
1954 It is a comparison of our legal provisions with the Criminal Procedure Code and the proposed Code of Criminal Procedure.
Under our current Criminal Procedure Code Rule 63, a person loses his right to bail if he has been charged with a crime punishable by more than 15 years and the injured person is expected to die or die. Although there is no consensus among legal experts on the interpretation of the article, the interpretation that many legal scholars agree on and that is in line with human rights provisions is that the law deprives a person of the right to bail only when two conditions are met.
If one person is killed or injured, the person is expected to die tomorrow, and the other is sentenced to more than 15 years in prison if the person is charged or suspected of a crime. In addition, other proclamations stipulate that a person suspected of terrorism or corruption for more than a decade is not entitled to bail.
Under Section 154 (3) of the Criminal Procedure Code, however, a person suspected of a crime punishable by life imprisonment or death (whether or not the person died as a result of the crime) is denied bail. Also, a person suspected of corruption under Article 154 (2) shall not be released on bail if the type of offense is punishable by more than ten years or if he is convicted of multiple corruption offenses and the sentence may be more than ten years. In addition, under Article 154 (1) of the same law, crimes against the Constitution and the constitutional order, crimes against the State Security and Defense Forces, terrorism, human trafficking, and rape of women and children are denied bail. ፡ Searching
Now, in the 1954 draft. The big difference between the law is that under current law, a person does not lose his or her right to bail unless he or she has committed suicide or the victim has died and the alleged crime (homicide) is punishable by more than 15 years. In other words, under current law, a defendant could not be sentenced to life imprisonment and up to 15 years in prison unless convicted of murder. This means that if the courts think that the person will be acquitted or found guilty of murder, they will be granted bail, even if the crime is not related to murder. In contrast, under the current Criminal Procedure Code, if a person is charged with a crime punishable by life imprisonment or death, the right to bail is prohibited. On the one hand, under current law, defendants who have been charged with aggravated manslaughter and are not liable to life imprisonment or death penalty for a crime punishable by up to 20 years will be released on bail when the draft law is enacted. On the other hand, under the current law, people who have been released on bail for crimes related to human life but not for life or death will be denied bail when the bill is passed by parliament.
According to the author, the draft law has two unfair consequences.
First of all, why should a person be denied bail because he is suspected or charged with a crime punishable by life imprisonment or death?
50 years ago, our law concluded that even if a person is charged with a crime punishable by life imprisonment, his right to bail should not be denied except by the decision of a judge and a conscientious objection, how can the rights of these people be promoted when the world is civilized and our country recognizes international human rights? Are we going backwards? The reason for the release of a suspect on bail is Article 20 (3) of our Constitution, which states that a person has the right to be presumed innocent until proven guilty and convicted in a court of law, in accordance with international human rights law and conventions. That is to say. In particular, the accused has the constitutional and human right to be released on bail so that he or she can be returned to his or her home and not be harmed. He should also have the right to stand on his own two feet to defend himself so that he does not become a victim. The right to bail should not be denied as much as possible, since even if the person has done something wrong, the only way to present his case and give a fair trial is if the person has collected the evidence on bail. There is no compelling and valid reason for the legislature to relinquish the power to release suspects on bail in cases of life and death. Constitutional human rights should not be restricted unless there is a good reason and no alternative. In fact, when restricted, the restrictions should be as small and reasonable as possible. Instead, instead of denying the accused the right to bail in Article 156, the bill introduces new and innovative ideas to prevent the defendant from posting bail, moving away from a place or participating in certain places in accordance with the provisions of Articles 134 to 156 of the Criminal Code. While judges can use these practices, instead of leaving the jurisdiction to the courts to determine the rights of people convicted of crimes punishable by life imprisonment, it is unfair to deny the rights of the Proclamation and not to use other alternatives. Recognizing that the defendant is likely to be acquitted, the judges in each case will be able to decide (revoke the bail), but the revocation of the judges’ power and the general revocation of the bail will not be appropriate unless it is absolutely necessary and optional. Our courts have many problems, but we need to trust them. In this regard, both the Anti-Terrorism Proclamation and the Anti-Corruption Proclamation need to be re-examined. Crimes against the constitutional order, defense, and security were also reported in 1954. According to the current and current law, unless the loss of life is a criminal offense, but in the draft law, the loss of life of the suspects is not a matter of enrichment of the law, but a matter of justice.
