የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀገሪቱ የቆዳ ስፋት የያዘ ነው።


የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትልቁን የሀገሪቱን የቆዳ ስፋት የያዘ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትም በ12 አሰተዳደራዊ ዞኖችና በ180 ወረዳዎች የተዋቀረ ነው፡፡ ከነዚህ 12 ዞኖች ውስጥ፣ የባሌና ቦረና ዞኖች 45.7 ከመቶ የሚሆነውን የክልሉን መሬት ሲይዙ በህዝብ ሰፈራ ረገድ ግን የክልሉን 14 ከመቶ ብቻ ይኖርባቸዋል፡፡ የኦሮሚያ ምክር ቤት የክልሉ አስተዳደር ከፍተኛው መዋቅር ነው፡

ርዕሰ ከተማ
አዲስ አበባ (ፊንፊኔ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ ከተማ ነች፡፡
የስፍራው አቀማመጥ
የኦሮሚያ ክልል በሰሜን ከአፋር፣ ከአማራ እና ቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልሎች፣ በምስራቅ ከሶማሌ ክልል፣ በምእራብ ከሱዳን ሪፐብሊክ፣ ከቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልልና ከደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ እንዲሁም በደቡብ ከኬንያና ከጋምቤላ ክልል ጋር ይዋሰናል፡፡
የቆዳ ስፋት
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት 353‚690 ስኩ.ኪ.ሜ የሚገመት የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፡፡ ይህም የሀገሪቱን 32 ከመቶ የቆዳ ስፋት ይይዛል፡፡
ስነ-ህዝብ
በ1994 በተገኘው የህዝብ ቆጠራ መሰረት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ብዛት 18,732,525 ሲሆን ከዚህም ውስጥ 9,371,228 ወንዶች እና 9,361,297 ሴቶች ናቸው፡፡ 89.5 ከመቶ የሚሆነው በገጠራማው የክልሉ ቦታዎች ይኖራል፡፡ በሀይማኖት ረገድም 44.3 ከመቶ የእስልምና፣ 41.3 ከመቶ የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ 8.6 ከመቶ የፕሮቴስታንት የተቀረው 4.2 ከመቶ የባህላዊ እምነት ተከታይ ነው፡፡
በክልሉ የከተማ አካባቢዎች ግን 67.8 ከመቶ የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ 24.0 ከመቶ የእስልምና እንዲሁም 7 ከመቶ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው፡፡ በብሄር ስብጥር አኳያም 85 ከመቶ የኦሮሞ፣ 9.1 ከመቶ የአማራ፣ 1.3 ከመቶ የጉራጌ፣ የተቀረው 4.6 ከመቶ የሌሎች ብሄረሰቦች ይኖራሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በላቲን ፊደላት የተቀረፀው የኦሮሚኛ ቋንቋ የክልሉ የስራ ቋንቋ ሲሆን 85.5 ከመቶ በክልሉ ይነገራል፣ አማርኛ 11 ከመቶ፣ ጉራጊኛ 0.98 ከመቶ፣ ጌዴኦኛ 0.98 ከመቶ እንዲሁም ትግርኛ 0.25 ከመቶ በክልሉ የሚነገሩ ቋንቋዎች ናቸው፡፡
ዋነኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትከሚገኘው ህዝብ 90 ከመቶየሚሆነው ህዝብ ኑሮውን የግብርና ስራ ላይ ያደረገ ነው፡፡ በክልሉ በቆሎ፣ ገብስ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ሽንብራ እና ባቄላ እንዲሁም የተለያዩ የቅባት እህሎች በከፍተኛ ደረጃ የሚመረቱ ሰብሎች ናቸው፡፡ ቡና ለገበያ የሚቀርብ ምርት ነው፡፡ ክልሉ 51.2 ከመቶ የሚሆነውን የሰብል ምርት ከዚህም ውስጥ 45.1 ከመቶ የሚሆነው ጊዜያዊ ሰብሎች፣ እንዲሁም 44 ከመቶ የሚሆነውን የቁም ከብት ሀብት ለሀገሪቱ ያበረክታል፡፡
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህ አካላት ፡-

