ክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ ፌዴራል ቦርድ ደንብ ቁጥር 242/2003” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ትርጓሜ


ክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ ፌዴራል ቦርድ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 242/2003” ይችላል፡፡

ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡-
“ክልሎች” ማለት የአፋር ክልል፣ የሶማሌ ክልል፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል እና የቤኒሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ናቸው፤
“ልዩ ድጋፍ” ማለት በዋነኛነት ክልሎችን በወሳኝ የልማትና መልካም አስተዳደር መስኮች አቅማቸውን በሚገነባ መንገድ ልዩ እገዛ በመስጠት ፈጣንና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማረጋገጥ የሚደረግ እገዛ ነው፡፡
መቋቋም
ለክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ ፌዴራል ቦርድ (ከዚህ በኋላ “ቦርድ” እየተባለ የሚጠራ) በዚህ ደንብ ተቋቁሟል፡፡
የቦርዱ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል፡፡
የቦርዱ አባላት

ቦርዱ የሚከተሉት የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡-

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰየም ኃላፊ ……….. ሰብሳቢ

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ……………….. ምክትል ሰብሳቢ

የግብርና ሚኒስትር ……………………………… አባል

የትምህርት ሚኒስትር…………………………… አባል

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር …………………………. አባል

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ………………………. አባል

የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ………….. አባል

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰየሙ ሌሎች ኃላፊዎች …………….. አባላት

ዓላማ

ቦርዱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡-

የፌዴራል መንግስት አካላት ለክልሎች የሚሰጡትን ልዩ ድጋፍ የማስተባበር፣ የመምራትና ውጤታማነቱን የማረጋገጥ፣
ክልሎቹ ቀጣይ የልማት ማስፈጸም አቅም ለመገንባትና አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ ለሚያደርጉት ጥረት ተገቢውን ድጋፍ የማድረግ፣
ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎችና በአጎራባች ክልሎች መካከል የትብብር ግንኙነት እንዲጠናከር የማበረታታት፡፡
የቦርዱ ኃላፊነትና ተግባር
ቦርዱ የሚከተሉት ኃላፊነትና ተግባራት ይኖሩታል፡-
ክልሎች ራሳቸውን እንዲችሉ ቀጣይነት ያለው የማስፈጸም አቅም ግንባታ እገዛ ያደርጋል፤
በክልሎቹ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል የዕቅድ ሐሳብ ያመነጫል፣ በዕቅድ አዘገጃጀት፣ አፈጻጸምና ክትትል የተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣል፤
በልማትና በመልካም አስተዳደር ለክልሎቹ የሚደረገውን የፌዴራል ልዩ ድጋፍ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ውጤታማነቱንም ያረጋግጣል፤
ለክልሎቹ የሚደረገውን የፌዴራል ልዩ ድጋፍና የአጎራባች ክልሎችን ትብብር ያቀናጃል፤
ተገቢ ሙያና ልምድ ያላቸው አባላት የሚገኙበት የፌዴራል የልዩ ድጋፍ የቴክኒክ ኮሚቴ ያቋቁማል፤
ዓላማውን በብቃት ለማሳካት መገኘት አለባቸው ብሎ ያመነባቸውን አካላት በቦርዱ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ያደርጋል፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር
የቦርዱ ሰብሳቢ የቦርዱን ስራዎች በበላይነት ይመራል፡፡
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የቦርዱ ሰብሳቢ፡-
በዚህ ደንብ አንቀጽ 6 እና 10 የተመለከቱትን ኃላፊነትና ተግባራት በስራ ላይ እንዲውሉ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፣
የቦርዱን ስብሰባዎች ይጣራል፣ ይመራል፡፡
የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር
የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ፡-
የቦርዱ ሰብሳቢ በሌለበት ወቅት ተክቶ ይሰራል፤
የልዩ ድጋፍ የቴክኒክ ኮሚቴን በሰብሳቢነት ይመራል፤
የቦርዱ አባላት የወልና የተናጠል ኃላፊነትና ተግባሮቻቸውን በአግባቡ መፈፀማቸውን ይከታተላል፣ ያስተባብራል፡፡
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ኃላፊነት እና ተግባር
