የክልል የአስተዳደር ህግ ፌደራላዊ የመንግስት


የክልል የአስተዳደር ህግ ፌደራላዊ የመንግስት
አወቃቀር የመንግስትንና የግለሰብን ግንኙነት ሁለትዮሽ ገፅታ ያላብሰዋል፡፡ በፌደራል ደረጃ በፌደራሉ መንግስትና በግለሰቡ መካከል የሚፈጠር ግንኙት ሲኖር ይኸው ተመሳሳይ ግንኙነት በክልል ደረጃ በክልሉ መንግስትና በግለሰቡ መካከል ይፈጠራል፡፡ የኢትዮጵያ የአስተዳደር ህግ ይዘት፣ ወሰንና መገለጫ ባህሪያት ከዚህ ሀሳብ ይነሳል፡፡ መንግስትና የህዝብ የአስተዳደር በፌዴራልና በክልል ደረጃ የተዋቀረ እንደመሆኑ የአገራችን የአስተዳደር ህግ የፌደራል እና የክልል አስተዳደር ህግ ድምር ውጤት ነው፡፡ ከድምሩና ከውጤቱ በፊት ግን በፌደራላዊ የመንግስት ስርዓት ውስጥ ሁለት ዓይነት የአስተዳደር ህግ የመኖሩ ጉዳይ ግልጽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም ክልሎች የራሳቸውን የአስተዳደር ህግ ማውጣት ይችላሉ? የሚል የስልጣን ክፍፍል ጥያቄ ሊነሳ አይገባም፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በፌደራል እና በክልል የተዋቀረ ሲሆን ሁለቱም በተመሳሳይ መልኩ ህግ አውጪ፤ አስፈፃሚና ህግ ተርጓሚ የሚባሉ የመንግስት አካላት አቅፈዋል፡፡a እነዚህ ሶስት የመንግስት አካላት በህገ-መንግስቱ ለፌደራል እና ለክልሎች በተሰጡት ስልጣናት ስር ህግ የማውጣት፤ የመተግበር እና የመተርጐም ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ በክልል ደረጃ ህግ አስፈፃሚው አካል የክልሉ መስተዳድር ሲሆን የክልሉ ምክር ቤት ያወጣቸውን ህጐች ይተገብራል፡፡b ስልጣንን በመገልገል የሚፈጸሙ ተግባራት አስተዳደራዊ (ለምሳሌ የምርመራ፤ የክትትል፤ ቁጥጥርና ምክር መስጠት)፣ ህጉን ለመተግበር የሚረዱ መመሪያዎችን የማውጣት እንዲሁም የአስተዳደር ውሳኔዎችንና እርምጃዎችን የመውሰድ (ለምሳሌ የንግድ ድርጅት የመዝጋት፤ የንግድ ፍቃድ የመስጠት፤ የማገድ፤ የመሰረዝ) ተግባራትን ያጠቃልላል፡፡ የክልል አስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ህጋዊነትና ፍትሐዊነት በተመለከተ የክልል ምክር ቤት እና የክልል ፍ/ቤቶች የየራሳቸውን ሚና ይጫወታሉ፡፡ ለምሳሌ የክልሉ ምክር ቤት አነስተኛ የውሳኔ እና የመመሪያ አወጣጥ ስነ-ስርዓቶችን ሊደነግግ ይችላል፡፡ ፍ/ቤቶች ደግሞ የአስተዳደራዊ ውሳኔዎችና መመሪያዎች ህጋዊነት በመመርመር መስተዳደሩ ለህግ ተገዢ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡ በዚህ መልኩ የአስተዳደር ህግ በእያንዳንዱ ክልል የግድ ይፈጠራል፡፡ በአሁኑ ወቅት ያለው የፌደራል የአስተዳደር ህግ ገና በቅጡ ያልዳበረና ጥልቀት ያለው ጥናትና ምርምር ተደርጐበት ትክክለኛ ይዘቱ፤ ቅርፁ፤ መገለጫውና ወሰኑ ተለይቶ የሚታወቅ አይደለም፡፡ ከዚህ በባሰ ደግሞ በክልሎች ያለው የአስተዳደር ህግ በአግባቡ ሊጠናና ሊታወቅ ቀርቶ እስከ መኖሩ ሳይቀር ተዘንግቷል ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ የተነሳ በፌደራሉ የአስተዳደር ህግ እና በክልል የአስተዳደር ህግ መካከል ያለው ዝምድና እና መወራረስ ራሱን የቻለ ጥናትና ምርምር ይፈልጋል፡፡ በየክልሉ ያሉትን አዋጆች፤ ደንቦች፤ መመሪያዎችና የፍ/ቤት ውሳኔዎች ብሎም የየአስተዳደር መስሪያ ቤቱ ውሳኔዎችና ሌሎች የህጉን ምንጮች ለማግኘት ካለው አዳጋችነት የተነሳ የዚህ መጽሀፍ ዋነኛ ትኩረትም የፌደራል የአስተዳደር ህግ ብቻ ነው፡፡

የአስተዳደር ህግ እና የህገ መንግስት ትስስር እና ተዛምዶ


የአስተዳደር ህግ እና የህገ መንግስት ትስስር እና ተዛምዶ

የአስተዳደር ህግ ጽንስቱ ሆነ ውልደቱ ከህገ መንግስት እንደመሆኑ ከዚህ የህግ ክፍል ጋር ብዙ ባህርያትን ይጋራል፡፡ ሁለቱም የመንግስትና የግለሰብ ግንኙነትን በሚመራው ‘የህዝብ አስተዳደር ህግ’ ተብሎ በሚጠራው የህግ ክፍል ውስጥ ይመደባሉ፡፡ አብዛኛዎቹ የአስተዳደር ህግ ጥያቄዎች በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የህገ መንግስታዊነት ጥያቄዎችን ያስነሳሉ፡፡ የአስተዳደር ህግን በጥልቀት ለመረዳት ከተፈለገ ሂደቱ መጀመር ያለበት ህገ መንግስትን በማጥናት ነው፡፡ በምሁራኑ አንደበት ይኸው እውነታ እንዲህ ይገለፃል፡፡ የአስተዳደር ህግ ከህገ መንግስታዊ መሰረቱ ተለይቶ በደንብ ሊታወቅ ሆነ ሊጠና አይችልም፡፡ የአስተዳደር ህግ በህገ መንግስት ማስፈጸሚያ መሳሪያነቱ የዝምድናቸውን ገጽታ በሚገባ ለማወቅ ይረዳናል፡፡ በዚህ የተግባሪነት ሚናው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ላይ የተቀመጡትን የህገ መንግስታዊነትና የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች እንዲሁም የግለሰቦች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በተጨባጭ እንዲረጋገጡ በማድረግ ህገ መንግስቱን በማስፈጸም ረገድ እንደ አንድ መሳሪያ ያገለግላል፡፡ እ.ኤ.አ በ1959 ዓ.ም. የጀርመን የፌደራል አስተዳደር ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት እንደተናገሩት የአስተዳደር ህግ ‘ተጨባጭ ህገ መንግስት’ ማለትም በተግባር የሚታይ ህገ መንግስት ነው፡፡a የአንድ አገር ህገ መንግስት በዋነኛነት የዜጐችን ሰብአዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፖለቲካዊ መብቶችና ነጻነቶች ይደነግጋል፡፡ የዜጐች መብት በሌላ ግለሰብ፣ ማህበር ወይም የንግድ ድርጅት ሊጣስ ይችላል፡፡ ትልቁ አደጋ ያለው ግን ከመንግስት በተለይም ከስራ አስፈፃሚው አካል በኩል ነው፡፡ መብቶች በሚገባ እንዲጠበቁ የመንግስት አስተዳደር ልኩ ተለይቶ በታወቀ የስልጣን ገደብ ውስጥ ሊከናወን ይገባል፡፡ ሆኖም ስልጣን ሁልጊዜ በህጉ መሰረት ግልጋሎት ላይ ይውላል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ የግድ በአግባቡ ሊገራና ልጓም ሊበጅለት ይገባል፡፡ የአስተዳደር ህግ የስልጣን መቆጣጠሪያ መሳሪያ ነው፡፡ በዚህ ተግባሩ ውጤታማ የስልጣን ቁጥጥር የዜጐች ህገ መንግስታዊ መብትና ነፃነት እንዳይጣስ ዋስትና ይሰጣል፡፡ መንግስቱን በተግባር እንዲተረጐም የሚደርገውም በዚህ መንገድ ነው፤ ስልጣንን በመቆጣጠር የዜጐችን መብት በተጨባጭ ማቀዳጀት፡፡ ይህ ሚናውን በሌሎች ህገ መንግስታዊ መርሆዎች አንጻርም ጎልቶ ይታያል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት በዋነኛነት ከሚደነግጋቸው የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች መካከል ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና የህዝብ ተሳትፎ ይገኙበታል፡፡b ግልጽነት እውን የሚሆነው የመንግስት ባለስልጣናትና የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ለዜጐች መረጃ የመስጠት ግዴታቸው ከነዝርዝር አፈፃፀሙ ጭምር በህግ ተደንግጐ ሲገኝ ነው፡፡ ተጠያቂነት፤ ጠያቂውና ተጠያቂው ተለይቶ የተጠያቂነት ስልቱ በዝርዝር ህግ ካልተቀመጠ በተግባር አይረጋገጥም፡፡ የህዝብ ተሳትፎ እንዲሁ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች በሚሰጡት ውሳኔ በተለይም ደንብና መመሪያ ሲያወጡ በጉዳዩ ጥቅም ካላቸው ወገኖች ሀሳብና አስተያየት እንዲቀበሉ የሚያስገድድ የህግ ድንጋጌ ከሌለ የህዝብ ተሳትፎ በተጨባጭ አይታይም፡፡ ግልፅነትን፣ ተጠያቂነትንና የህዝብ ተሳትፎን በተግባር ለማረጋገጥ የሚወጡ ህጐች በአስተዳደር ህግ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ህጉ እነዚህ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች በተግባር እንዲረጋገጡ በማድረግ ህገ መንግስቱን ያስፈጽማል፡፡ በህገ መንግስትና በአስተዳደር ህግ መካከል ያለው የጠበቀ ግንኙነት ልዩነታቸው የላላ መሆኑን ያሳያል፡፡ ሊጠቀስ የሚችል ቀጭን ልዩነት ቢኖር የወሰን እና የህጎች የተፈጻሚነት ደረጃ (Hierarchy of Laws) ልዩነት ነው፡፡ ከወሰን አንፃር ህገ መንግስት አጠቃላዩን የመንግስት አወቃቀርና የሶስቱን የመንግስት አካላት ብሎም በፌደራልና በክልል መንግስታት ያለውን የስልጣን ክፍፍል ስለሚወስን በይዘቱ በጣም ሰፊ ነው፡፡ በአንፃሩ የአስተዳደር ህግ የአንደኛውን የመንግስት አካል ማለትም የስራ አስፈፃሚውን ስልጣን፣ ግዴታና ተግባር ብሎም የውሳኔዎቹን ህጋዊነት የሚመለከት ህግ ነው፡፡ በህግ አውጭው የሚወጣ ህግ እና ፍ/ቤቶች የሚሰጡት ውሳኔ ህገ መንግስታዊነት ከጥናት አድማሱ በላይ ነው፡፡ ስለሆነም ከወሰናቸው አንጻር ህገ መንግስት መስፋቱ የአስተዳደር ህግ መጥበቡ እንደ አንድ የልዩነት ነጥብ ተደርጐ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ሁለተኛው ልዩነት የህጎች መሰላል (Hierarchy of Laws) ሲሆን በህጐች መካከል ያለውን የደረጃ ዝምድና ይመለከታል፡፡ ህገ መንግስት የአንድ አገር የበላይ ህግ እንደመሆኑ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የአሰራር ልምዶች ዋጋ የላቸውም፡፡ የአስተዳደር ህግ በደረጃው ከህገ መንግስት ዝቅ ብሎ የሚገኝ እንደመሆኑ መቼም ቢሆን ከህገ መንግስቱ ጋር መጣጣም አለበት፡፡ ግጭት በተነሳ ጊዜ የበላይ የሆነው ህገ መንግስት ሁልጊዜ ተፈፃሚነት አለው፡፡

