በጋራ ገቢዎች ላይ ማብራሪያ ስለመስጠት ።Explaining common income.


በጋራ ገቢዎች ላይ ማብራሪያ ስለመስጠት ።
“””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””
የጋራ ገቢዎችን በተመለከተ ከምንሰጠው መረጃ በመነሳት የተለያዩ አስተያይቶች ሲሰጡ ተመልክተናል ። አንዳንዶቹ ደግሞ ከአስተያይት ተቆጥበው የፊዴሬሽን ም/ቤት የወሰነው የሚባለው የማከፋፈያ ቀመሩ ምንድን ነው የሚል ጥያቄ ያነሳሉ ። በመሆኑም የጋራ ገቢዎች የሚባሉት ምንድን ናቸው ? ማከፋፈያ ቀመሩ ምንድን ነው ? የሚሉትን መልስ መስጠትና ለህዝባችን ግልፅ ማድረግ ሃላፊነትና ግዴታችን በመሆኑ እንደሚከተለው ቀርቧል ። ጨርሰው አንብበው ይረዱ ለሌሎችም ያስረዱ ። በቀጣይ መታየት ያለበት ገንቢ አስተያየትም ካለ ለመቀበልና ለውሳኔ ሰጭ አካል ለማቅረብ ዝግጁ መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እፈልጋለሁ ።

የጋራ ገቢ ማለት ፦ በኢ.ፊ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 98 መሠረት የፌዴራል መንግስትና የክልል መስተዳድሮች በጋራ እንዲጥሉና እንዲሰበስቡ ስልጣን ከተሰጣባቸው (concurrent power of taxation) የታክስ/ግብር ምንጮች እንዲሁም በአንቀፅ 99 መሠረት የፌዴራሽን ምክር ቤትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጋራ በመሆን በ2/3 ድምፅ የጋራ የታክስ ስልጣን መሆኑን (concurrent power of taxation) ከሚለያዋቸውን የታክስ/ግብር ምንጮች በፌዴራል መንግስት ተሰብስቦ የሚተላለፍ የክልሎች መብት የሆነ ገቢ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን የጋራ ገቢ ማለት ፌዴራል መንግስት በህገ መንግስት አንቀፅ 62/7 መሠረት ለክልሎች የሚሰጥ ድጎማ አይደለም፡፡
በዚህም መሠረት የጋራ ገቢዎች የሚባሉት፡-

  1. የክልል መስተዳድሮችና የፌዴራል መንግስት በጋራ ከሚያቋቁሟቸው የልማት ድርጅቶች የሚሰበሰብ የንግድ ሥራ ገቢ ግብርና የሥራ ገቢ ግብር፤

1.1 የንግድ ሥራ ገቢ ግብር፡-
የንግድ ሥራ ገቢ ግብር ማለት በፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ 979/2008 አንቀፅ 3 መሠረት የንግድ ሥራ ላይ ከተሰማሩ ታክስ ከፋዮች የሚሰበሰብ ግብር/ታክስ ማለት ነው፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሠረት የንግድ ሥራ የሚባለው በተከታታይ ወይም ለአጭር ጊዜ ለትርፍ የሚከናወን ማንኛውም የኢንዱስትሪ፣ የንግድ፣ የሙያ ወይም ቮኬሽናል ሥራ ሲሆን ተቀጣሪ ለቀጣሪው የሚሠጠውን አግልግሎት ወይም ቤት ማከራየትን አይጨምርም፡፡ እንዲሁም በንግድ ሕግ መሠረት የንግድ ሥራ ነው ተብሎ እውቅና የተሰጠው ሌላ ማንኛውም ሥራ ወይም ህንፃ ማከራየትን ሳይጨምር የኩባንያው ዓላማ ምንም ቢሆን ማንኛውም የአክሲዮን ማህበር ወይም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚሠራው ማንኛውም ሥራ የንግድ ሥራ ይባላል፡፡

