የክልል አስተዳደር ህግ


ፌደራላዊ የመንግስት አወቃቀር የመንግስትንና

የግለሰብን ግንኙነት ሁለትዮሽ ገፅታ ያላብሰዋል፡፡ በፌደራል ደረጃ በፌደራሉ መንግስትና በግለሰቡ መካከል የሚፈጠር ግንኙት ሲኖር ይኸው ተመሳሳይ ግንኙነት በክልል ደረጃ በክልሉ መንግስትና በግለሰቡ መካከል ይፈጠራል፡፡ የኢትዮጵያ የአስተዳደር ህግ ይዘት፣ ወሰንና መገለጫ ባህሪያት ከዚህ ሀሳብ ይነሳል፡፡ መንግስትና የህዝብ የአስተዳደር በፌዴራልና በክልል ደረጃ የተዋቀረ እንደመሆኑ የአገራችን የአስተዳደር ህግ የፌደራል እና የክልል አስተዳደር ህግ ድምር ውጤት ነው፡፡
ከድምሩና ከውጤቱ በፊት ግን በፌደራላዊ የመንግስት ስርዓት ውስጥ ሁለት ዓይነት የአስተዳደር ህግ የመኖሩ ጉዳይ ግልጽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም ክልሎች የራሳቸውን የአስተዳደር ህግ ማውጣት ይችላሉ? የሚል የስልጣን ክፍፍል ጥያቄ ሊነሳ አይገባም፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በፌደራል እና በክልል የተዋቀረ ሲሆን ሁለቱም በተመሳሳይ መልኩ ህግ አውጪ፤ አስፈፃሚና ህግ ተርጓሚ የሚባሉ የመንግስት አካላት አቅፈዋል፡፡a እነዚህ ሶስት የመንግስት አካላት በህገ-መንግስቱ ለፌደራል እና ለክልሎች በተሰጡት ስልጣናት ስር ህግ የማውጣት፤ የመተግበር እና የመተርጐም ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ በክልል ደረጃ ህግ አስፈፃሚው አካል የክልሉ መስተዳድር ሲሆን የክልሉ ምክር ቤት ያወጣቸውን ህጐች ይተገብራል፡፡b
ስልጣንን በመገልገል የሚፈጸሙ ተግባራት አስተዳደራዊ (ለምሳሌ የምርመራ፤ የክትትል፤ ቁጥጥርና ምክር መስጠት)፣ ህጉን ለመተግበር የሚረዱ መመሪያዎችን የማውጣት እንዲሁም የአስተዳደር ውሳኔዎችንና እርምጃዎችን የመውሰድ (ለምሳሌ የንግድ ድርጅት የመዝጋት፤ የንግድ ፍቃድ የመስጠት፤ የማገድ፤ የመሰረዝ) ተግባራትን ያጠቃልላል፡፡ የክልል አስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ህጋዊነትና ፍትሐዊነት በተመለከተ የክልል ምክር ቤት እና የክልል ፍ/ቤቶች የየራሳቸውን ሚና ይጫወታሉ፡፡ ለምሳሌ የክልሉ ምክር ቤት አነስተኛ የውሳኔ እና የመመሪያ አወጣጥ ስነ-ስርዓቶችን ሊደነግግ ይችላል፡፡ ፍ/ቤቶች ደግሞ የአስተዳደራዊ ውሳኔዎችና መመሪያዎች ህጋዊነት በመመርመር መስተዳደሩ ለህግ ተገዢ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡ በዚህ መልኩ የአስተዳደር ህግ በእያንዳንዱ ክልል የግድ ይፈጠራል፡፡ በአሁኑ ወቅት ያለው የፌደራል የአስተዳደር ህግ ገና በቅጡ ያልዳበረና ጥልቀት ያለው ጥናትና ምርምር ተደርጐበት ትክክለኛ ይዘቱ፤ ቅርፁ፤ መገለጫውና ወሰኑ ተለይቶ የሚታወቅ አይደለም፡፡ ከዚህ በባሰ ደግሞ በክልሎች ያለው የአስተዳደር ህግ በአግባቡ ሊጠናና ሊታወቅ ቀርቶ እስከ መኖሩ ሳይቀር ተዘንግቷል ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ የተነሳ በፌደራሉ የአስተዳደር ህግ እና በክልል የአስተዳደር ህግ መካከል ያለው ዝምድና እና መወራረስ ራሱን የቻለ ጥናትና ምርምር ይፈልጋል፡፡ በየክልሉ ያሉትን አዋጆች፤ ደንቦች፤ መመሪያዎችና የፍ/ቤት ውሳኔዎች ብሎም የየአስተዳደር መስሪያ ቤቱ ውሳኔዎችና ሌሎች የህጉን ምንጮች ለማግኘት ካለው አዳጋችነት የተነሳ የዚህ መጽሀፍ ዋነኛ ትኩረትም የፌደራል የአስተዳደር ህግ ብቻ ነው፡፡

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.