ጋብቻ እንዳይፈጸም ስለመቃወም


ጋብቻ እንዳይፈጸም ስለመቃወም

አንቀጽ ፲፯ ስለመቃወም

 

ጋብቻ ለመፈፀም አስፈላጊ የሆነ ሁኔታ አልተሟላም በማለት ሊፈፀም የታሰበ ጋብቻ እንዳይፈፀም ተቃውሞ ማቅረብ ይቻላል፡፡

አንቀጽ ፲፰ መቃወም ስለሚችሉ ወገኖች ጋብቻ እንዳይፈፀም መቃወም የሚችሉት ወገኖች የሚከተሉት ብቻ ናቸው፡፡

 

ሀ) በዕድሜ ምክንያት ሲሆን ወላጆች፣ ዐቃቤ ሕግ ወይም ሌላ ማንኛውም ያገባኛል የሚል ሰው፣

ለ) በሥጋ ወይም በጋብቻ ዝምድና ምክንያት ሲሆን፣ የተጋቢዎቹ ወይም የአንደኛው ተጋቢ ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች፣ ፲፰ ዓመት የሞላቸው ወንድሞች ወይም እህቶች ወይም ዐቃቤ ሕግ፣

ሐ) በጋብቻ ላይ ጋብቻ ሊፈፀም ሲሆን ሌላ ጋብቻ ከሚፈጽመው ሰው ጋር የቀደመ ጋብቻ አለኝ የሚለው ተጋቢ ወይም ዐቃቤ ሕግ፣

መ) በፍርድ በመከልከል ምክንያት ሲሆን አሳዳሪው ወይም ዐቃቤ ሕግ፡፡

 

አንቀጽ ፲፱ መቃወሚያ ስለሚቀርብበት ሥርዓትና ጊዜ

 

፩. ጋብቻ እንዳይፈፀም የሚቀርበው መቃወሚያ በጽሑፍ ሆኖ እጅግ ቢዘገይ ጋብቻው ከሚፈፀምበት ከ፲፭ ቀን በፊት ለጋብቻ አስፈፃሚው ባለሥልጣን መቅረብ አለበት፡፡

፪. ጋብቻ አስፈፃሚው ባለሥልጣን በመቃወሚያው ላይ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት የተጋቢዎቹን አስተያየት መቀበል ይኖርበታል፡፡

 

አንቀጽ ፳ በመቃወሚያ ላይ ስለሚሰጠው ውሳኔ

 

፩. ጋብቻ የሚያስፈጽመው ባለሥልጣን በሚቀርብለት መቃወሚያ ላይ በአምስት ቀን ጊዜ ውስጥ ውሳኔ መስጠት አለበት፡፡

፪. ጋብቻ አስፈፃሚው ባለሥልጣን መቃወሚያውን ባለመቀበል ጋብቻው እንዲፈፀም የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡

፫. ጋብቻ አስፈፃሚው ባለሥልጣን መቃወሚያውን የተቀበለው እንደሆነ ጋብቻው እንዳይፈጸም ማድረግ አለበት፡፡

፬. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) የተመለከተው ውሳኔ የተሰጠ እንደሆነ ባለሥልጣኑ ለውሳኔው ምክንያት ያደረገውን ጉዳይ ተጋቢዎቹ ወዲያውኑ እንዲያውቁት ያደርጋል፡፡

 

አንቀጽ ፳፩ ስለይግባኝ

 

፩. በዚህ ሕግ አንቀጽ ፳ ንዑስ አንቀጽ (፫) በተመለከተው ሁኔታ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ተጋቢዎቹ ወይም ከተጋቢዎቹ አንዱ ለፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይችላል፡፡

፪. ይግባኝ የቀረበለት ፍርድ ቤት የጋብቻ አስፈፃሚውን ባለሥልጣን ውሳኔ የሻረው እንደሆነ ባለሥልጣኑ ጋብቻውን ያስፈጽማል፡፡

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.