
From the day Prime Minister Abiy Ahmed came to power, the slogan, politics or patriotism that Ethiopia has been saying will not fall apart? Who said Ethiopia will be destroyed or Ethiopia will be destroyed? Why did Prime Minister Abiy Ahmed, with his tribute to Isaias Afewerki, repeatedly use slogans unless he himself had the intention of destroying Ethiopia? Apart from Eritrean President Isaias Afewerki, who wants Ethiopia to fall apart? In the absence of a party that wants to overthrow it, Prime Minister Abiy Ahmed. Why do they always shout “Ethiopia will not fall apart”? The Prime Minister says Ethiopia will not fall apart. It is not a scientific political analysis, but a mediation that tells us that Ethiopia will not fall apart like any other country because God protects it. Once the egg yolk is shed, it is useless. God, who created in His image and sacrificed His only begotten Son, killed innocent people who raped women with their soldiers and massacred innocent people, and killed innocent people on TV and radio. They are pretending to be believers and trying to deceive people. The fact that Ethiopia did not fall under the Italian invasion does not mean that Ethiopia will not fall apart. The slogan “Ethiopia will not fall” is determined by the hammer of the destroyer. There is no reason why Ethiopia should not fall apart, as the current negative and unhappy government is a corrupt government and a group of very fast-moving genocides. Ethiopia will collapse like any other country. This means that it cannot continue to be a country until it is in the hands of a murderous and murderous government. ጠ/ም አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ቀን ጀምሮ ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ የሚያሰሙን መፈክር፣ ፖለትካ ወይስ ሀገር ወዳድነት? ማንስ ኢትዮጵያ ትፍረስ ወይም ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ብሎ ተናገረ? ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከግብራቸው ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር ሆኖ እራሳቸው ኢትዮጵያን የማፍረስ አላማ ይኖሯቸው ካልሆነ በስተቀር ለምን ደጋግሞ መፈክር ማሰማታቸው ተፈለገ? ከኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ውጪ ማንስ ኢትዮጵያ እንዲትፈርስ ፈላጎት አለው? እንድትፈርስ ፍላጎት ያለው ተከራካሪ ወገን በሌለበት ሁኔታ፣ ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ። ሁልጊዜም ኢትዮጵያ አትፈርስም የሚል መፈክር የሚያሰሙን ለምንድነው? እንግዲህ ጠቅላይ ሚንስቴሩ ኢትዮጵያ አትፈርስም የኢትዮጵያ አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቃታል፣ የሚሉት የኢትዮጵያ አምላክ ከሌሎች የተለየ ነው? የሚሉና እግዚአብሔር አብዝቶ ህዝቧንና ራሷን እንዲባርክ የሚማልዱላት ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገራት ሁሉ ተለይታ የማትፈርሰው እግዚአብሔር ስለሚጠብቃት እንደሆነ የሚነግሩን ሽምገላ እንጂ ሳይንሳዊ የፖለቲካ ትንተና አይደለም። አንድ እንቁላል አስኳሉ ከፈሰሰ በኋላ ጥቅም አይሰጥም። እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረውን እና አንድ ልጁን የሰዋለትን የሰው ልጅ እንዲገደል ትዕዛዝ እየሰጡ፣ በወታደሮቻቸው ሴቶችን አስገድዶ የሚደፍሩ ንጹሃንን በእሳት የሚያቃጥሉና ህዝብን በቁም የምረሽን መንግሥት፣ ከዚያም አልፎ የንጹሃን ህይዎት ቀርጥፈው ገደልነው፣ ብሎም በቴሌቪዥን እና በራዲዮ ገደልናቸውገደልናቸው፣ ተደመሰሱ ብሎም ለህዝብ የሚነግሩ ሰዎች ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቃል ኢትዮጵያ አትፈርስም ወዘተ፣ የሚሉት አማኝ መስሎ ህዝብን ለማታለል ነው። በጣልያንም ወረራ ኢትዮጵያ አልፈረሰችም ማለት ኢትዮጵያ አሁንም አትፈርስም ማለት አይደለም። ኢትዮጵያ አትፈርስም የሚል መፈክርን ውሳኔ የሚወስነው አፍራሹ የያዘው መዶሻ ነው። የአሁኑ አፍራሽ ደግሞም የሰው ልጆች በህይወት መኖር ደስታ የማይሰጠው አፍራሽ መንግሥትና በጣም ፈጣን ሃገር አጥፊዎች ስብስብ ሹማምንት ስለሆነ ኢትዮጵያ የማትፈርስበት ምክንያት የለም። ኢትዮጵያ እንደማንኛውም ሃገር ትፈርሳለች። ይህ ማለትም ጨፍጫፊና ገዳይ መንግስት እጅ ውስጥ አስከካለች ድረስ ሃገር ሆና መቀጠል አትችልም።

You must be logged in to post a comment.