትሃዊ ለማድረግ በምርጫ አፈጻጸም በየደረጃው የሚነሱ አቤቱታዎችን ተመልክቶ ወቅታዊ መፍትሄ የሚሰጥ በየደረጃው የሚቋቋመውን አካል አደረጃጀት እና አሠራር በመደንገግ በምርጫ ሂደት ለሚነሱ አቤቱታዎችና ክርክሮች አፈታት ግልጽ አሰራር ማስፈን በማስፈለጉ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በተሻሻለው የኢትዮጵያ ምርጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 19፣ አንቀጽ 19 ንዑስ አንቀጽ 12፣ አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 5፣ አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ 10፣ አንቀጽ 92 ንዑስ አንቀጽ 4 እና አንቀጽ 110 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል።
  • ክፍል አንድ
    ጠቅላላ
    • አጭር ርዕስ
    • ይህ ደንብ “በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየደረጃው የሚቋቋም አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀትና አሠራር ደንብ ቁጥር 1/2001 ዓ.ም” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
    • ትርጓሜ
    • የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ፤
    • “ኢ.ፌ.ዲ.ሪ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነው።
    • “የምርጫ ሕግ” ማለት የተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም. ነው።
    • “ቦንድ” ማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ነው።
    • “ተንቀሳቃሽ ወኪል” ማለት በምርጫ ለመወዳደር በተመዘገበ የፖለቲካ ድርጅት ወይም በግል እጩ ተወክሎ በአንድ ምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች እየተንቀሳቀሰ የምርጫ ሂደትንና የወከለውን ድርጅት ወይም የግል እጩ መብት መከበር የሚከታተል ሰው ነው።
    • “ተቀማጭ ወኪል” ማለት በምርጫ ለመወዳደር በተመዘገበ የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል እጩ የሚወከልና በምርጫ ክልልና በምርጫ ጣቢያ ተቀምጦ የምርጫ ሂደትንና የወከለውን አካል መብት መከበርን የሚከታተል ሰው ነው።
    • “የሕዝብ ታዛቢ” ማለት በእያንዳንዱ ምርጫ ክልል እና ምርጫ ጣቢያ ምርጫን እንዲታዘቡ በህዝብ የሚመረጡ ገለልተኛ የአካባቢ ነዋሪዎች ናቸው።
    • “ክልል” ማለት በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 47 መሠረት የተቋቋመ ክልል ሲሆን ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል አዲስ አበባንና ድሬዳዋን ይጨምራል።
    • “የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት” ማለት በምርጫ ሕጉ መሠረት በክልል ደረጃ ምርጫን የሚያስተባብር በቦርዱ በቋሚነት የሚቋቋም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ነው።
    • “አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ” ማለት በየደረጃው በሚገኝ በክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት፣ ምርጫ ክልል እና የምርጫ ጣቢያ ለሚነሱ ቅሬታዎች አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሰጥ በምርጫ ህጉ እና በዚህ ደንብ መሠረት ለምርጫ ወቅት የሚቋቋም ኮሚቴ ነው።
    • “የምርጫ ክልል” ማለት ለምርጫ አፈጻጸም እንዲያመች እና ህዝቡ ወኪሎቹን እንዲመርጥ በሕግ መሠረት የሀገሪቱ ግዛት ተከፋፍሎ የሚደራጅ የምርጫ አካባቢ ነው።
    • “የምርጫ ጣቢያ” ማለት በየደረጃው በሚካሄዱ ምርጫዎች ምዝገባ የሚካሄድበት፣ መራጮች ድምፅ የሚሰጡበት እና ቆጠራ የሚካሄድበት ቦታ ነው።
    • “የምርጫ አስፈጻሚ” ማለት በየደረጃው ለሚካሄዱ ምርጫ በተቋቀሙ የምርጫ ጽሕፈት ቤቶች በቋሚነት፣ በኮንትራት ወይም በጊዜያዊነት ተመድቦ በህግ መሠረት ምርጫን የሚያስፈጽም ሰው ነው።
    • “አቤቱታ” ማለት በየደረጃው ለሚገኙ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አካላት በጽሑፍ የሚቀርብ ቅሬታ ነው።
    • “ይግባኝ” ማለት በየደረጃው በሚገኙ የበታች አቤቱታ ሰሚ አካላት ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ሰው በዚህ ደንብና ቦርዱ ባዘጋጀው ቅጽ መሠረት በጽሑፍ ለበላይ አቤቱታ ሰሚ አካል የሚቀርብ አቤቱታ ነው።
    • “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው።
    • አተረጓጎም
    • በዚህ ደንብ ለሚፈጠር የህግ ክፍተት የኢፌዲሪ ህገመንግሥትን እና የተሻሻለውን የኢትዮጵያ ምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም ጋር በማጣጣም መተርጎም አለበት።
    • የተፈጻሚነት ወሰን
    • ይህ ደንብ በምርጫ ህጉ መሠረት በየደረጃው በሚካሄዱ ምርጫዎች ለሚነሱ ቅሬታዎች ተፈጻሚ ይሆናል።
    • የጾታ አገላለፅ
    • በዚህ መመሪያ ውስጥ በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም ፆታ ያካትታል።
  • ክፍል ሁለት
    ስለአቤቱታ ሰሚ አካል አደረጃጀት
    • ጠቅላላ
    • ቦርዱ በምርጫ ህጉ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 11 መሠረት በምርጫ ሂደት ለሚከሰቱ አለመግባባቶች አስተዳደራዊ መፍትሄ የመስጠት፣ ጉድለቶችን የማረምና ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን አለው።
    • ለቦርዱ በመጀመሪያ ደረጃ ወይም በይግባኝ የሚቀርቡ አቤቱታዎች በምርጫ ህጉ ላይ በተደነገገው እና ቦርዱ የራሱን አሠራር እና የስብሰባ ስነስርዓት አስመልክቶ በሚያወጣው ደንብ መሠረት መርምሮ ውሳኔ ይሰጥባቸዋል።
    • ቦርዱ ለሚቀርቡለት አቤቱታዎች በወቅቱ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችለው አሠራር በየደረጃው በሚገኙ የምርጫ ጽሕፈት ቤቶች ይዘረጋል።
    • በምርጫ ሂደት በየደረጃው ስለሚኖሩ አቤቱታ ሰሚ አካላት
    • ቦርዱ በምርጫ ህጉ እና በዚህ ደንብ መሠረት የሚከተሉት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴዎች በየደረጃው እንዲቋቋሙ ያደርጋል፤
    • የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ፣
    • የምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ፣
    • የምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ፣
    • የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀት
    • በምርጫ ህጉ አንቀጽ 19(12) መሠረት እያንዳንዱ የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ያደራጃል።
    • የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ፣ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ሶስት ይሆናሉ።
    • የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ በመሆን ያገለግላል።
    • የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከቦርዱ ጋር በመመካከር ከክልሉ የሕዝብ ታዛቢዎች መካከል ሁለት አባላት በቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይመደባሉ።
    • ከህዝብ ታዛቢዎች መካከል የሚመረጡት የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት በተቻለ መጠን የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በተገቢው ሁኔታ በመመርመር ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል እውቀትና ልምድ ያላቸው እንዲሆኑ ይደረጋል።
    • የምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀት
    • በምርጫ ህጉ አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 5 ድንጋጌ መሠረት፤
    • በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ሦስት አባላት ያሉት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ያደራጃል።
    • የምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ያገለግላል።
    • የምርጫ ክልሉ ሁለት ታዛቢዎች የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባል ይሆናሉ።
    • ከላይ በ ‘ሐ’ የተጠቀሱት ሁለት ታዛቢዎች በምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይሰየማሉ።
    • ከሕዝብ ታዛቢዎች መካከል የሚመረጡት የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት በተቻለ መጠን የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በተገቢው ሁኔታ በመመርመር ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል እወቀትና ልምድ ያላቸው እ ንዲሆኑ ይደረጋል።
    • የምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀት
    • በምርጫ ህጉ አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ 1ዐ ድንጋጌ መሠረት፤
    • እያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያ ሦስት አባላት የያዘ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ያደራጃል።
    • የምርጫ ጣቢያው የምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ይሠራል።
    • የምርጫ ጣቢያው ሁለት የህዝብ ታዛቢዎች የምርጫ ጣቢያው የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባል ይሆናሉ።
    • ከላይ በ ‘ሐ’ የተጠቀሱት ሁለት ታዛቢዎች በምርጫ ጣቢያው ኃላፊ ይሰየማሉ።
    • ከሕዝብ ታዛቢዎች መካከል የሚመረጡት የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት በተቻለ መጠን የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በተገቢው ሁኔታ በመመርመር ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል እውቀትና ልምድ ያላቸው እንዲሆኑ ይደረጋል።
    • ከአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ስለመነሳት
    • ማንኛውም የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለኮሚቴው የቀረበን አቤቱታ ቀደም ሲል በሥራው ምክንያት ያየውና ውሳኔ የተሰጠበት ከሆነ በአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነቱ ተሰይሞ ለማየት አይችልም።
    • ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ሁኔታ ሲከሰት ከሌሎቹ የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ ተተክቶ ጉዳዩን በጊዜያዊ ሰብሳቢነት እንዲያይ ይደረጋል።
    • ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ሁኔታ የተከሰተው በክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሲሆን ከቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች አንዱ ተተክቶ በጊዜያዊ ሰብሳቢነት እንዲያይ ይደረጋል።
    • ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ጉዳይ ውሳኔ ካገኘ በኋላ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ መደበኛ የሰብሳቢነት ሥራውን ይቀጥላል።
    • የተጓደሉ አቤቱታ ሰሚ አባላትን ስለመተካት
    • የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት በተለያየ ምክንያት ሲጓደሉ ወዲያውኑ መተካት አለባቸው።
    • የተጓደሉት አባላት የሚተኩት በሚከተለው አሠራር ይሆናል፤
    • የክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ሲጓደሉ ወዲያውኑ በክልሉ ውስጥ ከተመረጡ የሕዝብ ታዛቢዎች መካከል በክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አማካኝነት ይተካሉ።
    • የተጓደለው አባል የምርጫ ክልሉ ኃላፊ ሲሆን ከምርጫ ክልሉ እንዲሁም ከምርጫ ጣቢያው ሲሆን ከምርጫ ጣቢያ የምርጫ አስፈጻሚዎች መካከል አንዱ ተክቶ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴን በሰብሳቢነት ይመራል።
    • የተጓደለው አባል ከሕዝብ ታዛቢዎች የተመረጠው ከሆነ በሰብሳቢው አማካኝነት ከቀሩት ታዛቢዎች መካከል አንዱ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው አባል ሆኖ እንዲተካ ይደረጋል። የተጓደለው ታዛቢ በተጠባባቂ ታዛቢነት ተመርጠው ከተያዙት ውስጥ ከፍተኛ ድምጽ ያለው እንዲተካ ይደረጋል።
  • ክፍል ሦስት
    አቤቱታ ሰሚ አካላት በምርጫው ሂደት ለሚነሱ ቅሬታዎች ውሳኔ የሚሰጡበት አሠራር
    • በመራጮች ምዝገባ ሂደት ስለሚነሱ ክርክሮች
    • በመራጮች ምዝገባ ሂደት የሚነሱ ክርክሮች በምርጫ ሕጉ አንቀጽ 93 መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሁኔታ ውሳኔ ያገኛሉ፤
    • ማንኛውም ሰው በመራጭነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ሲያጋጥመው ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታውን አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው።
    • መብት የሌለው ወይም በመራጭነት መመዝገብ የሌለበት ሰው ያለአግባብ ተመዝግቧል የሚል ተቃውሞ ያለው ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ተቃውሞውን ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው።
    • የምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረቡለትን አቤቱታዎች መርምሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሣኔ ያሰጣል።
    • የምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 ለቀረበለት አቤቱታ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ካልሰጠ፤
    • በመራጭነት ከመመዝገብ የተከለከለ ሲሆን በአቤቱታ አቅራቢው ጥያቄ እንደተስማማ ይቀጠራል። ለአቤቱታ አቅራቢው ይህንኑ የሚገልፅ ማስታወሻ ይሰጠዋል። ምርጫ ጣቢያውም በማስታወሻው መሠረት ይመዘግበዋል።
    • አቤቱታው በመራጭነት መመዝገብ የሌለበት ሰው ያለአግባብ ተመዝግቧል የሚል ሲሆን አቤቱታ አቅራቢው ለምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በ48 ሰዓት ውስጥ ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው።
    • በምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሚቀርብ ይግባኝ ውሣኔ ከተሰጠበት በ48 ሰዓት ውስጥ መቅረብ አለበት።
    • የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ይግባኝ መርምሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል።
    • የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ለወረዳው ፍርድ ቤ ት በ24 ሰዓት ውስጥ ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው። የወረዳው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔም የመጨረሻ ይሆናል።
    • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 መሠረት የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ለቀረበለት ይግባኝ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ካለሰጠ፤
    • አቤቱታው ለመራጭነት ከመመዝገብ የተከለከለን ሰው ሲሆን በአቤቱታ አቅራቢው ጥያቄ እንደተስማማ ይቆጠራል። ለአቤቱታ አቅራቢው ይህንኑ የሚገለፅ ማስታወሻ ይሰጠዋል። ምርጫ ጣቢያውም በማስታወሻው መሠረት ይመዘግበዋል።
    • ይግባኙ በመራጭነት የተመዘገበን ሰው በመቃወም ሲሆን ይግባኝ ባዩ በ24 ሰዓት ውስጥ ለወረዳ ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው። የወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል።
    • የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት የምርጫ ጣቢያው ጽሕፈት ቤት ሥራውን ያከናውናል።
    • በመራጭነት ከመመዝገብ በተከለለ ሰው የሚቀርብ አቤቱታ የመራጮች የምዝገባ የጊዜ ሠሌዳ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ይሆናል።
    • የተመዘገበን መራጭ በመቃወም የሚቀርብ አቤቱታ ከመራጮች የምዝገባ ቀን ጀመሮ የመራጮች መዝገብ ለሕዝብ ይፋ የሚሆንበት ጊዜ እስከሚያልቅ ድረስ ይሆናል።
    • በዕጩዎች ምዝገባ ሂደት ስለሚነሱ ክርክሮች
    • በዕጩዎች ምዝገባ ሂደት የሚነሱ ክርክሮች በምርጫ ህጉ አንቀጽ 94 መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሁኔታ ውሳኔ ያገኛሉ፤
    • ማንኛውም ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት በዕጩነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ሲያጋጥመው ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታውን በፅሑፍ አቅርቦ መልስ የማግኘት መብት አለው።
    • አንድ ዕጩ በዕጩነት መቅረብ የለበትም የሚል ተቃውሞ ያለው ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታውን በፅሑፍ አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው።
    • የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮማቴ የቀረበለትን አቤቱታ መርምሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል።
    • የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2 ለቀረበለት አቤቱታ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ካልሰጠ፤
    • በእጩነትት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ያጋጠመው ሰው ሲሆን የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በአቤቱታ አቅራቢው ጥያቄ እንደተስማማ ይቆጠራል። ለአቤቱታ አቅራቢው ይህንኑ የሚገልፅ ማስታወሻ ይሰጠዋል። አቤቱታ አቅራቢው ከአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው የተሰጠውን ማስታወሻ ለምርጫ ክልሉ በማቅረብ በእጩነት ይመዘገባል።
    • አቤቱታው አንድን ዕጩ በእጩነት መቅረብ የለበትም የሚል ተቃውሞ ሲሆን አቤቱታ አቅራቢው በ72 ሰዓት ውስጥ ለክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል።
    • ለዕጩነት ከመመዝገብ የተከለከለ የፖለቲካ ድርጅት ዕጩ ወይም የግል ዕጩ እንዲሁም የአንድን ዕጩ ምዝገባ የሚቃወም ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት የምርጫ ክልሉን አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ በመቃወም ለክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በ72 ሰዓት ውስጥ ይግባኝ ለማቅረብ ይችላል።
    • የክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ ሲቀርብለት በ48 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል።
    • በክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ይግባኝ ባይ ይግባኙን ውሳኔ ከተሰጠበት ጊዜ አንስቶ በ48 ሰዓት ውስጥ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል። ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል።
    • ለክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ይግባኝ መርምር በ48 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ካልሰጠ፣
    • አቤቱታው በዕጩነት ከመመዝገብ የተከለከለው ሲሆን በይግባኝ አቅራቢው ጥያቄ እንደተስማማ ይቆጠራል። ለአቤቱታ አቅራቢው ይህንኑ የሚገልፅ ማስታወሻ ይሰጠዋል። አቤቱታ አቅራቢው ከአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው የተሰጠውን ማስታወሻ ለምርጫ ክልሉ በማቅረብ ይመዘገባል።
    • የቀረበው ይግባኝ የአንድን ዕጩ ምዝገባ በመቃወም ሲሆን ይግባኝ ባዩ በ48 ሰዓት ውስጥ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው።
    • የክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት የምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤት ሥራውን ያከናውናል።
    • በዕጩነት ከመመዝገብ የተከለከለን የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል ዕጩን በሚመለከት የሚቀርብ አቤቱታ የዕጩ ምዝገባ የጊዜ ሠሌዳ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ይሆናል።
    • የአንድን ዕጩ ምዝገባ በመቃወም የሚቀርብ አቤቱታ ከዕጩዎች የምዝገባ ቀን ጀምሮ የተመዘገቡ ዕጩዎች ይፋ እስከሚሆንበት ቀን ድረስ ይሆናል።
    • በድምፅ አሰጣጥ ሂደት ስለሚነሱ ክርክሮች
    • በድምፅ አሰጣጥ ሂደት የሚነሱ ክርክሮች በምርጫ ህጉ አንቀጽ 95 መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሁኔታ ውሳኔ ያገኛሉ፣
    • አንድ መራጭ ድምፅ ከመስጠት የሚያግደው ሁኔታ ሲፈጠር ወይም በመራጭነት መብቱ ላይ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቅሬታውን ወዲያውኑ ለምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በፅሑፍ በማቅረብ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው።
    • የምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴውም፦
    • ጊዜያዊ ድምፅ እንዲሰጥ በማድረግ ጉዳዩን ወደ ምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት በመላክ ውሳኔ እንዲያገኝ ሊያደርግ ይችላል ወይም
    • ጊዜያዊ ድምፅ መስጠት የለበትም ብሎ ሊወስን ይችላል።
    • ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2 (ሀ) መሠረት ጊዜያዊ ድምፅ የሰጠ መራጭ ከምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ወይም እንደ ሁኔታው ከወረዳው ፍርድ ቤት የመምረጥ መብት እንዳለው የሚገልፅ ውሳኔ የድምፅ ማዳመሩ ከመጠናቀቁ በፊት ለምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት ካላቀረበ የሰጠው ጊዜያዊ ድምፅ ውድቅ ይደረጋል።
    • ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2(ለ) የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት የሚቀርብ አቤቱታ የድምፅ መስጫ ሰዓት ለማለቁ በፊት ውሳኔ ማግኘት ይኖርበታል። ምርጫ ጣቢያውም በውሳኔው መሠረት ይፈፅማል።
    • በምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ጊዜያዊ ድምፅ ከመስጠት የተከለከለ ሰው ወዲያውኑ ይግባኙን ለወረዳው ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል። የወረዳው ፍርድ ቤት የድምፅ መስጫው ሰዓት ከመጠናቀቁ በፊት ውሳኔ ይሰጣል፣ ውሳኔውም የመጨረሻ ይሆናል።
    • ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2 “ለ” መሠረት ጊዜያዊ ድምፅ መስጠት የለበትም የተባለ ይግባኝ አቅራቢ በምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ወይም በወረዳው ፍርድ ቤት ድምፅ እንዲሰጥ ከተወሰነ፤
    • የድምፅ መስጫ ሰዓት ከመጠናቀቁ በፊት ለምርጫ ጣቢያው ውሳኔውን ካላቀረበ ድምፅ ሊሰጥ አይችልም።
    • ከላይ በዚህ ንዑስ አንቀጽ “ሀ” የተደነገገው ቢኖርም የምርጫ ጣቢያው ተዘግቶ እና በምርጫ ጣቢያው በግቢ ውስጥ የተሰለፉ መራጮች ድምፅ በመስጠት ላይ ባሉበት ጊዜ ውሳኔውን ይዞ ከደረሰ እንዲመርጥ ይደረጋል።
    • የአንድን መራጭ ድምፅ መስጠት የሚቃወም ሰው ከላይ በተደነገገው መሠረት አቤቱታውን በየደረጃው በፅሑፍ የማቅረብና ውሳኔ የማግኘት መብት አለው።
    • ከላይ በንዑስ አንቀጽ 7 መሠረት የሚወሰን ውሳኔ እንደሁኔታው በዚህ አንቀፅ ከንዑስ አንቀጽ 2 እስከ 6 ባለው ድንጋጌ መሠረት ይፈፀማል።
    • በቆጠራ ሂደትና ውጤት ስለሚነሱ ክርክሮች
    • በቆጠራ ሂደትና ውጤት የሚነሱ ክርክሮች በምርጫ ህጉ አንቀጽ 96 መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሁኔታ ውሳኔ ያገኛሉ፤
    • በድምፅ ቆጠራ ሂደትና በውጤት ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል ዕጩ ወይም ወኪል ቅሬታውን ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አስመዝግቦ ይህንኑ ቅሬታ በ48 ሰዓት ውስጥ ለምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ከነማስረጃው በጽሑፍ ሊያቀርብ ይችላል።
    • ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ቅሬታ የሚያቀርብ ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል ዕጩ ወይም ወኪል፤
    • ለምርጫ ጣቢያ ቅሬታ ያስመዘገበበትን ማስረጃ ከሚያቀርበው አቤቱታ ጋር ማያያዝ አለበት።
    • ቅሬታ አቅራቢው በምርጫ ጣቢያ ካስመዘገበው ጭብጥ ውጪ የሆነ አዲስ ነገር ማቅረብ አይችልም።
    • የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበለትን አቤቱታ እና ማስረጃ መርምሮ በ48 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል።
    • የምርጫ ክልሉ ውሳኔ፤
    • ቅሬታ የቀረበበት ቆጠራ እንደገና እንዲካሄድ ወይም
    • ቅሬታ የቀረበበት ቆጠራ ትክክል ስለሆነ ቅሬታው አግባብነት የለውም የሚል ሊሆን ይችላል።
    • በቆጠራ ላይ የቀረበው ቅሬታ የምርጫ ክልሉን አጠቃላይ ውጤት በመሠረቱ የማይለውጠው ከሆነ ድጋሚ ቆጠራ ማካሄድ አያስፈልግም ብሎ ሊወሰን ይችላል።
    • ሌላ አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነበትን ውሳኔ በህጉ መሠረት ሊወሰን ይችላል።
    • የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ አቤቱታ አቅራቢ ውሳኔ በተሰጠው በ5 ቀን ውስጥ ይግባኝ ለቦርዱ ማቅረብ ይችላል። ቦርዱ የቀረበውን ይግባኝ መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል።
    • ይግባኝ ባዩ ቦርዱ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም በ5 ቀን ውስጥ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይችላል።
    • የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ከላይ በንዑስ አንቀጽ 6 መሠረት ለቀረበለት ይግባኝ በተቻለ ፍጥነት ውሳኔ ይሰጣል። ውሳኔውም የመጨረሻ ይሆናል።
    • የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ተግባርና ኃላፊነት
    • በየደረጃው የሚገኝ የምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፤
    • በምርጫ ህጉ እና በዚህ ደንብ መሠረት በያለበት ደረጃ ለሚቋቀም አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ያገለግላል።
    • በዚህ ደንብ መሠረት የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላትን ይሰይማል።
    • ለአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ሥራ ያከፋፍላል። የሥራ ክፍፍሉ በቃለ- ጉባኤ ተመዝግቦ እንዲያዝ ያደርጋል።
    • የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ውይይት እና ውሳኔ በቃለጉባኤ እንዲያዝና ለሚመለከተው አካል እንዲላክ ያደርጋል።
    • ማናቸውንም ሰነዶች በአግባቡ እንዲጠበቁ ያደርጋል።
    • ይግባኝ የማቅረብ መብት ላለው ሰው የተሟላ ሰነድ በመስጠት በይግባኝ መብቱ እንዲጠቀም ያደርጋል።
    • በየደረጃው የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ከተመደቡ ሰዎች አንደኛው አባል በተደራቢነት በቃለጉባኤ ያዥነት በኮሚቴው ሰብሳቢ ተመድቦ የኮሚቴውን ቃለ ጉባኤዎች እና ውሳኔዎች በጽሁፍ ይይዛል።
    • የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት በአቤቱታ የቀረበላቸውን ጉዳይ በመመርመር አፋጣኝ እና ህጋዊ ውሳኔ የመስጠት ኃላፊነት አለባቸው።
  • ክፍል አራት
    ስለአቤቱታ አቅራቢ፣ አቤቱታ አቀራረብ እና አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አሠራር
    • ስለ አቤቱታ አቅራቢ
    • በምርጫ ህጉ አንቀጽ 79፣ 90 እና 91 ከተደነገገው በስተቀር የሚከተሉት አካላት ወይም ሰዎች የምርጫውን ሂደት አስመልክቶ አቤቱታ በፅሑፍ የማቅረብና በየደረጃው ውሳኔ የማግኘት መብት አላቸው።
    • ማንኛውም ሰው በመራጭነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ሲያጋጥመው ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታውን አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው።
    • በመራጭነት ለመመዝገብ መብት የሌለው ወይም በመራጭነት ለመመዝገብ ብቁ ያልሆነ ሰው ያለአግባብ ተመዝግቧል የሚል ተቃውሞ ያለው ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ተቃውሞውን ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው።
