ሌሎች የጋብቻ አፈፃፀም ሥርዓቶች
አንቀጽ ፳፮ በሃይማኖት ሥርዓት የሚፈፀም ጋብቻ
፩. በሃይማኖት ሥርዓት መሠረት ጋብቻ ሊፈፀም የሚችልበትና የአፈፃፀሙ ሥርዓት እንደየሃይማኖቱ ይወሰናል፡፡
፪. በዚህ ሕግ ለማንኛውም የጋብቻ አፈፃፀም መሟላት አለባቸው የተባሉት ሁኔታዎች በሃይማኖት ሥርዓት መሠረት ለሚፈፀም ጋብቻም መሟላት አለባቸው፡፡
አንቀጽ ፳፯ በባህል ሥርዓት ስለሚፈፀም ጋብቻ
፩. በባሕል ሥርዓት መሠረት ጋብቻ ሊፈፀም የሚችልበትና የአፈፃፀሙ ሥርዓት በአካባቢው ባሕል ይወሰናል፡፡
፪. በዚህ ሕግ ለጋብቻ አፈፃፀም መሟላት አለባቸው የተባሉት ሁኔታዎች በባህል ሥርዓት መሠረት ለሚፈፀም ጋብቻም መሟላት አለባቸው፡፡