According to the author, this is not the end of the draft law. According to the draft law, those charged with aggravated homicide (excluding extrajudicial killings) will be released on bail even if the victim dies. In 1954, which is currently under construction. Under the Penal Code, however, a person charged with murder is not released on bail. It is extremely difficult in our country to be released on bail, even if the suspect is innocent, even if the suspect is innocent, even if he or she is innocent enough to kill us because of negligence or incapacity, or because of a deliberate murder and bloodshed. If the killer disappears after being released on bail, the moral damage to the family and the community will be severely curtailed. In addition to the traditional law and practice of bloodshed and self-inflicted revenge in many areas, the fact that he himself is a suspect and has disappeared will lead his innocent family to revenge and endless bloodshed. Therefore, according to the author, allowing people who are suspected of killing a person with serious negligence (punishable by up to 15 years in prison) or murder (as a result of a bloodbath) may be more dangerous and harmful to society.
Restricting the right to bail of people suspected of murder and aggravated murder by law is proportional and constitutional, as it protects the suspects themselves from retaliation and protects the community from bloodshed.
In conclusion, our draft Criminal Procedure Code, 1954, is currently in force. People who have been charged with aggravated or aggravated murder or genocide and other similar war crimes should be deprived of their bail only if the victim is expected to die or die. Apart from this, the guarantee should not be revoked only for crimes that have resulted in loss of life or death and are punishable by more than 16 years, but should not be enacted by a proclamation that guarantees the right to bail for those charged with backwardness and life imprisonment, but not for murder. .
በ1954 ዓ.ም. በወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ሕጋችንና በመረቀቅ ላይ ባለው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ መካከል ዋስትና በሕግ የሚከለከልበትን ሁኔታ ማነፃፀርና የመፍትሔ አስተያየት መሰንዘር ነው፡፡