    • ማንኛውም ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት በእጩነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ሲያጋጥመው ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታውን አቅርቦ መልስ የማግኘት መብት አለው።
    • አንድ እጩ በእጩነት መቅረብ የለበትም የሚል ተቃውሞ ያለው ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታውን አቅርቦ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው።
    • አንድ መራጭ ድምፅ ከመስጠት የሚያግደው ሁኔታ ሲፈጠር ወይም በመራጭነት መብቱ ላይ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቅሬታውን ወዲያውኑ ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በማቅረብ ውሳኔ የማግኘት መብት አለው።
    • በድምፅ ቆጠራ ሂደትና በውጤት ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል እጩ ወይም ወኪል ቅሬታውን ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አስመዝግቦ ይህንኑ ቅሬታ በ48 ሰዓት ውስጥ ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሊያቀርብ ይችላል።
    • የአቤቱታ አቀራረብ
    • እያንዳንዱ አቤቱታ አቅራቢ የሚያቀርበው አቤቱታ በፅሁፍ ሆኖ ሌላ አከራካሪ ጉዳይ በማያስከትል ሁኔታና ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት በሚያስችል መልክ ተዘጋጅቶ፤
    • አቤቱታው የተፃፈበት ቀን እና ሰዓት፣
    • የአቤቱታ አቅራቢውን ሙሉ ስምና አድራሻ፣
    • ለአቤቱታ መነሻ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ፣
    • እየተጠየቀ ያለውን መፍትሄ፣
    • የማስረጃ ዝርዝር፣
    • የሚቀርበው የሰው ማስረጃ በሆነ ጊዜ የምስክሮቹን ማንነት ዝርዝር እና
    • አቤቱታው የሚቀርብበት አካል በግልፅ ያመላከተ መሆን አለበት።
    • ለአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሚቀርብ አቤቱታ ወይም ይግባኝ ቦርዱ ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው ቅፅ በሶስት ቅጂ ተዘጋጅቶተ በአቤቱታ አቅራቢው መፈረም አለበት።
    • ማንኛውም አቤቱታ በአቤት ባዩ ወይም በሕጋዊ ወኪሉ መቅረብ ይኖርበታል።
    • አቤቱታ አቅራቢው የማያነብ እና ወይም የማይፅፍ ከሆነ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው አቤቱታው በቃል እንዲቀርብ በማድረግ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው አባላት በተገኙበት፤
    • የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው የአቤቱታ አቅራቢውን ቃል ሰምቶ በጽሁፍ ይመዘግባል።
    • የአቤቱታ አቅራቢውን ቃል ከላይ በዚህ ንዑስ አንቀጽ “ሀ” መሠረት ሲመዘግብ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን መስፈርት ያሟላ እንዲሆን ያደርጋል።
    • ከላይ በዚህ ንዑስ አንቀጽ “ለ” መሠረት ወደ ጽሑፍ የተለወጠው አቤቱታ ለአቤቱታ አቅራቢው ተነቦለት በፅሁፍ ወይም በጣት አሻራ ወይም ጣት የሌለው ከሆነ በሚችለው ሌላ ምልክት እንዲፈርምበት ያደርጋል።
    • ማንኛውም አቤቱታ ወይም ይግባኝ ለሚመለከተው አካል ከቀረበ በኋላ አቤቱታ አቅራቢው ወይም ይግባኝ ባዩ ወይም ህጋዊ ወኪሉ ጉዳዩን እንደማይቀጥልበት ወይም እንዳቋረጠ በፅሁፍ ከገለፀ አቤቱታ ወይም ይግባኝ ሰሚው አካል ይህንኑ ፅሁፍ ከአቤቱታው ወይም ከይግባኙ ጋር በማያያዝ በአጭር ቃለ ጉባኤ ጉዳዩን ይዘጋል።
    • አቤቱታ ስለመቅረቡ የሚሰጥ ማስረጃ
    • በየደረጃው ያለ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በማንኛውም ሰው ወይም አካል አቤቱታ ሲቀርብለት በዚህ ደንብ አንቀፅ 19 ያለውን መመዘኛ ያሟላ መሆኑን በማረጋገጥ የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ለአቤቱታ መረከቢያ ማረጋገጫነት የተዘጋጀውን ቅፅ ሞልቶ በመፈረም ለአቅራቢው ይሰጠዋል፤
    • የአቤቱታ መረከቢያ ማረጋገጫ ቅፅም፤
    • አቤቱታው ገቢ የተደረገበት ቀንና ሰዓት፣
    • አቤቱታው የቀረበለትን አካል፣
    • አቤቱታው በዚህ ደንብ አንቀጽ 19 ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን ያሟላ መሆኑን፣
    • የአቤቱታውን መነሻ በአጭሩ እና
    • የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ስምና ፊርማ መያዝ ይኖርበታል።
    • ስለ ይርጋ
    • ማንኛውም አቤቱታ ወይም ይግባኝ ሊቀርብ የሚችለው በምርጫ ህጉ መሠረት ሆኖ፤
    • በዚህ ደንብ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ መሠረት በመራጭነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ያጋጠመው ሰው በሆነ ጊዜ የመራጮች የምዝገባ የጊዜ ሠሌዳ እስከሚጠናቀቅበት ቀን ይሆናል።
    • በዚህ ደንብ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ መሠረት መብት የሌለው ሰው ወይም በመራጭነት መመዝገብ የሌለበት ሰው ያለአግባብ ተመዝግቧል የሚል ሲሆን ከመራጮች የምዝግባ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ የመራጮች መዝገብ ለሕዝብ ይፋ እስከሚሆንበት የመጨረሻ ቀን ድረስ ይሆናል።
    • በእጩነት ከመመዝገብ የተከለከለን የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል እጩን በሚመለከት ሲሆን የእጩ ምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ይሆናል።
    • የአንድን እጩ ምዝገባ በመቃወም የሚቀርብ ሲሆን ከእጩዎች ምዝገባ ቀን ጀምሮ የተመዘገቡ እጩዎች ይፋ እስከሚሆኑበት ቀን ድረስ ይሆናል።
    • በዚህ ደንብ አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ መሠረት አንድ መራጭ ድምፅ ለመስጠት የሚያግደው ሁኔታ ሲፈጠር ወይም በመራጭነት መብቱ ላይ ተቃውሞ ሲቀርብ እና ከተጣራ በኋላ ለማዳመር ወይም ለመጣል ጊዜያዊ ድምፅ በፖስታ እንዲሰጥ ከተደረገ የድምፅ ማዳመሩ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ሊያቀርብ ይችላል።
    • ከላይ በንዑስ አንቀጽ 5 መሠረት ድምፅ ለመስጠት የሚያግደው ሁኔታ ተፈጥሮ ወይም በመራጭነት መብቱ ላይ ተቃውሞ በመቅረቡ ጊዜያዊ ድምፅ መስጠት የለበትም ተብሎ ሲወሰን የድምፅ መስጫ ሰዓት ከማለቁ በፊት ድረስ ውሳኔ እንዲሰጠው ማቅረብ ይኖርበታል።
    • የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ስብሰባና ውሳኔ አሠጣጥ
    • በየደረጃው የሚቋቋም የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ስብሰባ በሙሉ አባላት ይካሄዳል።
    • የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የአቤቱታ አቅራቢውን አቤቱታና ማስረጃ እና አቤቱታ የቀረበበትን አካል ወይም የምርጫ አስፈጻሚውን ክፍል ምክንያትና መልስ ከሰማ እና የቀረበለትን ማስረጃ ካገናዘበ በኋላ ውሳኔ ይሰጣል።
    • አቤቱታ አቅራቢውም ሆነ ቅሬታ የቀረበበት ሰው በኮሚቴው የመሰማት፣ ማስረጃውን የማሰማትና ራሱን የመከላከል መብት አለው።
    • አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበለትን አቤቱታ ከመረመረ በኋላ በተባበረ ድምፅ ወይም በድምፅ ብልጫ ውሳኔ ይሰጣል።
    • ድምፅ እኩል ከተከፈለ ሰብሳቢው የደገፈው ወገን የኮሚቴው ውሳኔ ይሆናል።
    • የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው አቤቱታ የቀረበበት የምርጫ አስፈጻሚ ወይም አካል መልስ እንዲሰጥ አስፈላጊ አይደለም ብሎ ሲያምን ወይም መልስ መስጠት ሳይችል ሲቀር የአቤቱታ አቅራቢውን አቤቱታና ማስረጃ በመመርመር ብቻ ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል።
    • የሀሳብ ልዩነት ያለው የኮሚቴ አባል ልዩነቱ በአጭሩ እንዲመዘገብለት ሊያደርግ ይችላል።
    • ማንኛውም አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የውይይት ቃለ ጉባኤውን ወይም የሚሰጠውን ውሳኔ በጋራ ፊርማ ማረጋገጥ አለበት።
    • የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ የሚከተሉትን አካቶ የያዘ መሆን ይኖርበታል፤
    • አቤቱታው የቀረበለትን ኮሚቴ ስም እና አድራሻ፣
    • የኮሚቴውን አባላት ስም ዝርዝርና ፊርማ፣
    • የአቤቱታ አቅራቢውን ሙሉ ስምና አድራሻ፣
    • የማስረጃዎች ይዘት እና/ወይም የምስክሮች ቃል በአጭሩ፣
    • ምክንያታዊ የሆነ የውሳኔ ሀተታ፣
    • በውሳኔው መሠረት መወሰድ ስለሚኖርበት እርምጃ እና
    • ውሳኔው የተሰጠበት ቀንና ሰዓት።
    • እያንዳንዱ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ፤
    • የቀረበን አቤቱታ ከቀረበለት ማስረጃ ጋር በማገናዘብ ይመረምራል፣ ውሳኔውንም በፅሁፍ ያሰፍራል።
    • ከቀረበለት አቤቱታ ጋር ግንኙነት ያለው ወይም ያገባኛል ባይ ጥያቄ ሲያቀርብ ከአቤት ባዩ ጋር አብሮ እንዲሰማ እድል ሊሰጥ ይችላል።
    • አቤቱታ ሰሚው ጥያቄ ሲያቀርብ ኮሚቴው በራሱ አስተያየት አቤቱታ አቅራቢውን እና አቤቱታ የቀረበበትን ወይም ውሳኔ ለመስጠት ይረዳኛል የሚለውን ሰው ጠርቶ ሊጠይቅ ወይም አስፈላጊ ማስረጃ እንዲቀርብለት ሊያደርግ ይችላል።
    • አቤቱታ ሲቀበል መቼና በስንት ሰዓት እንደሚታይ እና የት እንደሚታይ እንዲሁም ውሳኔ መቼ እንደሚሰጥ ለአቤቱታ አቅራቢውና ለሚመለከታቸው ማሳወቅ አለበት።
    • በየደረጃው የሚገኝ አቤቱታ ሰሚ አካል የቀረበለትን አቤቱታ ከተመለከተ በኋላ ውሳኔውን አቤቱታ ላቀረበው ሰው ወይም አካል በወቅቱ ማሳወቅ አለበት።
    • የእያንዳንዱ አቤቱታ ውሳኔ በሶስት ቅጂ ተዘጋጅቶ፤
    • አንዱ ቅጂ ለአቤቱታ አቅራቢው ይሰጣል።
    • ሁለተኛው ቅጂ በውሳኔው መሠረት ለሚፈፅም ወይም ውሳኔው ይግባኝ ለተባለበት አካል ይሰጣል።
    • ሦስተኛው ቅጂ አቤቱታውን መርምሮ ውሳኔ በሰጠው አካል እጅ በሰነድነት ይያዛል።
    • እያንዳንዱ ውሳኔ በአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተፈረመበት መሸኛ ይኖረዋል።
    • ስለይግባኝ መብት
    • ማንኛውም አቤቱታ አቅራቢ አቤቱታውን ባቀረበበት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ቅር ከተሰኘ በምርጫ ህጉ መሠረት በተደነገገው የጊዜ ገደብ ውስጥ ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው።
    • በየደረጃው ያለ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮሚቴው በሰጠው ውሳኔ ላይ የይግባኝ መብት ላለው ሰው ወይም አካል፤
    • ይግባኝ የማቅረብ መብት እንዳለው፣
    • ይግባኙን ለማን ማቅረብ እንዳለበት፣
    • ይግባኙን ኮሚቴው ውሳኔ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ማቅረብ እንዳለበት፣ የማስረዳት ኃላፊነት አለበት፣
    • ማንኛውም አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የይግባኝ መብት ላለው ሰው፤
    • የኮሚቴውን ውሳኔ አንድ ቅጂ፣
    • ውሳኔ የተሰጠበትን አቤቱታ አንድ ቅጂ እና
    • የተሰጠውን ውሳኔ እና አቤቱታ ቅጂዎች በአባሪነት የያዘ በአቤቱታ ሰሚው ኮሚቴ ሰብሳቢ ፊርማ የተረጋገጠ መሸኛ ደብዳቤ ሊሰጠው ይገባል።
    • በየደረጃው የሚገኙ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴዎች፤
    • የዚህ ደንብ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 4 (ለ) እና አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 4 (ለ) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በየደረጃው በሚገኙ የበታች አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴዎች ተመርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ ያላገኘን ጉዳይ ማየት የለባቸውም።
    • የቀረበላቸውን ይግባኝ በመመልከት የበታች አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴዎችን ውሳኔ ሊያፀኑ፣ በከፊል ወይም በሙሉ ሊለውጡ ወይም ሊያሻሽሉ ይችላሉ።
    • የቀረበላቸውን ይግባኝ ተመልክተው አፋጣኝ ውሳኔ በመስጠት በየደረጃው ያሉ የምርጫ አስፈጻሚዎች ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መስጠት አለባቸው።
    • ይግባኝ የቀረበለት አቤቱታ ሰሚ አካል በዚህ ደንብ መሠረት በተደነገገው ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል።
    • የምርጫ ህጉ አስገዳጅ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ይግባኝ የሚቀርበው ለመደበኛ ፍርድ ቤቶች በሚሆንበት ጊዜ አግባብ ያለው የሕግ ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናል።
    • የዚህ ደንብ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 8(ለ) እና አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 8(ለ) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ፍርድ ቤቶች በምርጫ ህጉ አንቀጽ 92/11/ መሠረት ቦርዱ ወይም በየደረጃው በሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚ አካላት በቅድሚያ ያልታየና የመጨረሻ ውሳኔ ያላገኘን የምርጫ ጉዳይ ማየት አይችሉም።
    • ስለይግባኝ አቤቱታ አወሳሰን
    • ይግባኝ የቀረበው ይግባኝ ሰሚ ለሆነው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ከሆነ እንደሁኔታው በዚህ ደንብ ስለመጀመሪያ ደረጃ አቤቱታ የተመለከቱ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ።
  • ክፍል አምስት
    ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
    • ስለመተባበር
    • ማናቸውም የፌዴራልም ሆነ የክልል የመንግሥት መሥሪያ ቤት፣ የፖለቲካ ድርጅት፣ ቡድን፣ የግል ድርጅት ወይም ግለሰብ ይህንን ደንብ በሥራ ላይ ለማዋል የመተባበር ግዴታ አለበት።
    • ስለቅጣት
    • ይህ ደንብ በሥራ ላይ እንዳይውል ያወከ ወይም ድንጋጌዎቹን የጣሰ ማንኛውም ሰው አግባብ ባለው ህግ ይቀጣል።
    • የተሻሩ ደንቦች እና አሠራሮች
    • ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ደንብ ወይም አሠራር በዚህ ደንብ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም።
    • ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ
    • ይህ ደንብ በቦርዱ ከፀደቀበት ከነሐሴ 13 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል። መርጋ በቃና (ፕሮፌሰር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ

ስልጣንና ተግባራት


ስልጣንና ተግባራት

የመንግስት ስልጣን በህግ ከተቀመጠለት ገደብ እንዳያልፍና ይህንንም በተግባር ለማረጋገጥ መጀመሪያ የስልጣንን ምንጭ እና መገለጫ ባህርያት በቅጡ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ለመሆኑ ስልጣን ከየት ይመነጫል? እንዴትስ ይገለጻል? የስራ አስፈፃሚውና የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች የስልጣን ምንጭ ህግና ህገ መንግስት ብቻ ነው፡፡ በህገ መንግስታዊ እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ህዝብ የስልጣን ባለቤት መሆኑ የሚረጋገጠው የመንግስት ባለስልጣናት ስልጣን በህዝብ ከተመረጡ ተወካዮች የመነጨ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትሩንና የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ስልጣናት ጠቅለል ባለ አነጋገር ይዘረዝራል፡፡ የእያንዳንዱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስልጣንና ተግባር ብዙውን ጊዜ አዲስ የምርጫ ዘመንን ተከትሎ በተወካዮች ምክር ቤት የሚወጣው የስራ አስፈፃሚውን ስልጣንና ተግባር የሚወስን አዋጅ ላይ ተዘርዝሮ ይቀመጣል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት በይፋ ከታወጀ ወዲህ የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጡ አዋጆች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ ወደ ህትመት እስከገባበት ጊዜ ድረስ ፀንተው ያሉ ህጎች አዋጅ ቁ. 916/2008 እና አዋጅ ቁ. 942/2008 (ማሻሻያ) ሲሆኑ የተቀሩት በሙሉ ተሽረዋል፡፡

የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጡ

አዋጆች ዝርዝር፤

አዋጅ ቁ. 4/1987

አዋጅ ቁ. 93/1990 (ማሻሻያ)

አዋጅ ቁ. 134/1991 (ማሻሻያ)

አዋጅ ቁ. 256/1994

አዋጅ ቁ. 380/1996 (ማሻሻያ)

አዋጅ ቁ. 411/1996 (ማሻሻያ)

አዋጅ ቁ. 465/1997 (ማሻሻያ)

አዋጅ ቁ. 471/1998

አዋጅ ቁ. 546/1999 (ማሻሻያ)

አዋጅ ቁ. 603/2001 (ማሻሻያ)

አዋጅ ቁ. 641/2001 (ማሻሻያ)

አዋጅ ቁ. 642/2001 (ማሻሻያ)

አዋጅ ቁ. 691/2003

አዋጅ ቁ. 723/2004 (ማሻሻያ)

አዋጅ ቁ. 803/2005 (ማሻሻያ)

አዋጅ ቁ. 916/2008

አዋጅ ቁ. 942/2008 (ማሻሻያ)

የሌሎች የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ስልጣን ደግሞ የተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው አዋጅ እንዲሁም ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብa በግልጽ ወይም በተዘዋዋሪ ተደንግጐ ይገኛል፡፡ እነዚህ በየጊዜው የሚወጡ ማቋቋሚያና ሌሎች ተጓዳኝ ህጐች የአስተዳደሩ የስልጣን ምንጭ በመሆን ያገለግላሉ፡፡
ስለሆነም የአስተዳደር መ/ቤቶችን የስልጣን ገደብ ለመወሰን የተወካዮች ም/ቤት ያወጣውን አዋጅ ብቻ ሳይሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንቦችን ማመሳከር ያስፈልጋል፡፡ ከሁለቱ ህጎች ውጭ ከልማድ፣ ከመመሪያ ወይም ከሌላ የስልጣን ምንጭ በማንኛውም የአስተዳደር መ/ቤት የተፈጸመ ድርጊት፣ የተሰጠ ውሳኔ፣ የወጣ መመሪያ ወይም ደንብ ከስልጣን በላይ እንደ መሆኑ ህጋዊነት ኖሮት በህግ ፊት ሊፀና ሆነ ውጤት ሊኖረው አይችልም፡፡ በህግና በህጉ መሰረት መሰረት ብቻ መስራት የህግ የበላይነት የቆመበት ምሶሶ እንደመሆኑ የህዝብ ወይም የመንግስት አስተዳደር ሊከናወን የሚገባው ከህግ በመነጨ ስልጣን መሰረት ብቻ ነው፡፡

የአስተዳደር ህግና ህገመንግስታዊ መርሆዎች/እና የህግ የበላይነት


የአስተዳደር ህግ እና ህገ መንግስታዊ መርሆዎች የአስተዳደር ህግ እና የህገ መንግስት ትስስር እና ተዛምዶ የአስተዳደር ህግ ጽንስቱ ሆነ ውልደቱ.