ስለሆነም የክልል መስተዳድሮችና የፌዴራል መንግስት በጋራ ከሚያቋቁሟቸው የልማት ድርጅቶች የሚሰበሰብ የንግድ ሥራ ገቢ ግብር የጋራ ገቢ ነው፡፡ ከአዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፊት የነበረው የ1989 ዓ.ም ቀመር መሠረት ክፍፍሉ የካፒታል መዋጮ ድርሻን መሰረት አድርጎ የነበረ ሲሆን አዲሱ ቀመር ግን 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ለክልል እንዲሆን ተደርጓል፡፡

1.2 የሥራ ግብር፡-
የሥራ ግብር ማለት ደግሞ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ላይ በፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ 979/2008 በአንቀፅ 11 ምጣኔዎች መሠረት የሚጣልና የሚሰበሰብ ግብር ነው፡፡ ስለሆነም የክልል መስተዳድሮችና የፌዴራል መንግስት በጋራ ከሚያቋቁሟቸው የልማት ድርጅቶች የሚሰበሰብ የሥራ ግብር የጋራ ገቢ ነው፡፡ ስለሆነም ክፍፍሉ ከአዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፊት የነበረው የ1989 ማከፋፈያ ቀመር መሠረት 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ለክልል ሲሆን በአዲሱ ቀመር ግን 100% ለክልል እንዲሆን ተደርጓል፡፡

1.3 የሽያጭ ታክስ (የተጨማሪ እሴት ታክስና ተርንኦቨር ታክስ)፡-
የሽያጭ ታክስ በተጨማሪ እሴት ታክስና በተርንኦቨር ታክስ የተተካ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ማለት በተጨማሪ ታክስ አዋጅ ቁ. 285/2002 እንዲሁም የተርኦቨር ታክስ ማለት ደግሞ በተርንኦቨር ታክስ አዋጅ ቁ. 308/2002 መሠረት ታክስ ከሚከፈልባቸው ግብይቶች የሚሰበሰቡ ታክሶች ናቸው፡፡ ስለሆነም የክልል መስተዳድሮችና የፌዴራል መንግስት በጋራ ከሚያቋቁሟቸው የልማት ድርጅቶች የሚሰበሰብ የሽያጭ ታክስ (የተጨማሪ እሴት ታክስና ተርንኦቨር ታክስ) ገቢ የጋራ ገቢ ነው፡፡ ከአዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፊት በነበረው የ1989 ዓ.ም ቀመር ክፍፍሉ 70% ለፌዴራል መንግስት 30% ለክልል ሲሆን በአዲሱ ቀመር ግን 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ደግም ለሁሉም ክልሎች የድጎማ ቀመርን መሠረት በማድረግ እንዲከፋፈል ተደርጓል፡፡

  1. ከግል ድርጅቶች ( ኩባንያዎች) የንግድ ሥራ ገቢ፣ ከባለ አክስዮኖች የትርፍ ድርሻ ገቢና የሽያጭ ታክስ ( የተጨማሪ እሴት ታክስና ተርንኦቨር ታክስ) የሚሰበሰብ ግብር/ታክስ፤

2.1 የንግድ ሥራ ገቢ ግብር፡-
የንግድ ሥራ ገቢ ግብር በተራ ቁጥር 01 የተሰጠውን ትርጉም የሚይዝ ሆኖ “ድርጅት” ማለት በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁ. 983/2008 አንቀፅ 05 መሠረት ኩባንያ፣ የሽርክና ማህበርና ሌሎች ሲሆን ከግል ድርጅቶች (ኩባንያዎች) የሚሰበሰብ የንግድ ትርፍ ግብር የጋራ ገቢ ነው፡፡ ከአዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፊት በነበረው የ1989 ዓ.ም ቀመር ክፍፍሉ 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ለክልል ሲሆን በአዲሱ ቀመር 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ገቢ ለመነጨበት ክልል ሆኖ ነገር ግን ድርጅቱ ከአንድ ክልል በላይ ሥራ ላይ ከተሰማራ 50%ቱ ገቢ ለመነጨባቸው ክልሎች ድርጅቱ በየክልሉ ለሠራተኞቹ ባወጣው ወጪ መሠረት እንዲሆን ተደርጓል፡፡

