

Guarantee Criminal Case
Anyone can suspect a crime. People arrested on suspicion of a crime have the right to bail provided for under international law and our constitution (FDRE cons 17 (2)). The right to bail is a guarantee that people arrested on suspicion of a crime will be released from detention without being detained for a period of time (warranty | Wex | US Law | LII / Legal InformationInstitute).
– Provided by the school
1st: Guarantee by the police (Article 28 of the Penal Code)
-If you are suspected of a crime punishable by up to 3 years in prison
-If you do not have enough information to suspect that you have committed a crime or that you have committed a crime, you will be signed by the Investigating Police or a bail bond will be set.
2nd: Court Guarantee (Article 63)
– The offense carries a maximum penalty of 15 years’ imprisonment
– This guarantee is only granted if the person injured by the crime does not die.
Not only this, with regard to Article 69 (2) (a) of the Penal Code, the courts must consider the possibility of granting bail.
If the suspect is released, it will not cause problems in gathering evidence (if it does not persuade witnesses)
If I comply with the obligation
If not a threat to public order
If you do not commit another crime
If not a recurring criminal
If the suspect’s address is not far away or out of the country, I may be granted bail.
The bail application can be filed with any court in accordance with Article 64. Although the amount of bail is determined by the court, the court will take into account the severity of the crime, the appointment, the amount of property and the duration of the bail.
Failure to comply with warranty obligation
If the defendant does not appear on the appointment, bail will be paid to the government and the missing defendant will be forced to appear at the police station. He will then be kept in custody until a decision is made (Article 73 (23)).
።።።።።።።// የዋስትና በወንጀል ጉዳይ //።።።።።።።።
ማንኛውም ሰው በወንጀል ልጠረጠር ይችላል። በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች ደግሞ በአለማቀፍ ህግና በህገመንግስታችን የተደነገገ የዋስትና መብት አለው(FDRE cons 17(2))። የዋስትና መብት ማለት ደግሞ በወንጀል ተጠርጥሮ የተያዙ ሰዎች ለጊዜ ተለቀው ሳይታሰሩ ጉዳያቸውን ከውጭ ሆነው እንድከታተሉና በተፈለጉበት ሰዓት ለመገኘት የምሰጠው ማረጋገጫ ነው(warranty | Wex | US Law | LII / Legal InformationInstitute)።
ዋስትና ደግሞ በሁለት መንገድ ይሰጣል
-በፖሊስ የሚሰጥና
-በፍ/ቤት የሚሰጥ
1ኛ፦በፖሊስ የሚሰጥ ዋስትና (የወ/ሥ/ሥ/ሕ/አንቀፅ 28)
-እስከ 3አመት ቀላል እስራት የምያስቀጣ ወንጀል የተጠረጠሬ ከሆነ
-ወንጀሉ ስለመሠራቱ አጠራጣሪ ሁነታ ስገጥም ወይም ወንጀል ሰርቷል የምያስብል በቂ መረጃ ስታጣ በመርማሪ ፖልስ አስፈርሞ ወይም የገንዘብ ዋስ የምሆን ዋስትና ወረቀት በማስፈረም የምቀርብበትን ቀን ወስኖ ይለቃል።
2ኛ፦በፍ/ቤት የምሰጥ ዋስትና (የወ/ሥ/ሥ/ሕ/አንቀፅ 63
-ወንጀሉ ከ15አመት በታች ጽኑ እስራት የምያስቀጣ ስሆንና
-በወንጀል የተጎዳ ሰው የማይሞት ከሆነ ነው ይህ ዋስትና የሚፈቀደው።
ይህ ብቻ አይደለም የወ/ሥ/ሥ/ሕ/አንቀፅ 69(2(ሀ-መ) እንደተደነገገው ፍ/ቤቶች ዋስትና ለመፍቀድ ማገናዘብ ያለባቸው ነገሮች ውስጥ
ተጠርጣሪ ከተለቀቀ በማስረጃ አሰባሰብ ላይ ችግር የማይፈጥር ከሆነ(ሚስክሮችን የማያባብል ከሆነ)
ግዴታውን አክብሮ የምቀርብ ከሆነ
ለህዝብ ጸጥታ አስግ ካልሆነ
ሌላ ወንጀል የማይፈጽሙ ከሆነ
ተደጋጋሚ ወንጀለኛ ካልሆነ
የተጠርጣሪ አድራሻ ሩቅ ካልሆነ ወይም ከሀገር የማይወጣ ከሆነ የዋስትና መብት ልከበርለት ይችላል ።
የዋስትናውን አቤቱታ በ64 መሠረት ለማንኛውም ፍ/ቤት ማቅረብ ወይም ማመልከት ይቻላል።የዋስትና መያዣ መጠን በፍ/ቤት የምወሰን ብሆንም የወንጀሉ ከባድነት ፣ ቀጠሮ አክባሪነት ፣የሀብት መጠኑ እና የዋስትና ቆይታ ጊዜ ፍ/ቤቱ ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባል ።
የዋስትና ግደታ ያለማክበር
ተከሳሽ በቀጠሮ ቀን ካልቀረበ የዋስትና ገንዘብ ለመንግስት ገብ ይደረግና ያልቀረበ ተከሳሽ በፖሊስ ተገዶ እንድቀርብ ይደረጋል ። ከዚያም ለላ ከባድ ዋስትና ይገባል ካልሆነ ውሳኔ እስክአገኝ ድረስ ማረፍያ ቤት ይቆያል (የወ/ሥ/ሥ/ሕ/አንቀፅ 73(23¾)።