ሁለቱም የመንግስትና የግለሰብ ግንኙነትን በሚመራው ‘የህዝብ አስተዳደር ህግ’ ተብሎ በሚጠራው የህግ ክፍል ውስጥ ይመደባሉ፡፡ አብዛኛዎቹ የአስተዳደር ህግ ጥያቄዎች በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የህገ መንግስታዊነት ጥያቄዎችን ያስነሳሉ፡፡ የአስተዳደር ህግን በጥልቀት ለመረዳት ከተፈለገ ሂደቱ መጀመር ያለበት ህገ መንግስትን በማጥናት ነው፡፡ በምሁራኑ አንደበት ይኸው እውነታ እንዲህ ይገለፃል፡፡ የአስተዳደር ህግ ከህገ መንግስታዊ መሰረቱ ተለይቶ በደንብ ሊታወቅ ሆነ ሊጠና አይችልም፡፡ የአስተዳደር ህግ በህገ መንግስት ማስፈጸሚያ መሳሪያነቱ የዝምድናቸውን ገጽታ በሚገባ ለማወቅ ይረዳናል፡፡ በዚህ የተግባሪነት ሚናው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ላይ የተቀመጡትን የህገ መንግስታዊነትና የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች እንዲሁም የግለሰቦች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በተጨባጭ እንዲረጋገጡ በማድረግ ህገ መንግስቱን በማስፈጸም ረገድ እንደ አንድ መሳሪያ ያገለግላል፡፡ እ.ኤ.አ በ1959 ዓ.ም. የጀርመን የፌደራል አስተዳደር ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት እንደተናገሩት የአስተዳደር ህግ ‘ተጨባጭ ህገ መንግስት’ ማለትም በተግባር የሚታይ ህገ መንግስት ነው፡፡a የአንድ አገር ህገ መንግስት በዋነኛነት የዜጐችን ሰብአዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፖለቲካዊ መብቶችና ነጻነቶች ይደነግጋል፡፡ የዜጐች መብት በሌላ ግለሰብ፣ ማህበር ወይም የንግድ ድርጅት ሊጣስ ይችላል፡፡ ትልቁ አደጋ ያለው ግን ከመንግስት በተለይም ከስራ አስፈፃሚው አካል በኩል ነው፡፡ መብቶች በሚገባ እንዲጠበቁ የመንግስት አስተዳደር ልኩ ተለይቶ በታወቀ የስልጣን ገደብ ውስጥ ሊከናወን ይገባል፡፡ ሆኖም ስልጣን ሁልጊዜ በህጉ መሰረት ግልጋሎት ላይ ይውላል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ የግድ በአግባቡ ሊገራና ልጓም ሊበጅለት ይገባል፡፡ የአስተዳደር ህግ የስልጣን መቆጣጠሪያ መሳሪያ ነው፡፡ በዚህ ተግባሩ ውጤታማ የስልጣን ቁጥጥር የዜጐች ህገ መንግስታዊ መብትና ነፃነት እንዳይጣስ ዋስትና ይሰጣል፡፡ መንግስቱን በተግባር እንዲተረጐም የሚደርገውም በዚህ መንገድ ነው፤ ስልጣንን በመቆጣጠር የዜጐችን መብት በተጨባጭ ማቀዳጀት፡፡ ይህ ሚናውን በሌሎች ህገ መንግስታዊ መርሆዎች አንጻርም ጎልቶ ይታያል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት በዋነኛነት ከሚደነግጋቸው የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች መካከል ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና የህዝብ ተሳትፎ ይገኙበታል፡፡b ግልጽነት እውን የሚሆነው የመንግስት ባለስልጣናትና የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ለዜጐች መረጃ የመስጠት ግዴታቸው ከነዝርዝር አፈፃፀሙ ጭምር በህግ ተደንግጐ ሲገኝ ነው፡፡ ተጠያቂነት፤ ጠያቂውና ተጠያቂው ተለይቶ የተጠያቂነት ስልቱ በዝርዝር ህግ ካልተቀመጠ በተግባር አይረጋገጥም፡፡ የህዝብ ተሳትፎ እንዲሁ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች በሚሰጡት ውሳኔ በተለይም ደንብና መመሪያ ሲያወጡ በጉዳዩ ጥቅም ካላቸው ወገኖች ሀሳብና አስተያየት እንዲቀበሉ የሚያስገድድ የህግ ድንጋጌ ከሌለ የህዝብ ተሳትፎ በተጨባጭ አይታይም፡፡ ግልፅነትን፣ ተጠያቂነትንና የህዝብ ተሳትፎን በተግባር ለማረጋገጥ የሚወጡ ህጐች በአስተዳደር ህግ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ህጉ እነዚህ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች በተግባር እንዲረጋገጡ በማድረግ ህገ መንግስቱን ያስፈጽማል፡፡ በህገ መንግስትና በአስተዳደር ህግ መካከል ያለው የጠበቀ ግንኙነት ልዩነታቸው የላላ መሆኑን ያሳያል፡፡ ሊጠቀስ የሚችል ቀጭን ልዩነት ቢኖር የወሰን እና የህጎች የተፈጻሚነት ደረጃ (Hierarchy of Laws) ልዩነት ነው፡፡ ከወሰን አንፃር ህገ መንግስት አጠቃላዩን የመንግስት አወቃቀርና የሶስቱን የመንግስት አካላት ብሎም በፌደራልና በክልል መንግስታት ያለውን የስልጣን ክፍፍል ስለሚወስን በይዘቱ በጣም ሰፊ ነው፡፡ በአንፃሩ የአስተዳደር ህግ የአንደኛውን የመንግስት አካል ማለትም የስራ አስፈፃሚውን ስልጣን፣ ግዴታና ተግባር ብሎም የውሳኔዎቹን ህጋዊነት የሚመለከት ህግ ነው፡፡ በህግ አውጭው የሚወጣ ህግ እና ፍ/ቤቶች የሚሰጡት ውሳኔ ህገ መንግስታዊነት ከጥናት አድማሱ በላይ ነው፡፡ ስለሆነም ከወሰናቸው አንጻር ህገ መንግስት መስፋቱ የአስተዳደር ህግ መጥበቡ እንደ አንድ የልዩነት ነጥብ ተደርጐ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ሁለተኛው ልዩነት የህጎች መሰላል (Hierarchy of Laws) ሲሆን በህጐች መካከል ያለውን የደረጃ ዝምድና ይመለከታል፡፡ ህገ መንግስት የአንድ አገር የበላይ ህግ እንደመሆኑ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የአሰራር ልምዶች ዋጋ የላቸውም፡፡ የአስተዳደር ህግ በደረጃው ከህገ መንግስት ዝቅ ብሎ የሚገኝ እንደመሆኑ መቼም ቢሆን ከህገ መንግስቱ ጋር መጣጣም አለበት፡፡ ግጭት በተነሳ ጊዜ የበላይ የሆነው ህገ መንግስት ሁልጊዜ ተፈፃሚነት አለው፡፡

የህግ የበላይነት ብዙ ምሁራን በየፊናቸው በምርምርና ጥናት ባገኙት እውቀት ተመርኩዘው የህግ የበላይነት መርህ ምንነት፤ ይዘትና ፋይዳውን አስመልክቶ አያሌ ንድፈ ሀሳባዊ ትንታኔዎችን አቅርበዋል፡፡ በአገራችን ደግሞ አባቶችና እናቶች በልባቸው ከተጻፈው እውነትና ከልምድ ከቀዱት ቱባ እውቀት በመነሳት የህግ የበላይነትን ጽንስ ሀሳብ በአንድ አባባል እንዲህ ይገልጹታል፡፡“በፍርድ ከሄደች በቅሎዬ ያለፍርድ የሄደች ዶሮዬ!”የዚህ ተረትና ምሳሌ አንኳር መልዕክት ለጥቂት ሰዎች ብቻ የተገለጠ ሳይሆን በመላው ማህበረሰብ ዘልቆ የገባ ሀቅ ነው፡፡ እናም ይህን የህግ የበላይነት ፅንሰ ሓሳብን ጠንቅቆ ያወቀው ማህበረሰብ ህግ ሲጣስ፤ ፍትህ ሲጓደል፤ መብት ሲታፈን፤ ስርዓት አልበኝነት ሲነግስ፤ ማን አለብኝነትና በዘፈቀደኝነት ሲንሰራፋ፤ የግሉ የሆነችው ዶሮ ከህግ እና ከፍርድ ውጭ ሲቀማ ድምፁን አጉልቶ ይጮሀል፤ በህግ አምላክ! ይላል፡፡ የጮኸው የዶሮዋ ዋጋ አንገብግቦት አይደለም፡፡ የተወሰደችበት መንገድ እንጂ፡፡ በፍርድ ከሆነ፤ በህጉ መሰረት ከሆነ እንኳንስ ለዶሮ ለበቅሎም ቄብ አይሰጠውም፡፡በህዝብ አስተዳደር፤ ፖለቲካ ሳይንስ፤ ህግ እና በሌሎችም የጥናት መስኮች የሚገኙ ምሁራን ስለ የህግ የበላይነት ምንነትና ይዘት ያላቸው ግንዛቤና አስተሳሰብ የተራራቀ ከመሆኑ የተነሳ ጽንሰ ሀሳቡ አሁንም ድረስ ቁርጥ ያለ ትርጓሜ አልተገኘለትም፡፡ አንድ የመስኩ ምሁር ይህንን ሀሳብ በማጠናከር እንዳብራራው፤‘[T]he rule of law’, like ‘democracy’, has no single meaning: it is not a legal rule, but a moral principle, which means different things to different people according to their particular moral positions.aበዚህ የተነሳ በተለያዩ አገራት የፖለቲካና የህገ መንግስት ስርዓት ውስጥ ይዘቱና አፈጻጸሙ የተለያየ አንዳንዴ የማይጣጣም መልክ በመያዙ መሰረታዊ እሳቤው ወጥነት ርቆታል፡፡ለምሳሌ በእንግሊዝ አንደኛውና የህግ የበላይነት መገለጫ በመንግስትና በግለሰብ መካከል የሚነሱ ክርክሮች በመደበኛ ፍ/ቤቶች ብቻ መዳኘታቸው ነው፡፡ ያ ማለት በእንግሊዛዊ አይን ፈረንሳይ ውስጥ የህግ የበላይነት የለም እንደ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በፈረንሳይ በግለሰብና በመንግስት መካከል የሚነሱ ክርክሮች ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ የሚዳኙት ከመደበኛ ፍ/ቤት ትይዩ ራሱን ችሎ በተቋቋመ የአስተዳደር ፍ/ቤት ስርዓት አማካይነት ነው፡፡ በእንግሊዝ ሌላኛው የህግ የበላይነት ትርጉም የግለሰቦች መብትና ነፃነት መደበኛ ፍ/ቤቶች በቀረቡላቸው ተጨባጭ ጉዳዮች የሚሰጡት ውሳኔ ውጤት ነው የሚል ይዘት አለው፡፡ ይህ አስተሳሰብ በእንግሊዝ እውነት ቢሆንም የኛን አገር ጨምሮ የተጻፈ ህገ መንግስት ባላቸው እንደ አሜሪካ ባሉ አገራት የዜጐች መብቶችና ነፃነቶች በህገ መንግስቱ ላይ በጽሑፍ ይዘረዘራል፡፡ከዚህ በተጨማሪ በሊብራል ዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ የህግ የበላይነት ማለት በህጉ መሰረት ከመግዛትና ከማስተዳደር ባለፈ የህጉ ይዘት (ለምሳሌ ፍትሐዊነቱ፤ የዜጐችን መብት ማክበሩ፣ ህጉ የወጣው ህዝብ ወዶና ፈቅዶ በመረጣቸው ተወካዮች መሆኑ ወዘተ…) ብሎም የገለልተኛና ነፃ ፍ/ቤቶች፤ የዲሞክራዊ ተቋማት፤ ነፃ ፕሬስ ወዘተ… መኖር ሁሉም በህግ የበላይነት ጽንስ ሀሳብ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ የሊብራል ዲሞክራሲ ጠበል አልተጠመቁም በሚባልላቸው መንግስታት (ለምሳሌ በቻይና) ጽንሰ ሀሳቡ ስልጣን ያለው አካል በሚያወጣቸው ህጐች መሰረት መግዛትና ማስተዳደር ላይ ብቻ የተገደበ ነው፡፡የህግ የበላይነት መርህ የአስተዳደር ህግ (በተለይ በእንግሊዝ) የተተከለበት መሰረት ነው፡፡ በዚህ መርህ መሰረት ስራ አስፈፃሚው፣ የአስተዳደር መ/ቤቶች እና የአስተዳደር ጉባዔዎች የሚሰጡት ውሳኔ በህጉ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡ በመንግስት አስተዳደር ውስጥ ህጋዊነት የሚሰፍነው ስልጣን የተሰጠው ማናቸውም የመንግስት አካል የሚወስዳቸው እርምጃዎች፣ የሚፈጽማቸው ድርቶች፣ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች እና የሚያወጣቸው ደንብና መመሪያዎች በህግ ጥላ ስር መሆናቸው ሲረጋገጥ ነው፡፡የመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡት ውሳኔ በህግ ከተቀመጠው የስልጣን ክልል በላይ ከሆነ ውሳኔው የህግ የበላይነት መርህን እንደሚጥስ ጥርጥር የለውም፡፡ ህጋዊነት መከበሩን ማረጋገጥ ማለት አስተዳደራዊ ድርጊት፣ ውሳኔ፣ እርምጃ፣ ደንብና መመሪያ በህግ በተቀመጠው የስልጣን ገደብ ውስጥ መሆኑን አሊያም አለመሆኑን ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የመደበኛ የፍርድ ቤቶች ተግባር ነው፡፡ ይህንን ተግባር በሚያሳንስ መልኩ በፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ላይ በህግ አውጭው የሚደረግ ገደብ በውጤቱ የህግ የበላይነት መርህን ይሸረሽራል፡፡ ገደቡ በህግ የበላይነት መርህ ላይ ከሚፈጥረው አደጋ በተጨማሪ የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት ያጣብባል፡፡ በተለይም ይህ መብት ህገ-መንግስታዊ እውቅና የተሰጠው ከሆነ የፍርድ ቤቶችን ስልጣን መገደብ ዞሮ ዞሮ የዜጎችን ህገ-መንገስታዊ መብት መገደብ ነው፡፡የህግ የበላይነት መርህ የአስተዳደር ህግ መሰረት ብቻ ሳይሆን ገደብ ጭምር እንደሆነ ማውሳት ያስፈልጋል፡፡ የውሳኔን ህጋዊነት ማረጋገጥ በይዘቱ ላይ መቆጠብን ያስከትላል፡፡ ፍ/ቤቶች የህግ የበላይነት በማስከበር ሚናቸው የአስተዳደራዊ ውሳኔዎች ይዘት እንዳያጣሩ ወይም በፖሊሲ ጥያቄዎች ጣልቃ እንዳይገቡ ይገድባቸዋል፡፡

ክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ ፌዴራል ቦርድ ደንብ ቁጥር 242/2003” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ትርጓሜ


ክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ ፌዴራል ቦርድ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 242/2003” ይችላል፡፡

ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡-
“ክልሎች” ማለት የአፋር ክልል፣ የሶማሌ ክልል፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል እና የቤኒሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ናቸው፤
“ልዩ ድጋፍ” ማለት በዋነኛነት ክልሎችን በወሳኝ የልማትና መልካም አስተዳደር መስኮች አቅማቸውን በሚገነባ መንገድ ልዩ እገዛ በመስጠት ፈጣንና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማረጋገጥ የሚደረግ እገዛ ነው፡፡
መቋቋም
ለክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ ፌዴራል ቦርድ (ከዚህ በኋላ “ቦርድ” እየተባለ የሚጠራ) በዚህ ደንብ ተቋቁሟል፡፡
የቦርዱ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል፡፡
የቦርዱ አባላት

ቦርዱ የሚከተሉት የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡-

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰየም ኃላፊ ……….. ሰብሳቢ

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ……………….. ምክትል ሰብሳቢ

የግብርና ሚኒስትር ……………………………… አባል

የትምህርት ሚኒስትር…………………………… አባል

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር …………………………. አባል

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ………………………. አባል

የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ………….. አባል

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰየሙ ሌሎች ኃላፊዎች …………….. አባላት

ዓላማ

ቦርዱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡-

የፌዴራል መንግስት አካላት ለክልሎች የሚሰጡትን ልዩ ድጋፍ የማስተባበር፣ የመምራትና ውጤታማነቱን የማረጋገጥ፣
ክልሎቹ ቀጣይ የልማት ማስፈጸም አቅም ለመገንባትና አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ ለሚያደርጉት ጥረት ተገቢውን ድጋፍ የማድረግ፣
ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎችና በአጎራባች ክልሎች መካከል የትብብር ግንኙነት እንዲጠናከር የማበረታታት፡፡
የቦርዱ ኃላፊነትና ተግባር
ቦርዱ የሚከተሉት ኃላፊነትና ተግባራት ይኖሩታል፡-
ክልሎች ራሳቸውን እንዲችሉ ቀጣይነት ያለው የማስፈጸም አቅም ግንባታ እገዛ ያደርጋል፤
በክልሎቹ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል የዕቅድ ሐሳብ ያመነጫል፣ በዕቅድ አዘገጃጀት፣ አፈጻጸምና ክትትል የተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣል፤
በልማትና በመልካም አስተዳደር ለክልሎቹ የሚደረገውን የፌዴራል ልዩ ድጋፍ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ውጤታማነቱንም ያረጋግጣል፤
ለክልሎቹ የሚደረገውን የፌዴራል ልዩ ድጋፍና የአጎራባች ክልሎችን ትብብር ያቀናጃል፤
ተገቢ ሙያና ልምድ ያላቸው አባላት የሚገኙበት የፌዴራል የልዩ ድጋፍ የቴክኒክ ኮሚቴ ያቋቁማል፤
ዓላማውን በብቃት ለማሳካት መገኘት አለባቸው ብሎ ያመነባቸውን አካላት በቦርዱ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ያደርጋል፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር
የቦርዱ ሰብሳቢ የቦርዱን ስራዎች በበላይነት ይመራል፡፡
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የቦርዱ ሰብሳቢ፡-
በዚህ ደንብ አንቀጽ 6 እና 10 የተመለከቱትን ኃላፊነትና ተግባራት በስራ ላይ እንዲውሉ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፣
የቦርዱን ስብሰባዎች ይጣራል፣ ይመራል፡፡
የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር
የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ፡-
የቦርዱ ሰብሳቢ በሌለበት ወቅት ተክቶ ይሰራል፤
የልዩ ድጋፍ የቴክኒክ ኮሚቴን በሰብሳቢነት ይመራል፤
የቦርዱ አባላት የወልና የተናጠል ኃላፊነትና ተግባሮቻቸውን በአግባቡ መፈፀማቸውን ይከታተላል፣ ያስተባብራል፡፡
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ኃላፊነት እና ተግባር
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፡-
የቦርዱና የልዩ ድጋፍ የቴክኒክ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ሆኖ ያገለግላል፤
የፌዴራል ድጋፉን የሚያቀናጅ ማዕከል በመሆን የቦርዱን ውሳኔዎች አፈጻጸም ይከታተላልለ፤
የልዩ ድጋፉን አፈጻጸም በሚመለከት በየሩብ ዓመቱ ለቦርዱና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ያቀርባል።
በቦርዱ አባላት የሚመሩ መስርያ ቤቶች ኃላፊነት እና ተግባር
በቦርዱ አባል የሚመራ ማንኛውም መሥሪያ ቤት በማቋቋሚያ ሕጉና በሌሎች ሕጎች የተሰጡት ኃላፊነትና ተግባራት እንደተጠበቁ ሆኖ ለክልሎች የሚሰጠውን ልዩ ድጋፍ በሚመለከት የሚከተሉት ኃላፊነትና ተግባራት ይኖሩታል፡-
ከክልሎቹና ከአጐራባች ክልል አቻ ሴክተር ቢሮዎች ጋር በመሆን ዘላቂ ልማትና እድገት ሊያመጡ የሚችሉ ወሳኝ የልማትና የአቅም ግንባታ ጉዳዮችን በመለየት ያቅዳል፣ ከሀገራዊ ግቦችና ስታንዳርዶች አኳያ የተጣጣሙ እንዲሆኑ በማድረግ ይተገብራል፣ ይገመግማል፣ ውጤታማነቱን ያረጋግጣል፤
በጋራ የተያዙ የወሳኝ ጉዳዮች ዕቅድ በተገቢው መንገድ ለማሳካት የሚያስችል የራሱን የልዩ ድጋፍ አደረጃጀት ይፈጥራል፤ እንደአስፈላጊነቱ ብቁ የሰው ኃይል በየክልሉ በማሰማራት ዕቅዱ ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል፤
የዕቅድ አፈጻጸሙን ተግባራዊ ለማድረግ በየክልሎቹ እና በየደረጃው በሚገኘው አቻ አደረጃጀት አቅም ከማሳደግ አኳያ በሰው ኃይል ስልጠና፣ በአደረጃጀትና በአሰራር ስርዓቶች የአቅም ግንባታ ስራ በተገቢው መንገድ ይተገብራል፤
ለዕቅድ አፈጻጸም ጠቃሚ የሆኑ የሀገር ውስጥና የውጪ ልምዶች እንደየክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታ ተቃኝቶ እንዲካተትና እንዲተገበር ያደርጋል፤
በክልሎቹ መካከልም በሴክተሩ የተሻሉ ልምዶች ልውውጥ በማድረግ እንዲስፋፉ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፤
በክልሎቹ ሊሸፈኑ የማይችሉ ግብዓቶችን በመለየት ያቀርባል፤ አፈጻጸሙን በቅርበት በመከታተል ይደግፋል፤
በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸምን ከክልሎቹና ከአጎራባች ክልሎች አቻ የሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በመሆን ይገመግማል፣ በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች አማካይነት ለቦርዱ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ያቀርባል።
የቦርዱ ስብሰባዎች
ቦርዱ በሶስት ወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሰብሳቢው ጥሪ በማንኛውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል፡፡
ከቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በስብሰባ ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፡፡
ቦርዱ ውሳኔ የሚያሳልፈው በድምፅ ብልጫ ይሆናል፤ ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው የደገፈው ሐሳብ የቦርዱ ውሳኔ ሆኖ ያልፋል።
የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ስነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል፡፡
ስለክትትልና ግምገማ
በቦርዱ አባላት የሚመሩ መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ ኃላፊዎች በአንደኛውና በሶስተኛው ሩብ ዓመት በየክልሉ በመገኘት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት የእቅድ አፈጻጸም ይገመግማሉ፤ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ወሳኝ ጉዳዮችን በጋራ ይለያሉ፣ ማካካሻ እቅድ ያፀድቃሉ፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላሉ፡፡
የቦርዱ አባላትና የየክልሉ የበላይ አመራሮች በሁለተኛውና በአራተኛው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም በጋራ ይገመግማሉ፣ ቀጣይ የልዩ እገዛ እቅድ አቅጣጫ ያፀድቃሉ፡፡
ተጠያቂነት
በዚህ ደንብ መሠረት የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባር ያልተወጣ የፌዴራል መሥሪያ ቤት አግባብ ባለው ሕግ መሰረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
የተሻረ ደንብ
በልማት ወደኋላ ለቀሩ ክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ የፌዴራል ቦርድ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 103/1996 (በደንብ ቁጥር 128/1999 እንደተሻሻለ) በዚህ ደንብ ተሽሯል፡፡
መመሪያ ስለማውጣት
ቦርዱ ይህን ደንብ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡

Costs in Criminal Cases


Costs in Criminal Cases Art.220. – Costs of public prosecution.  
(1) All the costs of public prosecutions, including appeals, shall be borne by the government.
(2) Where exceptional costs have been incurred by the prosecution for a reason attributable to the convicted person and he is a person of property, the court may, in addition to any other lawful punishment, order him to pay the whole or any of the costs incurred by the prosecution as taxed by the registrar of the court.
(3) Where a public prosecution has been instituted in respect of an offence. punishable on complaint and the injured party withdraws his complaint

(Art. 221 Penal Code), he shall be liable for all the costs of the prosecution.  

Art.221. – Costs of private prosecution.   (1) The costs of private prosecution shall be borne by the private prosecutor in accordance with Art. 46. (2) Where in a private prosecution the accused is acquitted and the court is on opinion that the charge was not made in good faith, it may order the private prosecutor to pay the whole or any part of the costs incurred by the accused. (3) Where a private prosecution is stayed as provided in Art. 48, all the costs of the private prosecution shall be borne by the government.   Art.222. – Injured party.   (1) Where the injured party claims compensation in a criminal case, he shall pay: (a) the court fees on the sum claimed as though it were a civil case; and (b) the costs of summoning witnesses and calling experts. (2) Where the injured party succeeds in his claim, the court shall order the accused to pay the court fees and costs mentioned in sub-art. (1).