2.2 ከባለ አክስዮኖች የትርፍ ድርሻ ግብር፡-
በፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁ. 979/2008 አንቀፅ 55/1ና2/ መሠረት በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነና ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው በቋሚነት በሚሠራ ድርጅት የትርፍ ድርሻ ያገኘ ሰው በጠቅላላው የትርፍ ድርሻ ገቢ ላይ 10% የትርፍ ድርሻ የገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ ስለሆነም ከባለ አክስዮኖች የትርፍ ድርሻ ገቢ የሚሰበሰብ የትርፍ ድርሻ ገቢ ግብር የጋራ ገቢ ነው፡፡ ከአዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፊት በነበረው የ1989 ዓ.ም ቀመር ክፍፍሉ 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ለክልል ሲሆን በአዲሱ ቀመር 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ገቢ ለመነጨበት ክልል ሆኖ ነገር ግን ድርጅቱ ከአንድ ክልል በላይ ሥራ ላይ ከተሰማራ 50%ቱ ገቢ ለመነጨባቸው ክልሎች ድርጅቱ በየክልሉ ለሠራተኞቹ ባወጣው ወጪ መሠረት እንዲሆን ተደርጓል ፡፡

2.3 የሽያጭ ታክስ (የተጨማሪ እሴት ታክስና ተርንኦቨር ታክስ)፡-
የሽያጭ ታክስ በተጨማሪ እሴት ታክስና በተርንኦቨር ታክስ የተተካ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ማለት በተጨማሪ ታክስ አዋጅ ቁ. 285/2002 እንዲሁም የተርኦቨር ታክስ ማለት ደግሞ በተርንኦቨር ታክስ አዋጅ ቁ. 308/2002 መሠረት ታክስ ከሚከፈልባቸው ግብይቶች የሚሰበሰቡ ታክሶች ናቸው፡፡ ስለሆነም ከግል ድርጅቶች( ኩባንያዎች) የሽያጭ ታክስ (የተጨማሪ እሴት ታክስና ተርንኦቨር ታክስ) የሚሰበሰብ ገቢ የጋራ ገቢ ነው፡፡ ከአዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፊት በነበረው የ1989 ዓ.ም ቀመር ክፍፍሉ 70% ለፌዴራል መንግስት 30% ለክልል ሲሆን በአዲሱ ቀመር ግን 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ለሁሉም ክልሎች የድጎማ ቀመርን መሠረት በማድረግ እንዲከፋፈል ተደርጓል፡፡

