የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 6ኛ አገራዊ የምርጫ ጉዳይ አለመግባባቶችን የሚመለከት አስር ባላሦስት ዳኞች የሚሰየሙበት አስር/10/ ችሎቶችን /30 ዳኞችን/ በልደታ ምድብ ፍትሃብሔር ምድብ ችሎት አደራጅቷል፡


የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 6ኛ አገራዊ የምርጫ ጉዳይ አለመግባባቶችን የሚመለከት አስር ባላሦስት ዳኞች የሚሰየሙበት አስር/10/ ችሎቶችን /30 ዳኞችን/ በልደታ ምድብ ፍትሃብሔር ምድብ ችሎት አደራጅቷል፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ አገራችን ጊዜ ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ የወጣውን የጊዜ የድርጊት መርሐ ግብር መሠረት በማድረግና የጊዜን ወሳኝነት /Time is of an essence/ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚነሱ አለመግባባቶችን ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ፣ ውጤታማ የሆነ የዳኝነት አገልግሎት ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ፍትሐዊና ህጋዊ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከወዲሁ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡

በምርጫ ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶች ላይ በተለይም በቦርዱ በሚሰጡ ውሳኔዎች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በግልጽነትና በተጠያቂነት ለማየት ጉዳዮቹን በአንድ ዳኛ ከማያት ይልቅ ሦስት ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት መታየት የተሻለ በመሆኑ ይህ እንዲሆን ስለሚቻልበት ሁኔታ ቀደም ሲል ለዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በሦስት እንዲታይ እንድወሰን የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ተቀባይነት በማግኛቱ ነው፡፡

በሌላ በኩል ለሁሉም ፍርድ ቤቱ ዳኞች የአቅም ግንባታ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚ አዋጅ 1133/2011 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡

በመሆኑም በምርጫ ቦርድ በወጣው የጊዜ ሰሌዳ የድርጊት መርሃ ግብር ባገናዘበ ሁኔታ ፈጣን፣ ውጤታማ፣ ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ፍትሐዊና ህጋዊ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን እየገለፀ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሚቀርቡ ክርክሮች ላይ ተገቢውን ፍትህ መስጠት ይቻል ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት በተለይም ተከራካሪ ሆነው የሚቀርቡ አካላት ከወዲሁ በቀናነትና በቅን ልቦነ እና በትጋት በመከራከር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችሉ ፍርድ ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በምርጫ ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶችን የተፋጠነ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት በተደራጁ ችሎቶች ለተመደቡ ዳኞች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ሰነዶች ማለትም ጉዳዩን የሚያስተዳድሩበትን አጀንዳዎችን፤ የስልጠና ሰነዶች፤ እና ከአዋጆቹን ጥራዝ ጋር እንዲደርሳቸው አድርጓል፡በቀጣይም አጫጭር ህጎቹ እና አለም አቀፍ ተሞክሮዎቹ ላይ ለሪፍሬሽንግ የሚሆን መድረኮችን ከባለሙያዎቹ እና ከ International Foundation for Election System/ IFES ጋር በመተባባር አስፈላጊውን በቂ ዝግጅት በቀጣይነት ያደርጋል፡፡

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ፍትህን በ6ኛው አገራዊ ምርጫ በተሻለ መልኩ በማረጋገጥ የተገልጋይ እርካታን እና የህዝብ አመኔታን ለመረጋገጥ እየተገ ያለ መሆኑን እና ምርጫው ውጤታማ እና ፍትሐዊ እንዲሆን ከወዲሁ መልካሙን ይመኛል፡፡

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.