የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ይህን የማይተካ ከሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ የኢ.ፌ.ዲሪ ሕገ መንግስትም በምዕራፍ ዘጠኝ አንቀጽ 78 እስከ 81 ባሉት ድንጋጌዎችም ሆነ ሕገመንግስቱን ተከትሎ የወጣው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25 በ 1988 ባወጣው መሰረት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው መሆኑን ደንግገዋል


የዜጎችን መብትና ጥቅም አስከብሮ ዘላቂ የአገር ሠላምና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን በማጠናር ከኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገትን ለማፋጠን ፍ/ቤቶች ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ይህን የማይተካ ከሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ የኢ.ፌ.ዲሪ ሕገ መንግስትም በምዕራፍ ዘጠኝ አንቀጽ 78 እስከ 81 ባሉት ድንጋጌዎችም ሆነ ሕገመንግስቱን ተከትሎ የወጣው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25 በ 1988 ባወጣው መሰረት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው መሆኑን ደንግገዋል፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25 በ 1988 ባወጣው ህግ መሰረት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንዱ የዳኝነት መስጫ ተቋም አድርጎታል። በመሆኑም ተቋሙ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ሲሰራ ቆይቷል።የፌደራል ስርዓቱ በህገ መንግስቱ ካወቀራቸው አደረጃጀቶች መካከል የፍርድ ቤቶች የስልጣን እርከን አንዱ ነው። በመሆኑም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአዋጁ በተሰጡት ስልጣኖች መሰረት በፍታብሔር እና በወንጀል የዳኝነት ስልጣን ታውጆ እንዲዳኝባቸው ተሰቶታል። የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዓላማውን ለማሳካት ቀጥሎ የተገለፁት ሥልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል፡-

የፍታብሔር የዳኝነት ስልጣን፡-

1. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግምታቸው እስከ 500,000 (አምሰትመቶ ሺ) ብር የሆኑ ጉዳዮችን የማዳኘት ስልጣን አለው ።
2. የፌደራል መንግስቱ ተከራካሪ አካል በሆነበት ጉዳዮች
3. መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልሎች ውስጥ በሆኑ ነዋሪዎች መካከል ክርክር ሲነሳ
4. የፌደራል መንግስቱ ባለስልጣኖችና ሰራተኞች በስራቸው ወይም በሃላፊነታቸው ምክንያት ተጠያቂ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች
5. የውጭ ሀገር ዜጋ ተከራካሪ በሆነበት ጉዳይ
6. ዜግነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በሚነሱ ክርክሮች
7. በፌደራል መንግስት በተመዘገቡ ወይም በተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶችና ማህበሮችን በተመለከቱ ክርክሮች
8. በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ላይ በሚነሱ ክርክሮች
9. በኢንሹራንስ ውል ላይ በሚነሱ ክርክሮች
10. ተገዶ የመያዝ ህጋዊነትን ለማጣራት በሚቀርብ አቤቱታ
11. በአዲስአበባና በድሬደዋ ውስጥ በሚነሱ የፍታብሄር ጉዳዮች

በወንጀል የዳኝነት ስልጣን፡-

1. በፌደራል መንግስቱ የቀረጥና የግብር ገቢዎች በጠቅላላ የገንዘብ ጥቅሞች ላበሚፈጸም ወንጀል
2. የሀሰት ገንዘብን በሚመለከቱ ወንጀሎች
3. በፌደራል መንግስቱ ሰነዶች ላይ የሐሰት ሰራ በመስራት በሚፈጸሙ ወንጀሎች
4. ከአንድ ክልል በላይ ውይም በአለም አቀፍ ደረጃ አገልግሎት በሚሰጡ መገናኛዎች ፀጥታና ነጻነት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች
5. የውጭ ሀገር ዜጎችን የሚመለከቱ ወንጀሎች
6. በአዲስ አበባና በድሬደዋ ውስጥ በሚነሱ በስራ ላይ ባሉ ሌሎች ሕጎች ለአውራጃና ለወረዳ ፍርድ ቤቶች በተሰጡ በሌሎች የወንጀል ጉዳዮች

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.