የአስተዳደር ህግ ውልደትና ዕድገት በኢትዮጵያ ስለ ኢትዮጵያ


የአስተዳደር ህግ ውልደትና ዕድገት በኢትዮጵያ ስለ ኢትዮጵያ

የአስተዳደር ህግ ብሎም ውልደቱ፣ አነሳሱና ታሪካዊ ዕድገቱ ለመጻፍ ብዕሩን የሚያሾል ጸሐፊ ጭብጥ እንዳጣ የልብለወለድ ደራሲ ከየት ልጀምር? በሚል ጭንቀት ተውጦ ጣራ ላይ ማፍጠጥ አይቀርለትም፡፡ ስራውን ፈታኝ የሚያደርገው በህዝብ አስተዳደር እና በአስተዳደር ህግ ላይ የተጻፉ የታሪክ መዛግብት፣ የምርምር ጽሑፎችና መጻህፍት አለመኖር ብቻ አይደለም፡፡ በእርግጥ ለጀማሪ አጥኚ ይህ በራሱ ራስ ምታት ነው፡፡ ከመነሻ ምንጭ እጥረት ባሻገር ሌሎች ዐቢይ ምክንያቶች የአገሪቱን የአስተዳደር ህግ ጉዞ መዘገብ አድካሚ ያደርጉታል፡፡ ለመጥቀስ ያህል፤ የጥናት አድማሱ ወጥነት እና ትኩረት ማጣትa የዲሞክራሲና ህገ መንግስታዊ ዳራውb የፖለቲካና አስተዳደር መደበላለቅc የህግ አውጭውና የፍርድ ቤቶች ሚና ማነስd ባደጉት አገራት የአስተዳደር ህግ ዕድገት ጥርት ባለ መልኩ ራሱን የቻለ የህግ ክፍል ሆኖ ብቅ ማለት የጀመረው የዘመናው ‘የአስተዳደር መንግስት’ (Administrative State) መከሰት ተከትሎ ስለመሆኑ ብዙዎች የመስኩ አጥኚዎች ይስማሙበታል፡፡ በተመሳሳይ ቅኝት ስለ አገራችን አስተዳደር ህግ ታሪካዊ ገጽታዎችና መገለጫዎች ከዘመናዊ አስተዳደር ማቆጥቆጥ ጋር አስታኮ አጠቃላይ ገለጻ መስጠት ይቻላል፡፡ በርካታ የአገራችን ሆኑ የውጭ አገር ታሪክ ጸሐፊዎች በአገራን ዘመናዊ አስተዳደር የተተከለው የኃይለስላሴ ዙፋን ላይ መውጣት ተከትሎ በነበሩት ዓመታት ውስጥ እንደሆነ ይስማሙበታል፡፡ በተለይም ከኢጣሊያ ወረራ ማብቃትና የንጉሱ ዙፋን መልሶ መረከብ አንስቶ ዘመናዊ አስተዳደር ፈጣን ለውጦች አሳይቷል፡፡ ስለ ኢትዮጵያ የመንግስት አስተዳደር ሲወራ የአጼ ቴዎድሮስ ውጥን እና ጥረት ሳይጠቀስ አይታለፍም፡፡ አጼ ቴዎድሮስ ብሔራዊ ጦር ለማደራጀት፣ የቤተክስርስትያን የመሬት ይዞታ ለመቆጣጠር፣ የአካባቢ የጦር አበጋዞች በማዕከላዊ መንግስት ስር ለማዋቀር እንዲሁም የመንገድ ግንባታና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ለመዘርጋት ያደረጓቸው ጥረቶች ለቀጣይ ነገስታት መሰረት ጥለዋል፡፡ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት ለማቆም እና ዘመናዊ አስተዳደር ለመትከል የነበራቸው ህልም፣ ውጥን እና ፖሊሲ እንዲሁም እነዚህን ለመተግበር የወሰዷቸው ስር ነቀል እርምጃዎች የለውጥና የስልጣኔ በር ከፍተዋል፡፡ የኢትዮጵያ የአስተዳደር ህግ ውልደት ከቴዎድሮስ ይጀምራል፡፡ አስተዳደራዊ ብልሹነት እንዲቀረፍና ሹመኞች በህዝብ አገልጋይነታቸው በደል እንዳይፈጽሙ በጊዜው ሲያደርጉት የነበረው ክትትል እና የስልጣን ቁጥጥር በኢትዮጵያ የታሪክ መጻህፍት ጎልቶ ባይወጣም በአንዳንድ ጽሁፎች ተዘግቦ ይገኛል፡፡ በደርግ ወታደራዊ መንግስት ልዩ ፍርድ ቤት ይዘጋጅ የነበረው ሕግና ፍትሕ መጽሔት በመጋቢት 1987 እትሙ አጼ ቴዎድሮስ ሙስና እና የአስተዳደር ብልሹነት እንዲወገድ ሲያደርጉት የነበረውን ተጋድሎ ሌላ ምንጭ ጠቅሶ እንደሚከተለው ዘግቦታል፡፡e ቴዎድሮስ ወዘልውጥ በመሆንና አልባሌ ልብስ በመልበስ በመንግስቱ ውስጥ ያለው የአስተዳደር መበላሸት መቆጣጠር፣ ጉቦኞች ሹማምንቶቻቸውን መከታተልና ማጋለጥ ያዘውትሩ ነበር፡፡ በሕዝብ ችግር የጨከኑትን፣ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የመንግስቱን ስራ የሚበድሉትንና ኅብረተሰቡን ያጉላሉትን ሹማምንት ከስልጣን ወንበራቸው ገልብጠዋል፡፡ አባ ታጠቅ ስልጣን በጨበጡ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ውስጥ የጯሂ ጠባቂ (የህዝብ ዕንባ ጠባቂ) ሹማቸው ጉቦ መቀበሉን በማወቃቸውና ራሳቸውም ሲቀበል በማየታቸው በአደባባይ አጋልጠው ሽረውታል፡፡…የጯሂ ጠባቂነቱንም ሥራ ራሳቸው ይዘዋል፡፡ አጼ ቴዎድሮስ የመንግስት ስልጣን በህግና በስርዓት እንዲገራ የነበራቸው ቆራጥ አቋም በታሪክ በተዘገቡ ጥቂት የጊዜው ፍርዶች ላይ ይታያል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንደኛው በጳውሎስ ኞኞ ‘አጤ ቴዎድሮስ’ መጽሐፍ ላይ እንደሚከተለው ተዘግቧል፡፡ ቴዎድሮስ ጋይንት ላይ ሰፍረው ሳለ ወታደሮቻቸውን በባላገሩ ላይ ተሰሪ አስገቡ፡፡ ባላገሩ እንዲቀልብ በየቤቱ ማስገባት ማለት ነው፡፡ ተሰሪ ከገቡት ወታደሮች መሀል አንዱ ወታደር አንዱን ባላገር ገደለው፡፡ የሟች ወገንም ከቴዎድሮስ ዘንድ መጥቶ አመለከተ፡፡ ቴዎድሮስም ወታደራቸውን ሁሉ አፈርሳታ አስቀምጠው ገዳዩን አውጣ ብለው ያዙ፡፡ ወታደሩም በመላው አድሞ ገዳዩን አላየንም እያለ በቄስ እየተገዘተ ወጣ፡፡ የሟች ገዳይ ወታደር በመጥፋቱ ቴዎድሮስ ተናደው ‘ወታደር ብላ፤ ባላገር አብላ ያልሁ እኔ ነኝ፡፡ ደመኛህም እኔ ነኝና እኔን ግደል’ ብለው ብለው ተነስተው ለከሳሹ ነገሩት፡፡ ከሳሹም ‘እኔ ንጉስ መግደል አይቻለኝም’ አለ፡፡ ቴዎድሮስም ደም በከንቱ አይቀርም ብለው ለሟቹ ወገን የደም ገንዘብ ዋጋ ሰጥተው ሸኙት፡፡f በሌላ ፍርድ ላይ እንዲሁ ለሁለት ወታደሮቻቸው የሰጡት እርስ በርሱ የሚጋጭ ትዕዛዝ የአንደኛውን ወታደር ሞት በማስከተሉ ለሞቱ መከሰት ተጠያቂ ተደርገው ስለተፈረደባቸው በዚያ ንጉስ በማይከሰስበት፤ ሰማይ በማይታረስበት ዘመን ቅጣታቸውን ተቀብለው ፍርዱን ፈጽመዋል፡፡ ታሪኩ በአጭሩ እንደዚህ ነው፡፡ ቴዎድሮስ አንዱን ወታደራቸውን ‘በፍርቃ በር በኩል እርጉዝ ሴት እንኳን ብትሆን እንዳታልፍ ጠንክረህ ጠብቅ’ ብለው ካዘዙት በኋላ በሌላ ቀን ደግሞ ሌላውን ወታደር ጠርተው ‘ፈረስ እያለዋወጥህ ይህን ወረቀት የጁ ሰጥተህ በአስቸኳይ በስድስት ቀን ውስጥ ተመልሰህ እንድትመጣ’ ብለው ሲልኩት እየጋለበ ሄዶ ፍርቃ በር ላይ ሲደርስ ጠብቅ ከተባለው ወታደር ጋር ‘አልፋለው! አታልፍም!’ እሰጥ አገባ ገጥሙ፡፡ በግዴታ ለማለፍ መንገድ ሲጀምር ዘበኛው ተኩሶ ገደለው፡፡ የንጉስ ትዕዛዝ ሲፈጽም የነበረ የንጉስ መልዕክተኛ በዚህ መልኩ መገደሉ ያንገበገባቸው የሟች ወገኖች ገዳዩን በመክሰስ ከቴዎድሮስ ዘንድ አቀረቡት፡፡ ቴዎድሮስም ችሎት አስችለው ፍርድ እንዲፈረድ አደረጉ፡፡ በችሎት የተቀመጠው ፈራጅ ሁሉ እየተነሳ ገዳዩን ‘በደለኛ ነህ እምቢ አልፋለው ቢልህስ ለንጉስ ታሰማ ነበር እንጂ ራስህ ፈርደህ እንዴት የንጉስ መልዕክተኛ ትገድላለህ? አሁንም ስትሞት ይታየናል’ እያሉ ፈረዱ፡፡ አንደኛው ፈራጅ ግን ከተቀመጡበት ተነስተው ከሌሎቹ ፈራጆች በመለየት ሁለት ተቃራኒ ንጉሳዊ ትዕዛዝ መስጠት አግባብ ስላልሆነ ጥፋቱ የሚመለከተው ንጉሠ ነገሥቱን እንደሆ ከተናገሩ በኋላ ‘ነገር ግን እሳቸው ብርሀን ስለሆኑ ምን ይደረግ?’ በማለት የፍርድ ሀሳባቸውን አሳርገው ተቀመጡ፡፡ አጤ ቴዎድሮስም ይህን የልዩነት የፍርድ ሀሳብ አድንቀው ከተቀመጡበት ተነስተው በተከሳሹ ወታደር ቦታ ወርደው ቆሙ፡፡ በመጨረሻም ፈራጆች በፈረዱት መሰረት በጊዜው የሚከፈለውን የደም ዋጋ አጠፌታውን ብር 500 ከፍለው ጉዳዩ በስምምነት አለቀ፡፡g የቴዎድሮስ ሞትን ተከትሎ የተነሱት ነገስታት ማለትም አጼ ዮሐንስ እና አጼ ምኒልክ በተለያየ ጊዜ በተደረጉ የውስጥና የውጭ የጦርነት ዘመቻዎች በመጠመዳቸው ዘመናዊ አስተዳደር መሰረታዊ ለውጥ አላሳየም፡፡ ሆኖም ከአድዋ ጦርነት በኋላ ማዕከላዊ መንግስት እየተጠናከረ ሲሄድ የተወሰኑ መሻሻሎች ታይዋል፡፡ በሚኒልክ ዘመነ መንግስት ዘመናዊ አስተዳደር ለመትከል ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል በ1900 ዓ.ም. የሚኒስትሮች መሾም በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም. የተሰየሙት ሚኒስትሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡h የፍርድ ሚኒስትር የጦር ሚኒስትር የጽህፈት ሚኒስትር የአገር ግዛት ሚኒስትር የገንዘብ ሚኒስትር እና የንግድ ሚኒስትር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የእርሻና መስሪያ ሚኒስትር የግቢ ሚኒስትር የመንግስቱን ስራ እንዲሰሩ የተደለደሉት ሚኒስትሮች ስልጣንና ተግባራቸው በዝርዝር ደንብ ተወስኖላቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እያንዳንዱ ሚኒስትር የሚያስፈጽማቸው የተለያዩ ህጎች ወጥተዋል፡፡ እነዚህ ህጎች እስከ ጣሊያን ወረራ ድረስ በአጼ ምኒልክና ሀይለስላሴ አልጋ ወራሽ በነበሩባቸው ዓመታት በግብር ብቻ ተወስኖ የነበረውን የመንግስትና የግለሰብ ግንኙነት አድማሱን አስፍተውታል፡፡ በእነዚህ ጊዜያት የመንግስት ሚና ከጠባቂነት ቀስ በቀስ ወደ የክትትልና ቁጥጥር (regulation) እና ማህበራዊ አገልግሎት አቅራቢነት ተሸጋግሯል፡፡ በቁጥጥር ረገድ በርካታ የንግድ እና የግብርና ተግባራት በቅድሚያ ከሚመለከተው ሚኒስቴር ፈቃድ እንደሚያስፈልግ በተለያዩ ህጎች ተደንግጓል፡፡ ለአብነት ያህል፤ የወፍጮ መዘውር ማቆምና መፍጨትi ትምባሆ መዝራትና መሸጥj አውሬ ማደን እና ዓሣ መያዝ (ማጥመድ)k በማህበራዊ አገልግሎት አቅርቦት ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል፣ ቴሌፎን እና ፖስታ፣ ባቡር እና ሌሎችም ቀስ በቀስ ተስፋፍተዋል፡፡ በ1927 ዓ.ም. የጡረታ ስርዓት ለጉምሩክ ሠራተኞችና የጉምሩክ ወታደሮች (እንደ አሁኑ ፌደራል ፖሊስ ዓይነት) ተዘርግቷል፡፡ የጡረታ መውጫ ዕድሜ ለወታደሮች ሃምሳ፣ ለሠራተኞች 60 ዓመት ሲሆን ለአበል የሚያበቃው የአገልግሎት ዘመን እንደ ቅደም ተከተሉ ሃያ አምስት እና ሰላሳ ዓመት ነው፡፡l በጊዜው የነበረው የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ ከሞላ ጎደል አሁን ካለንበት ዘመን ጋር ተቀራራቢ ነበር ለማለት ይቻላል፡፡ በጊዜው የነበረው የጉምሩክ ሹማምንትና ሠራተኞች ዲሲፕሊን አፈጻጸም ለዚህ አባባል ዐቢይ ምስክር ነው፡፡ የጉምሩክ ሠራተኛ በስራው ላይ ጥፋትና የሚጎዳ ነገር ከሰራ በየክፍሉ ያሉ ሹሞች ከስራ አግደው ስራውን በሌላ ሰራተኛ ያሰራሉ፡፡ ሆኖም በራሳቸው የቅጣት እርምጃ ለመውሰድ ስልጣኑ የላቸውም፡፡ ስለ ጥፋቱ አኳኋን መግለጫ አዘጋጅተው ከበላያቸው ላለው ዳይሬክተር ያስታውቃሉ፡፡ ዳይሬክተሩ እንደ ጥፋቱ ክብደት እና ድግግሞሽ እስከ አንድ ወር ሙሉ ደመወዝ ‘ቅጣት’ ለመወሰን ስልጣን ነበረው፡፡ ሆኖም ቅጣቱ አስገዳጅ ሳይሆን የውሳኔ ሀሳብ ዓይነት ይዘት ያለው ነው፡፡ ዳይሬክተሩ የወሰነውን ቅጣት እና የጥፋቱን ሁኔታ ገልጾ ማስታወቂያ ለሠራተኛው ከሰጠው በኋላ ሠራተኛው ዋስ ጠርቶ አዲስ አበባ ለነበረው የዋናው ዲሬክተር ጽ/ቤት ይልከዋል፡፡ በመቀጠል ክርክር የሚካሄድበት ቀነ ቀጠሮ ይቆረጣል፡፡ በቀጠሮ ቀን ጥፋት የሚገኝባቸውን ሠራተኞች ሥርዓት ለማየት የተመረጡት ሹማምንት ተሰብስበው ነገሩን ከመረመሩ በኋላ ፍርድ ይሰጣሉ፡፡ የፍርዱንም ግልባጭ ለሠራተኛው ይሰጠቱታል፡፡ በፍርዱ ቅሬታ ካለው ለንግድ ሚኒስትር ይግባኝ ማሰማት ይችላል፡፡ ሚኒስትሩም ፍርዱንና ነገሩን አይቶ መርምሮ የመጨረሻ ፍርድ ይሰጣል፡፡ ይህ ስርዓት ተፈጻሚነቱ በዋናው ዳይሬክተርና ሚኒስትሩ ለተቀጠሩ የበታች ሠራተኞች ብቻ ነው፡፡ በንጉሱ አዋጅ ስራ የተቀጠሩ ሠራተኞችና ሹማምንት ጉዳይ የመጀመሪያ ደረጃ ውሳኔ የሚያገኘው በሚኒስትሩ ሲሆን ይግባኝ የሚቀርበውና የመጨረሻ ፍርድ የሚሰጠው በንጉሱ ችሎት ነው፡፡m ከዲሲፕሊን ጉዳዮች በተጨማሪ በሌሎች ጉዳዮችም የውሳኔ አሰጣጥ እና ቅሬታ አፈታት ስርዓት በዘመኑ ህጎች በስፋት የሚታይ ነበር፡፡ ለምሳሌ በትምባሆ ሬዢ አፈጻጸም ደንብ በ30ኛው ክፍል ደንቡን በመተላለፍ የተቀጣ ሰው እንዳገሩ ርቀት ካንድ ወር እስከ አራት ወር ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ለእርሻ ሚኒስቴር ሊያመልክት እንደሚችልና ሚኒስቴሩም ነገሩን እንደገና እንደሚያደላድለው (ነገሩን ሰምቶ ውሳኔ እንደሚሰጥ) በደንቡ ላይ ተመልክቷል፡፡n የ1923 ህገ መንግስት ዜጎች የሚደርስባቸውን የአስተዳደር በደል ቅሬታ የማሰማት መብታቸውን ህገ መንግስታዊ ዕውቅና በመስጠት የመጀመሪያው ነው፡፡ በአንቀጽ 28 ላይ እንደተደነገገው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለመንግስት አቤቱታ የማቅረብ መብት ተጠብቆላቸዋል፡፡ በተሻሻለው የ1948 ህገ መንግስት ላይም ተመሳሳይ ይዘት ያለው ድንጋጌ በአንቀጽ 62 ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ደርግ ስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በታወጀው የኢ.