የፍትህና የህግ ጥናትና ምርምር ዘርፍ


የፍትህና የህግ ጥናትና ምርምር ዘርፍ

የፍትህና የህግ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል የጥናትና ምርምር ስራ አንዱና ዋንኛው ነው፡፡ በመሆኑም ተቋማችን በፍትህ ሥርዓቱ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመለየት የህብረተሰቡን ወቅታዊ የፍትህ ችግሮች ለመቅረፍ የሚረዱ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን በጥራትና በስፋት እያከናወነ ይገኛል፡፡፡
የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ጥናትና ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለመስራት የተደራጀ ሲሆን፣ በስሩ ሶስት ዳይሬክቶሬቶች የያዘና ተጠሪነቱም ለኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሲሆን የሚከተሉት ተግባራት ያከናዉናል፡-
• ዳይሬክተሩ በሚሰጠው ውክልና መሠረት ዳይሬክተሩ ሳይኖር የሱን ሥራ ተክቶ ይሠራል፣
• የሕግና ፍትህ ምርምሩን የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ መርሃ ግብርና በጀት አዘጋጅቶ ለዳሬክተሩ ያቀርባል፣ሲፈቅድም በሥራ ላይ ያውላል፣
• የቢሮውን ተግባር ያቅዳል ፣በሥሩ የተደረጁትን ዲፓርትመንቶች ሥራ በበላይነት ይመራል፣ያስተባብራል፣ይቆጣጠራል፣
• የሚካሄደው ምርምርና በአገሪቷ ውስጥ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ለማፋጠን በሚያስችል መልኩ እንዲነደፉ ያደርጋል፣
• የፐብሊክ ሕግ፣ የሲቪልሕግ እና የፍትሕ ሥርዓት ጥናት ጥናትና ምርምር ስራዎችን ማቀድ፣ ማስተባበር፣ መምራት እና መደገፍ፣
• የፍትሃብሄር ፍትህ፣ የወንጀል ፍትህ እና የአስተዳደር ፍትህ ተቋማት አፈጻጸም ከቅልጥፍና፣ ውጤታማነትና ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ምላሽ ሰጭነት፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት አንጻር የሚገኝበትን ሁኔታ በማጥናት አፈጻጸማቸውን ለማጠናከር የሚረዱ የማሻሻያ ሃሳቦችን ማቅረብ፤
• በሕግ ትምህርት እና ሥልጠና ሥርዓቱ ላይ ጥናት በማካሄድ በእውቀቱ፣ በክህሎቱ፣ በአመለካከቱ፣ እንዲሁም በሥነ ምግባሩ ብቁ የሆነ አመራር እና ባለሞያ ለማፍራት የሚቻልበትን ሁኔታ ለማጠናከር የሚያግዙ ሃሳቦችን ማመንጨት፤