አሁን ሥራ ላይ ባለው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ሕጋችን ቁጥር 63 መሠረት አንድ ሰው በዋስትና የመለቀቅ መብቱን የሚያጣው ከ15 ዓመት በላይ በሚያስቀጣ ወንጀል የተከሰሰ እንደሆነና በወንጀሉ ጉዳት የደረሰበት ሰው የሞተ ወይም ይሞታል ተብሎ የሚጠበቅ እንደሆነ ነው፡፡ ምንም እንኳን በሕግ ባለሙያዎች መካከል ስለአንቀጹ አተረጓጎም ስምምነት ባይኖርም በርካታ የሕግ ምሁራን የሚቀበሉትና ከሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ጋር የሚጣጣመው አተረጓጎም አንድ ሰው በዋስ የመለቀቅ መብቱን ሕግ የሚነፍገው ሁለት ነገር ሲሟላ ብቻ ነው፡፡
አንደኛው ሰው ከገደለ ወይም ጉዳት ያደረሰበት ሰው ከዛሬ ነገ ይሞታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሰውዬው የተከሰሰበት ወይም የተጠረጠረበት የወንጀል ዓይነት ከ15 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ በሽብርተኝነት ወይም ከአሥር ዓመት በላይ በሚያስቀጣ ሙስና ወንጀል የተጠረጠረ ሰው የዋስ መብቱ እንደማይጠበቅለት በሌሎች አዋጆች ተደንግጓል፡፡
እየተረቀቀ ባለው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 154 (3) መሠረት ግን በዕድሜ ልክ ወይም በሞት በሚያስቀጣ ወንጀል የተጠረጠረ ሰው (በወንጀሉ የተነሳ ሰው ሞተም አልሞተም) በዋስትና የመለቀቅ መብቱን በሕግ ተከልክሏል፡፡ እንዲሁም በዚሁ ድንጋጌ ቁጥር 154 (2) መሠረት በሙስና ወንጀል የተጠረጠረ ሰው የወንጀሉ ዓይነት ከአሥር ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ ወይም በተደራራቢ የሙስና ወንጀሎች ተከሶ ቅጣቱ ተደማምሮ ከአሥር ዓመት በላይ ሊበልጥ የሚችል ከሆነ በዋስትና መለቀቅ አይችልም፡፡ በተጨማሪም በዚሁ በረቂቁ ሕግ ቁጥር 154 (1) መሠረት በሕገ መንግሥቱና በሕገ መንግሥታዊው ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ በመንግሥት የውጭ ደኅንነትና መከላከያ ኃይል ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ የሽብርተኝነት ወንጀል፣ የሕገወጥ የሰው ዝውውር ወንጀል፣ በሴቶችና በሕፃናት ላይ በሚፈጸም አስገድዶ የመድፈር ወንጀል የተጠረጠረ ሰው በዋስትና የመለቀቅ መብቱን ተነፍጓል፡፡
እንግዲህ በረቂቁና ሥራ ላይ ባለው የ1954 ዓ.ም. ሕግ መካከል ትልቁ ልዩነት አሁን ሥራ ላይ ባለው ሕግ መሠረት አንድ ሰው (የፀረ ሙስናና የፀረ ሽብር አዋጆች እንደተጠበቁ ሆኖ) ነፍስ ካላጠፋ ወይም ተጎጂው የሚሞት ካልሆነና የተጠረጠረበትም ወንጀል (የነፍስ ግድያ ዓይነት) ከ15 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር በሕግ በዋስትና የመለቀቅ መብቱን አያጣም፡፡ በሌላ አባባል አሁን በሚሠራበት ሕግ መሠረት አንድ ተከሳሽ የሰው ነፍስ ካላጠፋ በስተቀር የተጠረጠረበት ወንጀል 15 ዓመት ቀርቶ በዕድሜ ልክና በሞት ሊያስቀጣ ቢችልም እንኳን በዋስትና የመለቀቅ መብቱ በአዋጅ አልተገፈፈም፡፡ ይህ ማለት ግን ፍርድ ቤቶች ሰውየው ቢለቀቅ የሚጠፋ ከመሰላቸው ወይም ማስረጃ የሚያጠፋ ሆኖ ካገኙት ወንጀሉ ከነፍስ ግድያ ጋር ባይያያዝም ዋስትና የመንፈግ ሥልጣን የተሰጣቸው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ነው፡፡ በአንፃሩ ግን እየተረቀቀ ባለው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት ግን ቁም ነገሩ የሰው ነፍስ መጥፋት አለመጥፋት መሆኑ ቀርቶ አንድ ሰው በዕድሜ ልክ ወይም በሞት በሚያስቀጣ ወንጀል ከተከሰሰ በዋስ የመለቀቅ መብቱ በሕግ ሊከለከል ነው፡፡ በአንድ በኩል አሁን ባለው ሕግ መሠረት በዋስ ሊለቀቁ የማይችሉ በዕድሜ ልክና በሞት ሳይሆን በ20 ዓመት ብቻ በሚያስቀጣ የተራ ነፍስ ግድያ ወንጀል የተከሰሱና ጉዳት ያደረሱበት ሰው የሞተ (ይሞታል ተብሎ የሚጠበቅ) ተከሳሾች ረቂቁ ሕግ አዋጅ ሆኖ በሚወጣበት ጊዜ በዋስ ሊለቀቁ ነው፡፡ በሌላ በኩል አሁን ባለው ሕግ መሠረት በዋስ ሊለቀቁ የሚችሉ ከሰው ሕይወት ጋር በማይያያዝ ነገር ግን እስከ ዕድሜ ልክ ወይም ሞት በሚደርስ በሚያስቀጡ ወንጀሎች የተከሰሱ ሰዎች ረቂቁ ሕግ በፓርላማ በሚፀድቅበት ጊዜ የዋስ መብታቸው ሊነፈግ ነው፡፡
እንደ ጽሑፍ አቅራቢው እምነት ከሆነ ረቂቅ ሕጉ ኢፍትሐዊ የሆኑ ሁለት ውጤቶችን ያስከትላል፡፡
በመጀመርያ አንድ ሰው እስከ ዕድሜ ልክ ወይም ሞት ድረስ በሚያስቀጣ ወንጀል ስለተጠረጠረ ወይም ስለተከሰሰ ብቻ ለምን በዋስ ወጥቶ የመከራከር መብቱን ይነፈጋል?