በፍርድ የማይዳኙ ጉዳዮች


በፍርድ የማይዳኙ ጉዳዮች

በፍርድ የማይዳኙ ጉዳዮች

በፍርድ የማይዳኙ ጉዳዮችን (justiciability) በተመለከተ በፍርድ ቤቶችና በህግ ምሁራን ያለው አረዳድ የፅንሰ ሀሳቡን ትክክለኛ ይዘት አያንጸባርቅም፡፡ በሰ/መ/ቁ. 51790 ቅጽ 12a በሰፈረው የሚከተለው ማብራሪያ መሰረት በፍርድ የማይዳኝ ጉዳይ ማለት ከፍርድ ቤት የዳኝነት ስልጣን ውጪ የሆነ ጉዳይ ማለት ነው፡፡ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ. ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37/1/ ድንጋጌ በግልጽ የሚያሳየው ጉዳይ ነው፡፡ ከዚሁ የሕገ መንግስት ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ፍርድ ቤቶች አንድን ጉዳይ (አቤቱታ) ተቀብለው ውሳኔ መስጠት የሚችለት ዳኝነት የተጠየቀበት ጉዳይ በሕግ ለሌላ አካል ያልተሰጠ ጉዳይ በሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ መሆኑን ነው፡፡ በሕግ ተለይተው በአስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲቋጩ በተባሉ ጉዳዮች ላይ መደበኛ ፍርድ ቤት የመዳኘት የስረ ነገር ስልጣን ስለሌለው በሕጉ መሰረት ለአንድ አስተዳደር አካል ቀርቦ አስተዳደራዊ ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ ወይም ለአስተዳደር መቅረብ የሚገባውን ጉዳይ ፍርድ ቤት ሊያስተናግደውም ሆነ አከራክሮ ውሳኔ ሊሰጥበት አይችልም፡፡ይኸው አቋም ጉዳዩ በፍርድ እንደሚዳኝ ድምዳሜ ላይ በተደረሰባቸው ውሳኔዎች ላይም ተፈጻሚ ተደርጓል፡፡ ለምሳሌ በሰ/መ/ቁ. 80202 ቅጽ 15b በተሰጠ የህግ ትርጉም መሰረት ግንባታ በጊዜው አለመጠናቀቁን ወይም የገንዘብ አቅም ማነስን አሊያም በሌላ ምክንያት አስተዳደሩ በሚወስዳቸው የኪራይ (lease) ይዞታ ማቋረጥ እርምጃዎች ላይ ባለይዞታው ቅሬታ ሲያድርበት ጉዳዩን ለማየት በሕግ በግልጽ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው ሌላ አካል እስከሌለ ድረስ ጉዳዩ በፍርድ ሊወሰን ይገባዋል፡፡በእርግጥ በአረዳድ ረገድ የሚታየው ብዥታ በእኛ አገር ብቻ ሳይሆን በሌሎች አገራትም ይስተዋላል፡፡ ለምሳሌ በአውስትራሊያ የአስተዳደር ህግ በፍርድ የማይዳኝ ጉዳይን አስመልክቶ ያለው ግንዛቤ በሚከተሉት ሀሳቦች ዙሪያ ይዋልላል፡፡
ጉዳዩ ከፍርድ ቤቱ የዳኝነት ስልጣን ውጪ ነው፡፡ ጉዳዩ በፍርድ ቤቱ የዳኝነት ስልጣን ክልል ውስጥ ቢወድቅም ሕዝባዊ የስልጣን መገልገልን አይመለከትም፡፡
ፍርድ ቤቱ የዳኝነት ስልጣን አለው ነገር፡፡ ግን ጉዳዩን ለመፍታት ተቋማዊ ብቃት የለውም፡፡ ፍርድ ቤቱ ስልጣንም ብቃትም አለው፡፡ ሆኖም ጉዳዩን በዳኝነት ለመጨረስ ህገ መንግስታዊ ተገቢነት የለውም፡፡ጉዳዩ ገና ያልበሰለ ነው፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤት ጣልቃ አይገባበትም፡፡ፍርድ ቤቱ ህጋዊነትን ከማጣራት አልፎ የጉዳዩን ይዘት (merit) ሳይፈትሽ በአጣሪ ዳኝነት ሊመረምር የሚችልበት በቂ ምክንያት (grounds of judicial review) የለም፡፡ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመወሰን የሚያስችል ቅቡልነት ያለው ማስረጃ ማግኘት ወይም ማስቀረብ አልቻለም፡፡cከዝርዝሮቹ መካከል በፍርድ የማይዳኝ ጉዳይ በሚገባ የተገለጸው በ3ኛ እና 4ኛ ላይ ነው፡፡ የዳኝነት ስልጣን ጉዳዩን ለመዳኘት ካለመቻል የሚመነጭ ባህርይ ሳይሆን በፍርድ ቤቶች ስልጣን ላይ በህግ የተቀመጠ ገደብ ነው፡፡ አንድን ጉዳይ እንዲያይ ጥያቄ የቀረበለት ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ወይም የይግባኝ ስልጣኑ ለሌላ አካል ከተሰጠ የስረ-ነገር የዳኝነት ስልጣን ያጣል፡፡ በህግ ጉዳይ ላይ ብቻ በከፊል ስልጣን አግኝቶ ከሆነም በፍሬ ነገር ረገድ የሚደርስበት ድምዳሜ የስልጣኑን ልክ ያልፋል፡፡ ወጣም ወረደ ግን የዳኝነት ስልጣን አለመኖር ራሱን ችሎ የቆመ ሀሳብ በመሆኑ ከጉዳዩ ለመዳኘት አለመቻል ጋር ሊቀላቀል አይገባውም፡፡በዝርዝሩ 2ኛ ላይ የተጠቀሰው ‘ህዝባዊ ስልጣን’ ጉዳዩ የአስተዳደር ህግ ጥያቁ እንደማያስነሳ ያመለክታል፡፡ ሁለት የተለያየ የአስተዳር ህግ እና የፍትሐ ብሔር ስርዓት ላለቸው አገራት ይህ ነጥብ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ መነሻው መንግስት እንደ ግለሰብ ያሉትን መብቶች ተጠቅሞ የፈጸመው ድርጊት ከሆነ በአጣሪ ዳኝነት አይስተናገድም፡፡ ከውል ውጪ ኃላፊነት ወይም ከውል በሚመነጭ ግዴታ መንግስት ተጠያቂነት ካለበት ጉዳዩ ከመነሻው የአጣሪ ዳኝነት ጥያቄ አያስነሳም፡፡የጉዳዩ አለመብሰል እና የይዘት ጥያቄ የአስተዳደር ህግ ወሰንን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ ፍርድ ቤቶች አስተዳደሩ ገና ውሳኔ ላይ ያልደሰበትን ጉዳይ የማያዩት ህጋዊነቱን የሚመዝኑበት በቂ ምክንያት ስለማያገኙ ነው፡፡ የውሳኔው ይዘት ማለትም ትክክለኛነቱ እንዲሁ ከህግ አንጻር የሚጣራበት መሰረት የለም፡፡ በመጨረሻም ማስረጃ ሊገኝ አለመቻሉ ወይም እንዲቀርብ የታዘዘው ማስረጃ ሚስጥራዊ ተብሎ በመፈረጁ የተነሳ ፍርድ ቤቱ እልባት ለመስጠት አለመቻሉ ጉዳዩ ከመነሻው በፍርድ እንደማይዳኝ አያመለከትም፡፡በዝርዝሮቹ 3ኛ እና 4ኛ ላይ የሰፈረውን ሀሳብ በከፊል በሚያቅፍ መልኩ በፍርድ የማይዳኝ ጉዳይ ማለት ምን እንደሆነ ትክክለኛ ትርጓሜ የተሰጠው በሰ/መ/ቁ. 42150 ቅጽ 12d ከአብላጫው ድምጽ በተለየው ሀሳብ ላይ ነው፡፡ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡አንድ ጉዳይ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል ነው የሚባለው የክርክሩ መሠረታዊ ባህሪ በፍርድ ለመጨረስ አመች የሆነ ሲሆንና ተከራካሪዎቹ የሚከራከሩበት ጉዳይ ንድፈ ሃሳባዊ ወይም ምናባዊ የፈጠራ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ሣይሆን በነባራዊ ዕውነታና ተጨባጭ በሆነ ችግር ወይም ክስተት መሠረት ያደረገ የመብት ወይም የሃላፊነት ጥያቄ ሲሆን እንደሆነ ነው፡፡በአብላጫው ድምጽ ላይ ግን ፅንሰ ሀሳቡ ከከሳሽነት ብቃት ጋር ተምታቷል፡፡ በአብላጫው አስተያየት አንድ ጉዳይ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል ነው ሊባል የሚችለው፤…የክርክሩ መሠረት በሕግ ጥበቃ ያገኘ መብት ወይም ግዴታ ሲሆን ወይም ለመብቱ ወይም ግዴታው መሠረት የሚሆን ውል መኖሩ ሲረጋገጥ ነው፡፡ይሁን እንጂ ‘ያለመዳኘት’ ከጉዳዩ ባህርይ እንጂ ከተከራካሪ ወገኖች ብቃት ወይም መብት አይመነጭም፡፡ ከባህርያቱ አንጻር ሲቃኝ አንድ ጉዳይ በፍርድ ሊዳኝ አይችልም የሚባለው አንድም ከፍርድ ቤቱ ተቋማዊ ብቃት አንጻር በፍርድ ለማለቅ አመቺ ባለመሆኑ አሊያም ከህግ መንግስታዊው የስልጣን ክፍፍል አንጻር ዳኝነት መስጠት ተገቢ ስለማይሆን ነው፡፡ከተቋማዊ ብቃት አንጻር አንዳንድ ጉዳዮች የብዙ ወገኖች ተጻራሪና ተነጻጻሪ ጥቅም ያዘሉ (polycemtric) በመሆናቸው በባህርያቸው በፍርድ ቤት ሙግት ለማለቅ አያመቹም ወይም አይመቹም፡፡ እንደ ፒተር ኬን ገለጻ፤
A polycentric issue is one which involves a large number of interlocking and interacting interests and considerations.e
የፍርድ ቤት የሙግት ስርዓት ተጻራሪ የጥቅም ግጭት ያለባቸውን ጉዳዮች በወጉ ለመፍታት አያመችም፡፡ ፍርድ ቤቶች የሚከተሉት ጥብቅ የሙግት ስነ ስርዓት ብሎም የሚመደብላቸው ውስን የገንዘብና የሰው ኃይል ቴክኒካልና ሳይንሳዊ መረጃና ማስረጃ ለማሰባሰብ ሆነ ተጻራሪ ጥቅሞችን በማቻቻል ዘላቂ መፍትሔ ለመቀየስ አያስችልም፡፡ በአጭር አነጋገር እነዚህን ጉዳዮች ለመዳኘት ተቋማዊ ብቃታቸው አይፈቅድላቸውም፡፡በፍርድ ለመዳኘት ህገ መንግታዊ ተገቢነት የሌላቸው ጉዳዮች በፈራጆች ውሳኔ ሳይሆን በተመራጮችና ፖለቲከኞች ጥበብና ብልሀት ዘላቂ መፍትሔ የሚሰጣቸው የፖሊሲ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ዳኞች ተሿሚዎች እንጂ ተመራጮች አይደሉም፡፡ ለመራጩ ህዝብም ቀጥተኛ ተጠያቂነት የለባቸውም፡፡ ስለሆነም አገራዊ ፋይዳ ባላቸው የፖሊሲ ጥያቄዎች ላይ ዳኝነት ለመስጠት የሚያስችል ህገ መንግስታዊ ስልጣን የላቸውም፡፡ ለምሳሌ የውጭ ጉዳይ፣ መከላከያ እንዲሁም የብሔራዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ዳኝነት መስጠት ከፍርድ ቤቶች ህገ መንግስታዊ ሚና አንጻር ተገቢነት የለውም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዓለም ዓቀፍ ስምምነት መዋዋል፣ የሚኒስትሮች ሹመትና ሽረት፣ ፓርላማ የመበተን ስልጣን፣ ለህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረግ፣ መንግስት በአንድ አካባቢ መሰረት ልማት ለመዘርጋት የሚደርስበት ውሳኔ በአጠቃላይ የመንግስት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ውሳኔ ፖለቲካዊ ተገቢነት መዝኖ ፍርድ ማሳረፍ የዳኝነት አካሉ ሚና አይደለም፡፡ እነዚህ ጉዳዮች በዳኝነት ማየት የስልጣን ክፍፍል መርህን ይጥሳል፡፡ ውሳኔ ሰጪው ፈቃደ ስልጣን የሚወሰኑ ጉዳዮች እንዲሁ በፍርድ ለማለቅ አመቺ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ የስራ ፈቃድ ወይም የግንባታ ቦታ ጥያቄዎች ተገቢነት በፍርድ ቤት ጭብጥ ተይዞበት የሚወሰን አይደለም፡፡ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶችና ሁኔታዎች አንድ ጉዳይ በፍርድ የማይዳኘው የክሱ ምክንያት በይዘቱ ዳኝነት ለመስጠት አመቺ ሳይሆን እንዲሁም ህገ መንግስታዊ ተገቢነት ሳይኖረው ሲቀር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለክርክሩ መነሻ የሆነው አስተዳደራዊ ውሳኔ ወይም ድርጊት ‘የጀርባ ምክንያት’ ፖለቲካዊ ነክ መሆኑ ፍርድ ቤቶች አከራክረው ውሳኔ ከመስጠት አያግዳቸውም፡፡ በሰ/መ/ቁ. 48217f አመልካች በህጋዊ መንገድ ተመርተው የሰሩት ቤት በ1ኛ ተጠሪ ተነጥቀው ለ2ኛ ተጠሪ እንደተሰጠባቸው በመግለጽ እንዲመለስላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ የቤቱ አሰጣጥ መነሻ አመልካች በጦርነት ምክንያት ቤትና ንብረት ስለወደመባቸው ለተፈናቃዮች ምትክ ቦታና ገንዘብ እንዲሰጥ መንግስት ባስተላለፈው ውሳኔ ነው፡፡ አመልካች በዚሁ መሰረት የራሳቸውን ገንዘብ ጨምረው ቤቱን ሰርተው ከጨረሱ በኋላ ‘ኤርትራዊ ነሽ’ በሚል ምክንያት 1ኛ ተጠሪ ቤታቸውን ነጥቆ ለ2ኛ ተጠሪ ሰጥቷል፡፡
ክሱ በቀረበበት ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ የቤቱ አሰጣጥ ፖለቲካዊ ውሳኔ መሆኑን በመጥቀስ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዳይዳኝ የመጀሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያነሳ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ሆኖም ክርክሩን በይግባኝና በሰበር ያዩት ፍርድ ቤቶች ጉዳዩ በአስተዳደር እንጂ በፍርድ እንደማያልቅ አቋም በመያዛቸው የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሸሯል፡፡ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/ሰ/ችሎት በበኩሉ በድርጊቱ ይዘት ላይ በማተኮር የአመልካች የክስ ‘አለአግባብ ቤቴን ተነጠቅኩኝ’ በሚል የቀረበ እንደሆነ በመጠቆም ጉዳዩ በፍርድ ሊያልቅ እንደሚችል ትክክለኛ ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡
የአገራችን ፍርድ ቤቶች በፍርድ አይዳኙም በሚል በራቸውን የሚዘጉባቸው ጉዳዮች አብዛኞቹ የተቋማዊ ብቃት ሆነ የፖሊሲ ጥያቄ አያስነሱም፡፡ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸው በሰበር ችሎት ከታረሙ አንዳንድ ውሳኔዎች ለመረዳት እንደሚቻለው በግለሰብና በመንግስት መካከል የሚነሱ አስተዳደራዊ ክርክሮችን ‘በፍርድ የማይዳኙት’ ውስጥ የመፈረጅ አዝማሚያ በፍርድ ቤቶቻችን ዘንድ ሰፍኖ ይታያል፡፡በሰ/መ/ቁ. 75414 ቅጽ 14g የባለቤትነት ምስክር ወረቀት እንዲሰረዝ የቀረበ አቤቱታ ‘በፍርድ አይዳኝም’ በሚል በስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ የተደረገ ቢሆንም የሰበር ችሎት የሚከተለውን ሐተታ በማስፈር ሽሮታል፡፡የንብረት ባለሀብትነት መብት ከአንዱ ወገን ወደ ሌላው እንዴት መተላለፍ እንዳለበት በህጉ የተመለከተውን ደንብና ሥርዓት ሳይከተል ስለሆነ የንብረቱ ባለሀብት ስለመሆኑ የህግ ግምት መውሰጃ የሆነው የባለቤትነት ምስክር ወረቀት ቀሪ ነው፤ ሊሰረዝ ይገባል በማለት የሚቀርብ ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1195፣ 1196 እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33/2/ እና 231/1/ሀ/ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት በፍ/ቤት ሊረጋገጥ የሚችል የዳኝነት ጥያቄ እንጂ ጉዳዩ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል ጉዳይ አይደለም ለማለት የሚያበቃ አይደለም፡፡