• የፍትህ ዘርፉ ለኪራይ ሰብሳቢነት ያለውን ተጋላጭነት በጥናት በመገምገም በዘርፉ ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመከላከል የሚያግዙ የመፍትሄ ሃሳቦችን መጠቆም፤
• በባህላዊ የፍትህ ተቋማት እና በአሰራራቸው ላይ ጥናት በማካሄድ ከመደበኛው የፍትህ ሥርዓት ጋር ተጣጥመው ስራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ የሚረዱ ምክረ ሃሳቦችን ማቅረብ፤
• የፍትህ ሥርአቱን በሚመለከት የማማከር አገልግሎት መስጠት፣
• የፍትህ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር የሚረዱ ስልቶች መለየት፤
• አስፈላጊ የሆኑ ጥናትና ምርምር ውጤቶችን እንዲታተሙና እንዲሰራጩ ውሳኔ ይሠጣል፣
• በሥሩ የሚገኙ የጥናትና ምርምር የስራ ክፍሎችን ጥረት ለማስተባበር፣ጥንካሬና ድክመቶቻቸውን ለመገምገምና በጋራም መፍትሄ ለመስጠት የስራ ክፍሎችን ስብሰባ ይመራል፣
• በስሩ ያሉ ዲፓርትመንቶችን ባለሙያዎች የሙያ ብቃታቸውን ለማዳበርና ከአዳዲስ ጽንሰ ሐሳቦች ጋር እንዲተዋወቁ አስፈላጊውን ሥልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፣
• የዲፓርትመንቶችን ውጤት ተኮር የዕቅድ አፈጻጸም ምዘና ያከናውናል፣
• በየዲፓርትመንቶቹ ያሉትን ሰራተኞች በ1 ለ 5 ማደራጀት ፣የውይይታቸውን ሪፖርት መከታተል እና በውይይቱ ለተነሱ ጥያቄች በአሰራር መፍትሔ መስጠት፣
• ከየዲፓርትመንቶቹ የሚቀርቡትን የሕግ ጥናት እና ምርምሮች የሚገመግም የቴክኒክ ኮሚቴ ያዋቅራል ፣በበላይነት ስራውን ይቆጣጠራል፣
• ከየዲፓርትመንቶቹ የሚቀርቡትን የሕግ ጥናት እና ምርምሮች በአቻላቻ ግምገማ ፣በቴክኒክ ኮሚቴ እንዲገመገሙ ያደርጋል ፣ሂደቱ ይከታተላል፣
• በስሩ ያሉትን ዲፓርትመንቶች ሥራቸውን ስለሚያስተባብሩበት፣ስለሚያቀናጁበትና ስለሚያቀላጥፉበት መንገድ እያጠና ሃሣብ ያቀርባል፣
• አግባብ ካለቸው መሥሪያ ቤቶች(ባለድርሻ አካላት) ጋር በመገናኘት በጋራ ሲለሚሰሩ ጥናት እና ምርምሮች እንዲሁም የሥራ ልምድና የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል፣
የፍትህና የህግ ጥናትና ምርምር ዘርፍ የተሰጠዉን ተግባራት ለማከናወን የሚከተለዉን መዋቅር ዘርግቷል፡-

