አንታራም ህጎች ከአገራችን


በአገራችን ከላይ እንዳየናቸው ዓይነት ፈገግታን የሚያጭሩ አንታራም ህጎች እስካሁን አልገጠመኝም፡፡ ሆኖም ከህገ-መንግስታዊነት መለኪያ አንጻር አንታራምነታቸው ጎልተው የወጡ የህግ ድንጋጌዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ እኔ የሚከተሉትን መርጫለው፡፡ ማብራሪያ አልተጨመረም፡፡
(የትራንፖርት አዋጅ ቁጥር 468/1997 አንቀጽ 27(2)
ክልሎች የራሳቸውን ህግ እስኪያወጡ ድረስ የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች ትራንስፖርት ነክ በሆኑት ጉዳዮች ላይ በክልሎች ውስጥ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡
(የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩል ባለስልጣን ሰራተኞች አስተዳደር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37)
በልዩ ሁኔታ ሰራተኞችን ስለማሰናበት
1) በዚህ ደንብ በሌላ ሁኔታ የተደነገገው ቢኖርም ዋና ዳይሬክተሩ በሙስና የተጠረጠረንና እምነት ያጣበትን ሰራተኛ መደበኛውን የዲስፕሊን አፈፃፀም ስርዓት ሳይከተል ከስራ ማሰናበት ይችላል
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ በየትኛውም የፍርድ አካል ውሳኔ ወደ ስራ የመመለስ መብት አይኖረውም፡፡
(የፍትሐ ብሔር ህግ እንደተሻሻለ አዋጅ ቁጥር 639/201)
ለባንክ ወይም ለአነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ብድር መያዣነት የተሰጠ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት የተደረገ ውል በፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 1723 መሰረት በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ስልጣን በተሰጠው አዋዋይ ፊት አልተደረገም በሚል ተፈጻሚነት እንዳይኖረው ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት በማናቸውም ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ አይጸናም፡፡ (ሰረዝ የተጨመረ)
(የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁ. 691/2003)
የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ደንብ በማውጣት፣ ማንኛውም አስፈጻሚ አካል እንዲታጠፍ፣ ከሌላ አስፈጻሚ አካል ጋር እንዲዋሃድ ወይም እንዲከፋፈል በማድረግ፣ ተጠሪነቱ ወይም ሥልጣንና ተግባሩ እንዲለወጥ በማድረግ ወይም አዲስ አስፈጻሚ አካል እንዲቋቋም በማድረግ የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን እንደገና የማደራጀት ሥልጣን በዚህ አዋጅ ተሰጥቶታል፡፡
(የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ማፅደቂያ አዋጅ ቁ. 542/1999 አንቀጽ 20) ንዑስ አንቀጽ 6ን ይመልከቱ

ቅጣት

የተፈጸመው ጥፋት በወንጀል የበለጠ የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር፤
፩/ በዚህ አዋጅና አዋጁን ለማስፈጸም በሚወጡ መመሪያዎች ካልሆነ በስተቀር ከመንግሥት ደኖች ዛፎችን የቆረጠ ወይም የደን ውጤቶችን የወሰደ፤ ያዘጋጀ ወይም በማንኛውም መንገድ የተጠቀመ ከ፩ ዓመት በማያንስና ከ፭ ዓመት በማይበልጥ እሥራት እና በብር ፲ሺ ይቀጣል፣
፪/ የደን የወሰን ምልክቶችን ያጠፋ፤ ያበላሸ ወይም ያዛባ ከ፩ ዓመት በማያንስና ከ፭ ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል፣
፫/ እሳት በመለኮስ ወይም በማናቸውም ሌላ ሁኔታ በደን ላይ ጉዳት ያደረሰ ከ፲ ዓመት በማያንስና ከ፲፭ ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል፣
፬/ በደን ክልል ውስጥ ያለፈቃድ የሰፈረ ወይም የእርሻ ቦታ ያስፋፋ ወይንም ማንኛውም የመሠረተ ልማት ግንባታ ያለፈቃድ በደን ቦታ የተጠቀመ ከ፪ ዓመት በማያንስ እስራት እና በብር ፳ሺ ይቀጣል፣
፭/ ለህገወጥ ደን ጨፍጫፊዎች ወይም የደን ውጤት አዘዋዋሪዎች በማንኛውም መልኩ ምርቱን እንዲደብቁ ወይም እንዲያሸሹ እገዛ ያደረገ በ፭ ዓመት እስራት እና በብር ፭ሺ መቀጫ ይቀጣል፣
፮/ ከላይ ከተራ ቁጥር ፩ እስከ ፭ ባሉት ውስጥ ያልተጠቀሱና ቅጣት ያልተቀመጠባቸውን ጥፋቶች ያደረሰ ከ፮ ወር በማያንስና እስከ ፭ ዓመት በሚደርስ እስራትና እስከ ፴ሺ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፣ (ሰረዝ የተጨመረ)
(የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ቻርተር አዋጅ ቁ. 87/1989 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 3)
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ደንቦች፤ መመሪያዎችና ውሳኔዎች አገራዊ ጥቅምን ይጎዳሉ ተብሎ ሲታመን በፌደራሉ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊታገዱና ሊሻሩ ይችላሉ፡፡

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.