ህ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 52 በመንግስት አካላት እና ህዝባዊ ድርጅቶች ላይ ቅሬታ የማሰማት መብት ተጠብቋል፡፡ በተጨማሪም የሚቀርቡ ቅሬታዎች ተመርምረው ምላሽ እንደሚሰጣቸው በድንጋጌው ላይ ተመልክቷል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት የተከተለው አቅጣጫ ከባለፉት ይለያል፡፡ አቤቱታ የማሰማት መብትን በተለይ ዕውቅና ከመስጠት ይልቅ በአንቀጽ 37 የዜጎችን ፍትሕ የማግኘት መብት ደንግጓል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ርዕስና ይዘት በወሰን (scope) አይጣጣሙም፡፡ ፍትሕ የማግኘት መብት ዜጎች ለሚደርስባቸው አስተዳደራዊ በደል በመደበኛ እና ኢ-መደበኛ የፍትሕ ተቋማት ቅሬታ አቅርበው መፍትሄ የማግኘት መብታቸውን ያካትታል፡፡o ይህን መሰረተ ሀሳብ በሚያንጸባርቅ አኳኋን የተቀረጸው የአንቀጽ 37 ርስስ በንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ የሚደነግገው በፍርድ የሚያልቁ ጉዳዮችን ለመደበኛና ፍ/ቤቶች እና ለአስተዳደር ጉባዔዎች (Administrative tribunals) አቅርቦ ዳኝነት የማግኘት መብት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የመብቱ ወሰን ለህግ አውጨው፣ ለአስተዳደሩና ለሌሎች ተቋማት (ለምሳሌ እንባ ጠባቂና ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን) ቅሬታ የማሰማት መብትን አይጨምርም፡፡ በአስተዳደር ህግ ታሪካዊ ዕድገት ውስጥ የአስተዳደር ጉባዔዎች (Administrative tribunals) ሚና ጉልህ ስፍራ ይይዛል፡፡ በብዙ አገራት እየተለጠጠና እየተወሳሰብ የመጣው የመንግስት አስተዳደር በግለሰብና በመንግስት መካከል የሚካሄዱ ክርክሮችን ሙሉ በሙሉ በመደበኛ ፍ/ቤቶች አማካይነት መዳኘት አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ በዚህ የተነሳ የአስተዳደር ጉባዔዎች (Administrative tribunals) አብዛኞቹን ክርክሮች በመዳኘት ውጤታማ የዳኝነት አካላት ለመሆን በቅተዋል፡፡ ሆኖም በአገራችን በተጨባጭ የሚታይ የረባ ውጤት አላስመዘገቡም፡፡ ድሮም ሆነ ዘንድሮ እነዚህን ተቋማት ከፍትሕ ስርዓቱና ከአስተዳደር ሂደቱ ጋር በማቆራኘት ለማደራጀት ሙከራዎች አልተደረጉም፡፡ የ1923 ህገ መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ ለአስተዳደር ጉባዔዎች ህገ መንግስታዊ ዕውቅና በመስጠት አስተዳደራዊ ጉዳዮችን የመወሰን ስልጣን እንዳላቸው የደነገገ ቢሆንም በተግባር ግን ተቋማዊ መዋቅር ተዘርግቶላቸው አልተቋቋሙም፡፡ በዚህ ህገ መንግስት አንቀጽ 54 ላይ እንደተመለከተው፤ በማናቸውም በመንግስት ስራ ምክንያት የሚነሡትን ነገሮች የሚፈርዱ በተለይ የቆሙት የፍርድ ቤቶች ናቸው እንጂ ሌሎች ዳኞች እነዚህን ነገሮች ለመፍረድ አይችሉም፡፡ የድንጋጌው ሀሳብ በእንግሊዝኛው ቅጂ ላይ ግልጽ ተደርጓል፡፡ Special courts shall judge all matters relating to administrative affairs, which are withdrawn from the jurisdiction of other courts. ህገ መንግስቱ በአማርኛው ‘በተለይ የቆሙት ፍርድ ቤቶች’ በእንግሊዝኛው Special courts በሚል በጥቅል የጠቀሳቸው ፍርድ ቤቶች ምን ዓይነት ፍርድ ቤቶች ሊቋቋሙ እንደታሰበ አይጠቁምም፡፡ ሆኖም ስለሚያዩት ጉዳይ የተቀመጠው ገለጻ የአስተዳደር ፍርድ ቤቶች እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ የህገ መንግስቱ ምንጭ ይህንን አባባል የበለጠ ያጠናክራል፡፡ የ1923 የኢትዮጵያ ህገ መንግስቱ በአብዛኛው የተቀዳው በጃፓን እ.ኤ.አ በ1889 ዓም. በይፋ ከታወጀው የመጂ ህገ መንግስት (Meji Constitution) ነው፡፡ በወቅቱ የነበሩት የጃፓን ገዢዎች አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ከመደበኛ ፍ/ቤቶች ለማግለል የነበራቸውን ጽኑ ፍላጎት የሚደግፍ የአስተዳደር ህግ ስርዓት ሲያጠኑ ከመደበኛ ፍ/ቤት ትይዩ ሆኖ ራሱን ችሎ የተቋቋመው የጀርመን የአስተዳደር ፍ/ቤት ተመራጭ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚሁ መሰረት በመንግስት ላይ የሚቀርቡ ክሶች ከመደበኛው በተለየ በሚቋቋሙ የአስተዳደር ፍርድ ቤቶች እንደሚዳኙ በህገ መንግስታቸው በመደንገግ እ.ኤ.አ በ1890 ላይ ይህን ፍ/ቤት አቋቁመዋል፡፡p በኢትዮጵያ እስከ 1928 ዓ.ም. ድረስ የዳኝነት መብት ከአስተዳደር ስልጣን ጋር የተያያዘ ስለነበር ዳኝነት ሲሰጥ የነበረው በአካባቢው ሹማምንት፣ አገረ ገዢዎችና በራሳቸው በነገስታቱ አማካይነት ነው፡፡q ዳኝነት ከአስተዳደር ተለይቶ መደበኛ ፍ/ቤቶች የተቋቋሙት በ1934 ዓ.ም. ነው፡፡r ዓበይት ህግጋት እስከተጠናቀሩበት እስከ 1950ዎቹ ድረስ እነዚህ ፍ/ቤቶች የሚሰሩባቸው ህጎች ከሞላ ጎደል ልማዳዊ ነበሩ፡፡ ስለሆነም የተጠናከረ አስተዳደር ሆነ ዘመናዊ የህግና የዳኝነት ስርዓት ባልነበረበት በ1923 ዓ.ም. እና ቀጣይ ዓመታት የአስተዳደር ፍ/ቤቶችን አስፈላጊ የሚያደርግ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታ አልነበረም፡፡ በተግባር ሲታይም ከወረቀት የዘለለ ህልውና አልነበራቸውም፡፡ እስካሁን ድረስ በአገራችን ራሱን ችሎ በተለይ የቆመ የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ የለም፡፡ በንጉሱ ጊዜ እ.አ.አ በ1967 የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ ረቂቅ ተዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም ከረቂቅነት ደረጃ አላለፈም፡፡ ቀጣይ ሙከራዎች የተደረጉት በ1993 ዓ.ም. እና 2001 ዓ.ም. ሲሆንም በሁለቱም ጊዜያት በፍትሕ እና የህግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት አማካይነት ረቂቅ የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህጎች ተዘጋጅተዋል፡፡ እንደባለፈው ሁሉ የእነዚህም እጣ ፈንታ ከረቂቅነት መሻገር አልቻለም፡፡  

የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት አፈፃፀም


የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት አፈፃፀም

ተደጋግሞ እንደተገለፀው የመንግስት ስልጣን በወርድም በቁመትም እየሰፋ በመጣ ቁጥር ለዜጐች መብትና ነፃነት ፀር ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ የስልጣንን አስፈላጊነት አምኖ ተቀብሎታል፡፡ ውጤታማ አስተዳደር እንዲሁም ቀልጣፋ የአገልግሎት አቅርቦት እንዲኖር የሚያስር ሳይሆን የሚፈታ ስልጣን ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ከህግና ከህገ መንግስት የሚያፈነግጥ ስልጣን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ የበዘፈቀደ ድርጊት፣ ‘እንደፈለግኩኝ እሆናለው እፈልጣለው እቆርጣለው!’ የሚል አካሄድ አቅመ ቢስ የሆነውን ዜጋ የመኖር፣ በነፃነት የመንቀሳቀስ፣ የመናገር፣ ሀሳብን የመግለፅና ንብረት የማፍራት መሰረታዊ መብት አለገደብ ይሸረሽራል፡፡ የአስተዳደር ህግ የሰብዓዊ መብትን በማስጠበቅ ረገድ ያለው ሚና የሁለቱን ትስስር በሚገባ ያሳየናል፡፡ ህጉ በሰብዓዊ መብት አጠባበቅና አፈፃፀም ላይ ያለውን አዎንታዊ ተፅእኖ በሚገባ ለመረዳት ከሰብዓዊ መብቶች አተገባበር አንፃር የመንግስትን ግዴታ መተንተኑ አግባብነት ይኖረዋል፡፡ እነዚህም ሚናዎች (ግዴታዎች) የማክበር (respect) የማስከበር (protect) እንዲሁም የመፈጸምና የማስፈፀም (enforcement) ናቸው፡፡ በመጀመሪያው መብቶችን የማክበር የመንግስት ሚና ዜጐች ነፃ ሆነው መብታቸውን ሲጠቀሙ ከየትኛውም የመንግስት አካል የሚመጣ ጣልቃ ገብነትን ይገድባል፡፡ በተለይም መሰረታዊ በሚባሉት በህይወት የመኖር፣ የመፃፍ፣ የመናገር፤ የፈለጉትን ሀይማኖት የመከተል፤ በነፃነት የመዘዋወርና ንብረት የማፍራት መብቶችና ነፃነቶች በተግባር የሚረጋገጡት መንግስት እጁን ሲሰበስብ ነው፡፡ እነዚህ መብቶች በመንግስት በተለይ በስራ አስፈፃሚውና በስሩ ባሉት የአስተዳደር ተቋማት ውሳኔ፤ ትዕዛዝ፤ ደንብና መመሪያ አማካይነት አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ ህገ መንግስቱ የበላይ ህግ እንደመሆኑ ይህን የሚቃረን ህግ፣ ውሳኔና አሰራር ሁሉ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ይህን መሰሉ የህገ መንግስታዊነት ጥያቄ በአስተዳደር ህግ ውስጥ አይወድቅም፡፡ ይሁን እንጂ የህገ መንግስታዊነት ብቻ የሚመስል ጥያቄ በአስተዳደር ህግ ማእቀፍ የሚሸፈንበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡ በአንድ የአስተዳደር ተቋም የወጣ መመሪያ በህግ አውጭው ከተሰጠ የውክልና ስልጣን በማለፍ የዜጐችን ሰብዓዊ መብት የሚገድብ ሆኖ ከተገኘ በውስጡ የህገ መንግስታዊነት (constitutionality) ጥያቄ ያዘለ ቢሆንም በዋናነት ግን የአስተዳደር ህግ ሊመልሰው የሚገባ የህጋዊነት (legality) ጥያቄ ነው፡፡ ልዩነታቸውን የበለጠ መረዳት እንዲያስችልን የሚከተለውን የድሮው የገቢዎች ሚኒስቴር የአሁኑ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መመሪያ እንመልከት፡፡ ማንኛውም የጉምሩክ ፖሊስ ሰላማዊ ስልፍና የስራ ማቆም አድማ ማድረግ አይችልም፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ለማንኛውም ሰው የተረጋገጠ መብት ነው፡፡ መብቱን የሚያጎናጽፈው የአንቀጽ 30 ንዑስ ቁጥር 1 እንዲህ ይነበባል፡፡ ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ አንድ መመሪያ በስራ አስፈፃሚው አካል ሲወጣ ከህግ አውጭው በግልጽ የተሰጠ የውክልና ስልጣን (Delegation) ሊኖር ይገባል፡፡ መመሪያው የውክልና ስልጣኑን ገደብ ካለፈ ከስልጣን በላይ (Ulta vires) ነው፡፡ ስለሆነም በህግ ፊት ዋጋ አልባ (null and void) ነው፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር ይህን መመሪያ ሲያወጣ የስልጣን ምንጩን የጉምሩክ ባለስልጣንን ለማቋቋምና አስራሩን ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁ. 368/1995 አንቀጽ 8 (2) (ሐ) እንደሆነ ይጠቅሳል፡፡ ይህ የተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ እንዲህ ይነበባል፡፡ የጉምሩክ ህግ እንዲያስከብር ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተመደበን የፖሊስ ኃይል ሚኒስቴሩ የፌደራል ፖሊስ አዋጅን ተከትሎ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት በስራ ያሰማራል፡፡ ያስተዳድራል፡፡ ጥፋት ሲገኝም ያሰናብታል፡፡ ይህ አንቀጽ የጉምሩክ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርግ በመመሪያ እንዲከለክል ለገቢዎች ሚኒስቴር ስልጣን አይሰጥም፡፡ ከተወካዮች ምክር ቤት ግልፅ ስልጣን ባልተሰጠበት ሁኔታ የወጣው ይህ መመሪያ ህጋዊነት ሆነ ተፈፃሚነት የለውም፡፡ የአስተዳደር ህግ ይህን መሰል መመሪያዎች በዘፈቀደ እየወጡ የዜጐችን መብትና ነፃነት እንዳይጥሱ በተለያዩ መንገዶች በመቆጣጠር መንግስት ሰብዓዊ መብት የማክበር ግዴታውን እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ የመንግስት የማስፈፀም ኃላፊነት አብዛኛውን ጊዜ ከማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ መብቶች ጋር በቀጥታ ተያይዞ ይነሳል፡፡ መንግስት በዜጐች መብት ላይ ጣልቃ አለመግባቱ ወይም እጁን መሰብሰቡ ብቻ አይበቃም፡፡ ለዜጋው መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማለትም ጤና፣ መብራት፣ ውሃ፣ መንገድ ወዘተ… ካላቀረበ ነፃ መሆን በራሱ ፋይዳ የለውም፡፡ የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት ትሰስር ከመንግስት የማስከበር ግዴታ አንጻርም ሊቃኝ ይችላል፡፡ ከዚህ አንጻር መንግስት ሰብዓዊ መብትን በማስከበር ኃላፊነቱ መብት እንዳይጣስ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶች በህግ እና በተቋማዊ አደረጃጀት የማጠናከር፣ በመብት መጣስ ጉዳት ለደረሰበት ዜጋ ፈጣን ፍትህ የሚያገኝበትን ስርዓት መዘርጋት አለበት ማለት ነው፡፡ በአጭር አገላለጽ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ መንግስት የዳበረ የአስተዳደር ህግ እና የአስተዳደር ህግ ስርዓት መቅረጽ፣ መትከልና ማጐልበት ይጠበቅበታል፡፡