የአስተዳደር ህግ ምንነት፣


የአስተዳደር ህግ ምንነት።
 
ለአስተዳደር ህግ ብያኔ በማበጀት ረገድ የመስኩ ባለሙያዎች በከፊልም ቢሆን የተለያየ እይታ አላቸው፡፡ በእርግጥ የአስተዳደር ህግ የጥናት ወሰኑን አስመልክቶ የሚከሰት ልዩነት ካልሆነ በቀር በመሰረታዊ እሳቤው ላይ የተራራቀ አቋም የለም፡፡ እንደ ህንዳዊው የአስተዳደር ህግ ምሁር አይ.ፒ. ማሴይ አገላለጽ በአስተዳደር ህግ ትርጓሜ ላይ ያለው ልዩነት ምንጩ በየጊዜው እያደገና እየተወሳሰበ የመጣው አስተዳደራዊ ሂደት ሲሆን ይህም ሂደቱን በሙሉ አጠቃሎ የያዘ ወጥ ትርጉም ለመስጠት አስቸጋሪ አድርጐታል፡፡

ያም ሆኖ የአስተዳደር ህግ ትርጓሜ ቢያንስ ሁለት መሰረታዊ አላባውያንን ማካተት ይጠበቅበታል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የአስተዳደር ህግ ከይዘት ይልቅ ስነ ስርዓት ላይ የሚያተኩር ህግ ስለመሆኑ ግልጽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም የአስተዳደር ውሳኔው እንዴት ተሰጠ? እንጂ ይዘቱ ትክክል ይሁን አይሁን ፍርድ ቤቶች ሆነ የአስተዳደር ህግ ጣልቃ የሚገባበት ጉዳይ አይደለም፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ማንኛውም የአስተዳደር ህግ ትርጓሜ የህጉን ዓላማ ግምት ውስጥ ያስገባ ተግባራዊ አቀራረብ እንዲያቅፍ ይጠበቅበታል፡፡ የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ዓላማ ወይም ተግባር ስልጣንን መቆጣጠር ነው፡፡h ያ ሲባል ግን የአስተዳደር አካላት ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩና እንዳይላወሱ ማነቆ ሆኖ ያግዳቸዋል ማለት አይደለም፡፡ የስልጣን ቁጥጥር ሲባል ማንኛውም ባለስልጣን ሆነ መስሪያ ቤት በህግ ተለይቶ ከተቀመጠለት የስልጣን ገደብ እንዳያልፍና ስልጣን ቢኖረውም እንኳን ስልጣኑን ፍትሐዊና አግባብ በሆነ መንገድ እንዲወጣ ያደርጋል ለማለት ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ዓላማና ተግባር ስልጣንን በተግባር መቆጣጠር እንደመሆኑ ይህን ባህርዩን ግምት ውስጥ ያላስገባ ብያኔ የተሟላ ተብሎ ሊወሰድ ሆነ ሊወደስ አይችልም፡፡

ለንጽጽር እንዲረዳን በመስኩ ባለሙያዎች ለአስተዳደር ህግ የተሰጡ ትርጓሜዎችን እንደሚከተለው እንጠቅሳለን፡፡
ቤርናርድ ሺዋሬዝ (Bernard Schwartz) የአስተዳደር ህግን ‘በውክልና ህግ የማውጣትና አስተዳደራዊ ዳኝነት የመስጠት ስልጣን ባላቸው የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ህግ’ በማለት ይገልፀዋል፡፡i ይህ ብያኔ ጠባብ ከመሆኑ በቀር ስለ ህጉ ይዘት ገላጭ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ በውክልና ስልጣን ህግ ከማውጣትና ከአስተዳራዊ የዳኝነት ስልጣን በተጨማሪ ይህ ስልጣን በፍርድ የሚታረምበትን የአጣሪ ዳኝነት (judicial review) ስነ-ስርዓት እንዲሁም በፖርላማና በተለያዩ ተቋማት የሚደረግ ቁጥጥርንም ያካትታል፡፡
ጄኒንግስ በበኩሉ የአስተዳደር ህግ ማለት ‘አስተዳደርን የሚመለከት ህግ ነው፡፡ ይህ ህግ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶችን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ግዴታ ይወስናል፡፡’ በማለት ይገልጸዋል፡፡j እንደ አይ.ፒ ማሴይ አስተያየት ይህ ትርጓሜ የአስተዳደር ህግን ከህገ መንግስት በግልጽ አይለይም፡፡ አስተዳደር ወይም ማስተዳደር ማለት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስልጣንን በመጠቀም የህብረተሰቡን ጉዳይ መምራት ማለት ነው፡፡k ለዚህም በዋነኛነት አደራ የተጣለባቸው አካላት የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የእነዚህ ተቋማት ስልጣንና ግዴታ በዝርዝር ህግ ተለይቶ ቢወሰንም የስራ አስፈፃሚው አካል ስልጣን በጠቅላላው የሚቀመጠው በህገ መንግስት ላይ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ሆነ ህገ መንግስት ሁለቱም የመንግስት አስተዳደርን ወይም የግለሰብና የመንግስትን ግንኙነት የሚመሩ ህጐች እንደመሆናቸው በመካከላቸው ያለው መለያ ክር በጄኒንግ ትርጓሜ ላይ በግልጽ ነጥሮ አልወጣም፡፡