  1. ከግል ድርጅቶች የሚሰበሰብ ኤክሳይዝ ታክስ፡-
    ከድርጅቶች የሚሰበሰብ ኤክሳይዝ ታክስ ማለት በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁ. 1186/2020 መሠረት የተጣለው ታክስ ነው፡፡ ይህን ታክስ በተመለከተ ቀድሞ በሕግ መንግስቱ አንቀፅ 98 ተለይቶ ካልተቀጡ የታክስና ግብር የመጣል ስልጣኖችን መካከል ስለነበር የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቁጥር 2-3/111/አ.21/12/1 በቀን 23/09/97 በፃፈው ደብዳቤ ሁለቱ (የፌዴሬሽንና የህዝብ ተወካዮች) ምክር ቤቶች በመስከረም 25/1996 ዓ/ም በጋራ ባደረጉ ስብሰባ የሕግ ሠውነት ተሰጥቷቸው ከተቋቋሙ የግል ድርጅቶች የሚሰበሰብ ኤክሳይዝ ታክስ ገቢ የጋራ ገቢ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ ከአዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፊት በነበረው የ1989 ዓ.ም ቀመር ክፍፍሉ ያልተወሰነ ሲሆን በአዲሱ ቀመር ግን 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ለሁሉም ክልሎች የድጎማ ቀመርን መሠረት በማድረግ እንዲከፋፈል ተደርጓል፡፡
  2. ከድርጅቶች የፈጠራ መብትን በማከራየት የሚገኝ የሮያልቲ፡
    ይህንም ታክስ በተመለከተ ቀድሞ በህግ,ገ-መንግስቱ አንቀፅ 98 ተለይቶ ካልተቀጡ የታክስና ግብር የመጣል ስልጣኖችን መካከል ስለነበር የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቁጥር 2-3/111/አ.21/12/1 በቀን 23/09/97 በፃፈው ደብዳቤ ሁለቱ (የፌዴሬሽንና የህዝብ ተወካዮች) ምክር ቤቶች በመስከረም 25/1996 ዓ/ም በጋራ ባደረጉ ስብሰባበተመሳሳይ መልኩ ከድርጅቶች የፈጠራ መብትን በማከራየት የሚገኝ የሮያልቲ ታክስ ገቢም የጋራ ገቢ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ ከአዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፊት በነበረው የ1989 ዓ.ም የሌለው ሲሆን በአዲሱ ቀመር 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ገቢ ለመነጨበት ክልል ሆኖ ነገር ግን ድርጅቱ ከአንድ ክልል በላይ ስራ ላይ ከተሰማራ 50%ቱ ገቢ ለመነጨባቸው ክልሎች ድርጅቱ በየክልሉ ለሠራተኞቹ ባወጣው ወጪ መሠረት እንዲሆን ተደርጓል፡፡
  3. ከፍተኛ የማዕድን፣ጋዝና ፔትሮሊየም ሥራዎች ከተሰማሩ ድርጅቶች የሚሰበሰብ የማዕድን ሥራ ገቢ ግብርና የሽያጭ ታክስ (የተጨማሪ እሴት ታክስና ተርንኦቨር ታክስ)

5.1 የማዕድን ሥራ ገቢ ግብር፡-
የማዕድን ሥራ ገቢ ግብር ማለት በማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅ መሠረት በከፍተኛ የማዕድን፣ ጋዝና ፔትሮሊየም ሥራዎች ላይ ከተሠማሩ ድርጅቶች የሚሰበሰብ ገቢ ነው፡፡ ከአዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፊት የነበረው የ1989 ዓ.ም ቀመር መሠረት ክፍፍሉ የካፒታል መዋጮ ድርሻን መሰረት አድርጎ የነበረ ሲሆን አዲሱ ቀመር ግን 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ለክልል እንዲሆን ተደርጓል፡፡

5.2 ከፍተኛ የማዕድን፣ጋዝና ፔትሮሊየም ሥራዎች ከተሰማሩ ድርጅቶች የሚሰበሰብ የሽያጭ ታክስ (የተጨማሪ እሴት ታክስና ተርንኦቨር ታክስ)፡-
የሽያጭ ታክስ በተጨማሪ እሴት ታክስና በተርንኦቨር ታክስ የተተካ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ማለት በተጨማሪ ታክስ አዋጅ ቁ. 285/2002 እንዲሁም የተርኦቨር ታክስ ማለት ደግሞ በተርንኦቨር ታክስ አዋጅ ቁ. 308/2002 መሠረት ታክስ ከሚከፈልባቸው ግብይቶች የሚሰበሰቡ ታክሶች ናቸው፡፡ ስለሆነም በከፍተኛ የማዕድን፣ጋዝና ፔትሮሊየም ሥራዎች ከተሰማሩ ድርጅቶች የሚሰበሰብ የሽያጭ ታክስ (የተጨማሪ እሴት ታክስና ተርንኦቨር ታክስ) የሚሰበሰብ ገቢ የጋራ ገቢ ነው፡፡ ከአዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፊት በነበረው የ1989 ዓ.ም ቀመር ክፍፍሉ 70% ለፌዴራል መንግስት 30% ለክልል ሲሆን በአዲሱ ቀመር ግን 50% ለፌዴራል መንግስት 50% ለሁሉም ክልሎች የድጎማ ቀመርን መሠረት በማድረግ እንዲከፋፈል ተደርጓል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ በተጠቀሰው አዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር ሥርዓት መሠረት ሚኒስቴር መ/ቤታችን በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከንግድ ትርፍና ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች ሥርዓቱን ለመተግበር በዘረጋው ሲስተም (Revenue Sharing System) መሠረት ብር 11,991,401,706.11 የጋራ ገቢ የክልሎች ድርሻ ማከፋፈል ችሏል፡፡ ይህ አፈፃፀም ከ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ለክልሎች ከተላለፈው የጋራ ገቢ ጋር ሲነፃፀር 8,681,102,030.61 ወይም 262% እድገት አለው፡፡