የሕግ የበላይነት


የህግ የበላይነት
ብዙ ምሁራን በየፊናቸው በምርምርና ጥናት ባገኙት እውቀት ተመርኩዘው የህግ የበላይነት መርህ ምንነት፤ ይዘትና ፋይዳውን አስመልክቶ አያሌ ንድፈ ሀሳባዊ ትንታኔዎችን አቅርበዋል፡፡ በአገራችን ደግሞ አባቶችና እናቶች በልባቸው ከተጻፈው እውነትና ከልምድ ከቀዱት ቱባ እውቀት በመነሳት የህግ የበላይነትን ጽንስ ሀሳብ በአንድ አባባል እንዲህ ይገልጹታል፡፡ “በፍርድ ከሄደች በቅሎዬ ያለፍርድ የሄደች ዶሮዬ!” የዚህ ተረትና ምሳሌ አንኳር መልዕክት ለጥቂት ሰዎች ብቻ የተገለጠ ሳይሆን በመላው ማህበረሰብ ዘልቆ የገባ ሀቅ ነው፡፡ እናም ይህን የህግ የበላይነት ፅንሰ ሓሳብን ጠንቅቆ ያወቀው ማህበረሰብ ህግ ሲጣስ፤ ፍትህ ሲጓደል፤ መብት ሲታፈን፤ ስርዓት አልበኝነት ሲነግስ፤ ማን አለብኝነትና በዘፈቀደኝነት ሲንሰራፋ፤ የግሉ የሆነችው ዶሮ ከህግ እና ከፍርድ ውጭ ሲቀማ ድምፁን አጉልቶ ይጮሀል፤ በህግ አምላክ! ይላል፡፡ የጮኸው የዶሮዋ ዋጋ አንገብግቦት አይደለም፡፡ የተወሰደችበት መንገድ እንጂ፡፡ በፍርድ ከሆነ፤ በህጉ መሰረት ከሆነ እንኳንስ ለዶሮ ለበቅሎም ቄብ አይሰጠውም፡፡ በህዝብ አስተዳደር፤ ፖለቲካ ሳይንስ፤ ህግ እና በሌሎችም የጥናት መስኮች የሚገኙ ምሁራን ስለ የህግ የበላይነት ምንነትና ይዘት ያላቸው ግንዛቤና አስተሳሰብ የተራራቀ ከመሆኑ የተነሳ ጽንሰ ሀሳቡ አሁንም ድረስ ቁርጥ ያለ ትርጓሜ አልተገኘለትም፡፡ አንድ የመስኩ ምሁር ይህንን ሀሳብ በማጠናከር እንዳብራራው፤ ‘[T]he rule of law’, like ‘democracy’, has no single meaning: it is not a legal rule, but a moral principle, which means different things to different people according to their particular moral positions.a በዚህ የተነሳ በተለያዩ አገራት የፖለቲካና የህገ መንግስት ስርዓት ውስጥ ይዘቱና አፈጻጸሙ የተለያየ አንዳንዴ የማይጣጣም መልክ በመያዙ መሰረታዊ እሳቤው ወጥነት ርቆታል፡፡ ለምሳሌ በእንግሊዝ አንደኛውና የህግ የበላይነት መገለጫ በመንግስትና በግለሰብ መካከል የሚነሱ ክርክሮች በመደበኛ ፍ/ቤቶች ብቻ መዳኘታቸው ነው፡፡ ያ ማለት በእንግሊዛዊ አይን ፈረንሳይ ውስጥ የህግ የበላይነት የለም እንደ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በፈረንሳይ በግለሰብና በመንግስት መካከል የሚነሱ ክርክሮች ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ የሚዳኙት ከመደበኛ ፍ/ቤት ትይዩ ራሱን ችሎ በተቋቋመ የአስተዳደር ፍ/ቤት ስርዓት አማካይነት ነው፡፡ በእንግሊዝ ሌላኛው የህግ የበላይነት ትርጉም የግለሰቦች መብትና ነፃነት መደበኛ ፍ/ቤቶች በቀረቡላቸው ተጨባጭ ጉዳዮች የሚሰጡት ውሳኔ ውጤት ነው የሚል ይዘት አለው፡፡ ይህ አስተሳሰብ በእንግሊዝ እውነት ቢሆንም የኛን አገር ጨምሮ የተጻፈ ህገ መንግስት ባላቸው እንደ አሜሪካ ባሉ አገራት የዜጐች መብቶችና ነፃነቶች በህገ መንግስቱ ላይ በጽሑፍ ይዘረዘራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሊብራል ዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ የህግ የበላይነት ማለት በህጉ መሰረት ከመግዛትና ከማስተዳደር ባለፈ የህጉ ይዘት (ለምሳሌ ፍትሐዊነቱ፤ የዜጐችን መብት ማክበሩ፣ ህጉ የወጣው ህዝብ ወዶና ፈቅዶ በመረጣቸው ተወካዮች መሆኑ ወዘተ…) ብሎም የገለልተኛና ነፃ ፍ/ቤቶች፤ የዲሞክራዊ ተቋማት፤ ነፃ ፕሬስ ወዘተ… መኖር ሁሉም በህግ የበላይነት ጽንስ ሀሳብ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ የሊብራል ዲሞክራሲ ጠበል አልተጠመቁም በሚባልላቸው መንግስታት (ለምሳሌ በቻይና) ጽንሰ ሀሳቡ ስልጣን ያለው አካል በሚያወጣቸው ህጐች መሰረት መግዛትና ማስተዳደር ላይ ብቻ የተገደበ ነው፡፡ የህግ የበላይነት መርህ የአስተዳደር ህግ (በተለይ በእንግሊዝ) የተተከለበት መሰረት ነው፡፡ በዚህ መርህ መሰረት ስራ አስፈፃሚው፣ የአስተዳደር መ/ቤቶች እና የአስተዳደር ጉባዔዎች የሚሰጡት ውሳኔ በህጉ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡ በመንግስት አስተዳደር ውስጥ ህጋዊነት የሚሰፍነው ስልጣን የተሰጠው ማናቸውም የመንግስት አካል የሚወስዳቸው እርምጃዎች፣ የሚፈጽማቸው ድርቶች፣ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች እና የሚያወጣቸው ደንብና መመሪያዎች በህግ ጥላ ስር መሆናቸው ሲረጋገጥ ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡት ውሳኔ በህግ ከተቀመጠው የስልጣን ክልል በላይ ከሆነ ውሳኔው የህግ የበላይነት መርህን እንደሚጥስ ጥርጥር የለውም፡፡ ህጋዊነት መከበሩን ማረጋገጥ ማለት አስተዳደራዊ ድርጊት፣ ውሳኔ፣ እርምጃ፣ ደንብና መመሪያ በህግ በተቀመጠው የስልጣን ገደብ ውስጥ መሆኑን አሊያም አለመሆኑን ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የመደበኛ የፍርድ ቤቶች ተግባር ነው፡፡ ይህንን ተግባር በሚያሳንስ መልኩ በፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ላይ በህግ አውጭው የሚደረግ ገደብ በውጤቱ የህግ የበላይነት መርህን ይሸረሽራል፡፡ ገደቡ በህግ የበላይነት መርህ ላይ ከሚፈጥረው አደጋ በተጨማሪ የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት ያጣብባል፡፡ በተለይም ይህ መብት ህገ-መንግስታዊ እውቅና የተሰጠው ከሆነ የፍርድ ቤቶችን ስልጣን መገደብ ዞሮ ዞሮ የዜጎችን ህገ-መንገስታዊ መብት መገደብ ነው፡፡ የህግ የበላይነት መርህ የአስተዳደር ህግ መሰረት ብቻ ሳይሆን ገደብ ጭምር እንደሆነ ማውሳት ያስፈልጋል፡፡ የውሳኔን ህጋዊነት ማረጋገጥ በይዘቱ ላይ መቆጠብን ያስከትላል፡፡ ፍ/ቤቶች የህግ የበላይነት በማስከበር ሚናቸው የአስተዳደራዊ ውሳኔዎች ይዘት እንዳያጣሩ ወይም በፖሊሲ ጥያቄዎች ጣልቃ እንዳይገቡ ይገድባቸዋል፡፡