ታዋቂው የህገ መንግስት ሊቅ ኤ. ቪ. ዲሴይ የአስተዳደር ህግን በሶስት ደረጃዎች ከፋፍሎ እንዲህ ይገልጸዋል፡፡l
የአስተዳደር ህግ የመንግስት ባለስልጣናትን የህግ ስልጣንና ተጠያቂነት የሚወስኑትን የአንድ አገር የህግ ስርዓት የሚመለከት የህግ ክፍል ነው፡፡
ግለሰቦች ከመንግስት አካላት ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ያላቸውን መብትና ግዴታ ለይቶ ይወስናል፡፡
እነዚህ መብቶችና ግዴታዎች ተፈጻሚ የሚሆኑበትን ስርዓት ይዘረጋል፡፡
እንደ ማሴይ ትችት ይህ ትርጓሜ የአስተዳደር ህግ አንድ አካል የሆነውን አጣሪ ዳኝነት (judicial review) ብቻ የሚመለከት እንደመሆኑ በይዘቱ ጠባብ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ከአጣሪ ዳኝነት በተጨማሪ በህግ አውጭውና በተቋማት (ለምሳሌ በእንባ ጠባቂ ተቋምና ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን) አማካይነት የሚደረግ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችንም ያካትታል፡፡ ህጉ ከመንግስት ባለስልጣናትና ከአስተዳደር መስሪያ ቤቶች በተጨማሪ ከፊል የአስተዳደር አካላት ተብለው የሚፈረጁትን መንግስታዊ ኮርፖሬሽኖች፤ ዩኒቨርሲቲዎች እና በከፊል መንግስታዊ ነክ ስልጣን ያላቸውን ማህበራትm በተመለከተም ተፈጻሚነት አለው፡፡
በመጨረሻም ታዋቂው የህንድ ምሁር አይ.ፒ. ማሴይ ከላይ ከተሰጡት ሰፋ ያለና የህጉን ባህሪያትና ተግባራት ጠቅልሎ የያዘ ብያኔ እንደሚከተው ያስቀምጣል፡፡
የአስተዳደር ህግ የህዝብ አስተዳደር ህግ አካል ሲሆን የአስተዳደርና ከፊል አስተዳደር መስሪያ ቤቶችን አደረጃጀትና ስልጣን የሚደነግግ፣ አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሰጥበትን ደንብና መርህ የሚያስቀምጥ፣ እንዲሁም ከግለሰቦች መብትና ነፃነት ውሳኔው የሚታረምበትን ስርዓት የሚወስን የህግ ክፍል ነው፡፡n
ይህ ትርጓሜ ከሞላ ጐደል ሁሉንም የአስተዳደር ህግ ባህርያት አጠቃሎ የያዘ በመሆኑ ተመራጭነት አለው፡፡ ከላይ ከቀረቡት የተለያዩ ትርጓሜዎች የሚከተሉት የጋራ ነጥቦች ይመዘዛሉ::

አንደኛ፤ የአስተዳደር ህግ የአስተዳደር እና ከፊል የአስተዳደር አካላት ያላቸውን ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት ያጠናል፡፡o የማንኛውም የአስተዳደር አካል የስልጣን ምንጭ የሚገኘው ከማቋቋሚያ አዋጁ (Enabling Act) ሲሆን አልፎ አልፎ በሌላ ዝርዝር ህግ ይወሰናል፡፡ በአስተዳደር ህግ የመጀመሪያው ጥያቄ ውሳኔ ወይም እርምጃ የወሰደው አካል በህግ የተሰጠው ስልጣን አለው? የሚል ነው፡፡ ከሌለ ድርጊቱ ከስልጣን በላይ ስለሆነ ዋጋ አልባ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ከድርጊቱ በስተጀርባ የህግ ስልጣን ካለ ውሳኔ ሰጪው ስልጣኑን በአግባቡና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንደተገለገለ ይጣራል፡፡ ካልሆነ ስልጣኑን ያለ አግባብ በሚገለገለው አካል ላይ ህጉ ቁጥጥር ያደርግበታል፡፡