Explaining common income.
“” “” “” “” “” “” “” “” “” “” “” “” “” “” “” “” “” “
Based on the information we provide about common income, we have seen different opinions. Some have questioned whether the House of Federation has decided on a distribution formula. So what are common income? What is the distribution formula? It is our responsibility and responsibility to respond and make it clear to our people. Read it and explain it to others. I would like to take this opportunity to express our readiness to accept any constructive comments that may be considered and to make a decision.

Joint Revenue: According to Article 98 of the FDRE Constitution, the Federal Government and State Governments are jointly authorized to collect and collect taxes (concurrent power of taxation) and in accordance with Article 99, the House of Federation and the House of Peoples’ Representatives. 3 Votes is the revenue of the states collected by the federal government from the tax sources that distinguish the concurrent power of taxation. However, common income does not mean that the federal government subsidizes states under Article 62/7.
Accordingly, common income
Business income tax and labor income tax collected from state governments and public enterprises jointly established by the federal government;
1.1 Business Income Tax
Business income tax is a tax that is collected from business taxpayers in accordance with Article 3 of the Federal Income Tax Proclamation 979/2008. According to this provision, business is any industrial, commercial, vocational or vocational work that is carried out on a regular or short-term basis, and does not include services provided or rented by the employer. Any work performed by any corporation or limited liability company, regardless of the purpose of the company, is considered business, except for the lease of any other work or building that is recognized as a business under commercial law.

Therefore, the business income tax collected by the state governments and the public enterprises established by the federal government is a common income. According to the 1989 formula, which preceded the new common income distribution formula, the distribution was based on the share of capital contributions, while the new formula was 50% for the federal government and 50% for the state.

1.2 Employment Tax
Labor tax is a tax that is levied and collected in accordance with Article 11 of the Federal Income Tax Proclamation 979/2008. Therefore, labor tax collected from state governments and joint ventures by the federal government is a common income. Accordingly, the division was 50% for the federal government, 50% for the state, and 100% for the state, according to the 1989 distribution formula, which preceded the new common income distribution formula.

1.3 Sales Tax (VAT and Turnover Tax) ፡
VAT is replaced by VAT and Turnover Tax. VAT means VAT Proclamation no. 285/2002 and Turnover Tax also means the Turnover Tax Proclamation no. 308/2002 are taxes levied on taxable transactions. Therefore, sales tax (VAT and Turnover Tax) collected from state governments and joint ventures by the federal government is a common income. Prior to the 1989 formula, the distribution was 70% to the federal government, 30% to the state, and 50% to the federal government, and 50% to the federal government, according to the subsidy formula for all states.

Taxes collected from business enterprises, shareholders’ profits and sales tax (VAT and Turnover Tax);
2.1 Business Income Tax
Business Income Tax shall be defined as No. 01, “Enterprise” in the Federal Tax Administration Proclamation no. According to Article 05 of 983/2008, a company, a partnership, etc., is a joint venture tax collected from private companies. According to the 1989 formula before the new common income distribution formula, 50% is for the federal government, 50% for the state, and 50% for the federal government, 50% for the state, but if the enterprise operates in more than one region, 50% of the state is in the region. It is based on the cost to the staff.

2.2 Tax Shares from Shareholders
Federal Income Tax Proclamation no. Pursuant to Articles 55 (1 and 2) of 979/2008, a person who is a resident of Ethiopia and who is not a resident of Ethiopia is liable to pay 10% dividend tax on his gross income. Therefore, the dividend income tax collected from shareholders is a common income. According to the 1989 formula before the new common income distribution formula, 50% is for the federal government, 50% for the state, and 50% for the federal government, 50% for the state, but if the enterprise operates in more than one region, 50% of the state is in the region. It is based on the cost to the staff.

2.3 Sales Tax (VAT and Turnover Tax) ፡
VAT is replaced by VAT and Turnover Tax. VAT means VAT Proclamation no. 285/2002 and Turnover Tax also means the Turnover Tax Proclamation no. 308/2002 are taxes levied on taxable transactions. Therefore, sales tax (value added tax and turnover tax) from private companies is a common income. In the 1989 formula, before the new common income distribution formula, 70% was distributed to the federal government, 30% to the state, and 50% to the federal government, and 50% to the federal government.

Excise tax collected from private companies
Excise tax collected from corporations is the excise tax proclamation no. 1186/2020 is the basis of the tax. In this letter, the House of Federation of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (FDRE) No. 2-3 / 111 / A21 / 12/1 dated 23/09/97 (the House of Representatives and the House of Peoples’ Representatives) dated 23/09/97, as it was one of the powers not subject to Article 98 of the Constitution. At a joint meeting on September 25, 2006, it was decided that the excise tax collected from legal entities should be a common income. The distribution was not limited to the 1989 formula, which preceded the new common income distribution formula, but in the new formula, 50% was distributed to the federal government and 50% to all states based on the subsidy formula.
Royalty Receipt from Leasing Creativity
In this regard, the House of Federation of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (FDRE) No. 2-3 / 111 / A21 / 12/1 dated 23/09/97 (the House of Representatives and the House of Peoples’ Representatives on 23/09/97) was among the powers that are not specified in Article 98 of the Constitution. In a joint meeting of the councils on September 25, 1996, it was also decided that the royalty tax on leasing patents from corporations should be shared. It did not exist in 1989, which preceded the new common income distribution formula. In the new formula, 50% of the revenue was generated by the federal government, but if the enterprise operates in more than one region, 50% of the revenue is allocated to the regions.
Mining Income Tax and Sales Tax (VAT and Turnover Tax) collected from large mining, gas and petroleum companies
5.1 Mining Income Tax
Mining Income Tax is a tax collected from companies engaged in major mining, gas and petroleum activities in accordance with the Mining Income Tax Proclamation. According to the 1989 formula, which preceded the new common income distribution formula, the distribution was based on the share of capital contributions, while the new formula was 50% for the federal government and 50% for the state.

5.2 Sales tax (VAT and Turnover Tax) collected from companies engaged in heavy mining, gas and petroleum operations
VAT is replaced by VAT and Turnover Tax. VAT means VAT Proclamation no. 285/2002 and Turnover Tax also means the Turnover Tax Proclamation no. 308/2002 are taxes levied on taxable transactions. Therefore, sales tax (value added tax and turnover tax) collected from large mining, gas and petroleum companies is a common income. In the 1989 formula, before the new common income distribution formula, 70% was distributed to the federal government, 30% to the state, and 50% to the federal government, and 50% to the federal government.

In general, according to the new common revenue distribution formula mentioned above, our Ministry has been able to distribute Birr 11,991,401,706.11 in the first half of the budget year under the Revenue Sharing System. This performance has increased by 8,681,102,030.61 or 262% compared to the same period in 2012/13.

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.