መሰረታዊ የመንግሥት አስተዳደር መርሆዎች


መሰረታዊ የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች

መልካም አስተዳደር ምንም እንኳን በጥቅሉ ሲታይ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ተቋማዊ እንዲሁም የአመራር እና የአሰራር ሂደቶችን የሚመለከቱ ዘርፈ ብዙ እንደምታዎች ያሉት ቢሆንም በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ሲታይ ግን ከአስተዳደር ፍትህ ጋር አቻ ሆኖ ሊገለጽ ይችላል፡፡ መልካም አስተዳደር ዋና ግቡ ዜጐች ብቁና ውጤታማ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል እንዲሁም የሚደርስባቸውን አስተዳደራዊ በደል መቅረፍ እና አስተዳደራዊ ፍትህን እውን ማድረግ እንደመሆኑ ሁለቱን ነጣጥሎ ማየት ያስቸግራል፡፡ መልካም አስተዳደር ሆነ የአስተዳደር ህግ በራሳቸው አቅጣጫና ሂደት ተጉዘው የግባቸው መድረሻ አስተዳደራዊ ፍትህን ማስፈን ነው፡፡ ስለሆነም በይዘቱ ሰፊ በሆነ የመልካም አስተዳደር እሳቤ ውስጥ የአስተዳደር ህግ አንድ ቁስ ሆኖ በማገልገል የተቆራኘና የተዛመደ ተግባራዊ እገዛ ያደርጋል፡፡ በመልካም አስተዳደርና በአስተዳደር ህግ መካከል ያለውን ተዛምዶ በቅጡ ለመቃኘት ህግ በአስተዳደሩ አካሄድ (Administrative behavior) ወይም በስራ አስፈፃሚው እንቅስቃሴ ላይ ምን አይነት አዎንታዊ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል? ለሚለው ጥያቄ በተግባር የታገዘ ጥልቅ ጥናት ምላሽ መስጠት ይጠይቃል፡፡ ይሁን እንጂ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያሉትን ሚናዎችና ተግባራት ቢያንስ እንደጠቅላላ ሀሳብ በመውሰድ የአስተዳደር ህግ እንደ አንድ የህግ ዘርፍ የራሱ አዎንታዊ ፋይዳ እንዳለው መደምደም እንችላለን፡፡ ያም ሆኖ ግን አስተዳደሩ መልካም እንዲሆን የአስተዳደር ህግ ስልጣን ከመቆጣጠር ባሻገር እንዴት ተቃኝቶ መቀረጽ አለበት? የሚለው ጥያቄ ለአስተዳደር ህግ አጥኚዎች ሆነ ምሁራን የውይይት ምንጭ ብቻ ሳይሆን የጥናት መሰረት መሆን ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ የመልካም አስተዳደር እና የአስተዳደር ህግን ተዛምዶ ለማየት የሁለቱም መድረሻ ከሆነው የአስተዳደር ፍትህ ትርጓሜ እንነሳለን፡፡ የአስተዳደር ፍትህ በህግ ስልጣን የተሰጣቸው የመንግስት አካላት ስልጣናቸውን በሚገለገሉበት ወቅት ከዜጐች መብትና ነፃነት አንጻር ፍትሃዊ መሆን እንዳለባቸው የሚደነግግ መርህ ነው፡፡ የመንግስት አስተዳደር ፍትሃዊ ሲሆን መልካም ይሆናል፡፡ የአስተዳደር ፍትህን በማሳካት ረገድ ሁለት ዓበይት ነጥቦች ቁልፍ ቦታ ይኖራቸዋል፡፡ ይኸውም፡- አንደኛ፦ የመንግስት ባለ ስልጣናት ወይም የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ስልጣናቸውን በሚገለገሉበት ወቅት አነስተኛ ለሆኑ የስነ-ስርዓት ደንቦች እና ተቀባይነት ላላቸው መርሆዎች መገዛት አለባቸው፡፡ ከአነስተኛ የስነ-ስርዓት ደንቦች በተጨማሪ የመንግስት አስተዳደር ተቀባይነት ባላቸው የህግ፣ የአስተዳደርና የፍትህ መርሆዎች መመራት አለበት፡፡ ከእነዚህ መካከል በዋናነት የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡ የህጋዊነት መርህ (ህጋዊ ስልጣን ሳይኖር አንዳችም እርምጃ አለመውሰድ፤ በህጉ መሰረት መወሰን) የሚዛናዊት መርህ (የአስተዳደር አካላት ውሳኔ ወይም እርምጃ እንደየሁኔታው ብዙ ነገሮች ግምት ያስገባ እንጂ ፍርደገምድል መሆን የለበትም፡፡) የተመጣጣኝነት መርህ (የሚወሰደው እርምጃ ተፈጸመ ከተባለው ጥፋት አንፃር ተመጣጣኝ መሆን አለበት፡፡) የእኩልነት መርህ (ተመሳሳይ በሆኑ ሁኔታዎች ወይም ጉዳዮች አስተዳደሩ የተለያየ ውሳኔ ላይ መድረስ የለበትም፡፡ ተመሳሳይ ሁኔታዎች በተመሳሳይ መንገድ መወሰን አለባቸው፡፡) ለውሳኔ በቂ ምክንያት መስጠት (አስተዳደራዊ ውሳኔ የተወሰደበት ምክንያት በግልጽ መጠቀስ አለበት፡፡ ውሳኔውም ፈጽሞ የማያሳምንና ኢ- ምክንያታዊ መሆን የለበትም፡፡) ሁለተኛ፦ ከላይ የተመለከቱትን ደንቦችና መርሆዎች በመጻረር በህግ ከተወሰነው ስልጣን በላይ እርምጃ ከተወሰደ መብታቸው የተጐዳ ዜጐች አቤቱታ አቅርበው ፍትህ (መፍትሄ) የሚያገኙበት መንገድ መኖር አለበት፡፡ በአስተዳደር አካላት መብታቸው የተጣሰ ሰዎች ቀላል በሆነ ስነ-ስርዓት አቤቱታ አቅርበው ቀልጣፋ መፍትሔ የሚያገኙበት አሰራር ወይም መንገድ ከሌለ የአስተዳደር ፍትህ አለ ለማለት አይቻልም፡፡ ለምሳሌ አካልን ነፃ የማውጣት መብት በህገ-ወጥ መንገድ ከ48 ሰዓት በላይ የታሰረ ሰው ራሱ በቀጥታ ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን በቀላሉ አቤቱታ አቅርቦ ነፃ የሚለቀቅበት ፈጣን ስነ-ስርዓት ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በህገ ወጥ መንገድ ንብረቱን በአስተዳደደሩ የተቀማ ወይም ፈቃዱ አለአግባብ የተሰረዘበት ሰው ቀላል በሆነ ስነ-ስርዓት መፍትሔ የሚያገኝበት የህግ ድንጋጌ ሊኖር ይገባል፡፡ ለዚህም ነው የአስተዳደር ህግ መኖር ለአስተዳደራዊ ፍትህ ሆነ ለመልካም አስተዳደር ወሳኝ መሳሪያ ነው የሚባለው፡፡ የአቤቱታው ስርዓት እንዳለ ሆኖ የአስተዳደራዊ ፍትህ የሚገኝበት ተቋም ገለልተኛ፣ ተደራሽ እና ነፃ ሆኖ ቀልጣፋና ውጤታማ ግልጋሎት መስጠት መቻሉ የአስተዳደር ፍትህን በማሳካት ረገድ ዋናውና መሰረታዊው ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

አንቀጽ 10


የሕገመንግስቱ አንቀጽ 10፡ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች
1-➢ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈ ጥሮ የሚመነጩ፣
2-➢የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው። የዜጐች እና የሕዝቦች ሰብዓዊና ዴሞክራሲ ያዊ መብቶች ይከበራሉ።

THE RULE OF LAW


The rule of law
What is the principle of the rule of law, based on the knowledge and experience of many scholars? He presented a number of theoretical analyzes regarding its content and benefits. In our country, fathers and mothers express the concept of the rule of law in one way or another, based on the truth written in their hearts and the knowledge they have learned from experience. “If she goes to court, my mule will go without justice!” The central message of this parable and parable is not just for a few people but for the whole community. And when a society that is well versed in this concept of the rule of law violates the law; When injustice is done, When rights are suppressed: When lawlessness reigns; Who spreads arbitrarily and arbitrarily; When the private chicken is snatched outside the law and justice, it shouts loudly; God of law! Says. The screaming chicken did not bother him. But the way she was taken. If in judgment, According to the law, even chickens and buffaloes are not allowed to eat. In public administration; Political Science; Scholars in the field of law and other fields of thought and understanding of the nature and content of the rule of law are so diverse that the concept has yet to be fully defined. As one scholar in the field reinforces this idea, ‘[T] he rule of law’, like ‘democracy’, has no single meaning: it is not a legal rule, but a moral principle, which means different things to different people according to their particular moral positions.a As a result, in the political and constitutional systems of different countries, the content and performance are different and sometimes inconsistent. In the UK, for example, one of the hallmarks of the rule of law is that disputes between the government and the individual are settled only by ordinary courts. That means there is no rule of law in France in the eyes of the English. Because in France, disputes between individuals and the government are adjudicated from beginning to end through an independent administrative court system parallel to the regular court. Another interpretation of the rule of law in the United Kingdom is that it is the result of decisions made by the formal courts on individual rights and freedoms. While this view is true in the United Kingdom, the rights and freedoms of citizens in countries such as the United States, including our own, are enshrined in the constitution. In addition, in a liberal democracy, the rule of law means more than just ruling and governing the rule of law (eg, fairness, respect for the rights of citizens, the rule of law by elected representatives, etc.) and independent and independent courts; Democratic Institutions: The existence of a free press, etc., is all part of the concept of the rule of law. In contrast, in liberal democracies, the concept of unbaptized governments (for example, in China) is limited to the rule of law. The rule of law is the basis on which administrative law (especially in the UK) is based. According to this principle, decisions made by the executive, administrative offices and governing councils must be in accordance with the law. Legal authority in government is vested in the government when it is established that the actions, actions, decisions, and directives of any government body are subject to the rule of law. If the decision of a government official is beyond the scope of the jurisdiction, the decision will undoubtedly violate the rule of law. Ensuring that legitimacy is upheld means that administrative actions, decisions, actions, rules and regulations are within the limits of the law. This is the function of ordinary courts. To minimize this practice, the legislature’s restriction on the jurisdiction of the courts undermines the rule of law. In addition to the threat to the rule of law, the restriction restricts citizens’ access to justice. In particular, if this right is constitutionally recognized, the power of the courts is limited, and in turn, the constitutional right of citizens is limited. It should be noted that the principle of the rule of law is not only the basis of administrative law but also the limit. Verifying the legitimacy of a decision results in saving on content. The courts’ role in upholding the rule of law prevents them from reviewing the content of administrative decisions or interfering with policy matters.