የከሳሽነት ብቃት
‘አንድን የአስተዳደር ተግባር በፍርድ ቤት ወይም በሌላ የዳኝነት ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መሞገት የሚችለው ማነው?’ የሚለው ጥያቄ በአስተዳደር ህግ ውስጥ መልስ አሁንም ድረስ መቋጫ የሌለው አንዳንዴም ውሉ የጠፋበት የክርክር ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በየአገራቱ ያለው ተሞክሮ ሆነ በአንድ አገር ውስጥ በሚገኙ ፍርድ ቤቶች ውስጥ የሚያዘው አቋም እንዲሁ ወጥነት አይታይበትም፡፡ የጽንሰ ሀሳቡን ምንነት እና ዘርፈ ብዙ ስለሆኑት መልኮቹ ከመቃኘታችን በፊት የቋንቋ አጠቃቀም ራሱን የቻለ እክል እንደሚፈጥር ማውሳት ያስፈልጋል፡፡ አንድን የህግ ጽንሰ ሃሳብ በጥልቀት ለመረዳት መጀመሪያ ጽንሰ ሀሳቡ የሚገለጽበት ቋንቋ አብዛኛው ሰው የሚረዳው ስያሜ ሊኖረው ይገባል፡፡ ለምሳሌ ያህል ‘ለ’ Judicial Review አንድ ወጥ የአማርኛ ፍቺ አለመኖሩ ፅንሰ ሀሳቡ በአገራችን ውስጥ ያሉትን ገጽታዎችና የተፈጻሚነት ወሰኑን በተመለከተ የተሟላ ትንተና ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት ያደበዝዘዋል፡፡በእንግሊዘኛ Standing በላቲን ደግሞ Locus Standi በመባል የሚታወቀው ቃል በኢትዮጵያ የህግ ስነ ጽሁፍ ውስጥ ገና መደበኛ ስያሜውን አላገኘም፡፡ ‘የመክሰስ መብት’፣ ‘የመክሰስ ችሎታ’ የሚሉት አገላለጾች አሁን አሁን በከፊልም ቢሆን ተቀባይነት እያገኙ ነው፡፡ ‘በጉዳዩ የሚያገባው ወገን’፣ ‘በጉዳዩ ጥቅም ያለው ወገን’፣ ‘ጉዳት የደረሰበት ወገን’ ወዘተ…የሚሉት አጠራሮችም በአቻነት ጥቅም ላይ ሲውሉ ይታያል፡፡‘የመክሰስ መብት’ በጥሬ ትርጉሙ የወሰድነው እንደሆነ ከህግ ወይም ከህገ-መንግስት የመነጨ መብት መኖርን እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ስለሆነ ፍቺ ሆኖ መቅረቡ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጥቅል የሆነ መብትን እንጂ በአንድ ጉዳይ በፍርድ ቤት አቤቱታ የማቅረብ መብትን በአግባቡ አያመለክትም፡፡ በመርህ ደረጃ ማንም ሰው የመክሰስ መብት አለው፡፡ ይህን መብቱን በተግባር ሊገለገልበት የሚችለው ግን ለመክሰስ የሚያበቃው ሁኔታ በህግ ተሟልቶ ሲገኝብቻ ነው፡፡በሌላ በኩል ‘የመክሰስ ችሎታ’ በተለመደው የቋንቋ አጠቃቀም ወይም በመደበኛ ፍቺው ‘ለ’ Standing ወካይ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም፡፡ የመክሰስ ችሎታ የሚመጣው ‘የ’ Standing ጥያቄ ከተመለሰ በኋላ ነው፡፡ አንድ ሰው ‘የመክሰስ ችሎታ የለውም’ የሚባለው ህጋዊ ሰውነት ወይም ውክልና በማጣቱ እንዲሁም በእድሜው ወይም በአእምሮ ጤንነቱ ምክንያት በፍርድ ቤት ቀርቦ ለመከራከር ሳይችል ሲቀር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር Standing ኖሮት ችሎታ ግን ላይኖረው ይችላል፡፡ በጉዳዩ የሚያገባው፣ በጉዳዩ ጥቅም ያለው፣ ጉዳት የደረሰበት፣ የሚሉት አገላለጾችም ፅንሰ ሀሳቡን አለአግባብ የማጥበብ ወይም የማስፋት እንደምታ ያዘሉ በመሆኑ በአቻ ትርጉም ለመውሰድ ያስቸግራል፡፡ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች በዚህ መጽሐፍ Standing የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ‘የከሳሽነት ብቃት’ በሚል ተተርጉሟል፡፡ አንድ ሰው በፍትሐብሔር ሆነ በአስተዳደር ክርክር ከሳሽ ሆኖ ለመሟገት እንዲፈቀድለት በቅድሚያ ክሱን ለማቅረብ ብቁ የሚያደርጉት የህግ ሁኔታዎች መሟላታቸው ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ ብቃት እንዳለው የሚወሰነው በከሳሹና ክስ ባቀረበበት ጉዳይ መካከል በበቂ ሁኔታ የሚታይ ግንኙነት (nexus) ሲኖር ነው፡፡የግንኙነቱ ገመድ በህግ ማዕቀፍ የሚገለጽበት መንገድ ከአገር አገር ይለያያል፡፡ በብዙ የካሪቢያን አገራት በአስተዳራዊ ድርጊት ወይም አልድርጊት (omission) መብትና ጥቅሙ የተጎዳ ሰው የከሳሽነት ብቃት የሚኖረው ሲሆን በተወሰኑ ሁኔታዎች ከግላዊ ጥቅሙ ባሻገር ህዝባዊ ጥቅሙን ለማስከበር ክስ ለማቅረብ ይፈቀድለታል፡፡a በአውስትራሊያ እንደሚጠየቀው የመፍትሔ ዓይነት ይለያያል፡፡ የዕግድ እና የማስገደጃ ትዕዛዞችን ለመጠየቅ የተፈጸመው ወይም ያልተፈጸመው ተግባር ግላዊ ጥቅም ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚጋራው ሕዝባዊ ጥቅም በሚሆንበት ጊዜ ግን ከሳሽ ለመሆን የሚፈቀድለት በጉዳዩ የተለየ ጥቅም እንዳለው ማሳየት ከቻለ ነው፡፡b የመሻሪያ (Certiorari)፣ የክልከላ (Prohibition) እና አካልን ነጻ የማውጣት (Habeas Corpus) ዳኝነት ለመጠየቅ በመርህ ደረጃ ማንኛውም ሰው ከሳሽ የመሆን ብቃት አለው፡፡በአገራችን በፍትሐብሔር እና በአስተዳደር ክርክሮች የከሳሽነት ብቃት የሚወሰነው በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ህጉ ድንጋጌዎች ነው፡፡ ይህ ጠቅላላ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የከሳሽነት ብቃት ገደቦችን የሚያስቀሩ በጣት የሚቆጠሩ ልዩ ሁኔታዎች ስለመኖራቸው መዘንጋት የለበትም፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሰው የፍትሐብሔር ህጉ ቁጥር 402/2/ ሲሆን እንደሚከተለው ይነበባል፡፡ከዚህ በላይ ባለው ቁጥር [401] የተመለከተውን ፈራሽነት ማንኛውም ባለጉዳይ ሁሉ ሊጠይቅ ይችላል፡፡