ከዛሬ 50 ዓመት በፊት የወጣው ሕጋችን አንድ ሰው እስከ ዕድሜ ልክና ሞትም ድረስ በሚያስቀጣ ወንጀል ቢከሰስም እንኳን በዳኞች ውሳኔና የህሊና ፍርድ ካልሆነ በስተቀር በዋስትና የመለቀቅ መብቱን በአዋጅ ሊነፈግ አይገባም የሚል አቋም ይዞ ሲያበቃ፣ አሁን ዓለም በሠለጠነችበትና አገራችንም ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶችን ባፀደቀችበት ወቅት እንዴት የእነኝህን ሰዎች መብት በአዋጅ በመግፈፍ ወደ ኋላ እንጓዛለን? በወንጀል የተጠረጠረ ሰው በዋስ እንዲለቀቅ የሚፈቀድለት ምክንያት በሕገ መንግሥታችን አንቀጽ 20 (3) ላይ አንድ ሰው በወንጀል ተከሶ፣ ጥፋተኝነቱ በማስረጃ ተረጋግጦ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ነው ተብሎ ካልተወሰነበት በስተቀር ንጹሕ ሆኖ የመገመት (እንደጥፋተኛ ያለመቆጠር) መብት አለው የሚለውንና በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችና ስምምነቶች ተቀባይነት ያለውን መርህ ለመተግባር ሲባል ነው፡፡ በተለይም የተከሰሰው ሰው በእስር ሆኖ ጉዳዩ ሲታይ ቆይቶ በኋላ ንፁህ መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ሊመለስና ሊተካ የማይችል ጉዳት እንዳይደርስበት ሲባል በዋስ የመለቀቅ ሕገ መንግሥታዊና ሰብዓዊ መብት አለው፡፡ እንዲሁም በሥሩ የሚረዳቸው ወይም የሚያግዛቸው ሰዎች ካሉ ከራሱ አልፎ እነሱም ተጎጂ እንዳይሆኑ ሲባል በዋስ ወጥቶ የመከራከር መብቱ ሊከበርለት ይገባል፡፡ ሌላው ቀርቶ ሰውዬው በተወሰነ ደረጃ በትክክል ያጠፋም እንኳን ቢሆን በእሱ በኩል ያለውን ማስረጃ በትክክል ለማቅረብና በእውነት ላይ የተመረኮዘ ፍርድ ለመስጠት የሚቻለው ሰውዬው በዋስ ሆኖ እንደልቡ ማስረጃዎቹን አሰባስቦ የተከራከረ እንደሆነ ብቻ ስለሆነ የዋስትና መብት በተቻለ መጠን ፈጽሞ በአዋጅ ሊከለከል አይገባም፡፡ ሕግ አውጪው እስከ ዕድሜ ልክና በሞት ሊያስቀጣ በሚችል ጉዳይ የተጠረጠሩ ሰዎችን በዋስ የመልቀቅና ያመልቀቅ ሥልጣንን ከዳኞች ላይ ቀምቶ የሁሉንም ተጠርጣሪዎች መብት በአዋጅ የሚገፍበትና በፊት የነበረውን ሕግ የሚያጠብቅበት አጥጋቢና ተቀባይነት ያለው ምክንያት የለውም፡፡ ሕገ መንግሥታዊ ሰብዓዊ መብቶች አጥጋቢና በቂ ምክንያት ከሌለና አማራጭ ካልታጣ በስተቀር ሊገደቡ አይገባም፡፡ ያውም ሲገደቡ በተቻለ መጠን የመብት ክልከላው አነስተኛና ተመጣጣኝ መሆን አለበት፡፡ ይልቁንም ረቂቅ ሕጉ በቁጥር 156 ላይ በወንጀል የተከሰሰን ሰው ዋስትና መብት ከመንፈግ ይልቅ ተከሳሹ ከወንጀል ሕግ ቁጥር 134 እስከ 156 በተደነገገው መሠረት ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ላለመፈጸም የእጅ ጠብቅ ዋስ እንዲያቀርብ፣ ከአንድ ቦታ ርቆ እንዳይሄድ ወይም ወደ አንዳንድ ቦታዎች ድርሽ እንዳይል መከልከል የሚቻልበትን ለአገራችን አዲስና የመጠቁ ሐሳቦችን ይዞና አስተዋውቆ እያለና ዳኞች እነኝህን አሠራሮችን መጠቀም ሲችሉ፣ በደፈናው እስከ ዕድሜ ልክና ሞት ድረስ በሚያስቀጣ ወንጀል የተከሰሱ ሰዎችን የዋስትና መብት በዳኞች እንዲወሰን ሥልጣኑን ለፍርድ ቤቶች ከመተው ይልቅ መብቱን በአዋጁ መግፈፉ ተመጣጣኝ ካለመሆኑም በላይ ሌሎች አማራቾችን ለመጠቀም አለመሞከሩን የሚያሳይ ነው፡፡ ተከሳሹ ይጠፋል ተብሎ የሚገመትበት ሁኔታ ካለ በእያንዳንዱ ጉዳይ የሚቀመጡት ዳኞች አመዛዝነው መወሰን (ዋስትናውን መንፈግ) እንደሚችሉ እየታወቀ፣ የዳኞችን ሥልጣን ቀምቶ በሕግ በጅምላ ዋስትና የመንፈግ አሠራር በእርግጥም አስፈላጊ ካልሆነና አማራጭ ካልጠፋ በስተቀር አግባብነት አይኖረውም፡፡ ፍርድ ቤቶቻችን ብዙ ችግር ቢኖርባቸውም አመኔታ ልንጥልባቸው ይገባል፡፡ ከዚህ አኳያ የፀረ ሽብር አዋጁም ሆነ የፀረ ሙስና አዋጆች እንደገና ሊፈተሹ ይገባል፡፡ እንዲሁም በሕገ መንግሥታዊው ሥርዓት፣ በመንግሥት መከላከያና ደኅንነት ላይ የሚፈጸሙትም ወንጀሎች ቢሆኑ በ1954 ዓ.ም. በወጣውና አሁን ሥራ ላይ ባለው ሕግ መሠረት የሰው ሕይወት ካልጠፋ በስተቀር በሕግ ዋስትና የማያስከለክሉ ወንጀሎች ሆነው እያሉ፣ በረቂቅ ሕጉ ግን የሰው ሕይወት ጠፋም አልጠፋም የተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት በጅምላ መገፈፉ ሕጉን የሚያበለጽገው ሳይሆን ፍትሐዊነቱን የኋሊት የሚያስኬደው ነው፡፡
በጽሑፍ አቅራቢው እምነት የረቂቁ ሕግ ችግር በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ በረቂቁ ሕግ መሠረት ከከባድ ግድያ (በቀድሞ ሕግ ከግፍ አገዳደል ውጪ) በተራ ነፍስ ማጥፋት ግድያ የተከሰሱ ሰዎች ተጎጂው ቢሞትም እንኳን በዋስ ሊለቀቁ ነው፡፡ አሁን እየተሠራበት ባለው በ1954 ዓ.ም. የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት መሠረት ግን በተራ ነፍስ ግድያ የተከሰሰ ሰው በዋስትና አይለቀቅም፡፡ ክቡር የሆነ የሰው ልጅ ሕይወት በቸልተኝነት ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት፣ ወይም በደም ፍላት ሳይሆን ሆነ ተብሎ በተፈፀመ ግድያ በተቀጠፈበትና ደም በፈሰሰበት ሁኔታ ገድሏል ተብሎ በበቂ ሁኔታ የተጠረጠረን ሰው ምንም እንኳን ተጠርጣሪው ንፁህ ቢሆንም በዋስ መልቀቅ ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር እጅግ በጣም ይከብዳል፡፡ ገዳዩ በዋስ ከተለቀቀ በኋላ የተሰወረ እንደሆነ በሟች ቤተሰቦችና በኅብረተሰቡ ላይ የሚደርሰው የሞራል ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡ በዚያ ላይ በብዙ አካባቢዎች ከዳበረው የደም መቃባትና ፍትሕን በራስ እጅ አስገብቶ ከመበቀል ባህላዊ ሕግና አሠራር አንፃር፣ ራሱ በዋስ የተለቀቀውን ተጠርጣሪና የተሰወረም እንደሆነ ንፁሃን ቤተሰቦቹን ለብቀላና ማለቂያ ለሌለው የደም መቃባት የሚዳርጋቸው ነው፡፡ ስለዚህ እንደ ጽሑፍ አቅራቢው እምነት ምናልባት በከባድ ቸልተኝነት ሰው በመግደል (እስከ 15 ዓመት በሚያስቀጣው) ወይም በደም ፍላት (በአልሞት ባይ ተጋዳይነት) ሰው በመግደል የተጠረጠሩ ሰዎች በዋስ ሊለቀቁ ከሚችሉ በስተቀር በተራ ነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ ሰዎችን በዋስ እንዲለቀቁ መፍቀድ የከፋ አደጋና ጉዳት በኅብረተሰቡ ላይ ያስከትላል፡፡
በተራ ነፍስ ግድያና በከባድ ነፍስ ግድያ በሚገባ የተጠረጠሩ ሰዎችን በዋስ የመለቀቅ መብቱን በሕግ መገደብ ራሳቸው ተጠርጣሪዎቹን ከበቀል የሚታደግና ኅብረተሰቡንም ከደም መቃባት የሚጠበቅ በመሆኑ ተመጣጣኝነት ያለውና ሕገ መንግሥታዊ ነው፡፡
ሲጠቃለል ረቂቅ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጋችን አሁን እየተሠራበት ያለውን የ1954 ዓ.ም. ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ፈለግ በመከተልና እሱንም ትንሽ በማሻሻል በተራ ወይም በከባድ የነፍስ ግድያ ወይም በዘር ማጥፋትና በሌሎች ተመሳሳይ የጦር ወንጀለኝነት ብቻ የተከሰሱ ሰዎችን ያውም ተጎጂው የሞተ ወይም ይሞታል ተብሎ የሚጠበቅ ከሆነ ብቻ የዋስትና መብታቸው በሕግ ሊነፈግ ይገባል፡፡ ከዚህ ውጪ የሰው ሕይወት በጠፋባቸው ወይም ተጎጂው ይሞታል ተብሎ በሚጠበቅባቸውና ከ16 ዓመት በላይ በሚያስቀጡ ወንጀሎች ብቻ ዋስትና በሕግ ሊነፈግ ይገባል እንጂ ሕጉ የኋሊት ተጉዞ እስከ ዕድሜ ልክና ሞት ሊያስቀጣ በሚችልና ነገር ግን ከነፍሱ ግድያ ጋር ግንኙነት በሌለው ወንጀል የተከሰሱ ሰዎችን የዋስትና መብት ሁሉ በጅምላ (በደምሰሳው) በአዋጅ ሊገፍ አይገባም፡፡


You must be logged in to post a comment.