ሁለተኛ፤ ህጉ ስልጣንን በመገልገል ሂደት ተፈጻሚ የሚሆኑ መሪ ደንቦችን፤ ስነ ስርዓቶችንና መርሆዎችን ያስቀምጣል፡፡ ህግ አውጭው ለአስተዳደር አካላት ስልጣን ሲሰጥ ስልጣኑ ተግባር ላይ በሚውልበት ጊዜ ህጋዊነቱንና ፍትሐዊነቱን የሚያረጋግጥ የስነ ስርዓት ቅድመ ሁኔታ አብሮ እንዲደነግግ ይጠበቃል፡፡ ለምሳሌ ያህል ደንብና መመሪያ በማውጣት ረገድ ከሚመለከተው አካል ጋር የመመካከርና የህትመት ቅድመ ሁኔታዎች፣ አስተዳደራዊ ውሳኔ ሲሰጥ የመሰማት መብትና የኢ- አድሎአዊነት መርሆዎችን በአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ ወይም በዝርዝር ህግ ማውጣት ይኖርበታል፡፡ እነዚህም በአስተዳደር ሂደቱ ውስጥ ፍትሐዊነትን በማረጋገጥ ረገድ ጉልህ ስፍራ አላቸው፡፡ ስልጣን በዘፈቀደ ሳይሆን በአግባቡ ስራ ላይ ዋለ ለማለት የሚቻለውም ያኔ ነው፡፡

ሶስተኛ፤ የአስተዳደር ህግ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችን በተመለከተ የሚያጠና ህግ ነው፡፡p ልጓም የሌለው ስልጣን ለዜጎች መብትና ነፃነት ፀር ነው፡፡ የተጠያቂነት መርሕ እውን እንዲሆን የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችም በግልጽ ተለይተው መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ስለሆነም የአስተዳደር ህግ በፍርድ ቤት፤ በአስተዳደር ፍርድ ቤት፤ በህግ አውጭው እና በተቋማት የሚደረጉ የስልጣን መቆጣጠሪያ መንገዶችን በተግባር እየፈተነ ያጠናል፡፡

አራተኛ፤ ህጉ በአስተዳደር አካላት ወይም በመንግስት ባለስልጣናት በተወሰዱ እርምጃዎች መብታቸው ለተጣሰና ነፃነታቸው ለተገፋ ዜጎች መፍትሔ ይሰጣል፡፡q መብት ያለ መፍትሔ ‘ላም አለኝ በሰማይ’ ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ መብቱ የተጓደለበት ሰው አቤቱታ አቅርቦ መፍትሔ የሚጠይቅበትና የሚያገኝበት የህግ ክፍል ነው፡፡
 
የአስተዳደር ህግ ግብና ተግባራት፣

የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ዓላማና ተግባር ስልጣንን መቆጣጠር ስለመሆኑ በመስኩ ምሁራን ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ሆኗል፡፡ ሆኖም በዚህ ብቻ ሳይወሰን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትንም ያከናውናል፡፡ እንደ ብዙዎች የአስተዳደር ህግ ሊቃውንት የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ግብ አስተዳደራዊ ፍትህን ማስፈን ሲሆን የሚከተሉት ተግባራት ይኖሩታል፡፡

ስልጣን መቆጣጠር (Control Function)፣

የአስተዳደር ህግ ስራ አስፈፃሚው የመንግስት አካልና የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች፣ ሚኒስትሮች፣ ባለስልጣናትና ሌሎች ሹመኞች በህግ ተለይቶ የተሰጣቸውን ስልጣን አልፈው እንዳይሄዱና ህጋዊ ስልጣናቸውንም አለአግባብ እንዳይገለገሉበት ለመቆጣጠር የሚያስችለን የህግ ክፍል ነው፡፡ በመሆኑም ስልጣን በህገ ወጥ መንገድ አለአግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል በመከላከል እንደ መገደቢያ መሳሪያነት ያገለግላል፡፡r