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፡-
የቦርዱና የልዩ ድጋፍ የቴክኒክ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ሆኖ ያገለግላል፤
የፌዴራል ድጋፉን የሚያቀናጅ ማዕከል በመሆን የቦርዱን ውሳኔዎች አፈጻጸም ይከታተላልለ፤
የልዩ ድጋፉን አፈጻጸም በሚመለከት በየሩብ ዓመቱ ለቦርዱና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ያቀርባል።
በቦርዱ አባላት የሚመሩ መስርያ ቤቶች ኃላፊነት እና ተግባር
በቦርዱ አባል የሚመራ ማንኛውም መሥሪያ ቤት በማቋቋሚያ ሕጉና በሌሎች ሕጎች የተሰጡት ኃላፊነትና ተግባራት እንደተጠበቁ ሆኖ ለክልሎች የሚሰጠውን ልዩ ድጋፍ በሚመለከት የሚከተሉት ኃላፊነትና ተግባራት ይኖሩታል፡-
ከክልሎቹና ከአጐራባች ክልል አቻ ሴክተር ቢሮዎች ጋር በመሆን ዘላቂ ልማትና እድገት ሊያመጡ የሚችሉ ወሳኝ የልማትና የአቅም ግንባታ ጉዳዮችን በመለየት ያቅዳል፣ ከሀገራዊ ግቦችና ስታንዳርዶች አኳያ የተጣጣሙ እንዲሆኑ በማድረግ ይተገብራል፣ ይገመግማል፣ ውጤታማነቱን ያረጋግጣል፤
በጋራ የተያዙ የወሳኝ ጉዳዮች ዕቅድ በተገቢው መንገድ ለማሳካት የሚያስችል የራሱን የልዩ ድጋፍ አደረጃጀት ይፈጥራል፤ እንደአስፈላጊነቱ ብቁ የሰው ኃይል በየክልሉ በማሰማራት ዕቅዱ ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል፤
የዕቅድ አፈጻጸሙን ተግባራዊ ለማድረግ በየክልሎቹ እና በየደረጃው በሚገኘው አቻ አደረጃጀት አቅም ከማሳደግ አኳያ በሰው ኃይል ስልጠና፣ በአደረጃጀትና በአሰራር ስርዓቶች የአቅም ግንባታ ስራ በተገቢው መንገድ ይተገብራል፤
ለዕቅድ አፈጻጸም ጠቃሚ የሆኑ የሀገር ውስጥና የውጪ ልምዶች እንደየክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታ ተቃኝቶ እንዲካተትና እንዲተገበር ያደርጋል፤
በክልሎቹ መካከልም በሴክተሩ የተሻሉ ልምዶች ልውውጥ በማድረግ እንዲስፋፉ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፤
በክልሎቹ ሊሸፈኑ የማይችሉ ግብዓቶችን በመለየት ያቀርባል፤ አፈጻጸሙን በቅርበት በመከታተል ይደግፋል፤
በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸምን ከክልሎቹና ከአጎራባች ክልሎች አቻ የሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በመሆን ይገመግማል፣ በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች አማካይነት ለቦርዱ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ያቀርባል።
የቦርዱ ስብሰባዎች
ቦርዱ በሶስት ወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሰብሳቢው ጥሪ በማንኛውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል፡፡
ከቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በስብሰባ ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፡፡
ቦርዱ ውሳኔ የሚያሳልፈው በድምፅ ብልጫ ይሆናል፤ ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው የደገፈው ሐሳብ የቦርዱ ውሳኔ ሆኖ ያልፋል።
የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ስነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል፡፡
ስለክትትልና ግምገማ
በቦርዱ አባላት የሚመሩ መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ ኃላፊዎች በአንደኛውና በሶስተኛው ሩብ ዓመት በየክልሉ በመገኘት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት የእቅድ አፈጻጸም ይገመግማሉ፤ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ወሳኝ ጉዳዮችን በጋራ ይለያሉ፣ ማካካሻ እቅድ ያፀድቃሉ፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላሉ፡፡
የቦርዱ አባላትና የየክልሉ የበላይ አመራሮች በሁለተኛውና በአራተኛው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም በጋራ ይገመግማሉ፣ ቀጣይ የልዩ እገዛ እቅድ አቅጣጫ ያፀድቃሉ፡፡
ተጠያቂነት
በዚህ ደንብ መሠረት የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባር ያልተወጣ የፌዴራል መሥሪያ ቤት አግባብ ባለው ሕግ መሰረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
የተሻረ ደንብ
በልማት ወደኋላ ለቀሩ ክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ የፌዴራል ቦርድ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 103/1996 (በደንብ ቁጥር 128/1999 እንደተሻሻለ) በዚህ ደንብ ተሽሯል፡፡
መመሪያ ስለማውጣት
ቦርዱ ይህን ደንብ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.