The assassination of Dr. Abiy Ahmed Ali by the tyrants and the attacks on civilians by the dictator Abiy Ahmed’s group. በአንባገነኖች የዶክተር የአብይ አህመድ አሊ በኢትዮጵያ ህዝብና ዜጎች ላይ አንባገነን መሪ በሆነው አብይ አህመድ ቡድኖች የተፈጸመው ግድያዎችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ የደረሱበትን ጥቃቶች።


የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት አፈጻጸም።


የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት አፈፃፀም
ተደጋግሞ እንደተገለፀው የመንግስት ስልጣን በወርድም በቁመትም እየሰፋ በመጣ ቁጥር ለዜጐች መብትና ነፃነት ፀር ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ የስልጣንን አስፈላጊነት አምኖ ተቀብሎታል፡፡ ውጤታማ አስተዳደር እንዲሁም ቀልጣፋ የአገልግሎት አቅርቦት እንዲኖር የሚያስር ሳይሆን የሚፈታ ስልጣን ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ከህግና ከህገ መንግስት የሚያፈነግጥ ስልጣን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ የበዘፈቀደ ድርጊት፣ ‘እንደፈለግኩኝ እሆናለው እፈልጣለው እቆርጣለው!’ የሚል አካሄድ አቅመ ቢስ የሆነውን ዜጋ የመኖር፣ በነፃነት የመንቀሳቀስ፣ የመናገር፣ ሀሳብን የመግለፅና ንብረት የማፍራት መሰረታዊ መብት አለገደብ ይሸረሽራል፡፡ የአስተዳደር ህግ የሰብዓዊ መብትን በማስጠበቅ ረገድ ያለው ሚና የሁለቱን ትስስር በሚገባ ያሳየናል፡፡ ህጉ በሰብዓዊ መብት አጠባበቅና አፈፃፀም ላይ ያለውን አዎንታዊ ተፅእኖ በሚገባ ለመረዳት ከሰብዓዊ መብቶች አተገባበር አንፃር የመንግስትን ግዴታ መተንተኑ አግባብነት ይኖረዋል፡፡ እነዚህም ሚናዎች (ግዴታዎች) የማክበር (respect) የማስከበር (protect) እንዲሁም የመፈጸምና የማስፈፀም (enforcement) ናቸው፡፡ በመጀመሪያው መብቶችን የማክበር የመንግስት ሚና ዜጐች ነፃ ሆነው መብታቸውን ሲጠቀሙ ከየትኛውም የመንግስት አካል የሚመጣ ጣልቃ ገብነትን ይገድባል፡፡ በተለይም መሰረታዊ በሚባሉት በህይወት የመኖር፣ የመፃፍ፣ የመናገር፤ የፈለጉትን ሀይማኖት የመከተል፤ በነፃነት የመዘዋወርና ንብረት የማፍራት መብቶችና ነፃነቶች በተግባር የሚረጋገጡት መንግስት እጁን ሲሰበስብ ነው፡፡ እነዚህ መብቶች በመንግስት በተለይ በስራ አስፈፃሚውና በስሩ ባሉት የአስተዳደር ተቋማት ውሳኔ፤ ትዕዛዝ፤ ደንብና መመሪያ አማካይነት አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ ህገ መንግስቱ የበላይ ህግ እንደመሆኑ ይህን የሚቃረን ህግ፣ ውሳኔና አሰራር ሁሉ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ይህን መሰሉ የህገ መንግስታዊነት ጥያቄ በአስተዳደር ህግ ውስጥ አይወድቅም፡፡ ይሁን እንጂ የህገ መንግስታዊነት ብቻ የሚመስል ጥያቄ በአስተዳደር ህግ ማእቀፍ የሚሸፈንበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡ በአንድ የአስተዳደር ተቋም የወጣ መመሪያ በህግ አውጭው ከተሰጠ የውክልና ስልጣን በማለፍ የዜጐችን ሰብዓዊ መብት የሚገድብ ሆኖ ከተገኘ በውስጡ የህገ መንግስታዊነት (constitutionality) ጥያቄ ያዘለ ቢሆንም በዋናነት ግን የአስተዳደር ህግ ሊመልሰው የሚገባ የህጋዊነት (legality) ጥያቄ ነው፡፡ ልዩነታቸውን የበለጠ መረዳት እንዲያስችልን የሚከተለውን የድሮው የገቢዎች ሚኒስቴር የአሁኑ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መመሪያ እንመልከት፡፡ ማንኛውም የጉምሩክ ፖሊስ ሰላማዊ ስልፍና የስራ ማቆም አድማ ማድረግ አይችልም፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ለማንኛውም ሰው የተረጋገጠ መብት ነው፡፡
መብቱን የሚያጎናጽፈው የአንቀጽ 30 ንዑስ ቁጥር 1 እንዲህ ይነበባል፡፡ ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ አንድ መመሪያ በስራ አስፈፃሚው አካል ሲወጣ ከህግ አውጭው በግልጽ የተሰጠ የውክልና ስልጣን (Delegation) ሊኖር ይገባል፡፡
መመሪያው የውክልና ስልጣኑን ገደብ ካለፈ ከስልጣን በላይ (Ulta vires) ነው፡፡
ስለሆነም በህግ ፊት ዋጋ አልባ (null and void) ነው፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር ይህን መመሪያ ሲያወጣ የስልጣን ምንጩን የጉምሩክ ባለስልጣንን ለማቋቋምና አስራሩን ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁ. 368/1995 አንቀጽ 8 (2) (ሐ) እንደሆነ ይጠቅሳል፡፡ ይህ የተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ እንዲህ ይነበባል፡፡ የጉምሩክ ህግ እንዲያስከብር ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተመደበን የፖሊስ ኃይል ሚኒስቴሩ የፌደራል ፖሊስ አዋጅን ተከትሎ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት በስራ ያሰማራል፡፡ ያስተዳድራል፡፡ ጥፋት ሲገኝም ያሰናብታል፡፡
ይህ አንቀጽ የጉምሩክ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርግ በመመሪያ እንዲከለክል ለገቢዎች ሚኒስቴር ስልጣን አይሰጥም፡፡ ከተወካዮች ምክር ቤት ግልፅ ስልጣን ባልተሰጠበት ሁኔታ የወጣው ይህ መመሪያ ህጋዊነት ሆነ ተፈፃሚነት የለውም፡፡
የአስተዳደር ህግ ይህን መሰል መመሪያዎች በዘፈቀደ እየወጡ የዜጐችን መብትና ነፃነት እንዳይጥሱ በተለያዩ መንገዶች በመቆጣጠር መንግስት ሰብዓዊ መብት የማክበር ግዴታውን እንዲወጣ ያደርጋል፡፡
የመንግስት የማስፈፀም ኃላፊነት አብዛኛውን ጊዜ ከማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ መብቶች ጋር በቀጥታ ተያይዞ ይነሳል፡፡ መንግስት በዜጐች መብት ላይ ጣልቃ አለመግባቱ ወይም እጁን መሰብሰቡ ብቻ አይበቃም፡፡ ለዜጋው መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማለትም ጤና፣ መብራት፣ ውሃ፣ መንገድ ወዘተ… ካላቀረበ ነፃ መሆን በራሱ ፋይዳ የለውም፡፡ የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት ትሰስር ከመንግስት የማስከበር ግዴታ አንጻርም ሊቃኝ ይችላል፡፡ ከዚህ አንጻር መንግስት ሰብዓዊ መብትን በማስከበር ኃላፊነቱ መብት እንዳይጣስ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶች በህግ እና በተቋማዊ አደረጃጀት የማጠናከር፣ በመብት መጣስ ጉዳት ለደረሰበት ዜጋ ፈጣን ፍትህ የሚያገኝበትን ስርዓት መዘርጋት አለበት ማለት ነው፡፡ በአጭር አገላለጽ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ መንግስት የዳበረ የአስተዳደር ህግ እና የአስተዳደር ህግ ስርዓት መቅረጽ፣ መትከልና ማጐልበት ይጠበቅበታል፡፡