ግዴታ ማስፈፀም (Command Function)፣

በአስተዳደሩ በሚፈፀም ድርጊት የዜጋው መብት ከሚጣስበት ሁኔታ ባልተናነስ ህጋዊ ግዴታን አለመወጣት በግል መብትና ጥቅም ላይ የከፋ ጉዳት ያስከትላል፡፡ የአስተዳደር ህግ ስልጣን በልኩና በአግባቡ ተግባር ላይ እንዲውል ከመቆጣጠር ባሻገር የአስተዳደር አካላት በህግ ተለይቶ የተጣለባቸውን ግዴታ እንዲወጡ አስገዳጅ የስነ ስርዓትና ተቋሟዊ ስልቶችን ይቀይሳል፡፡s አስገዳጅ የህግ ማዕቀፍ ከሌለ ግዴታ በፈቃድ ላይ የተመሰረተ ውዴታ ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡

የአስተዳደር ፍትህ ማስፈን፣

በየትኛውም ህግን ለማስፈፀም ስልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል የሚወሰዱ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና እርምጃዎች የህዝብ አመኔታና ተቀባይነት እንዲያገኙ ፍትሐዊነታቸው በተጨባጭ ሊታይ ይገባል፡፡ የአስተዳደር ህግ አይነተኛ ተልዕኮ የአስተዳደር ፍትህን ማስፈን ነው፡፡

ግልጽነት ተጠያቂነትና የህዝብ ተሳትፎ፣

የአስተዳደር ህግ በመንግስት አስተዳደር ስራ ውስጥ ግልፅነት፣
ተጠያቂነትና የህዝብ ተሳትፎ እንዲረጋገጥ ተግባራዊ መሳሪያ በመሆን ያገለግላል፡፡ የስልጣን ልኩ ሳይታወቅና ከልክ በላይ የሆነ ስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቱ ሳይቀየስ ስለተጠያቂነት ማውራት የማይመስል ነገር ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ዜጎች መረጃ የማግኘት መብታቸውን በህግ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ በህዝብ አስተዳደር ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ የሚያስችሉ የስነ- ስርዓት ደንቦችን ይዘረጋል፡፡

ለተበደለ ወገን መፍትሔ መስጠት፣

የአስተዳደር ህግ ዜጎች ለደረሰባቸው በደል በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ባሉ መንገዶች አቤቱታ አቅርበው በአነስተኛ ወጪ እና በቀላሉ መፍትሔ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡ ስለ አስተዳደር ህግ በተደጋጋሚ ቢወራ ‘አንጀት ጠብ’ የሚል፣ የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ፣ መፍትሔ እስከሌለ ድረስ ረብ የለሽነቱን ያጎላው እንደሆነ እንጂ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡

ባለስልጣናት በህዝብ ላይ ለሚፈፅሟቸው አስተዳደራዊ በደሎች በዝርዝር የተቀመጡ የመፍትሔ መንገዶች አሏቸው፡፡
በአንድ አገር ውስጥ የአስተዳደር ህግ ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራቱን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተወጥቷል ለማለት ከአገሪቱ የመንግስት አወቃቀር ስርዓት፤ ህገ መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ ዕድገትና የአስተዳደር ህግ ተቋማት መዳበር ከግምት ውስጥ በማስገባት አንፃራዊ በሆነ መልኩ የሚለካ ጉዳይ ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን በአንድ አገር ውስጥ ሁሉን አቀፍ ውጤታማና ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ የአስተዳደር ህግ ስርዓት አለ ለማለት ከሚከተሉት ሶስት ዋነኛ መርሆዎች አንጻር እየተመነዘረ መገምገም አለበት፡፡

