የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀገሪቱ የቆዳ ስፋት የያዘ ነው።


የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትልቁን የሀገሪቱን የቆዳ ስፋት የያዘ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትም በ12 አሰተዳደራዊ ዞኖችና በ180 ወረዳዎች የተዋቀረ ነው፡፡ ከነዚህ 12 ዞኖች ውስጥ፣ የባሌና ቦረና ዞኖች 45.7 ከመቶ የሚሆነውን የክልሉን መሬት ሲይዙ በህዝብ ሰፈራ ረገድ ግን የክልሉን 14 ከመቶ ብቻ ይኖርባቸዋል፡፡ የኦሮሚያ ምክር ቤት የክልሉ አስተዳደር ከፍተኛው መዋቅር ነው፡

ርዕሰ ከተማ
አዲስ አበባ (ፊንፊኔ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ ከተማ ነች፡፡
የስፍራው አቀማመጥ
የኦሮሚያ ክልል በሰሜን ከአፋር፣ ከአማራ እና ቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልሎች፣ በምስራቅ ከሶማሌ ክልል፣ በምእራብ ከሱዳን ሪፐብሊክ፣ ከቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልልና ከደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ እንዲሁም በደቡብ ከኬንያና ከጋምቤላ ክልል ጋር ይዋሰናል፡፡
የቆዳ ስፋት
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት 353‚690 ስኩ.ኪ.ሜ የሚገመት የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፡፡ ይህም የሀገሪቱን 32 ከመቶ የቆዳ ስፋት ይይዛል፡፡
ስነ-ህዝብ
በ1994 በተገኘው የህዝብ ቆጠራ መሰረት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ብዛት 18,732,525 ሲሆን ከዚህም ውስጥ 9,371,228 ወንዶች እና 9,361,297 ሴቶች ናቸው፡፡ 89.5 ከመቶ የሚሆነው በገጠራማው የክልሉ ቦታዎች ይኖራል፡፡ በሀይማኖት ረገድም 44.3 ከመቶ የእስልምና፣ 41.3 ከመቶ የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ 8.6 ከመቶ የፕሮቴስታንት የተቀረው 4.2 ከመቶ የባህላዊ እምነት ተከታይ ነው፡፡
በክልሉ የከተማ አካባቢዎች ግን 67.8 ከመቶ የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ 24.0 ከመቶ የእስልምና እንዲሁም 7 ከመቶ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው፡፡ በብሄር ስብጥር አኳያም 85 ከመቶ የኦሮሞ፣ 9.1 ከመቶ የአማራ፣ 1.3 ከመቶ የጉራጌ፣ የተቀረው 4.6 ከመቶ የሌሎች ብሄረሰቦች ይኖራሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በላቲን ፊደላት የተቀረፀው የኦሮሚኛ ቋንቋ የክልሉ የስራ ቋንቋ ሲሆን 85.5 ከመቶ በክልሉ ይነገራል፣ አማርኛ 11 ከመቶ፣ ጉራጊኛ 0.98 ከመቶ፣ ጌዴኦኛ 0.98 ከመቶ እንዲሁም ትግርኛ 0.25 ከመቶ በክልሉ የሚነገሩ ቋንቋዎች ናቸው፡፡
ዋነኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትከሚገኘው ህዝብ 90 ከመቶየሚሆነው ህዝብ ኑሮውን የግብርና ስራ ላይ ያደረገ ነው፡፡ በክልሉ በቆሎ፣ ገብስ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ሽንብራ እና ባቄላ እንዲሁም የተለያዩ የቅባት እህሎች በከፍተኛ ደረጃ የሚመረቱ ሰብሎች ናቸው፡፡ ቡና ለገበያ የሚቀርብ ምርት ነው፡፡ ክልሉ 51.2 ከመቶ የሚሆነውን የሰብል ምርት ከዚህም ውስጥ 45.1 ከመቶ የሚሆነው ጊዜያዊ ሰብሎች፣ እንዲሁም 44 ከመቶ የሚሆነውን የቁም ከብት ሀብት ለሀገሪቱ ያበረክታል፡፡
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህ አካላት ፡-

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.