የአስተዳደር ፍትህ፤

የአስተዳደር በደል በፍርድ የሚታረምበትና አስተዳደራዊ ፍትሕ የሚገኝበት የፍርድ ሂደትና መንገድ እንዲሁም ተሞክሮ በአገራችን ውስጥ በግልጽ የሚታወቅ አይደለም፡፡ የአስተዳደር ፍትሕ የአስተዳደር ህግ ‘ልቡ’ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አስተዳደራዊ በደል አለቅጥ በተንሰራፋበት አገር ውስጥ የአስተዳደር ህግ ትንፋሽ ያጠረው ህላዌነቱ የሚያጠራጥር ህግ ነው፡፡ የከለላው መጠን የአስተዳደር ፍትህ ደረጃ አንጻራዊ መለኪያ ነው፡፡

የስራ አስፈፃሚው ተጠያቂነት፤

የዚህ መርህ ዋና አላማ ህግ የማስፈፀም ስልጣን ያለው አካል ለሚፈፅመው ድርጊት እና ለሚወስደው እርምጃ በህዝብ ፊት ተጠርቶ እንዲጠየቅና ማብራሪያ እንዲሰጥ ለማስገደድ ነው፡፡ ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣንን የተቀበለ አካል ወይም ባለስልጣን የሚፈፅመው ድርጊት የህዝቡን ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆን ይኖርበታል፡፡ ውሳኔ ሰጭው ለድርጊቱ ትክክለኛነትና ፖለቲካዊ ተገቢነት ህግ አውጭው ፊት ተጠርቶ በመቅረብ ለማብራሪያ የሚገደድበት ስርዓት ከሌለ በቀር ተጠያቂነት አለ ማለት አይቻልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አስተዳደሩ በዜጎች መብት ለሚያደርሰው ጉዳት በፍርድ ሂደት ለድርጊቱ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡

መልካም አስተዳደር፣

በዚህ መርህ መሰረት አስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሁሉን አቀፍ ተቀባይነት ላገኙ መሪ ደንቦች መገዛት አለበት፡፡ እነዚህም የፍትሀዊነት፣ ምክንያታዊነት፣ ሚዛናዊነትና የግልፅነት መርሆዎችን ያጠቃልላሉ፡፡ አስተዳደራዊ ውሳኔ በህጉ መሰረት መወሰዱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የውሳኔው መሰረት ከቅን ልቦና የመነጨ፣ ለባለጉዳዩ ግልፅ በሆነ አሰራርና መንገድ ያልተወሰደ ካልሆነ በስተቀር የመንግስት አስተዳደር ወደ መልካምነት ደረጃ ለመድረስ ገና ብዙ ይቀረዋል፡፡ የአስተዳደር ህግ እነዚህን መርሆዎች እንዲዳብሩ ከማድረግ አንፃር አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ስለሆነም የህጉ የእድገት ደረጃ የአንድ አገር የመልካም አስተዳደር ሁኔታ ጠቋሚ መለኪያ ነው ማለት እንችላለን፡፡

በወንጀል የዳኝነት ስልጣን።


በወንጀል የዳኝነት ስልጣን፡-

1. በፌደራል መንግስቱ የቀረጥና የግብር ገቢዎች በጠቅላላ የገንዘብ ጥቅሞች ላበሚፈጸም ወንጀል

2. የሀሰት ገንዘብን በሚመለከቱ ወንጀሎች

3. በፌደራል መንግስቱ ሰነዶች ላይ የሐሰት ሰራ በመስራት በሚፈጸሙ ወንጀሎች

4. ከአንድ ክልል በላይ ውይም በአለም አቀፍ ደረጃ አገልግሎት በሚሰጡ መገናኛዎች ፀጥታና ነጻነት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች

5. የውጭ ሀገር ዜጎችን የሚመለከቱ ወንጀሎች

6. በአዲስ አበባና በድሬደዋ ውስጥ በሚነሱ በስራ ላይ ባሉ ሌሎች ሕጎች ለአውራጃና ለወረዳ ፍርድ ቤቶች በተሰጡ በሌሎች የወንጀል ጉዳዮች